ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(1 Vote)
የእንግሊዛዊው ፀሐፌ ተውኔት ዊሊያም ሼክስፒር ድንቅ የተውኔት ስራ የሆነው “ኦቴሎ” በትግርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በመፅሃፍ ወጣ፡፡ ተውኔቱን ወደ ትግርኛ ለመመለስ አንድ ዓመት እንደፈጀበት ያስታወሰው አንጋፋው ደራሲና መምህር ኃይለመለኮት መዋዕል፤ ለዚህ ሥራው ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን የተረጎመውንና በርካታ የተውኔቱን የእንግሊዝኛ ቅጂዎች እንደተጠቀመ ገልጿል፡፡…
Rate this item
(1 Vote)
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ፤ በዶክተር ዮናስ አድማሱ አርታዒነት አምና ለንባብ ያበቃው “የዮፍታሄ ህይወትና ስራ” ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በብሄራዊ ቤተመጻሕፍት ውይይት እንደሚደረግበት ሚዩዚክ ሜይዴይ አስታወቀ።ውይይቱን የሚመሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትያትር መምህር የሆኑት አቶ አሰፋ ወርቁ ናቸው፡፡
Rate this item
(0 votes)
ደራሲና ሀያሲ ፍቃዱ ልመንህ ያዘጋጀውና ስለ ፊልም ጥበብ የሚያትተው “የአቡጄዲ ግርግር” መጽሐፍ ዛሬ ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ በጣይቱ ሆቴል “ጃዝ አምባ” እንደሚመረቅ ዮዳሔ ሕትመትና ፊልም ሥራ አስታወቀ፡፡ በዕለቱ አንጋፋው የፊልም ባለሙያ ብርሃኑ ሽብሩ በመጽሐፉ ላይ ዳሰሳ የሚያቀርብ ሲሆን የአዲስ አበባ…
Rate this item
(0 votes)
አርባ ሠዓሊዎች ትናንት ሥራዎቻቸውን በሰኔሬድ አቀረቡየሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ ሥራዎች የሚቀርቡበት “የኔታ” የተሰኘ የስዕል ኤግዚቢሽን ከትላንት በስቲያ በላፍቶ አርት ጋለሪ ተከፈተ፡፡ በኤግዚቢሽኑ የቀረቡት ሥዕሎች አዳዲስ ሲሆኑ ኤግዚቢሽኑ ለሁለት ሣምንታት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል አርባ ሠዐሊዎች ትናንት ከሰአት በኋላ…
Rate this item
(1 Vote)
በተለያዩ የህትመት ውጤቶች ላይ በሚያቀርባቸው ወጎችና መጣጥፎች የሚታወቀው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ያዘጋጀው “አራቱ ኃያላን” አዲስ መጽሐፍ በመጪው ሳምንት እሁድ 4 ሰዓት ላይ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚመረቅ “አግዮስ ሕትመትና ጠቅላላ ንግድ” አስታወቀ፡፡ በምረቃው ዕለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለ፣…
Rate this item
(3 votes)
የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሀብቶች ዝርዝር የያዘ የተፈጥሮ ፓርኮች ማውጫ ታትሞ መውጣቱን “ሀገሬ ኮሙኒኬሽን” አስታወቀ፡፡ ከትናንት በስቲያ በነፃ መሠራጨት የጀመረው ቅጽ ፩ ማውጫ፣ 118 ገፆች ያሉት ሲሆን 59 ወንዞች፣ 40 ተራራዎች፣ 26 ሐይቆች፣ 24 ፓርኮች፣ 12 ዋሻዎች እና ሌሎችም በርካታ መረጃዎችን አካትቷል፡፡…