የአፍሪካ የሆቴል ኢንዱስትሪ መሪዎች በየዓመቱ በሚያደርጉት ቋሚ “አፍሪካ ሆቴል ኢንቨስትመንት ፎረም” (ኤኤችአይአፍ) ተገናኝተው

በአፍሪካ፣ ሆቴሎችን ማሳደግና ማስፋፋት በሚቻልባቸው ነጥቦች ላይ ተመካክረዋል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትስስር (Chain) ያላቸው፣

በርካታ እውቀትና ልምድ ያካበቱ ከፍተኛ የሆቴል ሥራ አስፈጻሚዎች፣ ዋና ዋና የዓለማችን የሆቴል ኢንቨስተሮችና በዘርፉ የላቀ እውቀት

ያላቸው በርካታ አማካሪ ባለሙያዎች በጉባኤው ተሳትፈው፣ በአፍሪካ ሆቴሎችን ለማስፋፋት አስፈላጊ ናቸው ያሏቸውን ነጥቦች

ተናግረዋል፡፡ የፎረሙ አዘጋጅ “ቤንች ኢቨንት” (Bench Event) የጉባኤው ተሳታፊዎች ቅድሚያ ሊሰጧቸው ይገባል ብለው የወሰኗቸውን

10 ነ ጥቦች - የረዥም ጊ ዜ እ ቅድ፣ ፋ ይናንስ፣ ዕ ድገት (ልማት)፣ ሕዝብ እ ና ልማት በ ማለት በ አምስት ክ ፍሎች አ ጠቃሎ አ ቅርቧቸዋል፡፡

 ሀ) የረዥም ጊዜ እቅድ

የአፍሪካ መንግሥታት፣ የአገራቸውን ሰፊ የቆዳ ሽፋን ያካለለ የረዥም ጊዜ ዕድገት (ልማት) ስትራቴጂ መንደፍ አለባቸው፡፡ ይህን ሲያደርጉ፣ በአገሪቷ ውስጥ አዲስ የተሠራ ወይም ማስፋፊያ የተደረገለት ሆቴል ያለበትን ደረጃ በከፍተኛ እርግጠኝነት ማወቅ ያስችላቸዋል፡፡ ይህም በተወሰነ አካባቢ ብቻ የሚደረገውን የኢንቨስትመንት ክምችት ስጋት በማስቀረት በመላ አገሪቱ የተመጣጠነ ልማትና ዕድገት እንዲኖር ያስችላል፡፡

በመሠረተ ልማት ላይ ኢንቨስት ማድረግ፡- የአፍሪካ መንግሥታት በራሳቸው ተነሳሽነት “መዳረሻ እሆናለሁ” ብለው ሩቅ በማለም፣ በመሠረተ ልማት (በመንገድ፣ ስልክ፣ ኢንተርኔት፣ ውሃ፣ መብራት፣..) ላይ ኢንቨስት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ መሠረተ - ልማት ሲያሟሉ፣ በራዕያቸው የተገረሙና የተደነቁ ቱሪስቶችን፣ የቢዝነስ ሰዎችንና ኢንቨስተሮችን መሳብ ይችላሉ፡፡ በጣም ጠቃሚ ከሆነው የትራንስፖርት መሠረተ ልማት አንዱ የአውሮፕላን ማረፊያ (ኤርፖርት) ነው፡፡ በዚህ ረገድ፣ በአንጐላ፣ በኬንያ፣ በናይጄሪያ፣ በሩዋንዳና ሴኔጋል (ኮትዲቯር) አዳዲስ አውሮፕላን ማረፊያዎች እየተሠሩ ነው፡፡

ለ) ፋይናንስ

ለፋይናንስ ችግር (እጥረት) ወደ ውጪ ተመልከቱ፡- የአፍሪካ መንግሥታትና ኢንተርፕርነሮች፣ ለሚያስፈልጋቸው የገንዘብ እጥረት መፍትሔ እንዲሆናቸው ወደ ውጭ አገር መመልከት ወይም በአገር ውስጥ በፕሮጀክታቸው አካባቢ ያሉ ኢንቨስተሮችን መቃኘት ይኖርባቸዋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ብዙ ዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮች፣ ከሌሎች አገሮች ጋር በንፅፅር ሲመለከቱ ብዙ የአፍሪካ አገሮች እያሳዩ ባሉት ከፍተኛ ዕድገት እየተሳቡ ናቸው፡፡

በአፍሪካ ኢንቨስት ያደርጋሉ ተብለው የሚጠበቁት፣ ጥሩ የአየር ትራንስፖርት ትስስር ካላቸው መካከለኛ ምሥራቅ አገሮችና በአኅጉሩ የተስፋፋ ቢዝነስ ካላት ቻይና ነው፡፡

