ዜና

Rate this item
(7 votes)
በፍትህ ሚኒስቴር የወንጀል ክስ ከተመሠረተባቸው 6 የሚዲያ ተቋማት መካከል የሎሚ መጽሔት አሣታሚና ባለቤት በትናንትናው እለት ፍ/ቤት ቀርበው በ50ሺህ ብር ዋስ የተለቀቁ ሲሆን የፋክትና የ“አዲስ ጉዳይ” አሣታሚዎች ባለፈው ረቡዕና ሃሙስ ባለቤቶች በሌሉበት ክሣቸው ቀርቧል፡፡ የ“ሎሚ” መፅሄት አሳታሚና ባለቤት አቶ ግዛው ታዬ፤…
Rate this item
(2 votes)
ወደ ምስራቅ አፍሪካ ሃገሮች ሊስፋፋ ይችላል ተብሎ የተሰጋውን የኢቦላ በሽታ በበቂ ደረጃ ለመከላከል ጥረት እያደረገ መሆኑን የገለፀው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፤ እስካሁን በሽታው ወደ ኢትዮጵያ ባይገባም አዲስ እየተገነባ ባለው የኮተቤ ሆስፒታል 10 አልጋዎች ያሉት የህክምና ክፍል ለቅድመ ጥንቃቄ ሲባል መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡…
Rate this item
(3 votes)
በምስራቅ አፍሪካ አገራት በተከሰተው የዝናብ እጥረትና የእርስበርስ ግጭቶች ሳቢያ የምግብ እጥረት መፈጠሩን የገለፀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፤ በቀጠናው ከ14 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው አስታወቀ፡፡ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ትብብር የምስራቅ አፍሪካ ቃል አቀባይ ማቲው ኮንዌይን ጠቅሶ የዘገበው አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ፤…
Rate this item
(19 votes)
በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኢዴፓ) ለአለፉት 15 ዓመታት በዋና ጸሃፊነት፣ በህዝብ ግንኙነትና በፕሬዚዳትነት ያገለገሉት አቶ ሙሼ ሰሙ፤ ራሳቸውን ከፖለቲካ ፓርቲ ው አገለሉ፡፡“ራሴን ከፖለቲካ ያገለልኩት ፋታ በመውሰድ ቆም ብዬ ስለትግሉ ሂደትና ወደፊት ማድረግ ስላለብኝ ነገር ማሰብ ስለምፈልግ ነው” ያሉት አቶ ሙሼ፤ እንደማንኛውም ሰው…
Rate this item
(2 votes)
ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በህገወጥ መንገድ ወደ ማላዊ አስገብቷል በሚል ተከስሶ ጉዳዩ በፍ/ቤቱ እየታየ የነበረውን ባሻ አድነው የተባለ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ከፍርድ እንዲያመልጥ አድርገዋል የተባሉት የማላዊ የአገር ውስጥ ጉዳዮችና የደህንነት ሚኒስትር ፖል ቺቢንጉና የኢሚግሬሽን ጉዳዮች ዋና ሃላፊ ሁድሰን ማንካዋላ መታሰራቸውን ኒያሳ ታይምስ የተሰኘው…
Rate this item
(3 votes)
የዩኒቨርሲቲ ምሁራን የተካተቱበት ገምጋሚ ካውንስል ተቋቁሟልየኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በአዲሱ ዓመት ዓ.ም 4 አዳዲስ የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማዎችና 2 የሬዲዮ ድራማዎች እንደሚያቀርብ የገለፀ ሲሆን አዳዲስ ድራማዎችን በዘርፉ ባለሙያዎች በተዋቀረ ካውንስል እያስገመገመ እንደሚያሳልፍ አስታውቋል፡፡ የታላላቅ አለማቀፍ የሚዲያ ተቋማትን ልምድ በመቅሰም ከእንግዲህ በኋላ…