ልብ-ወለድ
አንገቱ ላይ የተንጠለጠለውን ገመድ የሙጥኝ እንዳለ ነው፡፡ ቁርጠኛ ውሳኔውን ለማጨናገፍ የሚንከወከው ድንገቴ ቢመጣ ሳይቀድመው እንደሚቀድመው ተማምኗል፡፡ አንዲት እራፊ ጨርቅ ብቻ ነች ኃፍረተ - ሥጋውን የሸፈነችው፡፡ ገመዷ ከቦታዋ መኖር አለመኖሯን እያሰለሰ ይሰልላታል፡፡ጠደፍ ጠደፍ እያለ ሠፊውን ጎዳና በሰጎን ቅልጥሞቹ እየመተረ ማቋረጥ ጀመረ፡፡…
Read 4408 times
Published in
ልብ-ወለድ
እሣት እንደናፈቀው ምድጃ ፊቱ ቀዝቃዛ ነው። አይኖቹ እሣት አይወረውሩም፡፡ ይልቅ በረዶ ይረጭባቸዋል፡፡ ጥርሶቹ ብዙ ጊዜ ባይገለጡም አንዳንዴ ለቀቅ ሲያደርጋቸው፣ ክርክም ብለው የተደረደሩ ናቸው፡፡ ግን የትምባሆ ጢስ ፈርሞባቸው ያን ያህል ትኩረት አይስቡም፡፡ መርመራ ዳንሣሞን ያለ መጥረቢያ ማየት ይናፍቃል፡፡ ጧት ሻይ ቤት፣…
Read 3882 times
Published in
ልብ-ወለድ
“ተራሮች ጫፍ ላይ ጸጥታ ሰፍኗል” ዛፎች ሁሉ ረጭ ብለዋል፡፡ አዕዋፍ በዛፎቹ ላይ አሸልበዋል - ጠብቅ! አንተም አንድ ቀን እንዲህ ጸጥ ትላለህ!!!” የሚል የት እንዳነበብኩት የማላስታውሰው ጥቅስ በተደጋጋሚ በእዝነ ህሊናዬ አስተጋባ፡፡ “ጸጥ ትላለህ” ምን ማለት ነው? በዚህ ስገረም ይባስ ብሎ፣ ከእንቅልፌ…
Read 3919 times
Published in
ልብ-ወለድ
(ካለፈው የቀጠለ) ፍቅሯ ስላልወጣልኝ በአቋሜ ልፀና አልቻልኩም። ሌላ ጊዜ ጥቂት ቆይታ ደግሞ “ለጥፋቴ ይቅርታ ጠይቄ የለ? … ግንኙነታችንን ብንቀጥልና ባሌ ብትሆን ደስ ይለኝ ነበር፡፡ እንዲህ የምጠይቅህ ለሌላ ሳይሆን ስለምትወደኝ ነው፡፡” ፍቅር እንደገና! * * * ላንቺ፡- ስሜቴን መካድ እችላለሁ?! ……
Read 4399 times
Published in
ልብ-ወለድ
ላንቺ…እንደምወድሽ ክጄ አላውቅም፡፡ ትላንት አልካድኩም። ዛሬም፣ ነገም አልክድም፡፡ ፍቅርሽ ሰውነት እንዲሰማኝ አድርጓል፡፡ ቀዩ ፊትሽ መስታወቴ ነው፡፡ ሳይሽ እራሴን አያለሁ፡፡ ሳወራሽ ‘ራሴን ያወራሁ ያክል ይሰማኛል፡፡ አፍንጫሽ ቁሞ ሳየው፤ ቅጥና ልክ ባጣው ያንቺ ፍቅር አንድ ቦታ ላይ ቁሞ የቀረው ማንነቴ ትውስ ይለኛል፡፡…
Read 5816 times
Published in
ልብ-ወለድ
ስለ ገጣሚነቱ እርግጠኛ ነው፡፡ ገጣሚነትን ከፈጣሪ ያገኘው ፀጋ ነው፡፡ መታገል አስቦ አያውቅም፡፡ በተፈጥሮው ታድሏልና፡፡ ብዙ መጽሐፍት አሳትሟል፡፡ ለምን ስላሳተማቸው መጽሐፍት ሰው ሲወያይ እንደማይሰማ ግን አልገባውም። አምስት አመት ብቻ ነው ያለፈው፣ የመጨረሻውን መጽሐፉን ገበያ ላይ ካዋለ፡፡ እርግጠኛ ነው ስለገጣሚነቱ፡፡ እጣ ፈንታው…
Read 5130 times
Published in
ልብ-ወለድ