ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(2 votes)
ሚዩዚክ ሜይዴይ “አመኛው ክልስ” በተሰኘው የዳንኤል ሁክ መጽሐፍ ላይ ነገ ውይይት እንደሚካሄድ ገለፀ፡፡ ከቀኑ 8 ሰዓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመጻሕፍት የሚካሄደውን የሦስት ሰዓታት ውይይት፣ የመነሻ ሀሳብ በማቅረብ የሚመሩት የሥነ ጽሑፍ ባለሙያው አቶ አስቻለው ከበደ ናቸው፡፡
Rate this item
(1 Vote)
“አቦል፣ ቶና፣ በረካ” በሚል ርእስ ቡና ላይ ያተኮረ የሥዕል አውደርእይ እንደሚቀርብ አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ በመጪው አርብ በአምስት ኪሎው ብሔራዊ ቤተመዘክር ተከፍቶ እስከ ታህሳስ 7 ለሕዝብ በሚቀርበው አውደርእይ የሚገኘው ገቢ፣ ቦንጋ ላይ ለሚገነባው የቡና ቤተመዘክር ሕንፃ ማሰሪያ እንደሚውል አዘጋጆቹ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
Rate this item
(1 Vote)
መሳይ ፕሮሞሽን ከመንሱር ጀማል ፕሮሞሽን ጋር በመሆን የፀረ “የፆታ ጥቃት” ዘመቻ ቀንን የተመለከተ ኪነጥባዊ ዝግጅት ትናንት ጠዋት በሀገር ፍቅር ትያትር ቤት አዳራሽ አቀረበ፡፡ “እኔንም ይመለከተኛል” በሚል መሪ ቃል በቀረበው ዝግጅት ግጥሞች፣ ወግ፣ መነባንብ፣ ሙዚቃዊ ድራማ እና ሥነቃሎች ቀርበዋል፡፡
Rate this item
(1 Vote)
በብሩክ ገብረሚካኤል የተጻፈው “ንፋስ እና ንስር” የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ነገ ከምሽቱ 12 ሰዓት በጣይቱ ሆቴል ጃዝ አምባ አዳራሽ እንደሚመረቅ ገጣሚው ገለፀ፡፡ መጽሐፉ በ96 ገፆቹ፣ 77 ግጥሞች ይዟል፡፡ በኦላንድ ማተሚያ ቤት የታተመው መጽሐፍ በውጭ ሀገራት 20 ዶላር፣ በሀገር ውስጥ 35 ብር…
Rate this item
(35 votes)
በአብነት ስሜ የተጻፈው ‘የኢትዮጵያ ኮከብ’ የተሰኘ ኮከብ ቆጠራ (አስትሮሎጂ) መጽሃፍ ባለፈው ሳምንት ለንባብ በቃ፡፡ በአምስት ዋና ዋና ክፍሎችና በአስራ ሰባት ምዕራፎች የተከፋፈለው ‘የኢትዮጵያ ኮከብ’፣ 132 ገጾች ያሉት ሲሆን የግለሰቦችን፣ የአገራትንና የዘመናትን ኮከቦች በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይዟል፡፡ በመጽሃፉ ውስጥ የ500 ታዋቂ…
Rate this item
(1 Vote)
የነጭ ሪቫን ቀንን በተለያዩ የኪነጥበብ ዝግጅቶች እንደሚያከብር የኢትዮጵያ ሴት ደራስያን ማህበር አስታወቀ፡፡ በአሁኑ ወቅት የሚፈፀሙ የተለያዩ የጾታ ጥቃቶችን ለማስቆም ቃል የሚገባበት ቀን የሚዘከረው በአዲስ አበባ ራስ ሆቴል ትልቁ አዳራሽ፣ የፊታችን ሰኞ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ሲሆን ፕሮግራሙ ወንድ የኪነጥበብ ባለሙያዎች…