Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 September 2011 09:55

ላዮን ኪንግ በ3ዲ መጣ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከ17 ዓመት በፊት ለዕይታ የበቃው የካርቱን ፊልም ..ዘ ላዮን ኪንግ.. ከሳምንት በፊት በ3ዲ ለገበያ ሲቀርብ በከፍተኛ ሳምንታዊ ገቢ ቦክስ ኦፊስን እንደመራ ተገለፀ፡፡  የዋልት ዲዘኒ ፊልም የሆነው ..ዘ ላዮን ኪንግ 3ዲ.. በዓለም ዙሪያ በ2733 ስፍራዎች በሚገኙ ሲኒማ ቤቶች እየታየ ሲሆን፣ ሳምንታዊ ገቢ በሰሜን አሜሪካ ብቻ 40 ሚሊዮን ዶላር አስገብቷል፡፡ ከ17 ዓመት በፊት ላየን ኪንግ በመላው ዓለም ለእይታ በቅቶ ከ60 ሚሊዮን በላይ ተመልካች ያገኘ ሲሆን 4.6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማስገባቱ ታውቋል፡፡ ላየን ኪንግ፤ በዓለም ዙርያ ከ70 በላይ የምርጥ ፊልም ሽልማቶችን የተሸለመ ሲሆን 2 የኦስካር፣ 3 የጎልደን ግሎብ፣ 6 የቶኒ አዋርድ፣ 3 የግራሚ ሽልማቶችን ሰብስቧል፡፡ አቫተርን በ3ዲ የሰራው ጀምስ ካሜሮን፤ ሰሞኑን ..ላየን ኪንግ.. በተመሳሳይ ቴክኖሎጂ ታግዞ ለእይታ መብቃቱ የ3ዲ ተፈላጊነት መጨመሩን ያመለክታል ሲል ተናግሯል፡፡ ..ታይታኒክ..ም በቅርብ ወራት በዲቪዲ ተሰርቶ ለእይታ ይበቃል፡፡

Read 3938 times