ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(25 votes)
በገጣሚ ሲሳይ ታደሰ /ዘ-ለገሐሬ/ የተፃፉ የግጥም ስብስቦችን የያዘው ‹‹ለፍቅራችሁ›› የተሰኘ የግጥም መድብል ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ 106 ግጥሞችን ያካተተው መድበሉ፤ “ለፍቅራችሁ” የሚል ርዕስ የተሰጠው መጽሐፉ ለህትመት እንዲበቃ ያገዙትን ሁሉ ለማመስገን እንደሆነ ገጣሚው ገልጿል፡፡ የግጥሙ መድበል ለአገር ውስጥ በ30 ብር፤ ለውጭ ደግሞ…
Rate this item
(65 votes)
በአስፋው መኮንን የተፃፈውና አስቂኝ፣ ቀልዶችና ቁምነገሮች የተካተቱበት መፅሀፍ ሰሞኑን ለንባብ በቅቷል፡፡ በአገራችን በቃል የሚነገሩ በርካታ አዝናኝና ቁም ነገር አስተማሪ ቀልዶች ቢኖሩም ብዙዎቹ በመፃህፍት ተፅፈው ስለማይቀመጡ የሚረሱና የሚደበዝዙ ይሆናሉ፤ ስለዚህም መመዝገብ አለባቸው ብሏል አዘጋጁ፡፡ በ158 ገፆች የተቀነበበው መፅሀፉ፤ በ35 ብር ለገበያ…
Rate this item
(1 Vote)
በዕውቋ ድምፃዊት ዘሪቱ ከበደ ተፅፎ የተዘጋጀው “ቀሚስ የለበስኩለት” የተሰኘ ፊልም በሚቀጥለው ሳምንት እሁድ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽና በአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል፡፡ የድራማ ዘውግ ባለው የ1፡40 ደቂቃ ፊልም ላይ፤ ድምፃዊቷ ዘሪቱ ከበደ፣ የንግድ ም/ቤት ፕሬዚዳንቷ ሙሉ ሰለሞን፣ የጃኖ ባንዱ ድምፃዊ ዲበኩሉ…
Rate this item
(1 Vote)
የአፍሪካ ሞዛይክ የፋሽንና የባህል ትርኢት በሚቀጥለው አርብ ምሽት በሸራተን አዲስ የሚካሄድ ሲሆን በዝግጅቱ አለማቀፍ የፋሽን ሞዴሎችና ዲዛይነሮች ይሳተፋሉ፡፡ የአፍሪካን ሞዛይክ ዳይሬክተር አና ጌታነህ እንደገለፀችው፤ አስራ አምስት የውጪና የሀገር ውስጥ ዲዛይነሮች በሚሳተፉበት ትርኢት፤ እውቅ የዘርፉ ባለሞያዎች ከኒውዮርክ፣ ከደቡብ አፍሪካና ከሴኔጋል ይመጣሉ፡፡…
Rate this item
(9 votes)
በእናቱ ኢትዮጵያዊ፣ በአባቱ ሆላንዳዊ በሆነው ዳንኤል ጁፕሁክ የተፃፈውና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው “አመፀኛው ክልስ” የተሰኘ መጽሐፍ ሰሞኑን በገበያ ላይ ዋለ፡፡ ደራሲው በ12 ዓመት የእስር ቤት ቆይታው ያሳለፈውን ህይወት ከወህኒ ቤት ከወጣ በኋላ በደች ቋንቋ እንደፃፈው፣ ከዚያም ወደ አማርኛ በመተርጎም እንዳሳተመው…
Rate this item
(1 Vote)
በአሚር ዩኒስ ረሐስ የተፃፈው “የምሥራቅ ፈርጦች” የተሰኘ ታላላቅ የሐረሪ ተወላጆችን ታሪክ የያዘ መፅሃፍ ባለፈው ሳምንት ለንባብ በቅቷል፡፡ ስምንት የሚደርሱ የሐረሪ ሊቃውንቶችና የታሪክ ምሁራንን የሚያስተዋውቀው መፅሃፉ፤ መታሰቢያነቱን የሥነ ጽሑፍ ባለሙያ ለነበሩት ለአብዱል ሐፊዝ ከሊፋ መሐመድ እና ለመሐመድ ኢብራሒም ሱሌይማን አድርጓል፡፡ በመጽሐፉ…