Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 September 2011 12:14

የመጽሐፍትነገር

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

የዚህ ጽሑፍ ዓላማ በ2003 ዓ.ም ከመጽሐፍ
ጋር በተያያዘ ስለተፈጠሩ ክስተቶች ጥቂት ነገሮችን ለማንሳት እንጂ በዓመቱስለተከሰተው ነገር ሁሉ የተሟላ ዳሰሳ ለማቅረብ  አይደለም፡፡ ትኩረቴም     ፖለቲካና ታሪክ ነክ በሆኑት ላይ እንጂ፤ እንደ ልብ ወለድ ወይም የሥነልቦና መጻሕፍትን የመሳሰሉትን አላካተተም፡፡ በመጻሕፍቱ አጠቃላይ ኋና ላይ ካልሆነ የመጻሕፍቱን ግምገማንም የሚያካትት አይደለም፡፡
የመጻሕፍት ምርቃት

2003 ዓ.ም እንደ 2002 ዓ.ም የመጽሐፍ ምርቃት ትላልቅ ድግሶችን አላስተናገደም /የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት የተገኙበትን በሸራተን ሆቴል የተዘጋጀውን ምርቃት ያስታውሷል/፡፡ የሸራተኑን ጨምሮ ከእነዚህ የ2002 ዓ.ም ምርቃት ሁለቱ የምርቃቱን ማስተዋወቂያ ተግባር ያከናወኑት የፕሮሞሽን ድርጅቶች ነበሩ፡፡ በጨረስነው ዓመት እንዲህ ዓይነት ሰፊና ወጪ ያናሩ የመጽሐፍ ምርቃት ክንውኖች ባይካሄዱም በተወሰነ ደረጃ ብዙ ታዳሚ የተካፈለባቸው ዝግጅቶች ግን ዓመቱ ወደ መጠናቀቂያው ላይ ተደርገዋል፡፡ እነርሱም በብሔራዊ ቲያትር አዳራሽ የተካሄዱት በአስቴር ነጋ አሣታሚ የታተመው፣ በጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ የተሰበሰቡ የዳግማዊ ምኒልክ የሀገር ውስጥና የውጪ ደብዳቤዎችና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ የታተመው የሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን ታሪካዊ ተውኔቶች መጻሕፍት ምርቃት ናቸው፡፡ ሁለቱም ዝግጅቶች በርካታ ሰዎችን ያስተናገዱ ከመሆናቸው በተጨማሪ ዝግጅቱን አሣታሚዎቹ ስለሥራዎቻቸውና አሠራራቸው ለታዳሚዎች ለማብራራት ተጠቅመውበታል፡፡ በሀገር ፍቅር አዳራሽ የተከናወነው አበሻው የተሰኘው የትርጉም መጽሐፍ ምረቃም ሌላው አጋጣሚ ነው፡፡ በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት የተመረቁት የሞቲቬሽን መጽሐፍና የኳንተም ፊዚክስ /ይህ ጽሑፍ ሲዘጋጅ ምርቃቱ አልተካሄደም/ መጽሐፍ ለየት ያለ ስልት በመከተላቸው ይታወሳሉ፡፡ በሁለቱም ምርቃት አዳራሹ ለማንኛውም ሰው ክፍት ሆኖ ለመታደም ግን መጽሐፉን መግዛት ግድ ነበር፡፡
የመጽሐፍ ዋጋ
