Saturday, 20 August 2011 11:25

የግሎባላይዜሽን ፈር ቀዳጁ ሙስሊም

Written by  ጥላሁን አክሊሉ
Rate this item
(4 votes)

በዓለም ላይ ውቅያኖስን አቋርጠው ረጅም የባህር ጉዞ በማድረግ ከማታወቁት ውስጥየአሜሪካንን ክፍለ ዓለም ያገኘው ክርስቶፈር     ኮሎምበስ፣ ቻይናን ለአውሮፓዊያን ያስተዋወቀው ማርኮ ፖሎ እንዲሁም ምድርን ለመጀመሪያ ጊዜ በመርከብ በመዞር ምድር ክብ መሆኗን ያረጋገጠው ፈርዲናድ ማጂላን ይጠቀሳሉ፡፡ ነገር ግን ስማቸው የማይታወቅና ብዙም ያልተወራላቸው በርካታ የዓለማችን ተጓዦች አሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ሀጂ አቡ አብዱላህ መሀመድ ኢብን ባቱታ ይጠቀሳል፡፡ኢብን ባቱታ እ.ኤ.አ በ1940 ዓ.ም በሞሮኮ ውስጥ በምትገኝ ታንጂር በተባለው ስፍራ ተወለደ፡፡ እድሜው 21 ዓመት ሲሞላው የትውልድ ቦታውን ለቆ የመጀመሪያውን ጉዞ በእስልምና እምነት ቅዱስ ወደሆነው መካ ገሰገሰ፡፡

በመካ ሃጂነትን ከተቀበለ በኋላ የተለያዩ የሙስሊም አገሮችን ካካለለ በኋላ ወደ ህንድ፣ ሲሪላንካ፣ ማልዲቪስ፣ ቻይና እና የኢንዲያን ውቅያኖስ ሪፐብሊክ ድረስ ሄዷል፡፡ በአጠቃላይ ለ30 ዓመታት ያህል ባደረገው ጉዞ 120,000 ኪሎ ሜትር ተጉዟል፡፡
ኢብን ባቱታ ይህንን ያህል ረጅም ርቀት እንዲጓዝ ያደረገው ከልጅነቱ ጀምሮ እውቀትን ለማግኘት ካለው ጥልቅ ፍላጐት ሲሆን፣ ባገኘው እውቀት ሰዎችን ለማስተማር ነው፡፡ በይበልጥም ለእምነቱ በጣም ቀናተኛ በመሆኑና ጠንካራ የሞራልና የስነምግባር ደንቦችን የሚከተል በመሆኑ ሳይታክት የህይወቱን አጋማሽ ተጉዟል፡፡ ባረፈባቸው ቦታዎች ሁሉ በቂ እውቀት ያገኘ ሲሆን የተለያዩ ማህበረሰቦችን አኗኗር፣ ባህል፣ ወግ፣ ስልጣኔ እና ሃይማኖትን ለማወቅ ችሏል፡፡ ኢብን ባቱታ የሚያደርገውን ጉዞ ሪሂላ መገለጥ ብሎ የሚጠራው ሲሆን ..ወፍ ጐጆዋን እንደምትፈልግ ሁሉ፣ እኔም የማርፍበትን ቦታ ተጉዤ ነው የማገኘው.. በማለት ተናግሯል፡፡ ኢብን ባቱታ ጉዞውን የሚያደርገው በአህያ፣ በግመል፣ በእግርና በጀልባ ነበር፡፡
በወቅቱ ሙስሊሞች የሚኖሩበት ቦታ ዳር አል-ኢስላም በመባል ይታወቅ የነበረ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹን የዳር አል-ኢስላም ድንበሮች እንዲወሰኑና ሙስሊሞችም ድንበራቸውን እንዲጠብቁ አድርጓል፡፡
ለመካ ልዩ ክብር እንደሚሰጥ ይናገር የነበረው ኢባን ባቱታ ይህችን ቅድስት ከተማ “Congress of the Muslim World” በማለትም ይጠራታል፡፡
