Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 27 August 2011 13:59

ሚዛናዊ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል ወጣ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በ2011-12 የውድድር ዘመን ለሚቀጥለው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ የምድብ ድልድል ወጣ፡፡ በሌላ በኩል የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ለመጀመሪያ ጊዜ ባካሄደው የአውሮፓ ኮከብ ተጨዋች ምርጫን ሊዮኔል ሜሲ ዣቪ ኧርናንዴዝና ክርስትያኖ ሮናልዶን አሸንፎ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ሐሙስ ዕለት በወጣው የሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳታፊ የሆነው ማንቸስተር ሲቲ ከ3 የአውሮፓ ታላላቅ ሊጐች ከተወከሉ ጠንካራ ክለቦች ጋር መገናኘቱ ትኩረት ስቧል፡፡

ሪያል ማድሪድና ሊዮን በድጋሚ ኤሲሚላን እና ባርሴሎና በአንድ ምድብ መደልደላቸው አጓጊ የተባለ ሲሆን የምድብ ድልድሉ በአመዛኙ ሚዛናዊ እንደሆነ የተለያዩ ዘገባዎች ጽፈዋል፡፡ በሌላ በኩል ባለፈው የውድድር ዘመን በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግና ዮሮፓ ሊግ ላይ ተሳታፊ  ለሆኑ ክለቦች በሽልማትና በልዩ ልዩ ገቢዎች ድርሻ 750 ሚሊዮን ፓውንድ እንደተከፋፈለ ታውቋል፡፡
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ በምድብ ማጣሪያ ተሳታፊ ለነበሩ 32 ክለቦች 661 ሚሊዮን ፓውንድ ሲከፋፈል፤ በዩሮፓ ሊግ ተሳታፊ ለሆኑት የተሰራጨው ደግሞ 132 ሚሊዮን ፓውንድ ነው፡፡  የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን የወሰደው የስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ያገኘው 44.8 ሚሊዮን ፓውንድ ሲሆን 2ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው ማንዩናይትድ ግን በእንግሊዝ ክለቦች የቴቪ ገቢ ከፍተኛ ድርሻ ምንያት 46.7 ሚሊዮን ፓውንድ ደርሶታል፡፡ ለሩብ ፍጻሜ የበቁት የእንግሊዝ ክለቦች ቼልሲ 39 ሚሊዮን ፓውንድ ቶትንሃም 27 ሚሊዮን ፓውንድ እንዲሁም አርሰናል 26 ሚሊዮን ፓውንድ ደርሷቸዋል፡፡ የዩሮፓ ሊግ ሻምፒዮኑ የፖርቱጋሉ ክለብ ፖርቶ 6.9 ሚሊዮን ፓውንድ ሲደርሰው፤ ለጥሎ ማለፍ ምዕራፍ በቅተው የነበሩት የእንግሊዞቹ ሊቨርፑልና ማን. ሲቲ እያንዳንዳቸው 5.4 ሚሊዮን ፓውንድ አግኝተዋል””

 

Read 3851 times Last modified on Saturday, 27 August 2011 14:06