ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(0 votes)
ላፍቶ ጋለሪ ከአርባ በላይ የሴት ሰዓሊያን ሥራዎችን ያካተተ “Inspired women2” የተሰኘ የስዕል አውደርዕይ ከትላንት በስቲያ ለተመልካች ማቅረብ ጀመረ፡፡ ኢትዮጵያውያንና የውጭ አገር ሴት ሰዓሊያን የተሳተፉበት አውደርዕይ ከ150 በላይ የስዕል ስራዎች የያዘ ሲሆን ለአንድ ወር ለህዝብ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል፡፡
Rate this item
(0 votes)
በአንጋፋው ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል የተዘጋጀ “እንካስላንቲያ” የተሰኘ መፅሃፍ ሰሞኑን ለንባብ ቀረበ፡፡ ደራሲው ስለ መፅሃፉ ፋይዳ በገለፀበት መግቢያ፤ “የእንካስላንቲያ ሥነ-ቃል የግጥማዊ ዜማነት ባህሪይ ስላለው ወጣቶች እየተፈራረቁና እየተፎካከሩ በመሳተፍ አያሌ ቁምነገሮችን … ይማሩበታል” ብሏል፡፡ በ107 ገፆች የተቀነበበው መፅሃፉ፤ ዕውቀት፣ ዲሞክራሲ፣ ሙስና፣ ፍትህ…
Rate this item
(0 votes)
ባለፈው ሚያዝያ 2 መቅረብ የነበረበትና ታዳሚዎች በሥፍራው ከተገኙ በኋላ የተቋረጠው “ግጥም በጃዝ” በመጪው ረቡዕ እንደሚቀጥል አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ ቅድመ ዝግጅት አጠናቀን ልናቀርብ ከተዘጋጀን በኋላ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተቆጣጣሪ አካል ፈቃድ የላቸውም በማለቱ ስለሌላቸው አያቀርቡም በሚል ለራስ ሆቴል ዝግጅቱ መቋረጡን ተናግረዋል፡፡ ረቡዕ…
Rate this item
(1 Vote)
አርቲስት ፍቃዱ አያሌው ባጋጠመው የነርቭ ህመም ወደ ታይላንድ ባንኮክ ሄዶ ህይወቱን የሚታደግ ህክምና እንዲያገኝ በህክምና ባለሙያዎች ተወሰነ፡፡ የሰዓሊው ጓደኖችና ወዳጅ ዘመዶች በውጭ አገር በሚያደርገው ህክምና ጥሪ ለማሰባሰብ እያስተባበሩ ናቸው፡፡ ሰዓሊ ፍቃዱ የነርቭ ህመሙ ለመታከም አዲስ አበባ ለሚገኘው የሚዮንግ ሰንግ ሆስፒታል…
Rate this item
(9 votes)
የኢትዮጵያ የዜማ አባት የሚባለው ቅዱስ ያሬድ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተዘከረ ሲሆን አዲስ አበባ የሚገኘው የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስትያን፤ የዜማ አባቱ የተወለደበትን 1500ኛ የልደት በዓል ነገ ከረፋዱ አራት ሰዓት እንደሚያከብር አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አዲሱ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ…
Rate this item
(0 votes)
በሻሸመኔ ከተማ ጥበብ አፍቃሪዎች የተቋቋመው ከ “አድማስ ፊት” የኪነጥበብ ማህበር 42ኛ ዝግጅቱን ነገ ከሰዓት በኋላ በከተማዋ ሁለገብ አዳራሽ እንደሚያቀርብ ገለፀ፡፡ በዚህ ጥበባዊ ዝግጅት ላይ አርቲስት ታምሩ ብርሃኑ እና ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ልምዳቸውን ለታዳሚዎች እንደሚያካፍሉ ማህበሩ አስታውቋል፡፡