ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(1 Vote)
የኮሜዲያን ደረጀ ኃይሌ እና አሁን በህይወት የሌለው ባልደረባው ሀብቴ ምትኩ ሥራዎች የተካተቱበት “ወርቃማው ጊዜ” የኮሜዲ ቪሲዲ ከትናንት በስቲያ ወጣ፡፡ ቁጥር 1 በሚል በቀረበው የኮሜዲ ቪሲዲ ላይ 20 የኮሜዲ ሥራዎች የተካተቱ ሲሆን፤ ቪሲዲውን እያሰራጨ ያለው “ፒያሳ ዘ አራዳ ኢንተርቴይመንት” ነው፡፡
Rate this item
(0 votes)
ከአውሮፓ የስፔን እና የፖርቱጋል፣ ከአሜሪካ ደግሞ የብራዚል፣ ኩባ፣ ቬኔዚዋላ፣ ሜክሲኮ እና አርጀንቲና ፊልሞች የሚታዩበት ስምንተኛው “የኢብሮ-አሜሪካ” ፊልም ፌስቲቫል ከትናንት በስቲያ ምሽት በጣልያን የባህል ተቋም ተጀመረ። ሐሙስ ምሽት፣ “ኤርማኖ” የተሰኘው የቬኔዙዋላ ፊልም ሲታይ፤ ትናንት “ኖሶድሮስ ሎስ ኖብልስ” የተሰኘው የሜክሲኮ ፊልም ታይቷል፡፡…
Saturday, 02 November 2013 12:08

“የዛሌፍ ፋሽን” ዛሬ ይቀርባል

Written by
Rate this item
(0 votes)
ዛሌፍ የሥነ ጥበብ እና ፋሽን ዲዛይን ተቋም፣ በታዋቂ ዲዛይነሮች የተሰሩ አልባሳት የተካተቱበት የፋሽን ትርዒት ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት በኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡ ከተቋሙ የሥራ ውጤቶች መካከል በ2003 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሂልተን የቀረበው በኮንዶም የተሰሩ አልባሳት ዐውደርዕይ ይገኝበታል።
Rate this item
(0 votes)
በኮንስታብል ጌታቸው ዳምጠው የተፃፈው “የብልህ ፖሊስ ቁልፍ ምስጢር” የተሰኘ አነስተኛ መፅሐፍ ባለፈው እሁድ ካዛንቺስ በሚገኘው ወረዳ 8 አዳራሽ ተመረቀ፡፡ ፖሊሶች ሊገነዘቧቸው በሚገቡ አምስት መልእክቶች ላይ ያተኮረው መፅሐፍ 50 ገፆች ያሉት ሲሆን ዋጋው 25 ብር ነው፡፡
Rate this item
(0 votes)
ኢትዮጵያውያን እና እንግሊዛውያን ሠዓሊዎች የሚሳተፉበት የሥዕል አውደርእይ ሰኞ ከምሽቱ 12፡30 ቦሌ አውሮፓ ሕብረት መ/ቤት አካባቢ በሚገኘው ሲዳማ ሎጅ ይከፈታል፡፡ አውደርእዩ ለአንድ ሳምንት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
Rate this item
(7 votes)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን “መጽሐፈ ቅዳሴ” ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ ተተረጎመ፡፡ ለብዙ ዘመናት “መጽሐፈ ቅዳሴ”ን በግእዝ እና በአማርኛ ስትጠቀምበት የቆየችው ቤተክርስትያኗ፤መፅሃፉን በኦሮምኛ ማስተርጎም የጀመረችው በ1999 ዓ.ም እንደሆነ ታውቋል፡፡ የመጽሐፉ መተርጎም በኦሮሚያ ክልል ላሉ አብያተ ክርስትያናት በኦሮምኛ ለመቀደስ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡ የቤተክርስትያኒቱ ቅዱስ…