ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(1 Vote)
“ሞት ያልገታው ጉዞ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ መጽሐፍ ዛሬ ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ይመረቃል፡፡ በደራሲ ሶስና ደምሴና በበየነ ሞገስ የተዘጋጀው መጽሐፉ፤ በክቡር ብላታ ደምሴ ወርቅ አገኘሁ የህይወት ታሪክ ዙሪያ የሚያጠነጥን ሲሆን በአምስቱ ዓመታት የጠላት ወረራ ወቅት ወገኖቻችን የደረሰባቸውን…
Rate this item
(2 votes)
ዘወትር ሐሙስ ከቀኑ 9-10 ሰዓት እና እሁድ ከ11-12 ሰዓት የሚቀርብ “እፎይታ” የተሰኘ የሬዲዮ ዝግጅት በኤፍኤም አዲስ 97.1 እንደሚጀምር ኪኖ ፕሮዳክሽን እና አርት ሶሉሽን አስታወቁ፡፡ ፕሮግራሙን “የወንዶች ጉዳይ” ቁጥር ፩፣ እና የ“ፔንዱለም” አዘጋጅ ሄኖክ አየለ፣ የ“ሚስኮል” ፊልም አዘጋጅ ደረጄ ምንዳዬ፣ አንጋፋዋ…
Rate this item
(0 votes)
የሰዓሊ ሳሙኤል ሀብተአብ የፎቶግራፍ ሥራዎች የተሰባሰቡበት የፎቶግራፍ ትርዒት ትናንት ምሽት ሳር ቤት አካባቢ በሚገኘው ጋለሪአ ቶሞካ መቅረብ ጀመረ፡፡ ትርኢቱ እስከ ነሐሴ 23 ለተመልካች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ነሐሴ 19 ከጧቱ 4 ሰዓት በሰዓሊው ሥራዎች ላይ ውይይት ይካሄዳል ተብሏል፡፡
Rate this item
(1 Vote)
በፈለቀ ካሳ ጥንድ ፕሮሞሽን የሚዘጋጀው የጥበብ ምሽት፣ የመጀመሪያ ዝግጅቱን ከትናንት በስቲያ ማታ ቦሌ በሚገኘው ሻላ አዳራሽ ቀረበ፡፡ በየወሩ አንድ ደራሲና አንድ ሙዚቀኛ የሚቀርቡበት ኪነጥበባዊ ዝግጅት የመግቢያ ዋጋ በግለሰብ 50 ብር ሲሆን ከዚሁ ገቢ በየወሩ ለአንድ ሕጻን 200 ብር በመመደብ አምስት…
Rate this item
(0 votes)
በጋዜጠኛና ደራሲ ቴዎድሮስ ሽፈራው የተዘጋጁ ስድስት የተረት መፃህፍት ሰሞኑን ለንባብ በቁ፡፡ “ባለማሩ ገላ ሰውዬ”፣ “ደግ ለራሱ”፣ “ደጓ ዳክዬ ”፡ “ሆዳሙ ዘንዶ”፣ “ቀብራራዋ ድመት” እና “ትንሿ ሻሼ” የተሰኙት መፃህፍት ህፃናትን እያዝናኑ የሚያስተምሩ ሲሆኑ የንባብ ልምድ በማዳበር ረገድም ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርጉ አዘጋጁ…
Rate this item
(1 Vote)
ከሁለት ዓመት በፊት በደራሲ ሊዛ ተሾመ ተጽፎ የቀረበው “አሜኬላ ያደማው ፍቅር” ረዥም ልቦለድ መፅሃፍ ተሻሽሎ በድጋሚ ለንባብ በቃ፡፡ “በፍቅር ዓለም በራስ ላይ ማዘዝ ከባድ ነው” የሚለው ልቦለድ መጽሐፍ፤ ለደራሲዋ ሁለተኛዋ ሲሆን ካሁን በፊት “ፍትህን በራሴ” የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ አብቅታለች፡፡ 268…