ነገር ግን ዳር አል-ኢስላም የሙስሊሞች መኖሪያ ድንበር የሚለው ቃል ለኢብን ባቱታ ተጨማሪ ትርጉም ነበረው፡፡ ሁሉም ሙስሊሞች ተመሳሳይ ዓላማና አቋም ያላቸው በጣም ተቀራራቢ ባህል እና አንድነታቸውን የጠበቁ የአምላክ ማህበረሰቦች (ኡማ) እንደሆኑም ይገልፃቸዋል፡፡ በእርግጥ ኢብን ባቱታ ለሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን ከሙስሊም እምነት ውጪ ላሉ ሕዝቦችም ጥልቅ አክብሮትና ፍቅር ነበረው፡፡ በእርሱ ዘመን ሙስሊሞች በዓለም ላይ ኃያል የነበሩበት ቢሆንም፣ ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር ተከባብረው በፍቅር እንዲኖሩ ይናገር ነበር፡፡
አሜሪካዊ የታሪክ ፀሀፊ ሮስዱን ሲናገሩ ..ኢብን ባቱታ ተጓዥ ብቻ አይደለም፤ የተማረና አርቆ አሳቢ እንዲሁም ዓለም አቀፍ እውቀት የነበረው ሰው ነው.. ብለዋል፡፡ ሮስዱን አያይዘውም ..ኢብን ባቱታ ራሱን የሚመለከተው እንደ ሞሮኮ ዜጋ ሳይሆን የሁሉም አገር ሰው ነዋሪ  እንደሆነ ነበር፤ በሄደበት ቦታ ሁሉ የሚያሳየው ጥልቅ የሆኑት መንፈሳዊ፣ ሞራላዊና ማህበራዊ እሴቶቹ ተወዳጅ እንዲሆንና ታማኝነትን እንዲያተርፍ አስችሎታል.. በማለት ተናግረዋል፡፡
ሙስሊሞች ያላቸው ተመሳሳይ እምነት የአምልኮ ስርዓት፣ ልማድና ባህል ከእስልምና ሃይማኖት መስራች ከሆነው ከነብዩ መሀመድ የመጣ ቢሆንም፣ ሙስሊሞችም ለእነዚህ ሃይማኖታዊ እሴቶች ትልቅ ቦታ እንዲሰጡና አጥብቀው እንዲይዙት በማድረግ ኢብን ባቱታ ትልቅ አስተዋኦ አድርጓል፡፡ በሚሄድበት ቦታ ሁሉ ሙስሊሞች አንድ መሆን እንዳለባቸው የሚያስተምር ሲሆን፣ ከእስልምና ሃይማኖት ውጪ የሆኑ ድርጊቶችን ሲመለከትም ይቃወም ነበር፡፡ ለምሳሌ ወደ ቱርክ በሄደበት ወቅት፣ በቱርክ ሴት ከባሏ የበላይ በመሆን ባሏን እንደፈለገችው ስታዘው በማየቱ በጣም ያዘነ ከመሆኑ በላይ ተቃውሞውን ገልጿል፡፡
በሌላ በኩል በማልዴቪስ የሚገኙ ሴት ሙስሊሞች ልቅ የለሽ አለባበስም አስቆጥቶት ነበር፡፡ ወደ ሞንጐሊያ በሄደበት ወቅትም ቢሆን ሞንጐሎች ባሳዩት ኢ-ግብረገባዊ ባህሪይ የተከፋ ሲሆን፣ በተለይም እርሱ ካለው የላቀና ቀጥተኛ ስነምግባር አንፃር እጅግ የወረደ ድርጊት እንደሚፈሙ አስተውሏል፡፡ ይሁን እንጂ ለዳር አል-ኢስላም ሕዝቦች ግን “La ilah illa Allah; Muhammad resul Allah” (ከአንድ አምላክ (አላህ) በቀር ሌላ የለም፤ መሀመድ የአላህ መልእክተኛ ነው) የሚለውን የእስልምና መሰረት አጥብቀው እንዲይዙና በዚህም ጥላ ስር እንዲኖሩ ያስተምር ነበር፡፡
በኢብን ባቱታ ዘመን የነበረው የሙስሊሞች አንድነትና ተመሳሳይነት በዛሬው ጊዜ በአንዳንድ ልዩነቶችና አለመግባባቶች ቢተኩም፣ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ 1.6 ቢሊዮን እስላሞች አሁንም አንድ አምላክን (አላህን) ብቻ የሚያመልኩ ከመሆናቸው በላይ አንድ አይነት የአምልኮ ስርዓት አላቸው፡፡