ሆቴሎችን በንብረትነት (Asset) ማየት፡- በተለምዶ ሆቴሎች በራሳቸው እንደ ንብረት አይታዩም ነበር፡፡ አሁን ግን ሁኔታዎች እየተቀየሩ ነው፡፡ የሆቴል ባለቤት መሆን፣ በረዥም ጊዜ አገር የቱሪስት ወይም የቢዝነስ መዳረሻ ስትሆን እኔም ውጤታማ እሆናለሁ ብሎ በረዥሙ ማሰብ ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ኢኮኖሚው ደካማ (ቀዝቃዛ) በሆነበት ዓመት ከተገኘው ትርፍ ላይ እንደገና ኢንቨስት ማድረግ ለታክስ የሚከፈለውን ገንዘብ በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ (ማዳን) ነው፡፡

ሐ. ዕድገት (ልማት)

የዕድገት ሂደትን ማፋጠን፣ ኢንቨስተሩ አንድን ንብረት ለመግዛት ውል ከተፈራረመ በኋላ ወዲያውኑ ቢዝነሱን ከጀመረ በንግዱ ወይም በሥራው የበለጠ ስኬታማ የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ በ7 ዓመት (Time zone of 7 years) ቢዝነሴን (ሆቴሌን) እዚህ ደረጃ አደርሳለሁ ማለት አይታወቅም፡፡ በአንፃሩ ግን በሰንሰለት የተሳሰሩ ሆቴሎች ከምንም (Scratch) ተነስተው በወራት ፍጥነት ከፍተኛ ደረጃ የሚደርሱበትን የኮንስትራክሽን ሞጁል ውጤት ለማግኘት እየተመራመሩ ነው፡፡

የአየር መስመር መክፈት፡- አንዲት አገር የበለፀገች የቱሪስት ወይም የቢዝነስ መዳረሻ ለመሆን የአየር መስመር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በኢኮኖሚ የበለጠ ለመበልፀግ የአየር ትራንስፖርት ዋነኛው አንቀሳቃሽ ኃይል መሆኑን በርካታ ጥናቶች አመልክተዋል፡፡ ስለዚህ የበለጠ የአየር ትስስር መፍጠር ያስፈልጋል፡፡

መ. ሕዝብ

ከአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች ጋር ማስተሳሰር፡- ብዙ የውጭ ኢንቨስተሮች ጠንካራ ወይም ሁነኛ ሸሪክ ካላገኙ በአፍሪካ አዲስ ኢንቨስትመንት መጀመር አይፈልጉም፡፡ ስለዚህ፤ እነዚህን ሁለት ወገኖች ማስተሳሰር ቅድሚያ የሚሰጠው ስትራቴጂ መሆን አለበት፡፡

ኢንዱስትሪዎችን ማቀራረብ፡- አዲስ ሆቴል ለማቋቋም የሚያነሳሱ ውይይትን መፍጠር የሚችሉ ዝግጅቶችን መደገፍ ያስፈልጋል፡፡ እንዲሁም ጠቃሚ የሆኑ አዳዲስ ሰዎችን በማስተዋወቅ አነስ ያለ እውቀትና ልምድ ያላቸው ኢንቨስተሮች ስለሁሉም የስራ ሂደቶች እንዲያውቁ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ረ. ባህል

ፖለቲካው የተረጋጋ መሆኑን ማስተዋወቅ፡- ለአንድ አገር እንግዳ ተቀባይነትና (ለኢንቨስትመንት ምቹነትና ለኢንዱስትሪው ሰላም)  

የተረጋጋ ፖለቲካ እጅግ ወሳኝ ናቸው፡፡ በሰሜን አፍሪካ አገሮች የተከሰተው ዓይነት የፖለቲካ ብጥብጥ (ያለመረጋጋት) በአገሮቹ ሊካሄዱ የነበሩ የሆቴል ኢንቨስትመንቶች እንዲዘገዩ አድርጓል፡፡  እውነተኛ ዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮች ገንዘባቸውን ማፍሰስ የሚፈልጉት የተረጋጋ ሰላምና ፖለቲካ ባለበት አገር ነው፡፡ ስለዚህ የአፍሪካ መንግሥታት በአገራቸው የተረጋጋ ፖለቲካ እንዲኖር ከልብ መጣር አለባቸው፡፡

10. የሚታመንባችሁ ሆኑ (እምነት ፍጠሩ)

