Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 03 September 2011 12:28

ፈረሱ ምን ሆኖ ነው እየሳቀ የሚያለቅሰው?

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የተራበው- ፈረሱ የሳቀው የዶ/ር አቡሽን የኳንተም ሜካኒክስ መጽሐፍ አንብቦ ነው፡፡ ...በመጽሐፉ ማንም ሰው ..ኳንተም.. የሚባል ነገርን እስከሆነ ድረስ፤ በህይወት ላይ ያሉ ችግሮቹን መፍታት... አንድ ቦታ ብቻ ሳይሆን አርባ የተለያየ ቦታ በአንድ ቅበት መገኘት ይችላል፡፡ ፈረሱ ሳቀ፤ ኳንተም መሆን ብቻ ነው ያለበት፡፡ ሞገድ ሆኖ ከዛሬ ተወርውሮ ትናንት ላይ ለማረፍ... የማይቻል ነገር የለም፡፡

ፈረሱ ያለቀሰው ኳንተም ለመሆን እያቀደ ሳለ የሆዱ ረሀብ ትዝ አለው፡፡ አርባ ቦታ በአንድ ቅበት መገኘት ሳይሆን የሚፈልገው፤ በኳንተም (ኳንታ) ቋንጣ ፍርፍር መመገብ ነው፡፡ ኳንተም ቋንጣ ፍርፍር የማይሰጠው ከሆነ፤ ራሱን በአርባ ኮፒ ማባዛት  ምን ፋይዳ አለው አርባ ረሀብተኛ ሆድ በአንድ ቅበት አለም ላይ እንደ አንበጣ መልቀቅ መሆኑ ሲገባው፤ ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ፡፡ የዶ/ር አቡሽ መጽሐፍ ነው በቅበት ከአርባ ማተሚያ ቤት አርባ ቅዠት ይዞ የሚወጣው፤... እውነተኛ መካሪ የት ጠፍቶ ነው በዚህ ሰውዬ ቋንጣ የቅዠት ፍርፍር የምጐመጀው ብሎ ማልቀሱን ቀጠለ፡፡
አጥብቆ ጠያቂው- የማነቃቂያ መጽሐፍት በብዛት መታተም አስደስቶት ነበር ፈረሱ የሳቀው፡፡ ብዙ የማነቃቂያ መጽሐፍትን ገዝቶ ራሱን ንቁ ብቻ ሳይሆን ብቁ ለማድረግ ሲጥር ሰነበተ፡፡
...ፈረሱ ያለቀሰው ከመጽሐፍቶቹ ባገኘው እውቀት ነቅቶ የሚጋልብበት ሜዳ በማጣቱ ነው፡፡ ፈረሱ ይኸው ሜዳው የታለ? ብሎ በእልህ መንሰቅሰቅ ጀመረ፡፡ ንቃት ሜዳ ይፈጃል ለካ፡፡ ተመልሶ ተኛ፡፡
የዘንድሮ ወንድ ፈረሱ በሴት እህቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ይፋ ወጥቶ ወንጀለኞች ለፍርድ እየቀረቡ መሆኑ አስደስቶት ሳቀ፡፡ ...በተለይ ከሁሉ አሰቃቂ የሆነው የአሲድ ጥቃት፤ በምን ዓይነት ጨካኝ አንጀት እንደተፈመ ማሰብ ስለሚከብደው መፍትሔ እየተፈለገ መሆኑ አስደሰተው፡፡ አሳቀው፡፡
ያለቀሰው፤ ከህሊናው ጓዳ አንድ ድም ሹክ ካለው በኋላ ነበር፡፡ ..ሴቶቹ ላይ የተደፋው አሲድ የመነጨው ከወንዶቹ ጨጓራ ነው፡፡.. ፈረሱ ማልቀስ ጀመረ፡፡ እንባው ማንንም እንዳይጐዳ፣ እንዳይልጥ ተጠንቅቆ፡፡

 

Read 3429 times Last modified on Saturday, 03 September 2011 12:32