ኢብን ባቱታ እ.ኤ.አ በ1926 ዓ.ም የመጀመሪያ የሃጂ ጉዞ ወደ መካ ካደረገ በኋላ ለሦስት አመታት መካ ተቀምጧል፡፡ እ.ኤ.አ በ1930 ዓ.ም የባዛንታይን ዋና ከተማ ወደ ነበረችው ኮንስታንቲኖፕል ተጓዘ፡፡ በዚያም ለአንድ ወር ሲቀመጥ በርካታ ቤተክርስቲያኖችን፣ ገዳማትን እና መስጊዶችን ማየቱን ፏል፡፡ ቀጥሎ ወደ ሕንድ ያቀና ሲሆን፣ በዚያም ለስምንት አመት ያህል ተቀምጧል፡፡ በሕንድ እያለም በሕንድ ዋና ከተማ በዴሊሂ ውስጥ በሚገኝ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኗል፡፡ ይህም የሂንዱ እምነት ተከታዮች በበዙበት አገር የመጀመሪያው ሙስሊም ዳኛ ነበር፡፡ ስለ ዴሊሂ ሲናገርም፣ ..ታላቋ የሂንዱስታን ከተማ ከሁሉም የምስራቅ እስላም ከተሞች ትበልጣለች.. ብሏል፡፡  
ከሕንድ ቀጥሎ ወደ ማልዲቪስ ነበር የተጓዘው፡፡ በማልዲቪሶች ለ9 ወር ያህል ተቀምጧል፡፡ የማልዲቪስ ቆይታውን ከጨረሰ በኋላ፣ ወደ ሲሊዬ (አሁን ሲሪላንካ) ሄደ፡፡ ይህን ቦታ ሙስሊሞች አዳም ከኤደን ገነት ከተባረረ በኋላ ያረፈበት እንደሆነ የሚያምኑበት ሲሆን፣ ኢብን ባቱታ በዚህች ስፍራ ለሁለት ወር ያህል ተቀምጧል፡፡
ኢጣሊያዊ የባህር አሳሽ በ1271 ወደ ቻይና ከሄደ ከ70 ዓመት በኋላ፣ ኢብን ባቱታ ቻይና ተጉዟል፡፡ ቻይናዊያን ሃይማኖት እንደሌላቸው የገለፀው ባቱታ፤ በቻይና ያለውን የተትረፈረፈ የወርቅና የመዳብ ብዛት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶች በማየቱ ተደንቋል፡፡ ከቻይና ጉዞ በኋላ ወደ አገሩ ሲመለስ ሁለተኛውን የሃጂ ጉዞ ወደ መካ አደረገ፡፡ መካ እያለ በወቅቱ ከሜድትራንያን ባህር የተነሳው የሳንባ ምች ወረርሽኝ ተቀስቅሶ አካባቢውን አጥለቅልቆት ነበር፡፡ በሽታው ጥቁር ሞት በመባል የሚታወቅ ሲሆን እስከ አውሮፓ በመዝለቅ በአጠቃላይ 75 ሚሊዮን ሰዎችን ለህልፈት ዳርጓል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የኢብን ባቱታ ወላጅ እናት አንዷ ነበሩ፡፡
የኢብን ባቱታ አስተምህሮ የሙስሊሞችን ብቻ ሳይሆን በሄደባቸው አገሮች ሁሉ የሰዎችን አስተሳሰብና ህይወት ቀይሯል፡፡ በዱክ ዩኒቨርስቲ የማህበራዊ ሳይንስ ምሁር የሆኑት ስቴፈን ሮስ ሲናገሩ ..ኢብን ባቱታ የሰላም ተጓዥ ነበር፡፡ በወቅቱ ከማንኛውም የሃይማኖት አስተማሪ ይልቅ የሰዎች ቀልብ መግዛት የቻለና እምነትን ከተግባር ጋር ያጣጣመ ሰው ነው.. ብለውታል፡፡
የኢብን ባቱታ አሻራ በሙስሊም አገር ከተሞች ላይም ማረፉ አልቀረም፡፡ ከእነዚህ ውስጥም ዱባይ አንዷ ነች፡፡ በዓለም ታዋቂ ከሆኑት ከተሞች አንዷ የሆነችውን ዱባይ፣ ኢብን ባቱታ በ14ኛው ክ/ዘመን በተደጋጋሚ ሄዶባታል፡፡ በአሁኑ ወቅት በዱባይ የሚገኙ ጥንታዊና ታሪካዊ መስህቦች የኢብን ባቱታን ጉዞ መሰረት በማድረግ የተገነቡ ሲሆኑ በንግድ ከተማነቷ የምትታወቀው ዱባይ በአለም አንደኛ የሆነውነ የቡርጂ ከሊፋን ፎቅ ጨምሮ በርካታ ሕንፃዎች አሏት፡፡ እነዚህ ሁሉ ሕንፃዎች ደግሞ የኢብን ባቱታ አስተሳሰብ ተዕኖ ያሳደረባቸው ሰዎች የገነቧቸው እንደሆኑ የከተማዋ አስተዳዳሪ ይናገራሉ፡፡ ዱባይ ከለንደን፣ ከፍራንክፈርት እና ከፓሪስ ከተሞች ጋር የምትወዳደር ከመሆኗ ባሻገር በዓለም ኢኮኖሚ ላይም አይነተኛ ተእኖ ማሳረፍ ትችላለች፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ሲታዩ ዱባይ የኢብን ባቱታን ዳር አል-ኢስላም ዘመን የምታስታውስ ትመስላለች፡፡
በእስልምና እምነት ውስጥ ጠንካራ መሰረት ጥሎ ያለፈው ኢብን ባቱታ፤ ለእምነቱ ያለው ቀናዒነት ብቻ ሳይሆን፣ በወቅቱ ዓለምን እንዳቀራረበ (GlÖÆላይz¤>N) የሚጠቅሱት የዳኒሽ የፖለቲካ ፊሎሰፈር የሆኑት ሃንስ ሄኔሪክ ሆልም እና ጆርጅ ሶሪንሰን ናቸው፡፡ ከዛሬ 700 ዓመት በፊት ሙስሊሞች በእምነታቸው፣ በባህላቸው፣ በልማዶቻቸው እና በማህበራዊ እሴቶቻቸው በጣም ተቀራራቢ ነበሩ በማለት ምሁራን ይገልፃሉ፡፡
በዚያኔ በርካታ ሙስሊሞች የሚገኙበት ሞንጐሊያ፣ ሞንጐሎች ማዕከላዊ ኢሲያን፣ ሩሲያን እና ቻይናን በጦርነት ድል አድርገው የያዙ ቢሆንም፣ ሞንጐሎች በያዙት ግዛቶች ሁሉ የተለያዩ አገር ሕዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነት ነበራቸው፡፡ ነጋዴዎች እንደልብ በሞንጐሎች ግዛት እቃዎቻቸውን ይሸጡና ይለውጡ ነበር፡፡ ኢብን ባቱታም በሞንጐሎች ግዛት እንደፈለገ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ እስላሞች የማምለክ ነፃነታቸው በየትኛውም ቦታ የተጠበቀ ስለነበር ወደፈለጉት ቦታ በመሄድ አምልኳቸውን ይፈሙ ነበር፡፡ ታሪክ ፀሀፊው ማርሻል ሆድሰን ..ያ ዘመን ለሙስሊሞች ወርቃማ ዘመን ነበር፡፡ ኢብን ባቱታ በመካከለኛው ክ/ዘመን ከነበሩት ሰዎች ሁሉ በላይ ዓለምን በማቀራረብና ዓለም የጋራ እንድትሆን ያስቻለ ሰው ነው.. ብለውታል፡፡
በመካከለኛው ዘመን ሙስሊሞች በጣም ደስተኞች እንደነበሩ የሚገልፁት ሆድሰን፤ በሳይንስ፣ በንግድ፣ በሂሳብና በአርኪቴክት ከሌላው ህብረተሰብ የላቀ ችሎታ እንደነበራቸው ጠቅሰዋል፡፡ ታዲያ ያ ሁሉ የሙስሊሞች ክህሎት የት ገባ? ከመካከለኛው ክ/ዘመን በኋላ በምዕራባዊያን አገራት የኢምፔሪያሊዝም መስፋፋት፣ ቅኝ ግዛት፣ የእርስ በእርስ ጦርነት፣ ብሔራዊ ስሜትና አክራሪነት እየተበራከተ መምጣት በኢብን ባቱታ ዘመን የነበረው የሙስሊሞች ሃያልነትና ስልጣኔ ቀስ በቀስ እየወረደ እንዲመጣ ያደረገው ይመስላል፡፡ ከመካከለኛው ክ/ዘመን ጀምሮ ገናና የነበሩት አቶማን ቱርኮች እ.ኤ.አ በ1924 በአውሮፓዊያን የበላይነታቸውን ተነጠቁ፡፡ አቶማን ከሊፋት ከያዟቸው ግዛቶች በእንግሊዝና በፈረንሳይ በሃይል እንዲለቁ ተደረገ፡፡ የመካከለኛው ምስራቅ ድንበሮችም በኢብን ባቱታ ዘመን ከነበሩበት ቦታ በቅኝ ገዢዎች ተከፋፈሉ፡፡ ለምሳሌ የዛሬዋን የኢራቅን ድንበር እንግሊዞች ሲከልሉ፣ ከዚያ በፊት ራሳቸውን ኢራቃዊያን ነን የማይሉ ሕዝቦች ድንበሩ እነርሱን በማካለሉ ምክንያት ብቻ ኢራቃዊያን ለመሆን ችለዋል፡፡ ይህም ኋላ ላይ በኢራንና በኢራቅ መካከል እ.ኤ.አ ከ1980-88 በሱኑ ኢራቃዊያን ሙስሊሞችና በሺአይት ኢራናዊያን መካከል የተካሄደው የድንበር ግጭት እንዲከሰት አድርጓል፡፡