ያለመታደል ሆኖ በአንዳንድ የአፍሪካ ክፍሎች ዕቃዎች እንደሚጠፉና የተገባ ቃል እንደማይከበር በጣም ብዙ ታሪኮች ይነገራሉ፡፡

ይህ ነገር ሁሉንም የቢዝነስ ሰዎች እንዲሰጉ ያደርጋቸዋል፡፡ መታመንን ለመፍጠርና ለመገንባት የሚደረገው ሂደት፣ እንደ ፈታኝ የባህል ለውጥ ስለሚቆጠር፣ እጅግ የላቀ ጥንካሬና ትግል ይጠይቃል፡፡

ስለዚህ በቆራጥነት መሥራት አማራጭ የሌለው ነገር ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ከውይይቱ የተገኙ አስተያየቶችና ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮች ከሴፕቴምበር 30 እስከ ኦክቶበር 1 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚደረገው ዓለም አቀፍ የኤኤችአይኤፍ ጉባኤ ቀርበው በሚኒስትሮች፣ በከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ከደህንነት (ከሆስፒታሊቲ) ኢንዱስትሪ በመጡ ተሳታፊዎች ጠንካራ ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

50ኛ ዓመት ኢዮቤልዩ በዓሉን አከበረ

 የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ከፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ስር ካሉ የልማት ድርጅቶች መካከል ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘቱና የላቀ ውጤት በማስመዝገቡ የምስጋና የምስክር ወረቀትና ዋንጫ መሸለሙን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ገለጹ፡፡ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ አሰፋ ጉያ ትናንት በድርጅቱ ጽ/ቤት በሰጡት መግለጫ፣ ድርጅቱ በ2006 ዓ.ም በፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት የልማት ድርጅቶች የላቀ ውጤት በማስመዝገብ 12.5 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ በማስገኘቱ መሸለሙን ገልጸዋል፡፡

ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ከኤፕሪል 23-27, 2015 በተደረገው 4ኛው ልዩ ኢንተርናሽናል የቱሪዝም የአስጐብኚ ድርጅት  አውደ ርዕይ የላቀ ተሳትፎ በማበርከቱ ከአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ዋንጫና የምስክር ወረቀት መሸለሙን ሥራ አስኪያጁ አስታውቀዋል፡፡ ድርጅቱ የተመሰረተበትን 50ኛ ኢዮቤልዮ ክብረ በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች ማክበሩንና ለድርጅቱ መስራች ለአቶ ኃ/ሥላሴ ታፈሰና የላቀ የሥራ ውጤት ላስመዘገቡ ሠራተኞች የምስጋና ሽልማት መስጠቱን ገልጸዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

ውፍረትን ለመቀነስ በሚል ሰበብ በርካቶች የጂም ቤቶችን ማዘውተራቸው አዲስ ክስተት አይደለም፡፡ ሸንቀጥ ያለ ሰውነት እንዲኖራቸው፣ ሰውነታቸውን እንደልባቸው ለማዘዝና ከተለያዩ ውፍረት አመጣሽ በሽታዎች ራሳቸውን ለመጠበቅ በሚል በሚያዘወትሯቸው ጂም ቤቶች አንዳንድ ጊዜ ኢላማቸውን ስተው ለክብደት መጨመር የተዳረጉ ሰዎች ጥቂት አይደሉም፡፡

 ብዙ ጊዜ ከሰው የምትቀላቀልባቸውን አጋጣሚዎች አትወዳቸውም፡፡ የሰርግና ሌሎች ግብዣዎች ጥሪ ባይመጡላት ደስታዋ ነው፡፡ እንዲህ ያሉ አጋጣሚዎች ውፍረቷን ክፉኛ እንድትጣላው ያደርጋታል፡፡

በውድ ዋጋ የተገዙ በርካታ ልብሶቿ ቁምሳጥኗን ያጨናነቁት ሲሆን ልብሶቿ እየጠበቧት፣ ክብደቷ በየጊዜው እየጨመረ መሄዱን ትናገራለች፡፡ “ምን አባቴ ላድርገው?” ትላለች፤ ሰውነቷን ዘወትር በመስታወት በተመለከተች ቁጥር፡፡

