Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 20 August 2011 10:43

ፈረሱ ምን ሆኖ ነው እየሳቀ የሚያለቅሰው?

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

SMS አገልግሎት ሰጪ-  ፈረሱ ለመሳቅ የራሱን ብብት መኮርኮር ግድ ሆነበት፡፡ በSMS መልዕክት ለልማት አዋጣ፣ ለማይደርስ ሎተሪ አስበላ፣ . . . ለተመራቂ ተማሪዎች አድናቆትህን በመልዕክት ግለጽ ሲባል ራሱን ኮረኮረ. . . ለካ ፈረስ ሲኮረኮር ይፈረጥጣል እንጂ አይስቅም፡፡ . . . የስልክ ካርድ የሚሸጥለት ቴሌ. . . መልዕክት የሚልከው ለቴሌ፡፡ ፈረሱ ያለቀሰው የመብራት ኃይል ባለሥልጣን በስልኩ ቴክስት ሜሴጅ ልኮለት ሲያነብ ነው፡፡ ..የመብራት አቅርቦትን የኃይል እጥረት ወዳለባቸው ቦታዎች ለማድረግ ከመብራት ካርዷ በመቀነስ እርዳታ ይለግሱ.. የሚል መልዕክት፡፡ እንደተጠየቀው መብራቱን ለእርዳታ ልኮ በጨለማ እየተንሰቀሰቀ ተቀመጠ፡፡

የመቅደላ LJ- ሃያላን ሀገሮች ውስጥም አመጽ እና ብጥብጥ ተቀስቅሶ ሲመለከት ፈረሱ ከላይ ከላይ ..ይገርማል.. እያለ በውስጡ ግን በደስታ እየሳቀ ተፍነከነከ፡፡ ...ሁሌ ተረጋግቶ እየኖሩ ሌላው ደሀ ዓለም ሲበጠበጥ ማስታረቅ እና መዳኘት፤ አከተመለት፡፡ ጣይ እና አንሺው ራሱ ሊወድቅ ወይም ሊታወክ ይችላል ለካ? ከመቶ ሃምሳ ዓመት በፊት ወደ አፍሪቃ ወርዶ አፄ ቴዎድሮስን ከሥልጣን ያወረደው መንግሥት ዛሬ ከአፍሪካ ተሰድዶ በሄደው መንግሥት እየተበጠበጠ መሆኑ ደስ አሰኘው፡፡ እሰይ! ብሎ ሳቀ፡፡ እየሳቀ ዜና ሲመለከት፤ በአመ ላይ ከሚሳተፉት ሰዎች መሀል አንድ በጣም የሚያውቀው ዘመዱን መልክ ያየ መስሎት ክው አለ፡፡ ...የፈረሱ ሳቅ እንደ ቋንጣ ድንገት ፊቱ ላይ ደረቀ፡፡ ዘመዱ ሠርቶ በሚልክለት ዩሮ ነው ከእለት እለት የሚኖረው የሚንቀባረረው፡፡ ...እየሠራ አይላክና ድንጋይ ይ-ወ-ረው-ርልኛል... እሱ ከእንግሊዝ ቢባረር የሚፈላብኝን ጉድ አያውቅምና ነው?!... እዬዬ አለ ፈረሱ እዬዬ!
መጽሐፍ ሻጭ-\\ የይስማዕከ ወርቁ ሦስተኛ መጽሐፍ (ግጥሞቹን ሳይጨምር) ገበያ ላይ በመዋሉ ነው ተደስቶ የሳቀው፤ ፈረሱ፡፡ የመጽሐፍቱን ገበያ እንዲሁም ማንበብ ትቶ የነበረ ህዝብን ወደ ንባብ የመለሰው ልጅ፤ መጽሐፍት ሻጭን በዚህ ክረምት በብር ሊያንበሸብሽ ነው፡፡ ስም እንጂ ሥራ ለማይገደው አንባቢ በገፍ መጽሐፍት አምጥቶ ሲቸበችብ ታይቶት ፈረሱ ሳቀ፡፡
ፈረሱ ያለቀሰው\\\\ መጽሐፉን የገዛ ሰው ካነበበ በኋላ ወደ መሀል ላይ ሰልችቶት አቋርጦ ኤጭ! - ምናለ እያበሰለ ቢያወጣው... እያለ ሲማረር አይቶ ፈረሱ ተናዶ አለቀሰ... ፀሐፊው መች ደራሲ ነኝ አለ? ...መች ለእድሜ ልክ የሰው እንባ እና ላብ የሚያብስ የሀር መሐረብ አበረከትኩላችሁ አለ?... እሱ ያበረከተው (ተልሚድ) የናፕኪን ሶፍትን ነው፤ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውል፤ ተነቦ ወይም ተጠቅሞ የሚጣል... በፊልም እና ቲያትር ቤቶች አንዴ ተመርቆ ከታየ በኋላ የሚወርድ ዓይነት ሥራ፡፡ አንባቢ እና ሀያሲ ምን ሁን ነው ፀሐፊውን የሚሉት? ብሎ ፈረሱ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ፡፡

Read 3627 times

Latest from