Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 September 2011 09:33

ሰው፣ ስም፣ ሰላምታ(እና ማህበራዊ ኑሮ)

Written by 
Rate this item
(2 votes)

..እግዚአብሄር አምላክም የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ ከመሬት አደረገ፤ በምን ስም እንደሚ-ሯቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው፤ አዳምም ህያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስመ እንደ ጠራው ስሙ ያው ሆነ..  
(ኦሪት ዘፍጥረት፣ ምእራፍ ሁለት፣ ቁጥር አስራ ዘጠኝ)
አንድ
የተከበራችሁ አንባብያን
ሰው ገና ሲወለድ ቀዳሚው ጥያቄ ..ወንድ ነው ሴት?.. ነው፡፡ (..አፍንጫው ልክ የሴት አያቱን.. ..ቅንድቡ መገናኘቱ ቁርጥ አጎቱን.. ወዘተ ይባላል በጎን በቅንፍ)

ከፆታው የሚቀጥለው ጥያቄ ..ስሙ ማን ይሁን?.. ነው፣ ብዙ ያወያያል (አመል ያለባቸውንም ያጨቃጭቃል) እኛ ለጊዜው ማህበረሰቦች የጂኦግራፊ አቀማመጣቸውንና የመልክ የባህላቸውን ያህል ስም ሲያወጡም ያንኑ ያህል እንደሚለያዩ እያየን እንዝናና፣ ካጋ-መንም እንደነቅ!
ኮለምበስ በፊት አዲሲ አለም ውስጥ ይኖሩ የነበሩት Red Indians የወንድ ስም Sitting Bull, Red Cloud, Eagle Eye, Galloping Stallion. የሴት ስም Fleeing Antelope, Graceful, Deer, White Dove.
Tibet አገር ከተወለድክ ስምህ የተወለድክበት ቀን ስም ነው፡፡ ለምሳሌ Tuesday:- Lobsang Rampa የሚባሉት ሰው የተወለዱት ማክሰኞ እለት ነው፡፡
ሰው ብቻም አይደለም ስም ያለው፡፡ የቤት እንስሳታችን ሁሉ የተፀውኦ ስም አላቸው፡፡ ታላላቅ የጦር ጀግኖቻችን የፈረስ ስማቸው የታወቀ ነው - ምኒልክ አባ ዳኘው፣ መኰንን አባ ቃኘው፣ ኃይለ ሥላሴ አባ ጠቅል፣ የአፄ ዮሐንስ አባት ..አባ ፈንቅል.. እያለ ይሄዳል፡፡
ከልጅነታችን ጀምሮ ስለለመድነው ከምንም አንቆጥረውም እንጃ እንዲህ ብለን ..በአርምሞ.. እናስብ እስቲ ..ስም.. የሚባል ነገር ባይኖር ኖሮ፣ አብረን የመኖሩ ጉዳይ ምን ይውጠው ነበር?..
ሁለት
|እግዚአብሔር ሰጠ፤.. እግዚአብሔር ነሳ፤ yእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን፡፡.. (መሐፈ ኢዮብ)
X¾ ባለንበት ስማችንን ሲጠሩ አቤት እንላለን (ወይም እንገላመጣለን)፡፡ ሌላ የሚገርም ነገር አለ፤ ይኸውም እኛ በሌለንበት ስማችን የራሱ ምትሀት ወይም ተአምር አለው፡፡ ለምሳሌ ያህል የሚከተሉትን ነጥቦች XNmLkT:-
..የልጆች ጊዜ.. የሚባለው የአባባ ተስፋዬ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ውስጥ፣ ልጆቹ አድገው ሀኪም ወይም ፓይለት ወይም ሌላ የሚመኙትን ከሆኑ በኋላ ምን እንደሚሰሩ ሲጠየቁ ..ወላጆቼን እረዳለሁ.. ካሉ በኋላ ..ሌላስ?.. ሲሉዋቸው፣ ..ያገሬን ስም አስጠራለሁ.. ይሆናል መልሳቸው፡፡
እንግዲህ እቺ ሀገር ስምዋ መጠራቱ ምን ይጠቅማታል? እንድያውስ ስሟን የሚጠራ ማን ወይም እነማን ናቸው? ለአገሪቱስ ምን ልዩነት ያመጣል? ለነሱስ?
