ልብ-ወለድ

Rate this item
(24 votes)
የጥበብ አለም ሰው ነኝ፤ እላለሁ ለራሴ። ተደጋግሞ የሚባለውን ነገር ሳላምንበት ለምን ሰው በሌለበት ለራሴ እንደምደጋግም አላውቅም፡፡ የጥበብ አለም ሰው ነኝ!..ምን ማለት ነው? እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ምን ማለት ነው ሰው?...ፍቺው ለእኔ ቋጠሮ ነው፡፡ የጥበብ አለም ሰው ነኝ ከማለት ግን ቦዝኜ አላውቅም፡፡ ጥንቅቅ…
Saturday, 19 December 2015 10:32

ቁጣ ማለስለስ

Written by
Rate this item
(10 votes)
አጨሳለሁ!...ማለቴ የሠርጌ እለት ማጨስ እፈልጋለሁ፡፡ አንሙት ጓደኛዬ ሰሞኑን ከመካኒክነት ስራው ጋር ተያያዥነት ያለው ቁጣ ማለስለስ የሚል ስልጠና ወስዷል፡፡ በዚህ ስልጠና መሰረት ቁጣዬ እንዳይነድ ልተገብር ስለሚገባኝ የተለያዩ የቁጣ ማለስለሻ ዘዴዎች ነግሮኛል፡፡ ከዘዴዎቹ መሃከል ማጨስ ይገኝበታል፡፡ የሠርጌ እለት ለትዳር ጠይቄያቸው “እምቢ” ያሉኝ…
Rate this item
(12 votes)
ወይዘሮ ማላርድ የልብ ድካም በሽታ አለባት። እህቷና የባሏ ጓደኛ፣ የባሏን ድንገተኛ ሞት ለማርዳት ጭንቅ ጥብብ አላቸው፡፡ እህቷ ጆሴፍን እንድታረዳት ሆነ፡፡ ጆሴፊን በተቆራረጡ አረፍተ ነገሮች፣ በተድበሰበሰ ጥቆማ፣ ነገረቻት፡፡ መርዶው ለወይዘሮ ማላርድ ሲነገር የሟች የአቶ ማላርድ ጓደኛ ሪቻርድስ በቦታው ነበር። ሲጀመር ገና…
Rate this item
(7 votes)
መንገድ ዳር ካለችው አነስተኛ ሆቴል ወጥተው ትንሽ እንደተጓዙ ግራ-ቀኝ ዛፍ የበቀለበት ሰፊ መንገድ ተቀበላቸው፡፡ ዛፎቹ ቅጠላቸው አሁንም እንደረገፈ ነው፤ ጠቁረዋል፤ አይን አይስቡም፡፡ ለፀደይ ወራት የተረገዙ ሚጢጢ ቅርንጫፎች ይታያሉ፡፡ ቀና ሲባል እነኚሁ ሚጢጢ ቅርጫፎች በቅርቡ አብረቅራቂ፣ አረንጓዴ ሸማ ለብሰን እንመጣለን፤ ጠብቁን…
Rate this item
(9 votes)
መሽቷል፡፡ እሱም ብቻውን ነበር፡፡ እሱም በርቀት ተመለከተ፡፡ በግንብ የታጠረች ክብ ከተማም አየ፡፡ ወደ ከተማዋም አቀና፡፡ ወደ ከተማዋ በቀረበ ጊዜም ሶስት ድምፆች ሰማ፡፡ አንደኛውም፡- በፈንጠዚያ የሚዘሉ እግሮች ድምድምታ ነበረ፡፡ ሁለተኛውም፡- ከፍተኛ የሆነ የደስታ ማሽካካት ነበረ፡፡ ሶስተኛውም፡- ድብልቅልቁ የወጣ የዋሽንት ዝማሬ ነበረ፡፡…
Rate this item
(7 votes)
ክረምቱ ያመጣው ግራጫ የደመና ቡልኮ የሳሊናስ ሸለቆን ጀቡኗታል፡፡ ሳሊናስ ከሰማዩም፣ ከሌላው አለምም በደመናው ተከልላለች፡፡ በታህሳስ ወትሮም ፀሐይ የለችም፡፡ የፀጥታ ጊዜ ነው፡፡ የጥበቃ ጊዜ ነው፡፡ አየሩ ለሰስ ያለ ቀዝቃዛ ነው፡፡ ቀለል ያለ ነፋስ ከደቡብ ምዕራብ ይነፍሳል፡፡ ሄነሪ አለን እርሻው ላይ ብዙም…