Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 27 August 2011 13:16

ፈረሱ ምን ሆኖ ነው እየሳቀ የሚያለቅሰው?

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ታጋይ- ፈረሱ ራሱ ታጋይ መሆኑ አኩርቶት ሳቀ፡፡ እጅ ከመስጠት መታገል የተሻለ መሆኑን ስለሚያውቅ፡፡ ድንገት ሳያስበው የትግሉ ትርጉም ተገለለት፡፡ ለካ የሚታገለው ኢ-ፍትሐዊነትን ለማጥፋት፣ መልካም የፖለቲካ አስተዳደር ለማምጣት አይደለም፡፡ የሚታገለው የታደሉትን ለማጥፋት ነበር፡፡ ነጻነታቸው ያረጋገጡትን፣ የበለጉትን፣ የሰለጠኑትን ነው የሚታገለው. . . የሚታገለው የተሻለውን ለማምጣት ሳይሆን ለማጥፋት ነው፡፡ የእሱን የበታችነት የሚመሰክረው የነሱ የበላይነት ስለሆነ እነሱን በትግል አጥፍቶ ራሱን ትልቅ ማድረግ. . . ትግል ማለት የተመቻቹትን ማጥፋት መሆኑ ሲገባው አለቀሰ፡፡

በአነስተኛና ጥቃቅን ytd‰j- ፈረሱ የሳቀው የጋዳፊ ተቃዋሚዎች ትሪፖሊ በመግባታቸው ነው፡፡ አምባገነኖች ከአፍሪካ ተራ በተራ እየተሸነፉ ነው፡፡ . . .ጋዳፊ ሽጉጡን እንደ ፔፕሲ በራሱ እጅ መጠጣት አለበት ወይስ በጠላቶቹ እጅ. . . እያለ በሳቁ መሃል እያሰበ፤ ደስታውን አጣጣመ፡፡
ለቅሶው የመጣው ጋዳፊ የተደበቀበት ሊገኝ እንዳልቻለ በተደጋጋሚ ሲወራ ተረብሾ ነው፡፡ በተጨማሪ ጋዳፊን የሚመስል ረጅም ፊት ያለው ሰው በጨለማ ጥግ ጥጉን ሲሄድ አጋጥሞት አመዱ ቡን አለ፡፡ ኔቶ እሱን ፍለጋ መጥቶ የአርከበ ሱቁን ሲገለባብጥ ታይቶት. . . አኮረፈ፡፡ ግብር ሳልከፍል በፊት ቢገለባብጡት ምን nbrbT?. . . ..ጋዳፊ እዚህ ሀገር ገብቶ መደበቅ ከፈለገ፤ የሁሉንም ነዋሪ ግብር ቢያንስ ለአንድ ዓመት መክፈል አለበት.. የሚል አቋም ይዞ ከማልቀሱ በፊት ተጽናና፡፡
የኦሪት kt»- በቴሌቪዥን የተለያዩ ሙዚቃዎች ሲመለከት ቆይቶ ሳቀ፡፡ የባህላዊ ዘፈን ያዝናናዋል ፈረሱን፡፡ ግን ያዝናናዋል እንጂ የሱን የዘመናዊ ህይወት በቀጥታ አያረካለትም፡፡ አዲሳባ ያደገ ፈረስ የእንፍራንዝን እስክስታ አብሮ እንዲወርድ አይጠበቅም፡፡ ዘመናዊ ሙዚቃ ለማየት ጓጉቶ ሲጠብቅ ትዕግስቱ አለቀ፡፡ ያለቀሰው፤ ነገሩ ገባውና     ነው፡፡ አዲስ አበባ ያደገ ፈረስ እሱ ብቻ ነው ለካ የቀረው፡፡ ሌላው ተሰዶ አልቋል፡፡ የተቀረው የከተማ ሰው በሙሉ የመጣው ከገጠር ነው፡፡ የገጠሬ ወረራ በከተማው ላይ ተካሄዷል፡፡ በቴሌቪዥን የሚቀርበውም ሙዚቃ ብዙሀኑን የሚመለከት ነው፡፡ ብዙሀኑ ከባላገር የመጣ ነው፡፡ የከተማ ልጆችን ለማግኘት እያለቀሰ EBS ቻናል ከፈተ፡፡

Read 4000 times