ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(0 votes)
በሰዓሊና ፎቶግራፈር አይዳ ሙሉነህ የተዘጋጁ 29 የፎቶግራፍ ስራዎች የቀረቡበት የፎቶግራፍ አውደርእይ ባለፈው ሰኞ ምሽት በአስኒ ጋለሪ ተከፈተ፡፡ የ”ዋሽንግተን ፖስት” ጋዜጣ ፎቶ ጋዜጠኛ የነበረችው አይዳ፤ ሥራዎቿን በሀገር ውስጥ ስታቀርብ የመጀመሪያዋ ቢሆንም ካሁን በፊት በስፔን፣ በሰርቢያ፣ በማሊ፣ በግብጽ፣ በኩባ፣ በቻይና፣ በተባበሩት አረብ…
Rate this item
(0 votes)
በሰዓሊ ዳዊት ገረሱ የተዘጋጁ 34 የቀለም ቅብና ፎቶግራፍ ሥዕሎች የሚቀርቡበት “የአንበሳው ታሪክ” የተሰኘ የሥዕል አውደርእይ ዛሬ ማታ በታሊስማን የሥዕል አዳራሽ ይቀርባል፡፡ ስለ ስራዎቹ ይዘት ከዝግጅት ክፍላችን የተጠየቀው ሰዓሊው፤ በኢትዮጵያውያን የአንበሳ እሳቤ ላይ ተንተርሶ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጿል፡፡
Rate this item
(0 votes)
በጌታቸው አበበ አየለ የተዘጋጀው “መንታ መንገድ” ታሪክ ቀመስ ልቦለድ መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ በድሬዳዋ ተከስቶ የነበረው ጐርፍ ሰለባዎችን በመታሰቢያነት የዘከረው ዳጐስ ያለ መጽሐፍ፤ 408 ገፆች ያሉት ሲሆን በ50 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ በመምህርነት ሙያ የተሰማሩት ደራሲው ያዘጋጁት ከሁለት ሺህ ገጽ በላይ የሆነ…
Rate this item
(0 votes)
በአለሚቱ ዳመና የተፃፉ ግጥሞች የተካተቱበት “ተስፋአብ ዳካ” የግጥም መድበል ትናንት ማምሻውን በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ትያትርና ባህል አዳራሽ ተመረቀ፡፡ ለገጣሚዋ ሁለተኛ የሆነው ይሄ መጽሐፍ፤ 95 ገፆች ያሉት ሲሆን ዋጋው 20 ብር ነው፡፡ አለሚቱ ከዚህ ቀደም “ባትጋራኝ” የተሰኘ የግጥም መድበል አሳትማለች፡፡
Rate this item
(0 votes)
በግርማይ ከበደ ተጽፎ የተዘጋጀው “ቀጠሮ አለኝ” ትያትር ትናንት በጐንደር ከተማ ተመረቀ፡፡ በጐንደር ሲኒማ አዳራሽ የተመረቀው ትያትር፤ በአካባቢው ከተሞች ለእይታ እንደሚቀርብ አዘጋጁ ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡ ጉዛራ ኢንተርፕራይዝ ባቀረበው በዚህ ትያትር ላይ ማሩ አህመድ፣ ፋናዬ ታደሰ፣ አሳየሽኝ ምርጫ፣ ኃይሉ ፋንታሁን፣ ፋሲል ቀናው…
Rate this item
(0 votes)
ታደሰ ገብረወልድ ጽፎ ያዘጋጀው “የእስር ቤቱ ልጅ” የተሰኘ ልብ አንጠልጣይ ፊልም ነገ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል፡፡ ይኸንኑ ፊልም በልዩ መርሃግብር ሚያዝያ 1 ቀን 2004 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ለማስመረቅም ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ ዘጠኝ ወራት በፈጀው የ105 ደቂቃ…