Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 20 August 2011 10:26

..እስቲ ተመልከተው ይህ አወራረድ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ያልስማው ሲመጣ የሰማው ሲሄድ፡፡
ተግሳም ለፀባይ ካልሆነው አራሚ
መናገር ከንቱ ነው ካልተገኘ ሰሚ..
(ከበደ ሚካኤል)

ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ልዑል ባላጠፋው ጥፋት ይረገማል አሉ፡፡ ትልቅ ጫካ ውስጥ ብቻውን እንዲኖርም
ይደረጋል፡፡ እርግማኑም ..በአንድ ዓመት ውስጥ ያቺን የተፈቀደችለትን አንድ ቃል ሳይናገር ከቀረ በሚቀጥለው
ዓመት አንድ ቃል ይጨመርለታል፡፡ በሁለተኛው ዓመት ላይ ሁለት ቃል መናገር ይችላል ማለት ነው፡፡ በሁለተኛው ዓመት
ምንም ቃል ካልተናገረ በሶስተኛው ዓመት ሶስት ቃል ይናገራል፡፡


አንድ ቀን በዚያ ጫካ ውስጥ የምትንሸራሸር ውብ ልዕልት ያገኛል፡፡ ይህ ቀረው የማይባል ቁንጅና፣ ይህ ቀረው
የማይባል የሰውነት ቅር፣ ወገቧ ላይ የተኛ ፀጉር፣ ይቆጡኛል ያለ ልከኛ ባተ-ተረክዝ ያላት ናት፡፡ ልዑሉ በልዕልቲቱ
ውበት በጣም ይማረካል፡፡ መማረኩን ለመግለግና ፍቅሩን ለመግለ ቃላት ያስፈልጉታል፡፡ የተፈቀደለት ቃል ደግሞ
በዓመት አንድ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ እንዲህ ሲል አሰበ  
..በቃ የዛሬ ሁለት ዓመት ..የእኔ ቆንጆ.. ለማለት እንድችል፣ ሁለት ዓመት ሳልናገር መቆየት  አለብኝ አለ፡፡ ሁለት
ዓመት ከቆየ በኋላ ግን እንዲህ የሚል ሀሳብ  መጣላት
..የእኔ ቆንጆ ማለት ብቻውን ምን ይጠቅማኛል፡፡ አንድ ዓመት ምንም ሳልናገር ልቆይና ..የኔ ቆንጆ አፈቅርሻለሁ..
ብላት ይሻላል.. አለ፡፡
ሶስተኛ ዓመት ምንም ቃል ሳይናገር ቆየ፡፡ ሆኖም አንድ ሌላ ሀሳብ መጣላት
..የእኔ ቆንጆ አፈርቅሻለሁ ማለት ብቻውን አይጠቅመኝም፡፡ ላገባት እንደምፈልግ ልገልላት ይገባል፡፡ ስለዚህ ..የእኔ
ቆንጆ አፈቅርሻለሁ፣ ልታገቢኝ ፈቃደኛ ነሽ?.. ብላት ይሻላል.. አለና አሰበ፡፡
እነዚህን ቃላት ለመናገር የሚያስፈልጉት ስድስት ዓመታት ናቸው፡፡ ስለዚህ ስድስት ዓመት ምንም ቃል ሳይናገር
ቆየ፡፡
በመጨረሻ ወደ ልዕልቲቱ ሄደና በወጉ እጅ ነሣ፡፡ ከዚያም እፊቷ ተንበረከከና፤
..የእኔ ቆንጆ፤ አፈቅርሻለሁ፡፡ ልታገቢኝ ፈቃደኛ ነሽ?.. አለ፡፡ ልዕልቲቱ በደምብ አልሰማቸውም ነበረና፤
..ምናልከኝ?.. አለችው፡፡
የስድስቱ ዓመት ድካሙ ቀለጠ፡፡
***
አለመናገር ትልቅ እርግማን ነው፡፡ ተናግሮ አለመደመጥም ሌላ ትልቅ መርገምት ነው፡፡ ከሁለቱም ይሰውረን፡፡ ከአንድ ብር ላንድ ወገን ወደ አንድ ቃል ባንድ ዓመት እንዳንሸጋገር እንፀልያለን፡፡
..የምንፈልገውን ስናጣ እንጨነቃለን፡፡ እንደበራለን፡፡ የምንፈልገውን ስናገኝ ደግሞ እንሰለቻለን፡፡ በዚህ ምክንያት ህይወት የጨንቀት የመሰልቸት ዑደት ይሆንብናል.. ይላሉ ሻውፕነር እና ቡድሐ፡፡ ከዚህም ይሰውረን፡፡
አለቆችና የፖለቲካ መሪዎች የሚፈልጉትን መናገር የመናገር ነፃነት አይሆንም ይለናል ሮበርት ግሪን፡፡ በእርግጥም kn‰¹ù ካለመናገር ይቆጠራል ብንል ያስኬደናል፡፡ የልባችንን አልተናገርንምና፡፡ ፈረንጆች To Comply is to lie የሚሉት ነገር አለ፡፡ አጉል መስማማትና እሺ እሺ ማለት ከመዋሸት አንድ ነው፤ እንደማለት ነው፡፡ በየግምገማው፣ በየስብሰባው፣ በየኮንፈረንሱ የምናየውና የምንሰማው ነገር ይህንኑ ያፀኸይልናል፡፡ መናገር የሚችሉት የተስማሙት መሆናቸውና የማይናገሩት ያልተስማሙት መሆናቸው የሀገራችን ዕውነታ ከሆነ ቆይቷል፡፡ የፈሩ የዲሞክራታይዜሽኑ (ዲሞክራሲውN የማስፈኑ ሂደት) አካል ናቸው በሚል መቼም መስማማት ያዳግታል፡፡ የፍርሃት መንገድ የግልነቱ ተፃራሪ ነው፡፡ ግልነቱ ሳይኖር ዲሞክራሲው አለ ማለት ደሞ ቢያንስ የዋህነት ነው፡፡ እንዲህ ያለው ነገር በታሪክ ሲታይ የሩሲያውን ክሩስቼቭን ያስታውሰናል፡፡