ከዓመታት በፊት ሁለተኛ ልጇን ወልዳ ስትነሳ ነበር ክብደቷ መጨመር የጀመረው፡፡ ከአራስ ቤት ስትወጣ ከቀድሞ ክብደቷ 12 ኪሎ ያህል ጨምራ ነበር፡፡ ይሄ ራሔልን እምብዛም አላስደነገጣትም ነበር፡፡ የአራስ ሰውነት ንፋስ ሲነካው ይቀንሳል በሚባለው ልማዳዊ አባባል እምነት ነበራት፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ቀድሞ ክብደቷ እንደምትመለስ እርግጠኛ ነበረች፡፡ ሆኖም ክብደቷ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ፣ ውፍረቷ ለዓይን እያስጠላ መጣ፡፡ ችግሩ ሳይባባስ ጂም መግባት እንዳለባት ወሰነች፡፡ በወር 1240 ብር እንድትከፍል በተጠየቀችበት ጂምናዚየም ውስጥም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዋን ጀመረች፡፡ በሣምንት አራት ቀን ጠዋት ጠዋት ለሁለት ሰዓታት ያህል ላቧ በጆሮ ግንዷ እስኪንቆረቆር፣ ድካም ልቧን እስኪያፈርሰው የምትሰራው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ግን የፈለገችውን ለውጥ አላመጣም፡፡ በእርግጥ ሰውነቷን እንደ ልቧ ለማዘዝ አስችሏታል፡፡ ስፖርቱ የምግብ ፍላጎቷን የበለጠ ስለከፈተላት በየጊዜው እየጨመረ ከሚሄደው ክብደቷ አልታደጋትም፡፡ ጓደኞቹም “ያንቺ ውፍረት በጂም እምቢ ብሏል፤ እስኪ ደግሞ በጅብ አስሞክሪው፡፡” በማለት ያሾፉባት ጀመር፡፡ ሰውነታቸው ቀጠን ካሉ ጓደኞቿ ጋር መንገድ ላይ ስትሄድ ተላካፊ ወንዶች “እንትና… ከእሷ ላይ ተልጠሸ ነው? ልጣጯ ነሽ?” ይሏታል፤ አብራት የምትደድዋን ጓደኛዋን እያመለከቱ፡፡ ቀልዱ እሬት እሬት ቢላትም ፈገግ ትላለች - ላለመሸነፍ፡፡

ጂም ሲሰሩ ቆይቶ ማቆም ክብደትን የበለጠ ይጨምራል ሲባል መስማቷ ጂሙን እንዳታቆም አደረጋት፡፡ “ግን ምንድነው የሚሻለኝ?” የሚለው ጭንቀቷም አልቆመም፡፡ ከስፖርታዊ እንቅስቃሴ ስትወጣ ምግብ መብላት እንደሌለባት አንዳንድ ጓደኞቿ ቢነግሯትም ይህን ማድረግ ግን አልቻለችም ሁልጊዜም ከስፖርት በኋላ አንጀቷ በረሃብ ይንሰፈሰፋል፡፡

ከቤት አላደርስ የሚላትን የረሃብ ስሜት ለማስታገስ ጂም ቤቱ አጠገብ ካለው ሬስቶራንት በርገር በቀዝቃዛ እርጎ መብላትን ልማድ አድርጋዋለች፡፡ ይህ ልማዷ ለውፍረቷ ምክንያት መሆኑ ቢነገራትም አምና ለመቀበል ተቸግራለች። “ሊሆን አይችልም፤ ቢገባም የሚቃጠል እኮ ነው” ትላለች፡፡ ላለፉት ሶስት ዓመታት እያፈረሰች የምትገነባው ሰውነቷ ፤በየጊዜው እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አለመሄዱ አሁን ተስፋ አስቆርጧታል፡፡

በሆቴል ዲአፍሪክ ሰሞኑን ያገኘኋት ይህች ራሄል፤ ክብደቷ 89 ኪሎ መድረሱንና ጂም ከመጀመሯ በፊት 76 ኪሎ እንደነበረች አጫውታኛለች፡፡ በጂም ቆይታዋ ያተረፈችው 13 ኪሎ ኢላማውን በሳተ መንገድ የተገኘ እንደሆነም ነግራኛለች፡፡

አላስፈላጊ ክብደትን ለማስወገድና ውፍረትን ለመቀነስ በሚል ሰበብ በርካቶች የጂም ቤቶችን ማዘውተራቸው አዲስ ክስተት አይደለም፡፡ ሸንቀጥ ያለ ሰውነት እንዲኖራቸው፣ ሰውነታቸውን እንደልባቸው ለማዘዝና ከተለያዩ ውፍረት አመጣሽ በሽታዎች ራሳቸውን ለመጠበቅ በሚል በሚያዘወትሯቸው ጂም ቤቶች አንዳንድ ጊዜ ኢላማቸውን ስተው ለክብደት መጨመር የተዳረጉ ሰዎች ጥቂት አይደሉም፡፡ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚነገረው ክብደትን ለመቀነስ ውጤታማ አለመሆኑ ለብዙዎች አሳሳቢ ጉዳይ እየሆነ መጥቷል፡፡

