Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 September 2011 12:47

..የፖለቲካ ምህዳሩ እየተዘጋ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በ2003 ዓ.ም ከግል ህይወቴ ስጀምር የመኖሪያ ቤቴ ጉዳይ ነው የሚመጣው፡፡ ወይ ቤቱ ይታደስ ወይ ተተኪ ሌላ ቤት ይሰጠኛል የሚል ተስፋ ነበረኝ፡፡ በ2003 ክረምት ቤቱ እየፈረሰ ነው፤ አሁን ያለሁበት አንዱ ክፍል እስከ መኝታ ቤቴ ድረስ ያፈሳል፤ ሌሊት ሳልተኛ ነው የማድረው፡፡ በግሌ ያጣሁት ይሄን ነው፡፡ በፖለቲካው ዘርፍ በድርጅቶቻችን በኩል አንዳንድ ነገሮችን ብንሰራም የሚፈለገውን ያህል አልተንቀሳቀስንም፡፡ በውስጥ መደራጀትና መገማገም ቢኖርም ከህዝብ ጋር ለመወያየትና ለመከራከር እድል አላገኘንም፡፡

ከህዝብ ጋር የምንገናኘው በመግለጫዎቻችን በፕሬስ ኮንፈረንሶች ብቻ ነው፡፡ ያለቀቁን ብዙ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ነበሩ፡፡ በ2003 የነበረው ትግል በጣም ደካማ ነው፡፡ ህዝቡ የራሱን መብት ያስከብራል ብለን ጠብቀን ነበር፡፡ ይሄ አልተደረገም፡፡ በ2003 ዓ.ም የማልረሳው ክስተት በአንድ በኩል የኑሮ ሁኔታ መወደዱ እና ህዝቡ እየደኸየ መሄዱ ሲሆን ከዛም አልፎ በተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ ረሀብና ድርቅ መከሰቱ ነው፡፡በ2004 ዓ.ም የምመኘው ዋናውና ትልቁ ጉዳይ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ ማህበራት ለመብታቸው እንዲታገሉ ነው፡፡
የፖለቲካ ሂደቱ ከ1997 ጀምሮ እንዳየነው፣ ወደ ኋላ እየተመለሰ ነበር፡፡ መንግሥት በአንድ በኩል በ2002 እንዳየነው፤ ጠቅላላውን የፖለቲካ ምህዳር ማለትም የመንግሥትን አሰራር የተለያዩ ክፍሎችን (ህግ አስተርጓሚው፣ ህግ አውጪውና ህግ ፈፃሚው) በአንድ ድርጅት ፍላጐት ብቻ እየተመራ ነበር፡፡ ያ አልፎ ወደ አንድ ግለሰብ አምባገነናዊነት እየደረሰ ነው ያለው፡፡ የፖለቲካ ምህዳሩ እየተከፈተ ሳይሆን እየተዘጋ ነው፡፡ እንደ እኔ መንግስት ህዝቡንና አገርን እንዲሁም ራሱን ለማዳን የፖለቲካ ምህዳሩን እንደሚያሰፋ እና መብቶችን እንደሚጠብቅ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በህብረተሰቡ በኩል ደግሞ ከ2003 በተሻለ ሁኔታ ለመብቱ እንደሚከራከር ነው ተስፋ የማደርገው፡፡ የፖለቲካ ምህዳሩ እየተለወጠ ይሄዳል ብዬ አስባለሁ፡፡ በመንግሥት በኩል እያየለ የመጣውን ጫና ህዝቡ ካልታገለና መለወጥ ካልቻለ፣ ችግር ስለሚሆን ህዝቡ መብቱን ለማስከበር የራሱን ጥረቶች ያደርጋል ብዬ እገምታለሁ፡፡
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
(የአንድነት እና ለዲሞክራሲ ፓርቲ)
ም/ፕሬዝዳንት የመድረክ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ

 

Read 4162 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 12:52