በዓመቱ የመጻሕፍት ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ አሣይቷል፡፡ አዳዲስ የአማርኛ ሕትመቶች በመደበኛው የሽፋን ዋጋቸው ብቻ እስከ መቶ ሃያ ብር መሸጥ ደርሰዋል፡፡ ድጋሚ ሕትመቶችም ከ25 በመቶ የሚበልጥ የዋጋ ጭማሪ ያሳዩ አሉ፡፡ የዚህ ዋጋ መናር መንስኤ ከአጠቃላይ የኢኮኖሚ ግሽበት ጋር የሚያያዝ ቢሆንም፤ በርካታና እርስ በእርሳቸው የተያያዙ ተጨማሪ ምክንያቶችን ማንሳት ይቻላል፡፡ ከነርሱም መካከል በከፍተኛ ሁኔታ ከውጭ በሚገባ ወረቀት ላይ ጥገኛ መሆናችን፣ ዕውቀትን ለማጎልበት ታስቦ በወረቀት ላይ የሚጣል ግብር ቅናሽ አለመኖር፣ የሕትመት መጠን እጅግ አናሳነት፣ የአንባቢው ቁጥር ውሱንነት፣ ለከት የሌለው ትርፍ የማጋበስ ምኞትና አንዳንዴም አጭበርባሪነት፣ አንባቢዎች ይሄንን ለመከላከል የሚያስችል ግንዛቤም ሆነ አቅም ወይም ልምድ አለማዳበር ተጠቃሽ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በ50 ብር የሚሸጥ መጽሐፍን አሣማቃ ባልሆነ መልኩ እስከ 250 ብር ድረስ መሸጥ/መግዛት፣ የመጽሐፍ ዋጋን እየፋቁ በሌላ ቁጥር/ከፍ ያለ ዋጋ/ መቀየር፣ ከፍ ያለ ዋጋ ጽፎ መለጠፍና መሰል ሥራዎች በዚህ ዓመት የተፈጠሩ ችግሮች ባይሆኑም በዓመቱ ተባብሰው የቀጠሉ ይመስላል፡፡ የመጻሕፍት ሽፋን ላይ የሚቀመጠውን ዋጋ በቁጥር ከመጻፍ በቃላት ለመጻፍ እስከመገደድ የተደረሰው በዚህ ምክንያት nWÝÝxNÆbþãC መጽሐፍ የሚያገኙበት ዋጋ ለሕትመቱ፣ለማከፋፈያውና ለጸሐፊው ወጪና ሌሎች ተገቢ ትርፍ ጉዳዮች ታስበው ለጸሐፊው ከሚከፈለው በእጅጉ የላቀ መሆኑን መታዘብ ይቻላል፡፡ የራሳቸውን ሥራ ከሁለት እጥፍ በላይ በሆነ ዋጋ እንዲገዙ ያግባባቸው አዟሪ የገጠማቸው አንድ ፕሮፌሰር፤ ሁኔታው ክፉኛ ያናደዳቸው አለምክንያት እንዳልነበረ ስለጉዳዩ የሚከታተል ይረዳዋል፡፡ይሄ እንግዲህ አሣታሚዎችና አከፋፋዮች ተስማምተው እየሠሩበት ካለው ቀመር ጋር በተያያዘ ከሚነገረው ጫና በተጨማሪ መሆኑ ነው፡፡
መቼም የሕትመት ኢንዱስትሪው እንዲያድግ ጸሐፊው፣ አሣታሚውና አከፋፋዩ አሁን ባለው አሠራር አዟሪውም እንዲጠቀሙ ያስፈልጋል፡፡ እንዲህ ሁኔታውን ፍትሐዊ ለማድረግ ካልተሞከረ ግን አንዱ ለአንዱ ድጋፍ መሆኑ ቀርቶ እንቅፋት ሊሆንበት ስለሚችል ያስራል፡፡ አንዳንድ ጸሐፊዎች በእጅጉ በመማረራቸው ራሳቸው መጽሐፋቸውን ቤት ለቤት እስከማዞር ተገደዋል ጸሐፊዎቻችን አቅም ብዙም የሚያወላዳቸው ባለመሆኑ ለማያረካቸው ድርድር እንደተጋለጡ ጓደ ጓዳውን በማማት ብቻ ተወስነዋል፡፡
