Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 17 September 2011 09:37

ኢትዮጵያዊው ያዘጋጀው ፊልም በባርሴሎና ቴሌቪዥን ይታያል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ኢትዮጵያዊው የፊልም ባለሙያ ዮሐንስ ፈለቀ ከስመ ጥሩ የስፔን ፊልም አዘጋጅ ቤንቱራ ዱረል ጋር ያዘጋጀው ባለ 35 ሺህ ዩሮ በጀት ፊልም በሚቀጥለው ሳምንት  በባርሴሎና ቴሌቪዥን የሚታይ ሲሆን በዚህ ሳምንት በቱርክ አንካራ በተጀመረው ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል እየተሳተፈ ነው፡፡ በጐዳና ተዳዳሪ ወጣቶች ሕይወት ላይ ተመስርቶ “The Hidden Smile” በሚል የእንግሊዝኛ ርእስ የተሰራው ፊልም የእንግሊዝኛና የስፓኞል መግለጫ (Subtitle) አለው፡፡ የዘጠና ደቂቃው ባለ ሦስት ክፍል  ፊልም ሁለት ክፍል ተሰርቶ ተጠናቋል፡፡

ዮሐንስ ፈለቀ የኤዥያ ቢዝነስ ዘጋቢ ሲሆን የኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብት አስመልክቶ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ባደረገው ልዩ ቃለምልልስ፣ ሳምራዊ በተሰኘው ባለ ሁለት ክፍል ፊልሙ፣ “Just for one Day” እንዲሁም “Where is my Dog?” በተሰኙ አጫጭር የእንግሊዝኛ ፊልሞቹ ይታወቃል፡፡ በስፔኑ የባርሴሎና ቴሌቪዥን ጣቢያ የሚታየውን ፊልም እንዲሰራ የተመረጠው b”Where is my Dog?” ፊልሙ ሲሆን ፊልሙ መጀመርያ በብራዚል ሊሰራ ከታቀደ በኋላ በኢትዮጵያና በስፔን መሰራቱን ማወቅ ተችሏል፡፡

Read 3311 times

Latest from