Saturday, 27 August 2011 13:08

ጠ/ሚኒስትሩያልቀለዱበት ብቸኛው ዓመት

Written by  ኤልያስ
Rate this item
(0 votes)
  • የዘንድሮ ተሸላሚዎች እነማን ናቸው?
  • ኢህአዴግ፣ - መኢአድ፣ - ድምፃውያን፣ - ምሁራን፣ - ፓርላማ

የዘንድሮ 2003 ዓ.ም. በብዙ ነገሮች ስንመለከተው የትንግርት ዓመት ሊሰኝ የሚችል ነው፡፡ የኑሮ ውድነቱ በየጊዜው እየናረ እንጂ እየተሻለው አልመጣም፡፡ ለነጋዴዎችም ለሸማቾችም ምንም ያልተመቸ ዓመት ይሏችኋል ዘንድሮ ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ሁኔታም ብትመለከቱት ዓመቱ ለማንም የተመቸ አልነበረም - ለአምባገነን መንግሥታትም ሆነ ለዴሞክራቶቹ አገራት፡፡ በእርግጥ ሦስት አምባገነን መሪዎች ከሥልጣን ተፈናቅለዋል - የግብ፣ የቱኒዝያና የሊቢያ (በቋፍ ላይ ናቸው ብዬ ነው) የህዝብ አመፁ ግን በዲሞክራሲያዊ አሠራር የበለገ ልምድና ተመክሮ አላት የምትባለውን የንግሥት ኤልሳቤጥንም አገር እንግሊዝን አልማራትም - የጐዳና ላይ ነውጥ አገሪቷን ..ቀውጧት.. ነበር፡፡

ከሁሉም በላይ ግን ዓመቱ ጤና እንደሌለው ጥሩ ማሳያ የሚሆነው በአንደበተ ርዕቱነታቸውና በቀልድ (ተረብ) አዋቂነታቸው የምናውቃቸው የአገራችን ጠ/ሚኒስትር እንኳን በ2003 ዓ.ም. አንድም ለዛ ያለው ቀልድ ሳይቀልዱ ዓመቱ ሊጠናቀቅ ደርሷል፡፡ እንግዲህ የቀራቸው 15 ቀን ብቻ ነው፡፡ ለነገሩ አይፈረድባቸውም፡፡ በአንድ በኩል የኑሮ ውድነት እሮሮ፣ በሌላ በኩል የህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዢ ወጥሮ ይዟቸው ነበር፡፡ በቅርቡ ደግሞ የ..ባንዳዎች.. ወሬ (የእነቢቢሲ) ፋታ ነስቷቸዋል፡፡ እንዲህም ብለን እንዳናልፋቸው ግን በ97 ዓ.ም. በተቃዋሚዎች ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ውጥረት ውስጥ ሆነው እንኳ በመራር ንግግር መሃል ቀልድ ቢጤ ጣል ያደርጉ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ዘንድሮ ግን አልቻሉም፡፡ ከምር ጠ/ሚኒስትሩና ቀልድ ተራርቀዋል፡፡ በቂ መረጃ የለኝም እንጂ ከ20 ዓመታት የሥልጣን ዘመን ውስጥ ጠ/ሚኒስትሩ ያልቀለዱበት ብቸኛው ዓመት ዘንድሮ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ምን ያህል አስቸጋሪ ዓመት ቢሆንባቸው ነው ለእሳቸው ማለቴ ነው እንጂ እኛማ እናውቃለን፡፡
በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅና ረሃብ እንዲሁም መንግስት ከለጋሽ አገራት የሚያገኘውን እርዳታ የሚያከፋፍልበትን መንገድ በተመለከተ ቢቢሲ ባቀረበው ዝግጅት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የሰነዘረው ..ዘለፋ-አዘል.. ምላሽ በአብዛኛው የራስን ፖለቲካዊ ስምና ዝና መጠበቅ ወይም መከላከል ላይ ያተኮረ ይመስላል፡፡ ራሱ ኢህአዴግም ቢሆን ለጊዜው በብስጭት ..ባንዳዎች.. ብሎ ተሳደበ እንጂ ትንሽ ቆይቶ አቋሙን እንደሚቀይር አልጠራጠርም፡፡ ከባዶ ተነስቼ አይደለም እንዲህ የምለው፡፡ ከአገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎች ራሱን በመንቀፍና በመተቸት (በራሱ ቋንቋ ግለ-ሂስ በማድረግ) እስካሁን ሪከርዱን የሰበረው ብቸኛ ሃቀኛ ፓርቲ ኢህአዴግ እንደሆነ ማንም አይክድም ብዬ አምናለሁ - ተቃዋሚዎችም ቢሆኑ፡፡ እስቲ ማነው እስከዛሬ ራሱን (ፓርቲውን) ..