በ2003 ዓም የዚሁ ጋዜጣ ዓምደኛ ብርሃኑ ሰሙ /ራሱን እንደሚጠራው ጽፎ አደር/ በጋዜጣዋ ላይ ሲያወጣቸው ከነበሩት መጣጥፎች አቀናብሮ ከእንጦጦ ሐሙስ ገበያ እስከመርካቶ በሚል ርእስ ሲያሳትም አንድ መላ ለመዘየድ ሞክሯል፡፡ ብርሃኑ መጽሐፉን ለማሳተም ከመሄዱ በፊት ሊገዙት ወደሚችሉ ሰዎች በመሄድ ረቂቁን እያሳየ የተመነውን ዋጋ በመንገርና ኋል በማስገባት ብሩን ከወዲሁ ለመሰብሰብ ሞከረ፡፡ በዚህ መልክ ያገኘውን ብር በሌሎች መንገድ ካሰባሰበው ብር ጋር አዳምሮ መጽሐፉ የሕትመት ብርሃንን እንዲያይ አደረገ የመጀመሪያውን ሕትመትም ሙሉ ለሙሉ በራሱ ለአንባቢያን አዳረሰ፡፡ ስለዚህ በተሻለ መልኩ ተጠቃሚ ሆኖ መጽሐፉን ለሁለተኛ ጊዜ አሣተመ፡፡ ይህ መላ ግን እጅግ ፈታቃ፣ ጊዜ ያቂና ከጸሐፊዎች የዕለት ተዕለት ኃላፊነት ጋር የማይጣጣም በመሆኑ በቀላሉ የሚቻልና የሚመከር አይደለም፡፡
ለአንዳንድ አከፋፋዮችም ነገሮች አልጋ ባልጋ አልነበሩም፡፡ ለምሣሌ በከተማችን ለትምህርት፣ ዕውቀትና መረጃ ማዕከልነት እንደዕምብርት በሚቆጠረው አራት ኪሎ ከነበሩት የመጽሐፍ መሸጫ ሱቆች አንዱ ሙሉ ለሙሉ ወደካፌ አገልግሎት ሰጪነት መቀየሩ ይታወቃል፡፡ አንባቢዎች ለመጻሕፍት ግብይት ወደመሸጫ ሱቅ መሄድ መልመድ ካልቻሉ ሱቆቹ አደጋ ላይ የሚወድቁ ብቻ ሳይሆኑ አንባቢዎችም ከመጽሐፍ ዋጋ በላይ እንዲከፍሉ የሚያስገድዳቸው የተዛባ ሥርዓት ውስጥ ይበልጥ እየተዘፈቁ መሄዳቸው አይቀርም፡፡ ይሄን ስል በመጻሕፍት መሸጫ ሱቅነት ተደራጅተውም ዋጋ እየለጣጠፉ የዋጋ ማጭበርበሮችን የሚፈጽሙ እንዳሉ ሳልዘነጋ ነው፡፡
አልፎ አልፎ የሚታየው አሣታሚዎችና ጸሐፊዎች ምክንያታዊነት በጎደለው መልኩ ለመጻሕፍት የሚያወጡት ዋጋም ያነጋግራል፡፡ እንዲህ ዓይነቶች መጻሕፍትን አንባቢዎች ገዝተው ሄደው ውስጣቸውን ሲመለከቱ መጻሕፍቱ ፍጹም ዋጋቸውን የማይመጥኑ ሆነው ሊያገኛቸው ይችላሉ፡፡ በ2002 ዓም መጨረሻ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ኋለመጠይቆች ልክ እንደ ሕይወት ታሪክ አስመስሎ ባቀረበ መጽሐፍ ላይ ይሰጥ የነበረው አስተያየት ይህን ያመላከተ ነበር፡፡      
በመጻሕፍት ላይ የተደረጉ ውይይቶች
በሀገሪቱ የንባብ ክበባት ስላሉ ውይይቶች እንደሚኖሩ እገምታለሁ በተለያዩ የግጥም መጻሕፍትን አስመልክቶ ንባብና አንዳንድ ውይይቶች እንደሚደረጉ በመገናኛ ብዙኃን ሲነገር አድምጫያለሁ፡፡ ሚዩዚክ ኋይዴይ በዓመት 26 መጻሕፍትን ማስነበብ በሚል ዓላማ በየዐሥራ አምስት ቀን የሚመራው ውይይትም በመደበኛ ሁኔታ መከናወኑ በሆነ መልኩ ውይይት ለማድረግ ፍላጎት ስለመኖሩ ጠቋሚ ነው፡፡ ሸገር ኤፍ ኤምን ጨምሮ በሬዲዮ የሚተላለፉ ትረካዎችም ስለመጻሕፍቱ ሐሳብ ለማንሸራሸር ምክንያት እንደሚሆኑ በድፍረት መናገር ይቻላል፡፡ይሁን እንጂ እጅግ ዝቅተኛ ነው የሚባል ይመስለኛል፡፡
