በትዊተር ድረገ ጉዳዩን በተመለከተ በሰኮንድ 8860 መልእክቶች በዓለም ዙርያ መሰራጨታቸው በቢንላደን ግድያ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ሰብሮታል፡፡ ቢዮንሴ እድሜዬ 30 ሲሞላ ልጅ እወልዳለሁ ብላ በተደጋጋሚ መናገሯን የምስራቹን በገለፀችበት ወቅት ያሳወቀች ሲሆን የመጀመርያ ልጇን ያረገዘችው ከ3 ዓመታት በፊት በምስጢር ጋብቻ ከፈፀመችው ከ41 ዓመቱ ራፐር ጄይዚ መሆኑ እጅግ አስደስቷታል፡፡ ጄይ ዚ ዘንድሮ ለቢዮንሴ ያለውን ፍቅር ለመግለ በ27 ሚሊዮን ዶላር በትሮፒካል ደሴት መሬት ገዝቶላታል ያለው ዴይሊ ሜል፤ ራፐሩ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ገቢው በቢሊዮን ዶላር የሚሰላ ሊሆን እንደሚችል ገልፆ ከዚህ ጋር በተያያዘም አዲሱ ልጇቸውን ..የቢሊዮን ዶላር ህፃን.. አስብሎታል ሲል ዘግቧል፡፡ በአሜሪካ የመዝናኛ ኢንዱስትሪ በዓመታዊ ገቢያቸው ከፍተኛነት የመጀመርያውን ደረጃ የያዙት ቢዮንሴና ጄይዚ ዘንድሮ በድምሩ 72 ሚሊዮን ዶላር አግኝተዋል፡፡