በስብሰናል..፣ ..ነቅዘናል..፣ ..ተቸክለናል.. ወዘተ እያለ በራሱ ፓርቲ ላይ ሂስ ያደረገ - እኔ እስከማውቀው ድረስ ኢህአዴግ ብቻ ነው፡፡ እኔ እንደውም የማስበው ኢህአዴግ ራሱን በመተቸትና በማዋረድ ላሳየው ትልቅ ወኔና ድፍረት የዓመቱ ተሸላሚ ለማድረግ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ያከናወነው በጐ ተግባር የለም ለማለት ፈልጌ እንዳልሆነ ግን ይታወቅልኝ፡፡ ሆኖም ቀድሞ ወደ አዕምሮዬ የመጣው ይሄ ብቻ ስለሆነ ነው፡፡
ባለፈው ሰሞን ዩኒቨርስቲውንና ምሁሩን ..እንቅልፋም..፣ ..ለቴክኖሎጂ ዳተኛ.. በሚል ክፉኛ የተቹት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን (አመራር) በመቀጠል የትችት በትራቸውን የሰነዘሩት ራሳቸው የሚመሩት የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር መ/ቤት ላይ ሲሆን የአመራሮችን ኪራይ ሰብሳቢነት ሸፋፍነን እየሄድን ነው ሲሉ የራሳቸውን ከፍተኛ የሥራ አመራሮች አፈር ድሜ አስበልተዋቸዋል - በትችት፡፡ ራሱ ላይ አደገኛ ትችት በመሰንዘር ዝናው የናኘው ኢህአዴግ ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ የትችት ሮኬቶችን በራሱ ላይ ማስወንጨፉን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
እንደው ለማስታወስ ያህል አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣንና የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ኢቴቪ ላይ በሰነዘሩት የትችት ወንጭፍ ..ኢቴቪ በረት ነው.. ማለታቸው ይታወሳል፡፡ የኢህአዴግ ግንባር ድርጅት የሆነው ብአዴን በአንድ ጉባኤው፣ በራሱ አባላት ላይ በለቀቀው የትችት ተኩስ አባላቱ (ሁሉም ይሁኑ አንዳንዶቹ አላስታውስም) አድርባይነት የሚያጠቃቸው እንደሆኑ በይፋ ገልፆ ነበር፡፡ የሽልማትን ነገር አንዴ አንስተናልና ኢህአዴግ ሌላም የሚያሸልመው ድፍረት (አንዳንዶች ጀግንነት ይሉታል) እንዳለው ማንም አይክደውም፡፡ ይኸውም በክብሩና በስሙ ከመጡበት ሃያላን መንግስታት ይሁኑ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ደንታ የለውም - እስከ ዶቃ ማሰሪያቸው ልክ ልካቸውን ይነግርልናል - ኢህአዴግ ጋር ቀልድ የለም፡፡ እነ አምነስቲ፣ እነ ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ የአሜሪካ መንግስት፣ እነ ቢቢሲ ሁሉም ቀምሰዋል፡፡ የኒዮሊበራሊስት አቀንቃኞች፣ የቀለም አብዮት አራማጆች፣ መርዶ ነጋሪዎች፣ ሰላም አደፍራሾች ወዘተ የሚል ታርጋ እየተለጠፈባቸው አርፈው እንዲቀመጡ በአማርኛም በእንግሊዝኛም፤ በቲቪም በሬዲዮም እስኪበቃቸው ተነግሯቸዋል - ምንም እንኳ ከስህተታቸው የሚታረሙ ባይሆኑም፡፡ ዋናው ቁምነገርም የእነሱ መታረም አይመስለኝም፡፡ ዋናው ኢህአዴግ ክብሩንና መልካም ስሙን አለማስደፈሩ ነው - ይሄ ነው የፓርቲው |ጀግንነት´ በዚህም ኢህአዴግ ሌላ ሽልማት ይገባዋል ባይ ነኝ፡፡ በእርግጥ ይሄንን የሚቃወሙ ወገኖች አይጠፉም፡፡ ማን ጆሮ ሰጥቷቸው እንጂ!