2003 ዓ.ም. ጋዜጦች ለመጽሐፍ የሚገባውን ያህል በቂ ሽፋን ያልሰጡበት ዓመት ነበር፡፡ አልፎ አልፎ በአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ በንፍታሌም/የብዕር SM¼½XNÄ!h# በአለማየሁ ገላጋይ በአዲስ አድማስ፣የአንድ ዕጅ ጣት ቁጥር የማይሞላ ጊዜያት ያህል በጥበቡ በለጠ በሰንደቅ በተመስገንና አንድ ሁለት አስተያየት ሰጪዎች  በፍትህ ላይ የወጡ የመጻሕፍት ዳሰሳ ወይም ማስተዋወቂያ ሽፋን ካልሆኑ በስተቀር ጋዜጦች ለመጽሐፍ ቋሚ ዓምድ ሰጥተው ነበር የሚያስብል አይደለም፡፡ የአውራውምባው ዳሰሳ ዓምድ በተነጻጻሪ ተደጋጋሚ የመጻሕፍት ዳሰሳን አቅርቧል፡፡ ድክመቶችን በጥልቀትና በድፍረት ለማሳየት ያለመፈለጉ ግን ሊያጭር የሚገባውን መንፈስ እንዳያጭር ሳያግደው አልቀረም፡፡ የዳሰሳ ዓምዱ ከመጽሐፍ ውጪ የሆኑ ለምሳሌ እንደ ፊልም አስተያየት የመሳሰሉም የሚሰጥበት በመሆኑም አሁንም መጽሐፍ በራሱ የሚገባውን ያህል ትኩረት አግቃቷል ለማለት እንዲያስቸግር አድርጎታል፡፡ ይሁን እንጂ አውራምባ ታይምስ መጽሐፍን በመዝናኛ ዓምድ ከማስተናገድ ወጥቶ ለብቻው ራሱን ወደቻለ ዓምድ ለመቀየር መወሰኑ ተገቢ ሆኖ አግቃቼዋለሁ፡፡
ከመጽሐፍ ጋር በተያያዘ አነጋጋሪ ሆኖ የከረመው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ ያሳተመው የፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ደቂቀ እስጢፋኖስ ነው፡፡ ከመጽሐፉ ጋር በተያያዘ በተደረገ ውይይት ላይ በፕ/ር መስፍንና በአቦይ ስብሃት መካከል ስለተደረገ የቃል ልውውጥ ላይ ተመስርቶ የፍትሁ ተመስገን ስለአቦይ ስብሃት አስተያየት መስጠቱ እንደመንስኤ ሆኖ የተፈጠረው ምልልስ ፕ/ር መስፍንን፣ አቦይ ስብሃትን፣ የቀድሞ ታጋይ አስገደ ገ/ሥላሴን፣ ፕ/ር ጌታቸውን፣ አቶ አሥራት አብራሃምን፣ ራሱ ተመስገንን እንዲሁም በብዕር ስም የጻፉ ሁለት sãCN¼t”‰n! አስተያየት ባለቤት ሆነው የቀረቡ/ና ፕ/ር ገብሩ ታረቀን ሲያወዛግብ/ሲያወያይ ከርሟል፡፡
የተነሱትም ጉዳዮች የመጽሐፉ ቀዳሚ ኋል ለምን ተቀየረ? መጽሐፉን አሁን ለማተም ለምን አስፈለገ? የመጽሐፉ ጭብጥ መልዕክት ያለንበትን ዘመንም ይገልጻል/አይገልጽም የመሳሰሉ ነበሩ፡፡ ከዚህ ውጪ የኢትዮጵያ ታሪክ እንዴት ይጻፍ የሚሉና ሌሎች ፖለቲካዊ መግፍኤ ሐሳብ የሚያንደረድራቸው አስተያየቶችን ተሳታፊዎቹና አንባቢዎቻቸው እንዲለዋወጡ ሆኗል፡፡ አጋጣሚው ውይይት