በሩሲያው ስታሊን ይሠራ የነበረው ክሩስሼቭ አንድ ስብሰባ እየመራ ሳለ ስታሊንን ያወግዘዋል፡፡ ከተሰብሳቢዎቹ መካከል ከስታሊን ጋር አብረህ ትሠራ የነበርከው አንተ ራስህ ነህ፡፡ ያን ሁሉ ጥፋት ሲፈም ለምን ተው አላልከውም?.. ሲል ጠየቀው፡፡ ክሩስቼቭ የተናገረውን ሰው አላየውም ነበረና፤ ..ማነው አሁን የተናገረው? እጁን ያውጣ!.. አለና ጮኸ፡፡ ምንም እጅ ሳይወጣ ቀረ፡፡ ይሄኔ ክሩስቼቭ፤ ..ይሄውላችሁ፤ ያኔ ስታሊንን ለምን ተው እንዳላልኩት አሁን ገባችሁ.. አለ፡፡ በገዛ ምሣሌያቸው ስታሊንን መናገር እንዴት እንደሚያስፈራ፣ እያንዳንዱ ቃል እንዴት አንዳንድ ቅጣት እንዳረገዘ፣ በምን ተተርጉሞ ወንጀል ሊሆን እንደሚችል አስረዳቸ፡፡
ለነገሩ ባልታዛር ግራሺያን እንደሚለን ..ዕውነት በአጠቃላይ የሚታይ እንጂ የሚሰማ ነገር አይደለም፡፡ ያ ማለት ግን አንናገር ማለት አይደለም..፡፡ ምንም ሳይነካው ያስተካከለው እንዳስመሰለው የማይክል አንጄሎ ሐውልት አንዳንድ ዕውነት ፍንትው ብሎ ሊታይ ይችላል፡፡ አንዳንድ ዕውነት ግን ደጋግመው ካልተናገሩት አይሰማም፡፡ የመናገር ነፃነት ዋናነት አንዱ ገታው ይሄ ነው - ስለሚታየው ለመናገር መቻል፡፡ የሚታየውንና የሚሰማውን የማያምኑ ብፁዓን አይደሉም፡፡
የግብር አከፋፈል ሥርዓትን፣ የንግድ ህግን፣ የመንግሥት ፖሊሲዎችንና አተገባበራቸውን፣ የነዋሪውን ህዝብ አቤቱታና ብሶት፣ የወጣቱን ዕውነተኛ ስሜትና የተረካቢነት መንፈስ ማጣት፤ የምንናገርበት አንደበት፣ የምንጽፍበት አቅም የሚወለደው ከመናገርና መጻፍ ነጻነት ነውና ያንን ይባርክልን፡፡ ዕድገትም ልማትም ያለመናገርና መጻፍ ነፃነት ዕውን እንደማይሆኑ ልብ እንበል!
..በራሱ ሰናይ ምግባር ሆኖ የማይወሰድ ቢሆንም አንዳንዴ መታመም/መቸገር አስፈላጊ ነው.. የሚሉ አሉ፡፡ መቸገርና መሰቃየት ወደትክክለኛ የሥርየት መንገድ የሚያመራ ሊሆን ይችላል ከሚል እሳቤ ነው፡፡ አስቸጋሪ የሚሆነው እኛ ራሳችን የችግሩ መንስኤና አካል ስንሆን ነው፡፡ ዛሬ ስለሀገራችን ድርቅ የሚነግረን ሌላ ዲምብልቢ አያስፈልገንም፡፡
ረሀብና ድርቅን ለማሳወቅ የመናገር ነጻነት ነው የሚያስፈልገን፡፡ ይህንን ለማዳመጥ ዝግጁ የሆነ ሥርዓት ማግኘትም መታደል ነው፡፡ ምን ቢባል ምንም ግን ሊኖረን የምንፈልገው ዲሞክራሲ ከውጪ በውጪ ምንዛሪ የምንገዛው መሆን የለበትም፡፡
ረሀብና ድርቅን የሚታገል፣ ጠንካራ ዕምነት ያለው ህዝብ የሚፈጥርልን የመናገር ነጻነት ነው፡፡ የተጎዳው ህዝብ ቁጥር፣ የጉዳቱ መጠን፣ ምን ያህል ጉዳቱ ሊዘልቅ እንደሚችል ተጓዥ ጋዜጠኛ የእርዳታ ድርጅት ሠራተኛ ወይም ቱሪስት እስኪነግረን ወይም እስኪጽፍብን መጠበቅ የለበትም፡፡ እኛው እንናገረው! የመናገር ነጻነት የዚህ ዋስትና ነው፡፡ ደራሲ ከበደ ሚካኤልን ደግመን የምናስታውሳቸው ለዚህ ነው፡፡
..እስቲ ተመልከተው ይህ አወራረድ
ያልሰማው ሲመጣ የሰማው ሲሄድ
ተግሳጽም ለፀባይ ካልሆነው አራሚ
መናገር ከንቱ ነው ካልተገኘ ሰሚ፡፡..

 

Read 5915 times Last modified on Saturday, 27 August 2011 13:31