ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(1 Vote)
በአብነት ስሜ የተዘጋጀው “የኢትዮጵያ ኮከብ” የሥነ ከዋክብት መፅሐፍ ለንባብ በቃ። የአስትሮሎጂ መፅሐፉ በፋርኢስት ትሬዲንግ የታተመ ሲሆን በውስጡ የ500 ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገር ታዋቂ ሰዎች “ኮከብ” ይዟል። ለማዘጋጀት ሰባት ዓመት የፈጀው መፅሐፍ፤ አምስት ክፍሎቹና አስራ ሰባት ምዕራፎች አሉት። ባለ 132 ገፁ መፅሐፍ፤…
Rate this item
(1 Vote)
የመኢኒት ብሔረሰብ ማህበራዊ እሴቶች ላይ ተመስርቶ የተፃፈው የአንዱአለም አባተ (የአፀደ ልጅ) ረዥም ልቦለድ፤ ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በሚዩዚክ ሜይዴይ ለውይይት ይቀርባል፡፡ በብሔራዊ ቤተመፃህፍት የሚካሄደውን ውይይት የሚመሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ትምህርት ክፍል ባልዳረባ አቶ ተሻገር ሽፈራው ናቸው፡፡
Rate this item
(0 votes)
ባለፈው ሳምንት የስድስት ሰዓታት የሥዕል አውደርእይና ሽያጭ ያዘጋጀው ሠዓሊ ዳንኤል ታዬ፤ በአዳዲስ ሥራዎች ሌላ አውደርእይ ለማቅረብ እየተዘጋጀ መሆኑን የዳኒ ስቱዲዮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚፍታ ዘለቀ ገለፁ፡፡ አርቲስቱ የጤና እክል ገጥሞታል የተባለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን እና በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝም ሥራ…
Rate this item
(1 Vote)
የኮሜዲያን ደረጀ ኃይሌ እና አሁን በህይወት የሌለው ባልደረባው ሀብቴ ምትኩ ሥራዎች የተካተቱበት “ወርቃማው ጊዜ” የኮሜዲ ቪሲዲ ከትናንት በስቲያ ወጣ፡፡ ቁጥር 1 በሚል በቀረበው የኮሜዲ ቪሲዲ ላይ 20 የኮሜዲ ሥራዎች የተካተቱ ሲሆን፤ ቪሲዲውን እያሰራጨ ያለው “ፒያሳ ዘ አራዳ ኢንተርቴይመንት” ነው፡፡
Rate this item
(0 votes)
ከአውሮፓ የስፔን እና የፖርቱጋል፣ ከአሜሪካ ደግሞ የብራዚል፣ ኩባ፣ ቬኔዚዋላ፣ ሜክሲኮ እና አርጀንቲና ፊልሞች የሚታዩበት ስምንተኛው “የኢብሮ-አሜሪካ” ፊልም ፌስቲቫል ከትናንት በስቲያ ምሽት በጣልያን የባህል ተቋም ተጀመረ። ሐሙስ ምሽት፣ “ኤርማኖ” የተሰኘው የቬኔዙዋላ ፊልም ሲታይ፤ ትናንት “ኖሶድሮስ ሎስ ኖብልስ” የተሰኘው የሜክሲኮ ፊልም ታይቷል፡፡…
Saturday, 02 November 2013 12:08

“የዛሌፍ ፋሽን” ዛሬ ይቀርባል

Written by
Rate this item
(0 votes)
ዛሌፍ የሥነ ጥበብ እና ፋሽን ዲዛይን ተቋም፣ በታዋቂ ዲዛይነሮች የተሰሩ አልባሳት የተካተቱበት የፋሽን ትርዒት ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት በኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡ ከተቋሙ የሥራ ውጤቶች መካከል በ2003 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሂልተን የቀረበው በኮንዶም የተሰሩ አልባሳት ዐውደርዕይ ይገኝበታል።