Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 September 2011 13:04

..መና የቀረ ዓመት - 2003!´

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በ2003 ዓ.ም አጣሁት የምለው እርካታንና ነፃነትን ነው፡፡ አንድ ሰው ብቻውን አይደሰትም፤ አካባቢው ከተራበ እሱም አይጠግብም፡፡ ለመብላት ለመተኛት ለመልበስ አይደለም እኔ የምኖረው፡፡ ሌላው ሲደሰት እኔም እደሰታለሁ፤ ሌላው ሲራብ ግን እኔ ብቻዬን የምለውጠው ጉዳይ አይደለም፡፡
2003ን የማልረሳው የችግሩ ማግስት በመሆኑ ነው፡፡ የ2002 ዓ.ም ምርጫ ማለት ነው፡፡ አንድ ፓርቲ ያላገኘውን አገኘሁ፤ ያላሸነፈውን አሸነፍኩ፤ ህዝብ ወደደኝ ማለቱ ለኢትዮጵያ ምንም ፋይዳ የሌለው፣ ለወጣቱም ትምህርት የማይሰጥ ነው፡፡ በእኔ በኩል 2003 ዓ.ም. መና የቀረ አመት እለዋለሁ፡፡

በ2004 እኔ ለኢትዮጵያ የምመኝላትን ብናገር ህዝብ ይስቃል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ከረሃብ ይውጣ ብዬ ብመኝ አይሆንም፤ ደስታውንም ብመኝ አይሆንም፤ የመተማመን እና አብሮ የመሆን፤ የመተዋወቅ፤ ወጣትና አዋቂ የሚወያዩበትና የሚወስኑበት ዘመን እንዲሆን ነው የምመኘው፡፡
የኢትዮጵያን የፖለቲካ እድገት በግራፍ ማስቀመጥ ቢቻል፣ ወደ ላይ ወጥቶ በድንገት ተደርምሶ የወደቀበት ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡ ህዝቡ እና እኛ እረፍት ቤት የገባንበት፣ አፋችሁን ዝጉ የተባልንበት ጊዜ ነው፡፡
ህዝቡ ተሰብስቦ መወያየት አልቻለም፡፡ ስለዚህ 2004 ዓ.ም የመወያያ ጊዜ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በኢትዮጵያ ነፃ የሃሳብ መግለጫ መንገድ ስለሌለ በአሉባልታ ነው እየኖርን ያለው፡፡ እንደ ኮሚኒስት ታፍነን በአንድ ሃሳብ በአንድ እይታ፣ በአንድ ጆሮ ስሙ እየተባልን ስለሆነ፣ እኛ በዛ መንገድ ሄደን ስልጣኔ እናመጣለን የሚል ሃሳብ የለንም፡፡ ግን ስጋትም፤ ተስፋም አለኝ፡፡ ህዝቡ ራሱን ውሳኔ ለማንም ሳይነግር ሊወስን ይችላል፡፡ የእኛ ኃላፊነት እንግዲህ ህዝብ አላማውን እንዲመለከትና የተተበተበውን ሽቦ ሄዶ እንዳይደነቀርበት ነው፡፡
በአገሪቱ ውስጥ ፍቅር እየተገነባ አይደለም፤ ጥርጣሬ ግን በጣም እያየለ ሄዷል፡፡ አንዱ አንዱን አያምንም፤ ምክንያቱም ማን ወሬ አቀባይ ማን እውነተኛ እንደሆነ ካላወቀ በስተቀር አይነጋገሩም፡፡ ድንገተኛ ጉድ እንዳይወርድብን ከመጠበቅ በስተቀር ፖለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ ቢሰበሰቡ እንኳን (አንድ ፓርቲ ቢሆኑ) አንድ ስራ አይሰሩም፡፡ ! ህዝብ መሃል ያለ ለውጥ ያመጣል፡፡
ብዙ ጊዜ ለኢትዮጵያ ህዝብ አዲስ አመት የተድላና የደስታ እንዲሆንለት ብንመኝም እኛ ስላልን አይሆንም፡፡ ዛሬ እኔ ለኢትዮጵያ ህዝብ ተስፋ ካንተ ጋር ይሁን፤ ለልጆቻችን ነፃ የሆነ ሀገር እንዳድናመጣ እግዚአብሔር ይርዳን ብዬ እመኛለሁ፡፡
ኢ/ር ኃይሉ ሻውል (የመኢአድ ፕሬዝዳንት)

 

Read 4108 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 13:24