Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 September 2011 12:23

ኬንያ የዓለም ሻምፒዮናን የማዘጋጀት ፍላጎት አላት

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በ13ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በ7 ወርቅ፤ በ6 ብርና በ4 የነሐስ bxºÝላይ ከዓለም በሶስተኛ ደረጃ ያገባደደችው ኬንያ ከታላቆቹ አሜሪካና ራሽያ ተርታ መግባቷን የአገሪቱ ጋዜጦች አወሱ፡፡ በአንፃሩ ደካማ WºðT ያስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን  ከለንደን ኦሎምፒክ በፊት ስር ነቀል ለውጥ  እንደሚያስፈልገው እየተነገረ ነው፡፡ በዓለም ሻምፒዮናው በ47 የውድድር አይነቶች 1848 አትሌቶች 203 አገራትን በመወከል ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

41 ብሄራዊ ፤ 4 የስፍራው፤ 3 የዓለም ሻምፒዮናውና 1 የዓለም ሪኮርድ በተሻሻሉበት 13ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው ከቀረበው የ7.2 ሚሊዮን ዶላር የሽልማት ገንዘብ በየውድድሩ የኬንያ ሚሊዮን ዶላር ሲያልፍ፤ የኢትዮጵያ ሩብ ሚሊዮን አልደረሰም፡፡ ከ1-3 ሜዳልያ ላገኙ አትሌቶች በሚበረከተው ድርሻ ብቻ 25 ሜዳልያዎችን ያገኘችው አሜሪካ 1 ሚሊዮን 60ሺ ዶላር ስትወስድ በ19 ሜዳልያዎች  ራሽያ 780ሺ ዶላር እንዲሁም  17 ሜዳልያዎች የወሰደችው ኬንያ 680ሺ ዶላር ተበርክቶላቸዋል፡፡ 9ኛ ደረጃ ያገኘችው ኢትዮጵያ በ5 ሜዳልያዎቿ 140ሺ ዶላር ብቻ ደርሷታል፡፡ ኢትዮጵያ በዓለም ሻምፒዮናው ስኬታማ ይሆናሉ ተብለው ካልተሳካላቸው አገራት ተመድባለች፡፡ ለለንደን ኦሎምፒክ በሚደረግ ዝግጅት ከፍተኛ ትኩረት እንደሚያስፈልግ ባለድርሻ አካላቱ እየገለፁ ሲሆን ፌደሬሽኑ በአትሌቲክሱ ውድቀት ዙርያ ተጨባጭ የለውጥ እርምጃ እንዲያደርግብዙ ናቸው፡፡
በዓለም ሻምፒዮናው ከተሳተፉ 202 አገራት አርባ አንዱ ብቻ በሜዳልያ sNºr¢Ü ውስጥ የገቡ ሲሆን አሜሪካ በ25 ሜዳልያዎች 12 ወርቅ፤ 8 ብርና 5 ነሐስ ሰብስባ አንደኛ ደረጃ ስትወስድ ራሽያ በ19 ሜዳልያዎች 9 ወርቅ፤ 4ብርና 6 ነሐስ  በማግኘት ሁለተኛ ደረጃ አግኝታለች፡፡ 3ኛ ደረጃ የያዘችው ኬንያ ደግሞ 7 ወርቅ፤ 6 ብርና 4 የነሐስ ሜዳልያ በመውሰድ ተሳክቶላታል፡፡ የኬንያው ጋዜጣ ዴይሊ ኔሽን በዓለም ሻምፒዮናው በ46 አትሌቶች በአትሌቲክስ ብቻ የተሳተፈችው ኬንያ 155 እና 73 አትሌቶች እንደቅደም ተከተላቸው በአትሌቲክስ በሜዳ ላይ ውድሮች ከተሳተፉት አሜሪካና ራሽያ ጋር በተቀናቃኝነት መሰለፏ አስደናቂ ስኬት ብሎታል፡፡ የኬንያ አትሌቲክስ ስኬት ከ11 ወራት ለሚደረገው የለንደን ኦሎምፒክ ከፍተኛ መነቃቃት ይፈጥራል ያለው ዴይሊ ኔሽን የኦሎምፒኩ አዘጋጆች በኬንያውያኑ የዓለም ሻምፒዮና ገድል መርካታቸውን አውስቷል፡፡  በአይኤኤኤፍ ለቢሮው የኪራይ ሂሳብ ይከፈልለት የነበረው የኬንያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ዛሬ ከፍተኛ ለውጥ አሳይቶ በአስተዳደርም በውድድር መድረክም ከፍተኛ ስኬት እያስመዘገበ መሆኑን ያደነቁት ሴኔጋሊያዊው ላሚን ዲያክ ናቸው፡፡ አይኤኤኤፍ በኬንያና በኢትዮጵያ አትሌቲክስ እድገት በመሻት እንቅስቃሴ እያደረገ ሲሆን ኬንያ ከተሰጣት ግምት በተሻለ እየሰራች እንደምትገኝም ይገለፃል፡፡ የኬንያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት የሆኑት ዴቪድ ኦኬዮ የአይኤኤፍ የዓለም አገር አቋራጭና የጎዳና ላይ ውድድሮች ፕሬዝዳንት ሆነው እየሰሩ ሲሆን በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽንም የምክትል ፕሬዝዳንትነት ስልጣን አግኝተዋል፡፡ ኬንያ በ2018 እኤአ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ማስተናገድ እንደምትፈልግ ዴቪድ ኦኬዮ ሰሞኑን ተናግረዋል

 

Read 3400 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 12:27