Saturday, 10 September 2011 12:31

2004 ዓ. ም በሌሎች መቁጠሪያዎች ስንት ነው?

Written by  ሰሎሞን አበበ (saache43@yahoo.com
Rate this item
(2 votes)

7514 ዓመተ ቢዛንቲን፡- በኢትዮጵያ ዓመተ ዓለም ከሚባለው ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም 10 ዓመት ቀዳሚ ነው፡፡
1720 ዓመተ ሰማዕታት - ዘመነ ዲዮቅልጥያን ማለትም ይቻላል፡፡ በሮም ዲዮክልጥያን ቄሳር ሆኖ የነገሠበትን መነሻ የሚያደርግ የዓመት መቁጠሪያ ሲሆን፤ ሮማዊት ግብ ላይም ያገለግል ነበር፡፡ የግብ ክርስቲያኖች በግፍ የተጨፈጨፉበት ጊዜ ስለነበር፤ ኮፕቲክ ቸርች ያን ዘመነ ሰማዕታት ለማሰብ ስትል ይዛዋለች፡፡ በ613 ላይ ዓመተ ዲዮክልጥያን የነበረውን ..ዓመተ ሰማዕታት..፣ ..ዘመነ ሰማዕታት.. በሚለው ተክታ መጠቀሙን ቀጠለች፡፡

2011/12 ዓመተ ዲዮናሲየስ፣ አኖ ዶሚና (ግሪጐሪያን፣ አኖ ሳሉቲስ)፡-
የግሪጐሪያን መቁጠሪያ የሚባለው ዓመቱን ከሱ በፊት በ525 ዓ.ም. ዲዮናስየስ በቆጠረው መሠረት ዓመተ እግዚእ (አኖ ዶሚኒ) ብሎ ይቆጥራል፡፡ አኖ ሳሉቲስ ደግሞ ..ዓመተ ምሕረት.. እንደሚባለው ነው፡፡ ከአኖ ዶሚኒ ጋር አንድ የሆነ የዓመት ቁጥር አለው፡፡
2010/11 ዓመተ ፈለካውያን፡- የአስትሮኖሚ ሳይንስም የራሱን የዓመት መቁጠሪያ ይዟል፡፡ ከምዕራባውያን ጋር የሚጣጣም ሲሆን 1 ኤዲ  የተባለውን 0 ኤዲ ብሎ ስለሚጀምር ከግሪጐሪያን በ1 ዓመት ያንሳል፡፡
12015/6 ዓመተ ኤሚሊያ (ሆሊሴን)
ቄሳር ኤሚሊያኒ (ሮም) 10000 ቢሲ መነሻው ያደረገ የዓመት መቁጠሪያ ሠርቶ ነበር፡፡ ከዚያ ጀምሮ ሲቆጠር 12011/12 ዓመት ስለሚሆን የኛ 2004 ዓ.ም. 12015 ዓመተ ኤሚሊያ ይሆናል፡፡
6011/12 ዓመተ ሉቺስ፡-
ፍሪማሶንሪ የተባሉ ግንበኞች የራሳቸውን መቁጠሪያ አዘጋጅተዋል፡፡ ከኤ.ዲ. 4000 ዓመት የሚቀድም ዓመትን መነሻ አድርጐ ይቆጥራል፡፡
1432/33 ዓመተ ሂጂራ (አጋር)፡-
ነብዩ መሐመድ ከመካ ወደ መዲና የተሰደዱበትን (ሃጅ) ዓመት 1 ብሎ መነሻ ያደረገ መቁጠሪያ ነው፡፡ የዓመቱ ርዝመት በጨረቃ ስለተሠፈረ ከፀሐዩ ያንሳል፡፡ አንዱ ዓመት 354 ቀኖች ነው፡፡
1389/90 ዓመተ ኢራን፡-
ኢራን ኢስላማዊት አገር ብትሆንም የጨረቃ ዓመት አትጠቀምም፤ ዓረባዊ ባሕል እንደሆነ የሚያውቁት ፋርሳውያን (አፍጋኖችም፣ ሌሎችም አሉ) የፀሐይ ዓመትን እየቆጠሩ ነገር ግን የዓመት ቁጥሩን ሐጅ የተደረገበትን መነሻ ማድረጉን ብቻ ሃይማኖታዊ አድርገው ይዘውታል፡፡ ስለዚህም ነው በኛ 2004 - 1432 ዓመተ ሂጅራ ሲሆን ለኢራናውያን ከዚህ አንሶ 1389 የሚሆነው፡፡
5113 ዓመተ ሂንዱ (ካሊዩርጋ፣ አሪያብሃታ)
..ካሊ ዩርጋን.. መነሻ አድራጊ በአሪያብሃታም የተዘጋጀ የሂንዱ መቁጠሪያ ከልደት በፊት 3102 መነሻ ያደርጋል፡፡
20067/2068 ዓመተ ሂንዱ (ቪክራማ፣ ሳምቫት)
ያው የሂንዱ አቆጣጠርን የሚጠቀም ሆኖ መነሻ ዓመቱን ከልደት በፊት 56/7 የሚያደርግ ነው፡፡
5762 ዓመተ አይሁድ፡-
በማይሞናይድስ ጥንተ ዓመት በ3761 ቢሲ የተደረገው የአይሁድ ዓመት ቁጥር ከኛ ዓመተ ዓለም ጋር አንድ ቢሆንም መነሻው ከ1400 ዓመት በላይ ወደዚህ ስለሚመጣ፣ በኛ 7504 የሆነው 5762 ነው፡፡

 

Read 3316 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 12:37