የአስተዳደሩ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሀላፊ የሆኑትና የትያትር ቤቱ መሥራች ባልደረባ አርቲስት ሙሉ ገበየሁ በበኩላቸው ..መሥራቾቹ ትልቅ ቦታ ደርሰዋል፤ ቤቱ ግን እንዳለ ነው.. በማለት የአዲሱን ግንባታ ተገቢነት አስምረውበታል፡፡ እዚያው ተገኝቶ የነበረው ድምፃዊ ንዋይ ደበበ፤ ከእናት ከአባት ቀጥሎ ያሳደገን ይኼ መድረክ ነው፡፡ ኪም ኤል ሱንግ ጉንጉን አበባ ያደረጉልኝ ራስ ትያትር ለውጤት ስላበቃኝ ነው፡፡..
በቅድመ ጥናት ዲዛይን አዲስ የሚሰራው ትልቁ የራስ ትያትር አዳራሽ 1200 ወንበሮች የሚኖሩት ሲሆን ዲዛይኑ ሲከለስ ቁጥሩ 1500 ሊደርስ እንደሚችል ሥራ አስኪያጁ አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ በተለይ ለአዲስ አድማስ ገልል፡፡ በኩራባቸው ገለፃ መሠረት፤ ሰባት ፎቅ የሚኖረው የወደፊቱ ራስ ትያትር 500 ሰው የሚይዝ ሌላ አዳራሽ እና ሦስት የፓናል አዳራሾች፣ የውዝዋዜና የትያትር፣ ራሳቸውን የቻሉ ዘመናዊ ክፍሎች፣ የሙዚቃና የሥዕል ጋለሪዎች እና የአስተዳደር ሕንፃ ይኖረዋል ብሏል፡፡ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አሮጌውን ቦታ እንዳፀዳ፣ በ3000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ አዲስ ግንባታ ይጀመራል፡፡ ለዚህም ካሳ እየተጠናቀቀ ነው ብሏል ሥራ አስኪያጁ፡፡ አርቲስቶችና ሌሎች ድጋፍ ሰጪ አካላት እስከዚያ የት ይሆናሉ ብለን ለየጠቅነውም፣ ፒያሳ የሚገኘው ..እስክስታ አዳራሽ.. መድረክ ለትያትር እንዲመች ሆኖ ይዘጋጃል፣ ሌላ ቢሮ እንከራያለን ብሏል፡፡
አዲሱን የራስ ትያትር ኮምፕሌክስ እውን ለማድረግ የሐገር ውስጥ ትያትር ቤቶችን ጎብኝተናል፣ yWãcÜM የደረሱበትን ተረድተናል፣ ለአዲሱ ትውልድ ዘመናዊና የላቀ አገልግሎት እንሰጣለን ብሏል - የራስ ትያትር 14ኛ ሥራ አስኪያጅ አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ፡፡