የስማቸው መጠራት ልዩ እሴት እንዳለው የሚቆጥሩ ሰዎች አሉ፡፡ አንድ ሰውዬ እንዲህ ሲሉ ትዝ ይለኛል ..የቁልቢው ገብርኤል ስሜን የሚያስጠራ ልጅ እንዲሰጠኝ ለአመቱ በእግር ከድሬዳዋ እስከ ቁልቢ እየሄድኩ እንደተሳልኩ ነው፡፡ ከፈለገ ለምን የመጨረሻ ከሀዲ ከይሲ ጨካኝ አረመኔ አይሆንም!? ብቻ ስሜን ያስጠራልኝ!..
ስም ማጥፋት ምንድነው? ..ለመሆኑ ስም ይጠፋል እንዴ? ከጠፋስ የት ይሄዳል?.. የስም ማጉደፍ ዘመቻ ማካሄድ ምን ማለት ነው? ሀሜትና ይሉኝታ ባህል በሆነበት አገር ይህ ጉዳይ ከባድ ሳይሆን ይቀራል ወይ?
እዚህ ባህል ውስጥ ይሉኝታ የህሊናን ሚና ይጫወታል ቢባል ምን ያህል እውነት ይሆን ይሆን?
ሶስት  
ስም ባይኖረን ኖሮ፣ በማህበረሰብ መኖር ምንኛ ባስቸገረን ነበር!? እንዲሁም ከናታችን ቋንቋ ጋር ሰላምታን ያስተምሩናል፡፡ ..እማማን ሳማቸው!.. አባባን ሳሚያቸው!.. እየተባልን፣ ሲስሙን ከነንፍጣችን መልሰን እንስማቸዋለን ስንፈራ ስንቸር፡፡ ስላምታ ባይኖር ኖሮ ከሰው ጋር ስንገናኝ እንዴት እንጀምር ነበር? የምናውቀው ሰው ከሆነስ እንደምንም እናድበሰብሰዋለን እንበል? ከማናውቀው ሰው ጋር ስንገገናኝስ? ቆመን መፋጠጥ? ንግግሩን ማናችን ይጀምር? ምንስ ምንስ ብሎ ይጀምር? ..ላም እሳት ወለደች፡፡ እንዳትልሰው እሳት ሆነባት፣ እንዳትተወው ል ሆነባት.. የተባለው ሁኔታ ውስጥ የምንገኝ አይመስልም?
ቅድም የልዩ ልዩ ማህበረሰቦችን ስሞች እያየን እንዳደረግነው፣ አሁን ደግሞ የተለያዩ የሰላምታ አይነቶችን እያየን እንዝናና፣ ካጋጠመንም እንደነቅ!
ለክፍለ አለማችን የባህልና የስልጣኔ ምንጭ ከሆነችው ከፈርኦናዊት ግብ እንጀምር፡፡
ተራው ሰው ከፈርኦን ጋር ሊተላለፍ ሲሆን፣ ገና ፈርኦን ብቅ ሲል እንዳለ፣ በግምባሩ ተደፍቶ ጭንቅላቱ ላይ አፈር ይነሰንሳል፡፡ እና ፈርኦን ካለፈ በኋላ፣ የአንድ ባለሟል ድም ..መነሳት ትችላላችሁ.. ሲል፣ ተነስተው አፈሩን አራግፈው ወደ እለት ጉዳያቸው ይራመዳሉ፡፡
መሳፍንቱና መኳንንቱ ከፕሮቶኮል ስነስርአት ውጪ ከፈርኦን ጋር ሊተላለፍ የሆነ  እንደሆነ፣ በግምባራቸው መሬት ተደፍተው ጭንቅላታቸው ላይ አፈር መነስነስ ይኖርባቸዋል፡፡ ምክንያቱም ፈርኦን ሲባል አባቱ Horus ነው፡፡ (ፀሀይን እንደ ሰረገላው ከምስራቅ ወደ ምእራብ የሚነዳ አምላክ እሱ መሳፍንቱና መኳንንቱ (እንዲሁም ሚስቶቻቸው) ካጋጠሙትም ያው በግምባሩ ተደፍቶ ጭንቅላቱ ላይ አፈር መነስነስ ነው፣ የትህትና ትህትና ለማሳየት፡፡
ይህም በርቀት Voltaire የተናገረውን ያስታውሰናል |If God did not exist, He would have to be invented´
Anthropologist ሊቃውንት እንደሚነግሩን፣ የትም አገር ቢሆን፣ ማንም ዜጋ ከንጉስ ጋር ሲተላለፍ፣ ተሽቀዳድሞ በማጐምበስ (በመስገድ፣ እጅ በመንሳት) ትሁት ታዛዥ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡
ንጉስ በማንም ዜጋ ላይ የህይወትና የሞት ስልጣን ያለው መሆኑን እናስታውሳለን”” እንዲሁም እቺን በአምስት አመቱ የጠላት ዘመን ብቸኛ ወንድ ልጅ ያላት ሴት በጭንቀት ሰአት የገጠመችውን እናስታውሳለን ..ጌታው ሞሶሎኒ የዝጌር ታናሽ ወንድም የዛሬን ማርልኝ ሁለተኛ አልወልድም..
