አቶ በድሩ እንደተናገሩት ባታ ጫማዎች ከፍተኛ ስም ያላቸው እና በአለም ደረጃ ተቀባይነት ያላቸው ሲሆን በአውሮፓ እና በአሜሪካ የሚመረቱ ናቸው ብለዋል፡፡ የጫማዎቹ ጥራቶች በአውሮፓ ደረጃ ተሠርተው ይዞታቸውን ሳይቀይሩ ወደ አገራችን እንደሚገቡ ገልፀው አንዳንዴ ስም ብቻ በመያዝ ጥራቱ የቀነሰ ጫማዎች በውድ ዋጋ ለገበያ እንደሚቀርቡ ገልፀው የባታ ጫማ ምርቶች ግን በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራታቸውን እንደጠበቁ ለገበያ ይቀርባሉ ይላሉ - አቶ በድሩ ለዚህም ሲባል በሽያጭ ማዕከል ውስጥ የሚሠሩትን ሠራተኞች በኬንያ ማሠልጠኑን የተናገሩት ስራ አስኪያጁ ለማሳያነት ዛሬ በፒያሳ በሚከፈተው የሽያጭ ማዕከላት ስራውን እንደሚጀምር ገልፀው፤ በቀጣይ በክልል እና በተለያዩ የአዲስ አበባ ከተሞች የመሸጫ ማዕከሎች እንደሚኖሩ እና በቀጣይም የጀመሩትን የፋብሪካ ግንባታ በማጠናቀቅ የባታ ጫማዎችን በአገራችን ለማምረት መታሰቡን ገልፀዋል፡፡