እንግዲህ የኢህአዴግን መታወቂያ ባህርያት እያነሳን አይደል... በነካ እጃችን እንቀጥላ! ምናልባት የሚያሸልመው ከሆነ ሽልማቱ እንዳያመልጠው በሚል ነው ታዲያ! አዳዲስ ስሞች በማስተዋወቅ ወይም ታርጋዎችን በመለጠፍ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታሪክ እንደ ኢህአዴግ በስፋት የተንቀሳቀሰ ማንም የለም፡፡ ኪራይ ሰብሳቢ፣ ጥገኛ፣ መርዶ ነጋሪ፣ ኒዮሊበራሊስት፣ ነውጠኞች፣ የቀለም አብዮት አቀንቃኞች፣ ወዘተ የእነዚህ ሁሉ ስያሜዎች የኮፒራይት መብት የማን እንደሆነ ጠይቁ... የኢህአዴግና የኢህአዴግ ብቻ ነው፡፡ እና ሽልማት ይበዛበታል ትላላችሁ? ይበዛበታል ማለት ንፉግነት እንጂ ሌላ ምን ሊባል ይችላል! የአምዱ አንባቢያንም ሆኑ አፍቃሪ ኢህአዴጐች ዛሬ ለምን ስለሽልማት እንዳነሳሁ ይገባቸዋል ብዬ እገምታለሁ፡፡ የዓመቱ ማጠቃለያ እየተቃረበ በመሆኑ እንጂ ከበስተጀርባው ሌላ አጀንዳ እንደሌለው ይታወቅልኝ፡፡ ከዚህ አንፃር ፍትሃዊ ለመሆን ያግዘን ዘንድ (ሽልማቱ ሌሎችንም ያዳርስ ዘንድ) ሌሎች የውድድር ዘርፎችን ማከል ግድ ሆኖብናል፡፡ በዚሁ መሰረት በአገራችን ራሳቸውን ..ሳይለንት.. ላይ በማድረግ (ዝምታን በመምረጥ) ተሸላሚ የሚሆኑ ሁለት የህብረተሰብ ክፍሎች ተመርጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ ምሁራንና የኢትዮጵያ ድምፃውያን፡፡ ምሁራኑ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊው ህይወት አያገባንም ብለው በዝምታ ድባብ ውስጥ እንደሚገኙ እማኝ መጥራት አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ ዋሽተሃል የሚለኝ ካለ እስቲ ባለፉት 12 ወራት አንድ የተነፈሱትን ቃል በጐም ይሁን ክፉ ይጥቀስልኝ፡፡ በምን ጉዳይ ነው ያላችሁት?