በየዘመኑ በአየገሩ የነበረውንና ያለውን ወታደራዊ ተጠንቀቃዊ ሰላምታ እናስብ
ለማሳረግያም አለችላችሁ ሰላምታ እንደ ቄጠማ የለመለመች፣ እንደ ጌሬዳ የተዋበች፣ ለሰጪዋም ለተቀባይዋም ፀጋን የምትለግስ፡፡ Namaste ይሏታል ህንዶቹ፣ መዳፍና መዳፋቸውን እያነካኩ፣ አንገታቸውን በትህትና እየደፉ፡፡ ሲተረጎም |I bow to the Divinity within you´ (እርስዎ ውስጥ ለሚኖረው መለኮት እሰግዳለሁ) በነሱ እምነት እያንዳንዳችን ውስጣችን ወይም ነፍሳችን መለኮት ነው፡፡ በርቀትም ቢሆን እኛ ክርስቲያን እያንዳንዳችን የእግዚአብሔር ዘለአለማዊ ትንፋሽ ነን ብለን ከምናምነው ጋር ይቀራረባል፡፡ ናማስቴ!
አራት
የተከበራችሁ አንባብያን:-
የሁፋችን አርእስት እንደ¸ÃmlKtW ..ሰው፣ ስም፣ ሰላምታ.. አብቅቷል፤ በቅንፍ ..እና ማህበራዊ ኑሮ.. ወደሚለው መሸጋገራችን ነው፡፡ አብሮ መብላት መጠጣቱን በቸልታ አልፈነው ወደ ፆታዊ ግንኙነት ጎራ እንል ዘንድ ተጋብዛችኋል፣ እኔ አስጎብኚ guide ሆኜ
የዛሬ ወጣት ፍቅረኞች ወገብና ትከሻ ተቃቅፋችሁ በመንገድ ስትዘዋወሩ የዚያን ጊዜዎቹ ቢያዩዋችሁ አይናቸውን ማመን ያቅታቸዋል፣ ስምንተኛው ሺ የደረሰ ይመስላቸዋል (ደርሶ ይሆን እንዴ ምናልባት? ለጨዋታችን ምንም ልዩነት አያመጣም፡፡)
እንበል አንዲትዋ ላይ አይንህን ጣል አረግክባትና፣ እሷ ላይ ተተክሎ ቀረ፡፡ ልብህ ከጊዜው እንጉርጉሮጋር ያዜማል.. አይን የፈጠረው ሁሉን ለማየት ነው፣ አንቺን አይቶ ሌላ (አዬ!) አለይ አለኝ ምነው?..
