Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 17 September 2011 09:51

አርቲስት አቤል በቶሮንቶ እየገነነ ነው

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

የ21 ዓመቱ የአርኤንድቢ ሙዚቃ አቀንቃኝ አቤል ተስፋዬ በካናዳና በአሜሪካ በሥራው እየገነነ መምጣቱን ..ሃፊንግተን ፖስት.. ዘገበ፡፡ አቤል ሰሞኑን በአሜሪካ ሊያቀርበው የነበረውን የሙዚቃ ኮንሰርት ባልታወቀ ምክንያት ሰርዞታል፡፡ ..ዘዊከንድ.. በተሰኘ ስሙ በቶሮንቶ ከፍተኛ እውቅና እያገኘ የመጣው አቤል፤ ኢትዮጵያዊ የዘር ግንድ ቢኖረውም በዜግነቱ ካናዳዊ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በኦንቶናርዮ ካናዳ ስካርድ ብሮው በተባለ አካባቢ የሚኖረው አቤል ተስፋዬ፤ ከ2008 ጀምሮ በድምፃዊነት እየሰራ ሲሆን ኤክስኦ በተባለ የሙዚቃ ኣሳታሚ ..ሃውስ ኦፍ ባሉንስ..

በሚል የአልበም መጠርያ ዘንድሮ ለገበያ ያበቃውና 9 ምርጥ የሪሚክስ ዘፈኖች ያሉበት ስራው ተወዳጅ ሆኖለታል፡፡ ባለፈው ሳምንት በኦፊሴላዊ ድረገፁ  በነፃ የተለቀቀው  ..ዘ ዊከንድ.. የ9 ሪሚክስ ሙዚቃዎች አልበም በሁለት ቀናት ጊዜ ውስጥ በ180 ሰዎች ተገልብጧል፡፡..ሃይ ፎር ዚስ.. የተሰኘው የአቤል ዜማ ኢንትሩጅ የተባለ ፕሮግራም የመግቢያ ሙዚቃ ነው፡፡ ታዋቂ ከሆኑት የሰሜን አሜሪካ የአርኤንድቢ አርቲስቶች ድሬክ፤ ዶክ ማክኒና ኢላአንጀሎ ጋር በመስራት ላይ የሚገኘው አቤል፤ ከወር በፊት በቶሮንቶ ለመጀመርያ ጊዜ ሁለት ኮንሰርቶችን አቅርቧል፡፡ ከፍተኛ እገዛ እያደረገለት ያለው የአርኤንድቢ አቀንቃኙ ድሬክ አቤል ተስፋዬ ስኬታማ አቀንቃኝ እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለኝ ብሏል፡፡

 

Read 4122 times Last modified on Saturday, 17 September 2011 09:55

Latest from