Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 01 December 2012 14:10

ትራንስፎርመርስ “4” በቻይና ይሠራል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

የ“ትራንስፎርመርስ 4” ፊልም ዋና ዋና ትእይንቶች ቀረፃ በቻይና ለማከናወን እንደሚፈልግ ዲያሬክተሩ ማይክል ቤይ መግለፁን “ዘ ቢዝነስ ኢንሳይደር” አስታወቀ፡፡ ዲያሬክተር ማይክል ቤይ ፊልሙን ከታዋቂ የቻይና ፊልም ኩባንያ ጋር በመተባበር ለመስራት ፍላጎት እንዳለው ሲገልፅ የፊልሙ አከፋፋይ “ፐርማውንት ፒክቸርስ” ፊልሙ በቻይና መቀረፁ ለገበያው መሟሟቅ ከፍተኛ ድርሻ አለው በሚል ደግፎታል፡፡
“ሞሽን ፒክቸርስ አሶሴሽን ኦፍ አሜሪካ” ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው መረጃ፤ በሆሊዉድ የተሰሩ ፊልሞች የዓመት ገቢ ከፍተኛውን በማስገባት 2.3 ቢሊዮን ዶላር የሚገኝባት ጃፓን አንደኛ ስትሆን፣ ቻይና በ2 ቢሊዮን ዶላር ፤ፈረንሳይ በ2 ቢሊዮን ዶላር፣ ዩናይትድ ኪንግደም 1.77 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም ህንድ 1.4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ በማስገኘት እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ ወስደዋል፡፡

በ545 ሚ. ዶላር በጀት የተሰሩት ሶስቱ የትራንስፎርመር ፊልሞች በመላው ዓለም 2.67 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አስገኝተዋል፡፡ በ2014 ዓ.ም የሚሰራው አራተኛው የትራንስፎርመርስ ፊልም ወጪ 165 ሚ. ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል፡፡
ባለፉት ሶስት የትራንስፎርመር ፊልሞች ላይ መሪ ተዋናይ የነበረው ሻዬ ለበፍ በማርክ ዎልበርግ የተተካ ሲሆን ዎልበርግ በፊልሙ 4ኛ ክፍል የተዋጣለት ትወና ያሳያል ብሎ እንደሚያምን ዲያሬክተሩ ማይክል ቤይ ተናግሯል፡፡ ዘ ፐርፌክት ስቶርም፤ ዘ ኢታሊያን ጆብ እና ዘ ዲፓርትድ በተባሉ ፊልሞቹ የሚታወቀው የ41 አመቱ ማርክ ዎልበርግ፤ በፊልም ሙያው 150 ሚ. ዶላር ሃብት ማፍራቱን ሴሌብሪተሪ ኔትዎርዝ ያመለክታል፡፡

Read 3044 times