እንግዲህ ምን ትሆን? ከላይ እንደተገለፀው የስምና የሰላምታ ጉዳይ አስቸጋሪ ሆነብህ፡፡ ዘልለህ ..ወደድኩስ ሞትኩልሽ.. እንዳትላት ድፍረት ጠፋ፡፡ ፍቅር አሳብዶህ ድፍረቱን ቢሰጥህም እንኳ አይሳካልህም፡፡ ሴቶቹ እንደሆኑ፣ ክፋታቸው ብቻቸውን ሆነው በመንገድ አይታዩም - ቢያንስ ሁለት ናቸው፡፡  
አማላጅ ሊያስፈልግህ ነው፡፡፡ ኧረ ጉዳዩ ከባድ ስለሆነ የአማላጅ አማላጅ ይፈልጋል! በለስ ከቀናህ ወንድምህ ወይም ጓደኛህ እህትዋን ወይም ጓደኛዋን ያውቃል፡፡ የአማላጁ ሚና ለውቢቱ ደብዳቤ ማቀበል ነው፡፡
..ደብዳቤው ውስጥ ምን እላታለሁ?.. እያልክ አትጨነቅም፡፡ ደብዳቤ ፀሀፊዎች አሉ፡፡ ባይገርምህ ደሞ፣ የፍቅር ደብዳቤዎች (ማንም ለማንም ቢፋቸው) ሁሉም ቃል በቃል አንድ ናቸው - ያቺኑ ፎርሙላ ይከተላሉ፡፡ ግጥሞቹን በቃል ስለማላስታውስ፣ መንፈሳቸውን (ወይም መአዛቸውን ወይም ቃናቸውን) ብቻ L«qÜMH:-)
ስማዩ ብራና ሆኖ ባህሮቹ ቀለም ቢሆኑ፣ ያንቺ ውበት ተፎ አያልቅም መነኰሳትም፣ ፃድቃንም፣ መላእክትም ቢያዩሽ፣ በፍቅርሽ ይደነዝዛሉ ለኔ ፍቅርሽ ላሳበደኝ ምስኪን ከርታታ እዘኚልኝ፣ በአዛኚቱ እመቤታችን እማፀንሻለሁ ለደብዳቤዬ መልስ እንድትልኪልኝ... ከደብዳቤው በታች ስእል አለ፡፡ ፍላፃ (arrow) ልብ ውስጥ ተሰክቶ ያሳያል፡፡ ፍላፃው ፍቅሯ ከሷ ተወርውሮ ልብህ ውስጥ ተሰክቷል ማለት ነው፡፡
...እንበል በቀኝ ጐንህ በተነሳህባት ገዳም ቀን ደብዳቤዋ ደረሰህ፡፡ የተልእኮህ አንደኛ ደረጃ ተፈፀመ፡፡ በሁለተኛ ደረጃ በነዚያው አማላጆች መሀረብህን ትልክላታለህ፡፡ አንድ ሁለት ጊዜ አልቀበልም እያለች መሀረብህ ይመለስልሀል፡፡ አንድ ቀን ትቀበለዋለች፣ የፍቅር አምላክ ቀንቶሀል፡፡
በሶስተኛ ደረጃ እንግዲህ እሷ መሀረብዋን እንድትልክልህ የበፊቱ የአማላጅ ቀሰስተኛ ጋጋታ ይሰለሳል፡፡ ይሄ በወቅቱ ዘፈን እንዲህ
ወለቤ! ነይ መሀረቤ
ወለቤ! ነይ መሀረቤ
የመሀረቡን - ላኪ መልሱን
የመሀረቡን - ላኪ መልሱን
መሀረቡንማ - ወሰደው ለማ
መሀረቡንማ - ወሰደው ለማ
ይሄ ለማ የተባለው እድለኛ ምኞቱ ተሳካለት፡፡ ይሄ ሁሉ ውጣ ውረድ ሊሳካ ነው? ከንፈር ለከንፈር ለመሳሳም ብቻ! ከዚያ አያልፍም፣ የሰርጋችሁ እለት ..ብር አምባር ሰበረልዎ!.. ሊዘፈንላችሁ ካልሆነ፡፡
አምስት
ጠጅ ነጋዴ (..ኮማሪት..) ከሆነች ሴት ጋር ለማደርስ እንዴት ነው? ያው በአማላጅ መሄድ ይኖርብሀል፣ ወድያውም ንግድ ቤትዋ ገብተህ የማር ጠጅህን እየጠጣህ (ስካር በዚያን ዘመድ ውድ ነው ማር ይረክሳል) ሞቅ እያለህ ሲሄድ የበለጠ እያማረችህ ትሄዳለች፡፡
አምስት ምሽት ያህል እንዲህ ከተመላለስክ በኋላ እስከ ነገ ስትሰናበታት በሞቅታ ደፍረህ መሀረብህን ትተህላት ልትሄድ ትችላለህ