ለመጫር በጎ ቢመስልም ከውይይት ወደ ንትርክነት ያዘነበለ መሆኑና ከሙያዊ ግምገማ ይልቅ ስሜትና ሽሙጥ ድብልቅ ያደላበት በመሆኑ ገንቢነቱ ላይ እንዳያጠላበት ስጋት አለቃ፡፡ የአንድን አሣታሚ ቤት አሠራርንና የቀዳሚ ኋል ተፈጥሮን በቅጡ በማየት ብቻ የሚመለስ ጉዳይን በጉንጭ አልፋ ክርክር ማዳመቅ ውይይቱን ያሳንሰዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት አቀራረብ በአግባቡ ሳይቋጭ ይቀርና ከሚያሳፍሰው ቁም ነገር የሚያስፈስሰው ይበረታል፡፡ የፖለቲካ ፍጆታውን ታሳቢ ያደረገ የሚያገኙት ጥቅም እንዳለ ሆኖ ማለት ነው፡፡
በዓመቱ ስለ መጽሐፍት ከተነገሩ ..አስገራሚ.. ወይም ..አነጋጋሪ.. ንግግሮች መካከልም የፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ..የፈረንጅ መጽሐፍ ማንበብ ካቆምኩ ቆየሁ.. የሚለው አዎንታዊ አርአያነት የጐደለው ንግግር ተጠቃሽ ነው፡፡
በመጽሔት ደረጃም ነገሩ የባሰበት ሆኖ ዓመቱ አልፏል፡፡ አዳዲስ የወጡ መጻሕፍትን በአጭሩ ለማስተዋወቅ ከመሞከር የዘለለ ነገር ግን አልተመለከትኩም ለመጽሐፍ ዓምድ እይዛለሁ ያለ አንድ በዐስራ አምሥት ቀኑ የሚወጣ መጽሔትም ዓምዱ ከመጽሐፍ ሌላ ሌሎች ሦስት ልዩ ርእሰ ጉዳዮችን ለማስተናገድ አስቦ የነበረ በመሆኑ አንድ የመጽሐፍ ግምገማ/ዳሰሳ ተራ ሊያገቃ የሚችለው ከእያንዳንዱ ሦስት ቅጽ በኋላ ያደርገዋል፡፡ ይህንኑም ቢሆን ግን አልቀጠለበትም፡፡
ለነጋድራስ ገብረ ሕይወት በ2003 የአአዩፕ ካዘጋጀው አዲሰ የመጽሐፍ አውደ ርዕይ ጋር በተያያዘ የተዘጋጀው ሲምፖዚዬም ስለጸሐፊው የህይወት ሁኔታ፣ የሐሳቡ ምንጭና ስፋት ላይ ታዋቂ ምሁራን የተካፈሉበት በርካታ የጥናት ወረቀት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ዝግጅቱ መጽሐፍን አስመልክቶ የዓመቱ ከፍተኛ ክስተት የሚባል ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ዝግጅቶችን በየጊዜው ማካሄድ አስቸጋሪ ቢሆንም በዓመት ሁለትም ሦስትም ጊዜ ማድረግ ጥቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡የጥናቱ ስብስብ በመጽሐፍ መልክ ቢወጣም ሌላ ዕውቀት ይሆናል፡፡ ለጊዜው ትኩረቴ ባይሆንም ደራሲ አዳም ረታን ከአንባቢዎቹ ለማገናኘት የተዘጋጀው መርሃ ግብርም ያልተለመደ ከመሆኑ ባሻገር ለውይይት ዕድል መፍጠሩ ይበል የሚያሰቃ ነው፡፡
የመጻሕፍት ትኩረተ ጉዳዮች