ሌሎች የጂኦ ፖለቲካዊ ግጭቶችም ቢሆኑ ቅኝ ገዢዎች ትተውት የሄዱት ጦስ ነው፡፡ በኢብን ባቱታ ዘመን ሙስሊሞች አለም አቀፍ ዜግነትና እምነት እንዳላቸው ያምኑ የነበረ ሲሆን፣ በአውሮፓዊያን ተእኖ ስር ከወደቁ በኋላ ግን እነዚህን እሴቶች በመተው በብሔራዊ ስሜትና በአገር ፍቅር እንዲሁም አንዱ የሌላው የበላይ ለመሆን በመፈለግ ተቀየሩ፡፡ በብዙ ሙስሊም አገሮች በሱኒ (የነብዩ መሀመድ ተከታዮች) እና በሺአይት (የነብዩ መሀመድ ልጅ ባል በሆነው በአሊ ተከታዮች) መካከል ግጭቶች ተፈጥሮ ሙስሊሞች እርስ በእርስ መገዳደል ጀመሩ፡፡
ነገር ግን ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ ሙስሊሞች ተመሳሳይ የሆኑበት አጋጣሚ ተፈጥሯል፡፡ በሰሜን አፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ሙስሊሞች እንደገና ወደ ዳር አል-ኢስላም ዘመን ተመልሰዋል፡፡ በቱኒዚያ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥያቄ በማንሳት የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመ ከተሳካ በኋላ ወደ ግብ በማምራት በተመሳሳይ ሕዝባዊ ጥያቄዎች ምላሽ አግኝተዋል፡፡ ቀጥሎም ወደ ሊቢያ፣ ባህሬን፣ የመን፣ ሶሪያ፣ ዮርዳኖስ፣ ሞሮኮና ሌሎችም አገሮች ሙስሊሞች ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡ የመካከለኛውን ምስራቅ ሕዝባዊ አመ የሚመሩት ወጣቶች በኢንተርኔትና በማህበራዊ ሚዲያዎች በመጠቀም፣ ፍፁም ሊነኩ የማይችሉት የሚመስሉትን አምባገነን መሪዎች ገርስሰዋል፡፡ ሕዝባዊ አመፁ አሁንም እየተካሄደ ባለባቸው እንደ ሶሪያና ሊቢያ ባሉ አገሮች፣ ከኢብን ባቱታ አስተምህሮ ውጪ ሕዝባቸውን በፈላጭ ቆራጭነት የሚመሩ መሪዎችን ለማውረድ ጠንካራ ትግል እየተካሄደ Yg¾L””በመካከለኛው ምስራቅ የተነሳው ሕዝባዊ አመ ወደ እስያና ደቡብ አሜሪካ እንዲሁም አውሮፓ ዘልቋል፡፡ ምንም እንኳን መንግስት የወረበሎች አመ ነው ቢልም ወደ አገረ እንግሊዝም ተዛምቷል፡፡ አገሩ እንግሊዝ በመሆኑ ከሸፈ እንጂ በቱኒዚያና በግብ የነበረው የፌስቡክና የትዊተር ድረ ገ ግንኙነት በእንግሊዝም ተካሂዷል፡፡ በእርግጥም ኢብን ባቱታ እንዳለው ዳር አል-ኢስላም ከድንበር በላይ ነው፡፡

 

Read 8492 times Last modified on Saturday, 20 August 2011 11:32