እስካሁን ያጫወትካችሁ አብዛኛው ሰው የሚፈመውን ስነስርአት ነበር፡፡ ቀጥዬ የማቀርብላችሁ የእውነት ታሪክ ነው፡፡ ዘመኑንም፣ ገፀባህሪያቱንም እንደ ካሜራ ላንድ አፍታ ብልጭ አድርጎ ያሳየናል፣ በተጨማሪ አጤ ምኒልክን የገዛ ህዝባቸው ለምን ..እምዬ ምኒልክ.. ወይም ..እንቅልፌ ምኒልክ.. የሚል ቅል ስም እንዳወጣላችሁ ይታያችሁ ይሆናል፡፡
ሰውየው ከኮማሪቷ ጋር አብሮ ለማደር ሶስት ጠገራ (ወይም ማርትሬዛ) ብር ከፈላት፡፡ ፍቅር መቸስ እንደ ወፍ ዘራሽ ፍሬ የትም ይበቅላልና፣ ጧት ሲነቁ ሁለቱም ፍቅር ይዟቸዋል! ጠጅ ቤቷን ዘጋችው፡፡ በንግዱ አጠራቅማው የነበረውን አንድ መቶ ጠገራ ብር ..ቧሏ.. እንዲነግድበት ሰጠችው፡፡
ፍቅራቸው እየሞቀ፣ ትዳራቸው እየለመለመ አስራ አንድ አመት ኖሩ፣ ባይሰጣቸውም ፍቅር የለገሳቸውን አንድዬ አያመሰገኑ፡፡ ነጋዴ ባል ሲበዛ በለፀገ፡፡ ዳሩ ምን ይሆናል፣ ገነት ውስጥ ሲኖሩ ..ዘመድ.. የሚባል እባብ ተላከባቸው፡፡
..አንተን የመሰለ የተከበረ፣ የጨዋ ዘር፣ ምን ጐደለኝ ብሎ ከኮማሪት ጋር ተቆራኝቶ ይኖራል? ኧረ ወድያ ተዋትና የምትመጥንህን ጨዋ ሴት ታገባለህ! ለዚች ሴትዮህ ካዘንክላት አልፎ  እየመጣህ ታጫውታታለህ.. እያሉ ጐተጐቱት፣ በዙበት፣ አሸነፉት፡፡
እንፋታ አላት፡፡ እግዜር የሰጠንን ሲሳይ እምቢ ካልክ ንብረቴን አካፍለኝ አለችው፡፡ እንቺ ይኸው የሰጠሽኝ አንድ መቶ ብር፡፡ ያን ሁሉ ንብረት አብረን አይደለም ወይ ያተረፍነው? ብትለው፣ የነገድኩት እኔ! አሻፈረኝ አለ፡፡
ወረዳ ፍርድ ቤት ከሰሰችው፡፡ ዳኛው ..እንደ ሀቁ ቢሆን አንቺ ትረቺው ነበር.. አሏት ..እኔ ግን በህጉ መሰረት መፍረድ ግዴታዬ ስለሆነ፣ አንድ መቶ ብርሽን ተቀብለሽ መሰናበት ይኖርብሻል..
ይግባኝ አለች፡፡ የዳኛው ስሜትም ፍርድም ያው ሆነ፡፡ አሁንም ይግባኝ፣ አሁንም ያው፡፡ እንዲህ  ስትል አጤ ምኒልክ ችሎት ደረሰች፡፡ የሳቸውም ፍርድ ያው ሆነባት፡፡
እጅ ነሳችና፣ ድምን ከፍ አድርጋ ..ይግባኝ ለሀብተ ጎርጊስ!.. አለች፤ ሰው ጉድ አለ፣ አጉረመረመ፡፡ አንዳንዱ ነቀፋት፣ ጥቂቱ ሀይለኛ ቅጣት በየነባት፡፡
አጤ እጃቸውን አነሱ፣ ፀጥታ ሆነ፡፡  ..ልቀቁዋት አባ መላ ጋ ትሂድ.. አሉ ..መላ ያገኝላት ይሆናል..
አባ መላ ችሎት ከሳሽና ተከሳሽ ቀረቡ፡፡ ፍርዳቸው ያው çn ሰውየው የድል ስሜት እየታየበት እጅ ነስቶ ሊወጣ ሲል፣ ..ቆይ.. አሉት፡፡ ቆመ፡፡ ..አስራ አንድ አመት አብራችሁ ኖራችሁ፡፡ ለመጀመርያው አዳር ስንት ከፈልካት?..
..ሶስት ብር..
..እንግዲያው አስራ አንድ አመት ውስጥ ስንት ሌሊት እንዳለ ስሌቱን ሰርተህ፣ ለያንዳንድዋ ሌሊት ሶስት ብሯን ከፍለህ አሰናብታት..