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ታሪክ ነክ ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥኑ መጻሕፍት የመጽሐፍ ገበያውን ተቆጣጥረውታል፡፡ እነርሱም ጠቅላላ ታሪክ፣ የጦር ኋዳ ውሎዎች፣ በተለያዩ ኃላፊነት ያለፉ ሰዎች ግለ ታሪክና የሕይወት ታሪክ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የብሔረሰብ ታሪክ ናቸው፡፡  በ2003 ዓ.ም የመጀመሪያ ወራት ላይ በጀርመን ራዲዮ ጣቢያ የተሠራ ፕሮግራም ጋሽ አስፋው ዳምጤና ጋሽ ደረጀ ገብሬን ጋብዞ ያነጋገረበት ርእሰ ጉዳይ ታሪክ ነክ /ኢ-ልብወለድ/ ሥራዎች ከልብወለድ ሥራዎች ይልቅ እየበረከቱ ሄደዋል የሚል አስተሳሰብ በመስፋፋቱ ነበር፡፡ ከዚያ ወዲህም ይህ ነው የሚባል ለውጥ አልነበረም፡፡
አአዩና ያሳተማቸው ..የጐጃም ትውልድ በሙለ ከባይ እስከ አባይና.. ..የሐበሻ ጀብዱ.. የትርጉም ሕትመት የታሪክ መረጃዎችን ተደራሽነት የሚጨምር ዓይነት ነው፡፡ በጠቅላላ ታሪክ ዙሪያ ረጅም የታሪክ ምጣኔ ጊዜን ያካተተው የጋዜጠኛ ፍስሃ ያዜ መጽሐፍ 5 ሺህ ዓመት የኢትዮጵያ ታሪክ ከኖኅ እስከኢህአዴግ የመጀመሪያው ክፍል እስከ ምኒልክ ዘመን ድረስ በመሸፈን ያልተለመደ ክንውን ነበር፡፡‹‹ታሪክ›› ለመጻፍ በሚደረገው ሙከራ በዓመቱ የተስተዋለ ነገር ቢኖር የጦር ኋዳ ውሎዎችን አስመልክቶ የሚታተም መጽሐፍ ጋብ ማለቱ ነው፡፡በየማነ የቀረበው የበሻይ አውአሎምና የኢትዮጵያ ስለላ ታሪክ ታሪክም በይዘቱ ሊያስተላልፍ የሞከረው የትርጉም መልዕክት አነጋጋሪነት እንዳለ ሆኖ የዓመቱ ለየት ያለ ሥራ ነው፡፡ክልሎች ስፖንሰር እያደረጉ የሚያሳትሟቸው መጻሕፍትም በ2003ም ቀጥሏል፡፡ በዓመቱ የመጨረሻ ወር የተመረቀው የሲዳማ ሕዝብ ታሪክ በዚህ ክፍል የሚመደብ  ነው፡፡ በሐበሻ ጀብዱ መጽሐፍ ጀግንነቱ የተነገረለትን ..አብቹን.. የትውልድ ቦታ ለማሰብ በመጽሐፉ መንስኤነት አንድ ፕሮፌሰር ሰላሌ እስከመሄድ መድረሳቸው መጽሐፉ ከአሁኑ ተጽእኖ መፍጠር የጀመረ መሆኑን ያመላክታል፡፡
ከፖለቲካ ነክ ጽሑፍ ረገድ የቀድሞው ቅንጅት ሰዎችና የገዢው ፓርቲ ትግል ሂደት ዘገባ xNtnH\ የፍትህ ሁኔታውን እንዴት እንደሚያየው በጻፈው መጽሐፍ\ ትረካው ገና ያላለቀ መሆኑን አመልክቷል፡፡ በዚሁ ዓመት ከእስር የተፈታችው ብርቱካን ሚደቅሳም ግለ ታሪኳን እንደምትጽፍ ነግራናለች፡፡ ተነግሮ የሚያልቅ የማይመስለው የነገረ ኢህአፓ አንዱ ምልከታም በታክሎ ተሾመ ቀርቦልናል፡፡ የፕ/ር መስፍን በአንድ ወገን የክህደት ቁልቁለትን ዳግም ዕትም በሌላ ወገን ስለ ኢትዮጵያ ባህል፣ ፖለቲካ፣ ሥልጣን፣ ዲሞክራሲና ምርጫ ከተጻፉ ከሁለትና ሦሥት ዐስርት ዓመታት