የሥነ ምግብ ባለሙያው አቶ ተረፈ እውነቱ ይህንኑ ጉዳይ አስመልክተው ሲናገሩ፤ “ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በሰውነታችን ውስጥ የተጠራቀመውን ካሎሪ በማቃጠል፣ ሰውነታችን ውፍረትን እንዲቀንስ ማድረጉ የማይካድ ጉዳይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ብዙ ጊዜ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የመራብ ስሜትን በከፍተኛ ሁኔታ በመፍጠር ብዙ እንድንመገብና ክብደታችን እንዲጨምር ያደርጋሉ፡፡ ስፖርታዊ እንቅስቃሴን ስንሰራ በአንጎላችን የጡንቻዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል የሥጋ ክምችቶች ይቀንሳሉ፤ ይሄኔ ከአንጎላችን የመራብ ስሜትን የሚገልፅ መልዕክት ይላክልናል፡፡ እናም ብዙ እንመገባለን፡፡ በዚህ ምክንያትም ክብደታችን እየጨመረ ይሄዳል” ብለዋል፡፡

ከባድ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉ ሰዎች የመብላት ፍላጎታቸው እየጨመረ እንደሚሄድና ይህም ለአላስፈላጊ የክብደት መጨመር እንደሚዳርጋቸው ባለሙያው ይናገራሉ። ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ከዳይት ጋር ካልታገዘ በስተቀር ክብደትን ለመቀነስ እንደማይረዳ የጠቆሙት ባለሙያው፤ ይልቁንም የረሃብ ስሜትን በከፍተኛ ሁኔታ በመፍጠር ብዙ እንድንመገብ ያደርገናል ብለዋል፡፡

በአገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተስፋፉት ጂምናዚየሞች ውስጥም የዚህ ዓይነቱን ቅሬታና እሮሮ መስማት የተለመደ ሆኗል፡፡ “ውፍረት ለመቀነስ ገብቼ በሁለት ወራት አራት ኪሎ ጨመርኩ”፣ “ክብደቴን እቀንሳለሁ ብዬ ገብቼ በየጊዜው እየጨመርኩ ሄድኩ” - የሚሉ እሮሮዎች በዝተዋል፡፡ በዓለም ሲኒማ፣ በላፍቶ ሞል፣ በሆቴል ዲአፍሪክና በደሳለኝ ሆቴል ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ አግኝቼ ያነጋገርኳቸው ደንበኞች፤ ጂም መስራታቸው ክብደት ከመጨመር አላዳናቸውም። ሆኖም ሰውነታቸውን እንደልብ ለማንቀሳቀስ አስችሏቸዋል፡፡

በከተማችን ከሚገኙት ታላላቅ ሆቴሎች በአንዱ ለደንበኞች የስፖርታዊ እንቅሰቃሴ ስልጠና በመስጠት ሥራ ላይ የተሰማራው እስከዳር አድማሱ እንደሚናገረው፤ ወደ ሆቴላቸው ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ ከሚመጡት ደንበኞች አብዛኛዎቹ ዓላማቸው ክብደታቸውን መቀነስ አሊያም ከክብደት ጋር ተያይዘው የሚመጡ የጤና ችግሮች እንዳይከሰቱ መከላከል ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን ዓላማቸውን የሚያሳኩና ክብደታቸውን በመቀነስ ተያያዥ የጤና ችግሮችን ለማስወገድ የቻሉት በጣት የሚቆጠሩት ብቻ ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ ክብደታቸው በየጊዜው እየጨመረ በመሄዱ ምክንያት ይማረራሉ። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ከስፖርት እንቅስቃሴ በኋላ ውፍረት አምጪ የሆኑ ምግቦችን (እንደ ቅባትና ስኳርነት ያላቸው ምግቦችን) አብዝተው መመገባቸው ነው ብሏል ባለሙያው፡፡ 

“ታይም” መፅሔት በቅርቡ ባወጣው ዘገባ፤ ጂምን ከአመጋገባችን ጋር እየተቆጣጠርን ካልተገበርነው ለከፍተኛ ውፍረት እንደሚዳርግና አብዛኛዎቹ የጂም አዘውታሪዎች ውፍረት እየጨመሩ ለመሄዳቸው ዋንኛ ምክንያቱም አመጋገባቸው እንደሆነ ገልጿል። ሰዎች በተፈጥሮአቸው ሁለት ዓይነት የቅባት ቅንጣቶች እንዳሏቸው የጠቆመው ዘገባው፤ ከእነዚህ ነጭና ቡኒ የቅባት ቅንጣቶች ውስጥ ለሰውነት ክብደት መጨመር ተጠያቂ የሚሆነው ነጩ ቅንጣት እንደሆነና ቡኒው የቅባት ቅንጣት ሰውነታችን ከፍተኛ ኃይል ለማምረት የሚያስችለው ማይቶ አንድሪያን በማለዘብ፣ ለውፍረት የሚያጋልጡ የቅባት ለውጦች እንዳይኖሩ እንደሚያደርግ ጠቁሟል፡፡

ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ካደረጉ በኋላ ብዙ ውሃ መጠጣት የረሃብ ስሜቱን ለማስታገስ በእጅጉ እንደሚረዳ የጠቆመው ዘገባው፤ ቅባት ነክ የሆኑ ምግቦችን አለመወሰድ እንደሚገባም አመልክቷል። የጂም አዘውታሪዎች ከስፖርታዊ እንቅስቃሴው በበለጠ በአመጋገባቸው ላይ ጥንቃቄ ካላደረጉ እንደተመኙት ክብደት መቀነሳቸው ቀርቶ በየጊዜው እየጨመሩ እንደሚሄዱ ዘገባው ይጠቁማል፡፡

 

 

 

 

 

Published in ዋናው ጤና
Saturday, 30 May 2015 12:52

የትንፋሽ ህክምና

ክብደትን ለመቀነስ

በመሬት ላይ እግርዎን አጣጥፈው ይቀመጡ፤

ወገብዎን ቀና፣ ሆድዎን ወደ ውስጥ ሳብ ያድርጉት፤

ግራ እጅዎን ጉልበትዎ ላይ ያድርጉ፣ በቀኝ እጅዎ

ሌባ ጣት የግራ አፍንጫዎን ይዝጉት፡፡ ወደ ውጪ

ይተንፍሱ፣ ይ ህንን በ መደጋገም ይ ከውኑ። በቀን

ውስጥ በተመችዎ ጊዜ የቻሉትን ያህል ለመሥራት

ይሞክሩ፡፡ በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ክብደትዎ

መቀነሱንና የምግብ ፍላጎትዎ መቆጠቡን

ይታዘባሉ። እስቲ አሁኑኑ ይሞክሩት …

(ምንጭ፡- ታይም መፅሔት

June 2011)

Published in ዋናው ጤና
Saturday, 30 May 2015 12:44

የሰውነታችን እውነታዎች

 

 

 

- ጨጓራችን የላም ወተትን ለማብላላት አንድ

ሰዓት ይፈጅበታል

- የሴቶች አይን ከወንዶች ይልቅ በእጥፉ

ይርገበገባል

- አንድ ሰው በአማካይ 2 ሚሊዮን የላብ

እጢዎች ይኖሩታል

- ህፃናት ሲወለዱ የጉልበት ሎሚ

አይኖራቸውም፤ ይህ ሰውነት ክፍል

የሚወጣው ከ2-6 ዓመት ባለው የህፃናቱ

እድሜ ውስጥ ጊዜ ነው

- በፀደይ ወራት የህፃናት እድገት ፈጣን ነው

 

 

 

 

Published in ዋናው ጤና

 

 

 

                                                    አጭር ዳሰሳ

‹‹ትንፋሼ ተቀርጾ ይቀመጥ ማልቀሻ

ይህ ነው የሞትሁ’ለት የኔ ማስታወሻ››

 በእርግጥም የጥላሁን ገሠሠ ማስታወሻ ትንፋሹ እና ከ50 ዓመታት በላይ የነገሠበት ሕያው ድምጹ ነው፡፡ ዘከሪያ መሐመድ ደግሞ ‹የጥላሁን ማስታወሻ ትንፋሹ ብቻ አይደለም› ብሎ የአንጋፋውን ሙዚቀኛ ታሪክ በ432 ገጾች ቀንብቦ አስነብቦናል፡፡‹‹ጥላሁን ገሠሠ፡ የሕይወቱ ታሪክና ምሥጢር›› የተሰኘው መጽሐፍ የጥላሁን ገሠሠን ታሪክ እንደ ሙዚቀኛ እና እንደ ሰው አመዛዝኖና በግሩም ስነ ልቡናዊ ወደሮ አስተሳስሮ አቅርቦልናል፡፡ በዚህም የጥላሁንን ዕንባና ሳቅ፣ ድክመትና ብርታት፣ ዝምታና ጩኸት በሚገባ በማሳየት የሕይወት ታሪክ (ባዮግራፊ) ትርክተ-ገድል ብቻ ሳይሆን የባለታሪኩን ምሉዕ ስብዕና የማሳየት ጥልቅ ሥራ መሆኑን ለሌሎች ጸሐፍት ሳይቀር የሚበቃ ትምህርት ሰጥቷል፡፡

