ኢትዮጵያ ሃብተማርያም፤ በአዲሱ ሃላፊነቷ ምርጥ የግጥም ደራሲዎች፣ አርቲስቶችና፣ ፕሮዲዩሰሮችን የለማፈላለግ ሥራ ይጠብቃታል፡፡ በዩኒቨርሳል ሚዩውዚክ ግሩፕ በተሰጣት የሹመት ከእነሜሪ ጄ ብላይጅ፣ ማርያ ኬሪ፣ ኤሚነም፣ 50 ሴንት፣ ዲኤምኤክሰ አር ኬሊና ከሌሎች ታላላቅ ሙዚቀኞች ጋር እንደምትሰራ ይጠበቃል፡፡ ሞታውን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የዴፍ ጃም አሳታሚ ስራዎችን በማሻሻጥና በማከፋፈል ስራ ላይ ተሰማርቷል፡፡ ስቲቪ ዎንደርና ቤቢ ፌስ ሥራቸው በሞታውን ከሚታተምላቸው አርቲስቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ በኒውዮርክና ሎስአንጀለስ የምትሰራው ኢትዮጵያ ሃብተማርያም፤ ለዩኒቨርሳል እና ለአይስላንድ ዴፍ ጃም ኩባንያ ሊቀመንበርም በረዳት ታገለግላለች፡፡
በ17 ዓመቷ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን እንደጨረች ላፌስ ሪከርድስ በተባለ የሙዚቃ አሳታሚ መስራት የጀመረችው፤ ኢትዮጵያ በ2001 እ.ኤ.አ ላይ በሎስአንጀለስ በሚገኝ ኤድመንድ የሙዚቃ አሳታሚ የሠራች ሲሆን ከ2003 እ.ኤ.አ ጀምሮ ዩኒቨርሳል ሚዩዚክ ግሩፕን ተቀላቅላለች፡፡ በዩኒቨርሳል የሙዚቃ አሳታሚ መስራት ከጀመረች በኋላ ጀስቲን ቢበር፣ ክሪስ ብራውንና ሲያራን የመሳሰሉ ኮከቦችን ወደ ሙዚቃ ገበያው አምጥታለች፡፡