በላይ የሆኑ መጣጥፎች የተካተቱተበት መጽሐፍም በዚሁ ዓመት የታተመ ነው፡፡ በቋንቋ እክል ምክንያት ስለውስጥ ይዘቱ መናገር ባልችልም በሙሉጌታ ደባልቀው/የጋላህቲ ሠጊ ጸሐፊ/ የተጻፈው እና ማጋለጥን ያለመው በአሥራት አብርሃም ተዘጋጅቶ በመጠነኛ አርትኦት እንደገና የታተመው ከአገር በስተጀርባ መጽሐፍም በዓመቱ ስለህወሐት የተጻፉ ናቸው፡፡ ከፖለቲካዊ የሕይወት ታሪክም በ..ፍትሁ.. ዳንኤል ተፈራ ተጽፎ፣ ዓመቱ ወደመገባደዱ ላይ የወጣው የቀድሞው ፕሬዚዳንት የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የነጋሶ መንገድ መጽሐፍም የዓመቱ ትሩፋት ነበር፡፡ ናይልን አስመልክቶ የወጣ መጽሐፍ ሦስት መድረሱም ርዕሰ ጉዳዩን የዓመቱ ከአንድ በላይ መጽሐፍ የታተመለት ያደርገዋል፡፡
በጋዜጣና በድረ ገጽ ላይ ሲያወጧቸው የነበሩትን ጽሑፎች በመጽሐፍ መልክ ማሳተምም በ2003 ዓ.ም የመጽሐፍ ምርት ላይ የራሱን አሻራ አሳርፏል፡፡ ከላይ የጠቀስኩት የብርሃኑ ሰሙ መጽሐፍ፣ የዳንኤል ክብረት ጠጠሮቹ፣ የአቤ ቶክቻው ስላቆች፣ የመሐመድ ሰልማን የፒያሳ ልጅ እዚህ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡ እንዲህ ዓይነቶቹ ሕትመቶች በጋዜጣውና በጽሑፉ ጸሐፊ መካከል አንዳንድ ሽኩቻ ሊያስነሳ የሚችል ቢመስልም ባመዛኙ በስምምነት ተፈጽሟል፡፡ ለነገሩ በሃገራችን የአንዳንድ ጋዜጠኞች ክፍያ ማነስ አንጻር  የመብት ጥያቄ ጸሐፊዎቹ ላይ ቢያነሱ ማስተዛዘቡ አይቀርም ነበር፡፡ ጸሐፊዎቹም ከአንድ ሁለት እትሞቻቸው በኋላ ሌላ ወጥ ሥራ ቢሠሩና ባይሰለቹ ይመረጣል፡፡     
mA¼ፍት አታሚዎች
የዓመቱን በርካታ መጽሐፍት በማተም ሮሆቦት፣ ብራና፣ ንግድ ማተሚያ ቤት፣ አልፋ እና ኤክሊፕስ ማተሚያ ቤቶች ተጠቃሽ ሲሆኑ፣ በማጣበቂያው ጥንካሬን በአግባቡ የሚያካፍል በመሆኑ እና ተገቢውን ቅርጽ በመጠበቅ ኤክሊፕስ ቀዳሚ ሊባል ይችላል፡፡
የኤክሊፕስ ወረቀቶች ንፁህና ለስላሳ ለእጅም ለዐይንም አመቺ ቢሆንም የጀርባውን ጽሑፍ አሳልፎ የማሳየት ችግር ስለሚስተዋልበት ሊያስቡበት ይገባል፡፡
በመጨረሻ 2004 ዓ.ም ብዙ አንባቢ፣ በርካታ ደረጃቸውን የጠበቁ ጸሐፊዎች፣ አትራፊ የመጽሐፍ ውይይት፣ ቁምነገር የሞላቸው ዘርፈ ብዙ የመጽሐፍ ትኩረተ ጉዳዮች፣ አስተማሪ የመጽሐፍ ግምገማ የሚስተናገድበት መልካም የመጽሐፍ ዓመት ይሁንልን፡፡
/አቶ ብርሃኑ ደቦጭ የታሪክ ባለሞያ እና የቀድሞ የአዲስ ነገር ጋዜጣ ባልደረባ የነበሩ ናቸው

 

Read 3984 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 12:17