ለምሳሌ በኑሮ ውድነቱ፣ ወይም በዋጋ ተመኑ አሊያም በድርቁ ወዘተ ወዘተ... እኔ በበኩሌ ሲያስነጥሱም እንኳን ሰምቼያቸው አላውቅም (እንደው ለመሆኑ እየተነፈሱ ነው?) መቼም ኢህአዴግ ሁሉንም አባል አድርጓቸዋል ብዬ አላምንም፡፡ ከሆነ ግን ኢህአዴግ በዚህም ሊሸለም ይገባዋል ባይ ነኝ፡፡ (ይለይለት XNGÄþH) የድምፃውያኑ እንኳን የታወቀ ነው - መኖራቸውን የምናውቀው በአዳዲስ አልበሞቻቸው ነበር፡፡ እሱ ደሞ እንደናቀፈን ቀርቷል፡፡ ስለዚህ ክርክሬ ሚዛን ደፍቷል ማለት ነው፡፡ እናም ራሳቸውን ሳይለንት ላይ በማድረግ የዘንድሮ (የ2003) ተሸላሚዎች ምሁራንና ድምፃውያን ሆነዋል - ያለአንዳች ድምፀ ተዓቅቦ! የዓመቱን ሽልማት ለማዳረስ ሌላ የከፈትነው የውድድር ዘርፍ በውዝግብ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ባልተናነሰ ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን ያገኘ ተቋም የሚል ሲሆን ተሸላሚው የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አመራሮችና አንዳንድ ዲያቆናት ሆነዋል - ያለ አንዳች ድምፀ ተዓቅቦ!
ተመልካች ያጣና የፈዘዘ የደነዘዘ የቲቪ ፕሮግራም በሚለው ምድብ ተቃዋሚ አልባው ..ፓርላማ.. ያለምንም ተቀናቃኝ አሸናፊ ሊሆን በቅቷል፡፡ እርስ በእርስ በመጋጨትና እንደ ዱላና ስለት የመሳሰሉ ጥንታዊና ኋላ ቀር የጦር መሳሪያዎችን ጥቅም ላይ በማዋል የዘንድሮ ተሸላሚ መኢአድ ሆኗል - ያለማንም ተቀናቃኝ!
በቀጣዩ ዓመት (በ2004 ማለት ነው) የግል ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያ ፈቃድ አልሰጥም (ጠያቂም ቢኖር) በማለት ፈቃድ ያለመስጠት እቅድ የያዘና ይሄንንም ይፋ ያደረገ ብቸኛ የመንግስት መ/ቤት ደግሞ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በመሆን ብቸኛው ተሸላሚ ሆኗል - በልዩ የውድድር ዘርፍ! በ2003 ዓ.ም. የተለያዩ ፈተናዎችንና ውጣ ውረዶችን ተቋቁሞ በማለፍ ናቱን ያሳየው የንግድ ማህበረሰብ ደግሞ የናት ተሸላሚ ሆኗል፡፡ አሁን ደግሞ ዘንድሮ ትኩረታችንን የሳቡ ጉዳዮችን እናስታውስ - የህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዢ ቀዳሚውን ስፍራ ይወስዳል፡፡ የኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪም ሌላው ትኩረት የሳበ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ከሆሊውድ ጋር የሚስተካከል ፊልም ተሠርቶ እንዳይመስላችሁ. . . በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ይመረቃል በሚል ልዩ ማስታወቂያው ነው የትኩረት ዒላማ ሊሆን የበቃው፡፡
በመጨረሻ አንድ የተዘነጋ የውድድር ዘርፍ ተገኝቷል፡፡ ይኸውም የአባላት ቁጥሩን ከ100 ሺዎች ወደ 4 ሚ. ገደማ በማድረስ (የአዲስ አበባ ከተማን ነዋሪ የሚያህል ማለት ነው) ኢህአዴግ የህይወት ዘመን ተሸላሚ ሆኗል፡፡እስካሁን የውድድሩን ዘርፎችና የአሸናፊዎቹን ዝርዝር ተመልክተናል፡፡ አሁን ስለሽልማቱ እናውራ፡፡ ለመሆኑ የሽልማቱን ነገር በገንዘብ የሚደግፈን ማን ይሆን? ምናልባት የኢህአዴግ ደጋፊ ነጋዴዎች ፎረም ወይስ ራሱ ኢህአዴግ? መቼም ለሽልማትም ቦንድ ግዙ xNLM ለነገሩ አሸናፊዎቹ ከታወቁ ሽልማቱ bþqRS በኑሮ ውድነቱ የተነሳ በቃ TtnêL እዬዬም ሲዳላ ነው ይባል yl

 

Read 3510 times Last modified on Saturday, 27 August 2011 13:16