የግጥም ጥግ

Saturday, 18 June 2022 20:35

የግጥም ጥግ

Written by
Rate this item
(7 votes)
ይችን ጨቅላ መጽሐፍ፣ የምታነቡ ሁሉአደራ ስለኔ፣ ማሪያም ማሪያም በሉ።ከሆዴ ያለውን፣ የትምርት ሽልያለጭንቅ እንድወልድ፣ እድገላገልከሃያ ስድስቱ፣ ወንዶች ፊደላትአርግዣለሁና መዝገበ-ቃላት።ስንት እልፍ አበው ናቸው፣ አርግዘውየሞቱቀኝ እጃቸው አጥሮ፣ ፊደል በማጣቱ!ለትምክህት አይደለም፣ ይህን መናገሬለማስቀናት-እንጂ፣ ሰነፉን ገበሬሃዋርያው ሲናገር ወደ ምዕመናኑለምትበልጥ ፀጋ ይላል ቅኑ አስቀኑ!ከሣቴ ብርሃን___________________________
Tuesday, 07 June 2022 07:25

እሱማ አለቀሰ

Written by
Rate this item
(2 votes)
አለቀሰ ብዕር---በዱልዱም ቢቀርጹትብዕር አለቀሰጥቁር ቀለም ሳይሆንደም እያፈሰሰ---ያላሰበው ቢጻፍ---ያሰበው ተውጦእውነት ስትጨነግፍ---እብለት ሲታይ በልጦውሸት ነፍስ ዘርቶ---ደምቆ--ገዝፎ--ጎልቶ--ሲባባሉ አበጀህ በእምባው ሲጠቀሙ---ቅጥፈት ሲሆን ቤቱህጉ መገጥገጡ መላ መጀምጀሙ---ቢሰለቸው ጊዜ አታካች ስብከቱጥቁር ቀለም ሳይሆንደም እያፈሰሰ---ብዕር አለቀሰ፡፡መቅደስ ጀምበሩ
Monday, 16 May 2022 05:43

አንድ_ቤት

Written by
Rate this item
(4 votes)
በምትነድ ሀገር ላይ አይኖርም እልልታ ባዘነች እናት ቤት አይሰማም ፌሽታበስብሰባ ብዛት አያልቅም ስሞታትናንትናን እንጂ ...........ነገን አያውቀውም የዘፈን ትዝታ!በረገፈ ጥለት - ላይደረብ ኩታጥርስን ቢነቀሱት ...........ውስጡን እያመመው አይስቅም ለአፍታ!የሰው ልኩ ከብሮ ካልሞላ ሚዛኑዓመት በዓል ተብሎ .....ቢበላ ቢጠጣ መች ይደምቃል ቀኑ ?-ከልብ ካልፈለቀ…
Saturday, 07 May 2022 15:08

ወይኔ

Written by
Rate this item
(7 votes)
ከፀጉርሽ ዘለላ ከዓይኖችሽ ሽፋሽፍትከፈገግታሽ ላሕይ ከዚያ መቃ ደረትከአለንጋ ጣቶችሽ ከሎጋው ቁመትሽበዓይኖቼ ቆንጥሬ፤ለከርሞ አዝመራእዘራው ይመስል ከልቤ ሸሸግኹትፍቅርሽን ቋጥሬ፡፡ደጅ አዳሪ ልቤንያላደበ ቀልቤንበተስፋ ሣባብል፤ከአጥሬ ነቅዬ ሳበጅልሽ አልጋ፣መደብ ስደለድል፣እኔ የሰኔ ሟች ቀልደኛ ገበሬከደጄ ላይ ሞፈር ከቁናዬም ዘሬከሠራ አካላትሽ “ለዘር” የቋጠርሁትተሰወረ ከእጄ ከጉያዬ አጣኹት፡፡ከዓይኔ ላይ…
Saturday, 30 April 2022 14:46

የግጥም ጥግ

Written by
Rate this item
(1 Vote)
የሚሰዋ ፍቅርፍሬ ዛፍ ላይ እያለኮ፤ ቢበስልም እዚያው ላይ አይበላምፍሬ መልቀም የምንለው -ሥራ እንዳለ ስናውቅ ነው፡፡ምክንያቱም፡-ያለ ስራ ፍሬ የለምያለ ስቅለትም ትንሳኤ ያለ ትንሳኤም ስርየትየስጋ ወደሙ ብስራት፡፡በሂደት ነው ፍሬ ‘ሚበስልእዛፍ ላይ አይበላም፡፡ፍሬ በስሎ የሚበላው፡-ወይ ራሱ በስሎ ሲወድቅ፤ወይ እኛ ስንለቅመው ነው፤አልያ ወድቀን መጠበቅ…
Rate this item
(2 votes)
የሞላ ሽንት ቤት ጭር ያለ ቤተሰብየተጠረገ ድስት፥ ድርቅ የመታው ሞሰብ፥ያደፈ ቄጤማበበግ በሰው እግር ፥የተደቀደቀወዙ ባንድ ሌሊት፥ ተመጦ ያለቀመጥረጊያ ሚጠብቅ ፥ወድቆ ተበታትኖትናንት ጌጥ የነበር፥ ዛሬ ጉድፍ ሆኖ፥የተወቀጠ ፊት ፥ የነጋበት ድንገት በዳንኪራ ብዛት፥ወለም ያለው አንገት ፡ :የዞረበት ናላ ፥ጌሾ ያበከተው እንኳንስ…
Page 4 of 30