‹‹ስሜቱ ሲጨነቅ ባሳብ እያረረ

እራሱን በራሱ እያነጋገረ

ምስጢሩን በምስጢር ቀብሮ ያላኖረ

ኧረ ለመሆኑ ማነው ያልነበረ››

 ለዚህ መጽሐፍ መነሻ የሆነውንና ከ1934 ዓ.ም ጀምሮ በአቶ ፈይሣ ኃይሌ ሐሰና የተጻፈውን የቤተሰብ ታሪክ ማስታወሻ እንደመነሻ በመውሰድ ጸሐፊው እንደሚገልጸው፤ ጥላሁን ገሠሠ ከልጅነት ዕድሜው ጀምሮ በወላጆች የመተው አደጋ የተቀበለ፣ ወላጅ እናቱን በድንገተኛ አደጋ የማጣቱን መሪር ዕውነታ በልቡ ይዞ የኖረ፣ በልጅነት ሕይወቱ ጸሊም ጥላ ውስጥ እየኖረ በሙዚቃው ግን የሚሊዮኖችን ሕይወት ሲያፈካ የኖረ ግዙፍ ሰብዕና ያለው ምስጢራዊ ሰው ነበር፡፡

ዘፈን ለጥላሁን የእንጀራ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሕይወት ቁስል ማከሚያ መድኃኒት መሆኑንም በታሪኩ ውስጥ እናያለን፡፡ ምናልባትም ከብዙ አድናቂዎቹ በላይ በዘፈኖቹ ስሜቱ የሚነካው ጥላሁን ራሱ መሆኑን ስናነብ፣ ጥላሁንን እንደ አዲስ የማወቅ ስሜት ይሰማናል፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ትረካ ብቻ ሳይሆን ትንተናም ሰፊ ቦታ ተሰጥቶታል፡፡ ልጅነቱን፣ አስተዳደጉን እና ሙያዊ ሕይወቱን በስነ ልቦናዊ መነጽር እየፈተሽን፣ እንደዋዛ ካየነው እና ከሰማነው የጥላሁን ሰብዕና ውጪ በራሳችን ርትዕ ልቦና ዕውነቱን እንድንፈርድ ዕድሉ ተሰጥቶናል፡፡ ሰው ሰው በሚሸቱ ትርክቶቹ ጥላሁንን ሲዘፍን ብቻ ሳይሆን ሲያወራ፣ ሲጫወት፣ ሲፈራ፣ ሲተክዝ፣ ሲዝናና፣ ሲታመም እናየዋለን፡፡ ከመድረክ ጀርባ እንባውን እያዘራ ‹‹እኔ እዚህ ቆሜ እዘፍናለሁ፤ ይሄኔ የእናቴ ገዳይ አንድ ቦታ ቆሞ ይፏልላል›› የሚለውን መሪር ቃል ስናነብ የሙዚቀኛው ጥላሁንን ዝና ብቻ ሳይሆን፣ የሰውየው ጥላሁንን ስቃይ በሚገባ እንረዳለን፡፡

‹‹እምነት ተስፋ አለኝታዬ

ቀኝ ክንዴ መመኪያዬ

ዝና ክብሬ መጠሪያዬ

ያገሬ ሕዝብ ገበናዬ››

ጥላሁን ገሠሠን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ውጪ ማየትና መረዳት ፈጽሞ የሚቻል አይሆንም፡፡ የጥላሁንን ታሪክ የማውሳት ሥራም ይህን የ50 ዓመት ቁርኝት ከሁለቱም ወገን አጉልቶ ማሳየት እንዳለበት ዘከሪያ በቅጡ የተረዳ ይመስላል፡፡ መጽሐፉ በሦስት መንግሥታት ውስጥ የነበረውን ሕዝባችንን ኪናዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ታሪክ በጥላሁን ሕይወት ውስጥ በቅጡ ያስቃኘናል፡፡ ከዚህ ባለፈም የጥላሁንን ዜማዎች በየዘመኑ ከነበሩት ሁነቶችና ዕውነታዎች ጋር እያዛነቁ የኢትዮጵያን ሕዝብና የጥላሁንን ጥልቅ ትስስር የሚያወሱ ምዕራፎች በመጽሐፉ ውስጥ ተካትተዋል፡፡ ‹‹ሒሳብ ተከፍሏል››፣ ‹‹በዘፈን አንደኛ››፣ ‹‹ፍቅር ከሽፍታ ሲያስጥል››፣ ‹‹የመወደድ ፀጋ እና ፈተና››፣ ‹‹ሕዝብ ልጁን በፍቅር አከመ›› የሚሉት ተረኮች በጥላሁን ሕይወት ውስጥ እያንዳንዳችን የነበረንን ስፍራ በግልጽ ያሳያሉ፡፡ የሕይወት ታሪክን ጥሩ ከሚያስብሉት መስፈሪያዎች አንዱ፣ አንባቢው ራሱን በባለታሪኩ ሕይወት ውስጥ እንዲያይ ማስቻሉም ነውና እነዚህን ትረካዎች ስናነብ፣ በየዘመናቱ ውስጥ ያሳለፍነውን የራሳችንን ሕይወት እናስታውሳለን፡፡ ምናልባትም የጥላሁን ሕይወት የሁላችንም ሕይወት ማጀቢያ ሙዚቃ እንደሆነ እናያለን፡፡ በዕንባው ውስጥ ዕንባችን፣ በሳቁ ውስጥ ሳቃችን ታትሟልና፡፡

