Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 September 2011 13:32

.ኢትዮጵያ ጠግባ የምታድር ሀገር እንድትሆን ምኞቴ ነው..

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በ2003 ዓ.ም የሥነጥበብ ሞያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ክብር ያገኘበት ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ አንድ የአገር መሪ የኪነጥበብ ሰዎችን ..ችግራችሁ ምንድነው? ችግራችሁን እንፍታ?.. በሚል ያወያዩን ጊዜ ነበር፤ ይሄ ትልቅ ክብር ነው፡፡ ትልቅ ሥራ እንዲሠራ የተዘረጋ ነገር በመሆኑ አንድ ለየት ያለ ክንውን ያደርገዋል፡፡ ሌላው ባሳለፍነው ዓመት በርካታ ትልልቅ ፊልሞች ተሠርተዋል፡፡ ለእኔ ግን በዓመቱ ከተከናወኑ ክንውኖች ዋናውን ቦታ የሚይዘው መንግሥት ለጥበቡ ትኩረት መስጠቱ ነው፡፡ ጥበቡ እንዲያድግ አንድ እርምጃ ተሄዷል ማለት ነው፡፡

በበኩሌ ለኪነጥበቡ ያደረኩትን አስተዋጽኦ በሚመለከት በመደበኝነት ሥራዬን ከመሥራት ጐን ለጐን ለበርካታ ዓመታት በአዕምሮዬ ሳመላልሰው የነበረውን ..ሔሮሺማን.. ፊልም ሠርቼ ሠጥቻለሁ፡፡ የአገሪቱ መሪ የኪነጥበቡን አካላት እንዲያነጋግሩ በተደረገ ጊዜ የሕዝብ ግንኙነት ሆኜ በርካታ ሥራዎችን ሠርቻለሁ፡፡ ገና ሌላም ነገር እሠራለሁ፡፡ በ2003 ዓ.ም አሳዛኝ የሆነ ነገር ጃፓን ላይ የተፈጠረው አደጋ ነው፡፡
በአረቡ አለም በተፈጠሩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የእኛንም ጨምሮ በርካታ ዜጐች መጐዳታቸው አሳዛኝ ነው፡፡ ሌላው በዘፈንና በፊልም ስናነሳው የነበረው አባይ ለልማትና ለሥራ መነሳቱ አስደሳች ነገር ነው፡፡
በ2004 ዓ.ም ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር የምትሆንበትን ነገር ጀምራለች፡፡ የሥራና የጀርባ አጥንት ላይ የሚቆምና ተፍ ተፍ የሚል ትውልድ ያለባት በመሆኑ የተሻሉ ነገሮች ይከሰታሉ፤ ስለዚህ ኢትዮጵያ ጠግባ የምታድር ሀገር እንድትሆን ምኞቴ ነው፡፡
ሠራዊት ፍቅሬ
የማስታወቂያ ባለሞያ፣ የፊልም ፀሐፊና ተዋናይ

 

Read 3400 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 13:44