ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(0 votes)
የሠአሊ አዳምሰገድ ሚካኤል የሥእል አውደርእይ ከትናንት በስቲያ ተከፈተ፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም የተከፈተው አውደርእይ እስከ መጪው ረቡዕ ለሕዝብ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
Rate this item
(0 votes)
በምስጋና አጥናፉ ተጽፎ ዳይሬክት የተደረገውና በፓስፊክ ፊልም ፕሮዳክሽን የተዘጋጀው “ጥቁር እና ነጭ” ፊልም የፊታችን ሰኞ በብሔራዊ ትያትር ከቀኑ በ11 ሰዓት ይመረቃል፡፡ በዚህ የቤተሰብ ፊልም ላይ ሙሉአለም ታደሰ፣ እመቤት ወልደገብርኤል፣ ማክዳ አፈወርቅ እና ሌሎችም ተውነዋል፡፡
Rate this item
(0 votes)
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው የሉሲ አካዳሚ ተማሪዎች በየክፍላቸው ንዑስ ቤተመፃሕፍት አቋቋሙ። የሕፃናትንና ታዳጊ ወጣቶችን የንባብ ባህል ለማዳበር የተቋቋሙትና ትላንት የተመረቁት የየክፍሉ አብያተ መጻሕፍት በዝነኛ ሰዎች ስም ተሰይመዋል። ከ1ኛ-5ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ያቋቋሙት ቤተመጻሕፍት በደራሲ ሜሪ ጃፋር ስም የተሰየመ ሲሆን ቤተመጻሕፍቱን…
Rate this item
(0 votes)
በጋዜጠኛ፣ ደራሲና ጸሐፌ ተውኔት ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ የተዘጋጀው “ፍልስምና ፫” የተሰኘው መፅሃፍ ለንባብ በቃ፡፡ በቃለ ምልልስ መልክ በተዘጋጀው መጽሐፍ ውስጥ ስምንት ባለሙያዎች የተካተቱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ኬሚካል ኢንጂነር ጌታሁን ሄራሞ፣ በቀለማት ፍልስፍናና ሥነ ልቦናዊ ማንነታቸው፣ ተፊሪ ንጉሤ በገዳ ሥርአት፣ በዋቂፈናና ኢሬቻ፣…
Rate this item
(0 votes)
በኢትዮጵያ የመጀመርያው የኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ ኤፍኤም አዲስ 97.1 የተመሰረተበትን 13ኛ ዓመት በዓል ነገ ከጧቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በሐራምቤ ሆቴል እንደሚያከብር አስታውቋል፡፡ የ24 ሰዓት ስርጭት ያለው ብቸኛው የኢትዮጵያ ሬዲዮ ጣቢያ፣ ነገ በሚያከብረው በዓል ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ታደሰ…
Rate this item
(0 votes)
ለሩሲያዊው ባለቅኔ አሌክሳንደር ፔትሮቪች ፑሽኪን፣ ሦስት ቶን ክብደት ያለው ግዙፍ የነሐስ ሐውልት በአዲስ አበባ ሣር ቤት አካባቢ በሚገኘው “ፑሽኪን አደባባይ” ሊቆምለት እንደሆነ የሩሲያ የሳይንስ እና ባህል ማእከል አስታወቀ፡፡ ማእከሉ ለአዲስ አድማስ እንደገለፀው፣ የነሐስ ሐውልቱ በአፍሪካ አህጉር በግዙፍነቱ ተወዳዳሪ የሌለው ሲሆን…