Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 03 September 2011 12:52

ሩት ነጋ በፊልም አየርላንድን

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የ29 ዓመቷ ሩት ነጋ በፊልም ተዋናይነት በአየርላንድ ስኬታማ እየሆነችና በተለያዩ መድረኮች አገሪቱን እያስጠራች መምጣቷን የተለያዩ ዘገባዎች አመለከቱ፡፡ በቅርቡም በታዋቂዋ እንግሊዛዊ ድምፃዊት ሼሪሊ ቤሲ የህይወት ታሪክ ላይ የሚሰራውን ፊልም ሩት ነጋ በመሪ ተዋናይነት እንደምትሠራ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሼሪሊ ቤሲ በድሮዎቹ  የጀምስ ቦንድ ፊልሞች ላይ እጅግ ዝነኛ የሆኑ የማጀቢያ ሙዚቃዎችን የተጫወተች መሆኗን ያስታወሰው ቢቢሲ፤  የህይወት ታሪኳ 1 ሰዓት በሚፈጅ አጭር ፊልም ተዘጋጅ በሚቀጥለው ዓመት ለእይታ እንደሚበቃ ገልል፡፡ ከአየርላንዳዊት እናትና ከኢትዮጵያዊ አባቷ በአዲስ አበባ የተወለደችው ሩት በ4 ዓመቷ ወደ እንግሊዝ ተሰድዳ በአይሪሽ ዜግነት በለንደን ከተማ ትኖራለች፡፡ በአየርላንድ የፊልም ኢንዱስትሪ ምርጥ ተዋናይት የተባለችው ሩት፤ በበቢሲ አጫጭር የቲቪ ፊልሞችና በትያትር ስራዎቿ ትታወቃለች፡፡ ዘንድሮ በሆሊውድ ፊልም ሰሪዎች ትኩረት ያገኘችው ሩት ነጋ፤ በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ለእይታ  በሚበቃው ዘ ሳማሪታያን ፊልም ላይ ከሳሙኤል ጃክሰን ጋር ተውናለች፡፡

 

Read 3710 times Last modified on Tuesday, 06 September 2011 14:14