Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 September 2011 09:58

አንጋፋ ተዋናዮች ወደ ዲያሬክቲንግ አተኩረዋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በጣሊያኗ ከተማ ቬኒስ በተደረገው 68ኛው የቬኒስ ፊልም ፌስቲቫልና ሰሞኑን በተከናወነው የቶሮንቶ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ከቀዩ ምንጣፍ እስከ ግዙፎቹ ስክሪኖች አንጋፋ የፊልም ባለሙያዎች በተዋናይነትና በዲያሬክተርነት የደመቁበት ሲሆን አንጋፋ ተዋናዮች ፊልሞችን ዲያሬክት በማድረግና ሲኒማን በመተው ወደ ቲቪ ኢንዱስትሪ የመግባት ዝንባሌ እያሳዩ መምጣታቸውን ..ዘ ሆሊውድ ሪፖርተር.. ዘግቧል፡፡

ወደ ቲቪ ኢንዱስትሪው ከገቡ ታዋቂ ተዋናዮች መካከል ግሌን ክሎስ፤ አሌክ ባልድዊንና ሮበርት ዲኔሮ ተጠቃሽ ሲሆኑ ወደ ፊልም ዲያሬክቲንግ ስራ በመግባት ጆርጅ ኩልኒ፤ ማዶናና ደስቲን ሆፍማን ይገኙበታል፡፡ 22 ፊልሞች የተመረቁበት የቬኒስ ፊልም ፌስቲቫል የተከፈተው ጆርጅ ኩሉኒ ዲያሬክት ባደረገውና በመሪ ተዋናይነት በሰራበት ..አይድያስ ኦፍ ማርች.. ነበር፡፡ ጆርጅ ኩሉኒ በፊልም ዲያሬክተርነት ሲሰራ .. ዘ አይድያስ ኦፍ ማርች.. አራተኛው ፊልሙ እንደሆነ ሲታወቅ ይሄው ፊልሙ ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት በሚወዳደር የሆሊውድ ዝነኛ ታሪክ ላይ ያተኩራል፡፡ በፌስቲቫሉ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ካገኙ እንስት የፊልም ባለሙያዎች መካከል ..ደብሊው ኢ.. የተባለ ፊልሟን በዋና ዲያሬክተርነት ሰርታ ያስመረቀችው የ53 ዓመቷ ማዶና ዋንኛዋ ስትሆን በታይታኒክ ፊልም ላይ የምትታወቀው ኬት ዊንስሌት በመሪ ተዋናይነት የሠራችባቸው ሶስት ፊልሞቿ ታይተው አድናቆት አትርፋለች፡፡ አንጋፋ ተዋናዮች በዲያሬክተርነት የተሳተፉባቸው በርካታ ፊልሞች ለእይታ በበቁበት የፊልም ፌስቲቫል ላይ ..ዋይልድ ሶሎሜ.. የተሰኘ ፊልሙን ያስመረቀው አልፓቺኖ የክብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በዕድሜው አንጋፋነት በሚታወቀው የቬኒስ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ከፍተኛ ትኩረት የሳበችው ማዶና ያስመረቀችው ..ደብሊው ኢ.. የተባለ ፊልሟ በእንግሊዙ ንጉስ ኤድዋርድ 8ኛ ታሪክ ላይ ያተኮረ ሲሆን ፊልሙ ታሪክ አዛብቷል በሚል በበርካታ ሃያሲያን ተተችቷል፡፡ ማዶና ከ3 ዓመት በፊት ..ፊልዝ ኤንድ ዊዝደም.. የተባለ ፊልም ለመጀመርያ ጊዜ በዲያሬክተርነት መስራቷ ይታወሳል፡፡ የቀድሞ የትዳር ጓደኞቿ የነበሩት፤ በምርጥ ተዋናይነትና ፊልም ሰሪነት ዝና ያላቸው እነ ሲን ፔን እና ጋይ ሪቼ ወደ ፊልም ስራ እንድትገባ እንዳበረታቷት ተናግራለች - የ53 ዓመቷ ማዶና፡፡

 

Read 3738 times Last modified on Saturday, 17 September 2011 10:00