አጅበውት መጥተው የነበሩት ..መካር.. ዘመዶቹ ምንተ እፍረታቸውን አማላጅ ሆነው እየተመላለሱ እየጐተጐቱ እሺ አሰኙዋት፡፡
ተናግቶ የነበረው ትዳር ተመልሶ ቀጥ ብሎ ቆመ...
አምስት
የአባ መላ የስልጣን ዘመን ግማሹ በአጤ ምኒልክ ግማሹ በጃንሆይ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት ይሽከረከራል፡፡ ያንን ዘመን እነሆ ታሪካዊ የግርጌ ማስታወሻ ከተክለ ጻድቅ መኩሪያ በ1909 ..ንግስተ ነገስታት ዘውዲቲ፣ ወለቱ ለዳግማዊ ምኒልክ፣ ስይምተ እግዚአብሔር.. ተብለው በዙፋን ተቀመጡ፡፡ ...ደጃዝማች ተፈሪም ራስ ተብለው፣ ለኢትዮጵይ መንግስት አልጋ ወራሽና እንደራሴ ሆነው የራስ ወርቅ አሰሩ፡፡
በሁለቱም ዘመን ጌታ ፊታውራሪ የጦር ሚኒስትር፣ ያገር ግዛት ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ሶሶቱንም ነበሩ፡፡
ጊዜው የኮሎኒያሊዝም ስለሆነ፣ አውሮፓውያኖች (በተለይም ጣልያኖች) በንግድ ወይም በሌላ ሽፋን ወታራዊ ሰለላ ያካሂዱ ነበር፣ ወደፊት ለወረራ የሚረዳ መረጃ ለመሰብሰብ፡፡ ብዙዎቹን ሽፍቶች ይገድሉዋቸዋል ለመዝረፍ፡፡
እንበል ሶስት አብረው የመጡ የኢጣልያ ዜጎች ተገደሉ፡፡ የኢጣሊያ ቆንስል ለኢትዮጵያ መንግስት ይህን ወንጀል ሲያመለክት ጌታ ፊታውራሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ይቀበሉታል፡፡ ..ይህን ብርቱ ጉዳይ ባለን አቅም ሁሉ እንከታተላለን.. ይሉታል፡፡ ከሁለት ሶስት ሳምንት በኋላ ያስጠሩታል፡፡
..ሽፍቶቹንኮ ያዝናቸው፡፡ ይምጡማ ላሳይዎት.. ብለው ወስደው የአራት ሽፍቶች ስቅላት ያሳዩታል፡፡ ወደ አገሩ መንግስት የጌታ ፊታውራሪን ተባባሪነት እያመሰገነ ዘገባ ይልካል፡፡ (እንደ እውነቱ የሆነ እንደ ሆነ ግን፣ አራቱም የተሰቁት ባገራችን ህግ የተፈረደባቸው ወንጀሎች ናቸው፡፡ ሶስቱንም ጣልያኖች የገደሉዋቸው ..ሽፍቶች.. የጌታ ፊታውራሪ ታማኝ ወታደሮች ናቸው፡፡ ኦባ መላ አመስግው ሸልመው |bRtÜ ተግታችሁ ጥበቃችሁን ቀጥሉ.. ብለው ያሰናብቷቸዋል፡፡
ጌታ ፊታውራሪ በተዋጉዋቸው ጦርነቶች ሁሉ ድል ያደረጉ ጀግና የጦር ሀይሎች ዋና አዛዥ ናቸው፡፡ (የግል ወታደሮቻቸው ብቻ እንኳ ብዛታቸው አንድ ክፍለ ጦር ያክላል) ለሰራዊታቸው ምን ያህል እንደሚቆረቆሩ የምታሳይ አንዲት ታሪክ እቻትላችሁ፡፡
የዘማች ወታደር ሚስት ..እምነት በማጉደል.. ከአንድ ቆማጣ ውሽማዋ ጋር ..መርፌና ክር.. እንደሆኑ ተያዙ፡፡ ጌታ ፊታውራሪ ፊት አቀረቡዋቸው፡፡ ሴትየዋ ቆማጣ ውሽማዋን አዝላ ..እኔን ያያችሁ እያለች እየጮኸች የአጤ ምኒልክን ቤተ መንግስት የውጭ ካብ ሶስት ጊዜ ዞረችው (ጐደሎ ቀን ይሉታል እንዲህ አይነቱን)
ከጐደሎ ቀን ይሰውረን

 

Read 6888 times Last modified on Saturday, 24 September 2011 09:42