ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(1 Vote)
ከወር በፊት በአቅም መዳከምና በድርቀት ታምማ ሆስፒታል የገባችው ሪሃና፤ አሁንም በአሳሳቢ የጤና ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ተገለፀ፡ ሰሞኑን በእንግሊዝ ለ10 ሳምንታት የነበራትን ቆይታ የሰረዘችው የ24 አመቷ በርባዶሳዊት ያለችበት ችግር የዊትኒ ሃውስተንን አሳዛኝ መጨረሻ የሚያስታውስ እንዳይሆን ተሰግቷል፡፡ የቅርብ ወዳጇ የሆነው ጄይ ዚ…
Rate this item
(0 votes)
“ዱላ ቅብብል” ፊልም ይመረቃል በግሬት ዋሊያ ፒክቸርስ የተሰራው “ፈላሻው” ፊልም ትናንት ምሽት በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ትያትርና ባህል አዳራሽ ተመረቀ፡፡ የ105 ደቂቃ ርዝመት አለው የተባለውን አስቂኝ የፍቅር ፊልም የፃፉት አማኑኤል ተስፋዬ እና ዮሴፍ ተሾመ ሲሆኑ እስክንድር አሊ ፕሮዲዩስ አድርጐታል፡፡ሰርቶ ለማጠናቀቅ…
Rate this item
(0 votes)
ነዋሪነቷን በሀገረ እንግሊዝ ለንደን ከተማ ባደረገችው እታለም እሸቱ የተፃፈው “ሕልመኛዋ እናት” የተሰኘ መፅሐፍ ዛሬ እንደሚመረቅ የኢትዮጵያ ሴት ደራስያን ማህበር አስታወቀ፡፡በሐገር ፍቅር ትያትር ቤት ትንሿ አዳራሽ ከጧቱ 3 ሰዓት የሚመረቀው መፅሐፍ 475 ገፆች ያሉት ረዥም ልብወለድ ሲሆን ከምርቃት በኋላ ለገበያ እንደሚበቃ…
Rate this item
(0 votes)
የሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ የመፃህፍት ንባብ እና የውይይት ክበብ “ታሪካዊ እውነት፣ እምነትና ትንቢት በፍቅር እስከ መቃበር መፅሐፍ” የተሰኘ የጥናት ፅሁፍ ለውይይት እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡ ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት አምስት ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዘክር አዳራሽ የሚካሄደውን ውይይት የሚመሩት አጥኚው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ…
Rate this item
(0 votes)
በሻሸመኔ ከተማ ኪነጥበባት አፍቃሪዎች የተቋቋመው “ከአድማስ ፊት” ነገ ወርሃዊ የኪነጥበብ ዝግጅቱን እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡ የ37ኛ ዝግጅቱ የክብር እንግዳ አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ ልምድና ገጠመኙን የሚያጋራበት ኪነጥበባዊ ዝግጅት የሚቀርበው በሻሸመኔ ባህል አዳራሽ ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ ዝግጅቱ ከተጀመረ አራት አመቱ ነው፡፡
Rate this item
(0 votes)
በወጣት ገጣሚያን እና ሙዚቀኞች የሚንቀሳቀሰው “ግጥምን በጃዝ” አስራ አንደኛ ዝግጅቱን በመጪው ረቡዕ ምሽት በዋቢ ሸበሌ ሆቴል እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡አንጋፋው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም ከቀደምት ፀሐፍት ግጥሞች በሚያቀርብበት ዝግጅት አርቲስት ግሩም ዘነበ ትወና፣ ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም ወግ፣ እንዲሁም ለዝግጅቱ አዲስ የሆኑ ገጣሚያን ይርጋ…