ፍፁምነት ነበር ዋንኛ ምኞቱ
የፈጠረው ቅኔ ይጋባል ለስንቱ
ልክ እንደራሱ ኪስ፣ ልክ እንደመዳፉ
የሰው ልጅ ማጥፋትን ያውቀዋል በቅጡ
ሠራዊት፣ ክፍለ - ጦር እንደ ጉድ ይወዳል
እሱ የሳቀ እንደሁ
የፓርላማው ሰዎች በሳቅ ይመታሉ -
ይንፈቀፈቃሉ!
እሱ ካለቀሰ
በየጐዳናው ላይ ትናንሽ ህፃናት እንደጉድ ያልቃሉ!
ጃንዋሪ 1939
W.H. Auden
ገጽ 80
Saturday, 15 December 2012 13:54
በጨካኝ ሰው መቃብር ላይ የተፃፈ ጥቅስ
Written by ትርጉም ነ.መ
Published in
የግጥም ጥግ