ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(0 votes)
በብርሀኑ ደጀኔ የተሰናዳውና በእውነተኛ ታሪኮች ላይ ያጠነጥናል የተባለው፣ “በራስ እይታ የእማዬ ውለታ” መፅሀፍ ለንባብ በቃ።መፅሀፉ፤ የልጅነት፣ የስራ፣ የት/ቤትና ተለያዩ የህይወት አጋጣሚዎችን ያስቃኛል፤ ተብሏል። በ74 ገጽ የተመጠነው መፅሀፉ፣ በ70 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
Rate this item
(0 votes)
የቀድሞ የፓርላማ አባልና የተቃዋሚው አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት የነበሩት የአቶግርማ ሰይፉ “የተከበሩት” መፅሐፍ ለአንባብያን ቀርቧል፡፡ በ288 ገፆች ተዘጋጅቶ በ81 ብር ገበያ ላይ የዋለው“የተከበሩት” መፅሃፍ ለአንባብያን ቀርቧል መጽሐፉ፣ የፓርላማው ውሎዎችንና ሌሎችፖለቲካዊ ትዝብቶችን መሰነዱ ታውቋል፡፡ፀሐፊው አቶ ግርማ ሰይፉ፣ ከዚህ ቀደም፣“ነፃነት ዋጋው…
Rate this item
(1 Vote)
በዕውቁ ደራሲ ኸርቪንግ ዋላስ፣ “The second lady” በሚል ለንባብ የበቃውና በአብዱልመናን በሽር፣“ቀዳማዊቷ እመቤት” በሚል ወደ አማርኛ የተመለሰው ልቦለድ መፅሀፍ ለንባብ በቃ፡፡መፅሀፉ፣ ከኸርቪንግ ዋላስ፣ 33 ትልልቅ መፅሀፎች ውስጥ መሳጩና ልብ አንጠልጣዩ መሆኑ ተገልጿል።በ319 ገፅ የተቀበበው መፅሀፉ፣ በ71 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡
Rate this item
(0 votes)
በገጣሚ እፁብ ድንቅ ስለሺ የተፃፉ ከ70 በላይ ግጥሞችን የያዘው “የዘመን ሸለቆ” የተሰኘ የግጥም ስብስብመፅሀፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡መፅሀፉ በዋናነት፣በታሪክ፣ በፍልስፍና በፍቅርና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ 74 ያህል ግጥሞችን አካትቷል፡፡ በ102 ገፅ የተቀነበበው መፅሀፉ፣በ49 ብር ከ62 ሳንቲምና በ18 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡
Rate this item
(0 votes)
በደራሲ ካሳሁን ንጉሴ የተሰናዳውና መቼቱን ጎጃም ላይ ያደረገው ጥልፍልፍ መፅሀፍ፣ ለንባብ በቃ፡፡መጽሐፉ፣ በቤተሰብ መበተን፣በራስ ትግልና በተለያዩ የህይወት ጉዞ ላይ ተጠምዶ ያለፈን ወጣት የሚያስቃኝነው፤ ተብሏል፡፡ በ320 ገፅ ጥልፍልፍ ልቦለድ መጽሐፍ ለንባብ በቃ የተቀነበበ ሲሆን፣ በ95 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
Rate this item
(0 votes)
በክረምቱ ሲሠለጥኑ የነበሩ የስነ ጽሑፍ ሠልጣኞች በዕለቱ ይመረቃሉኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ጽ/ቤትና የፓን አፍሪካ ደራስያን ማዕከል እንደሚሆን የተነገረለት ህንፃ የመሰረት ድንጋይ፤ በበዓ፤ መስቀል እንደሚቀመጥ፣ የደራስያን ማህበር በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ አስታወቀ፡፡ በዕለቱ ማኅበሩ፣ በስነ-ፅሁፍ፣ በሂስ አቀራረብ፣ በስነ ግጥምና ተያያዥ ጉዳዮች ያሰለጠናቸውን ከ40…
Page 1 of 206