ተረካቢህ አያሳፍር፣ ድፍን - ታታሪ ጨዋ፡፡
ተንቀለቀለ ቀንዲሉ፣ ያድማስህ ድምር ደመራ
ጋመ ንብርብሩ ፍም፣ አንተኑ በእሳት ሊጠራ!
ቀን ይጠብቃል እንጂ፣ ድል የትጉህ እጅ ነው
ወትሮም ካድማስ ጎህ ይቀዳል፣ ጎርፍም የዥረት ጅራፍ ነው
ከእያንዳንዱ ድል ጀርባ፣ አንዳንድ ጀግና ካለ
አንተ ነህ አሴ ልባሙ፣ ህልምህ በድል የተኳለ!
ተስፋህ ንፍ አያቅምና፣ ገና ይበራል ቀንዲሉ
አድማስህ ኬላ የለውም፣ ገና ይሰፋል ፀዳሉ፡፡
..ህዝብ ሲያውቅ እኔም አውቅ.. እንዳልክ
እንካ ዋንጫውን ተረከብ፣ ሲያሸንፍም አንተ አሸነፍክ!!
(ለአሴዋ ለአዲስ አድማስ ተጫዋቾችና ድል ለሚገባቸው ሁሉ)
ሐምሌ 28 2003 ዓ.ም
የ2003 የሩጫና እግር ኳስ ድሎች መታሰቢያነት ለአሰፋ ጐሳዬ ሆነ