በሚያዝያ ወር 1985 ዓ.ም በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ከደረሰበት በስለት የመወጋት አደጋ ጋር በተገናኘ፣ ጥላሁን በሕይወት ሳለ ‹‹ሆድ ይፍጀው›› ከማለት በቀር በአንደበቱ የተናገረውን ሌላ ቃል ሳንሰማ 22 ዓመታት አልፈዋል፡፡ ድርጊቱን ማን ነው የፈፀመው የሚለው ጥያቄ ዛሬም ድረስ የብዙዎች ጥያቄ እንደሆነ አለ፡፡ ጥላሁን ገሠሠ፡ የሕይወቱ ታሪክና ምሥጢር  በተሰኘው በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ግን፣ ጥላሁን ከዚያ አደጋ ጋር በተገናኘ ለመጀመርያ ጊዜ ከ“ሆድ ይፍጀው” የተለየ ምላሽ የሰጠበትን አጋጣሚ እናነባለን፡፡ በወንጀል ነክ ጉዳይ ላይ ይፋዊ መግለጫ የመስጠት መብትም ሆነ ሥልጣን እንደሌለው የተረዳው የመጽሐፉ ደራሲ፣ በጽሑፍ ጥበብ አጥር ተከልሎ አዲስ መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡ በአንድ ወንጀል‑ነክ ጉዳይ ላይ ከመጽሐፍ ደራሲ ይፋዊ መግለጫ የመጠበቅ የዋህነት ካልጋረደን በቀር፣ በጉዳዩ ላይ በጥላሁን አንደበት የተባለው ተብሏል፡፡

‹‹አንዳንድ ሰው አለ ብዙ ‘ማይናገር

በተግባር የሚያሳይ ሰርቶ ቁም ነገር››

 ብዙ ሠርተው ያልተወራላቸው፣ የሚገባቸውን ዕውቅናና ምስጋና ያላገኙ አያሌ ሰዎች በየሙያ ውስጥ አሉ፡፡ ሙዚቃ ደግሞ ከሌሎች ሙያዎች በተለየ የሕብረት ሥራ ነውና፣ ከጥላሁን ንግሥና ጀርባ ያሉ እና የነበሩ የሙያ አጋሮቹ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በሥራዎቹ ላይ ካሳረፉት አሻራ አኳያ በወጉ ተወስተዋል፡፡ በተለይም ከወርቃማው የሙዚቃ ዘመን ፈርጦች ጀርባ ሆነው በግጥምና ዜማ ድርሠት፣ እንዲሁም በቅንብር የተሳተፉ አንጋፋ ባለውለታዎችን ዘከሪያ አስታውሷቸዋል፡፡ ‹‹የሙያ አባቶችና አጋሮች›› በሚለው ምዕራፍ፤ ኢዩኤል ዮሐንስ፣ አፈወርቅ ዮሐንስ፣ ሣህሌ ደጋጎ፣ ተዘራ ኃይለሚካኤል፣ ገዛኸኝ ደስታ፣ ግርማይ ሐድጎ፣ ሠይፉ ኃይለማርያም፣ አቡበከር አሸኪ፣ አየለ ማሞ፣ ሰሎሞን ተሰማ፣ ፋንታ አንተአለኸኝ፣ ተስፋዬ ለሜሳ፣ ክፍለየሱስ አበበ እና ሌሎችም የጥላሁን የሙያ አጋሮች ከነሥራዎቻቸው ተወስተዋል፡፡

የተወሰኑ የጥላሁን ገሠሠ ዜማዎች ታሪካዊ ዳራ መጠቀሱም ዜማዎቹን እንደ አዲስ በአዲስ ዐውድ እንድናጣጥማቸው ያደርጋል፡፡ የጥላሁን የአማኑኤል ሆስፒታል ቆይታና ‹‹አንቺ ጤና ሆነሽ፤ እኔ ጤና እያጣሁ›› የሚለውን ዜማ ‘ትስስር’፣ ‹‹እሩቅ ምሥራቅ ሳለሁ››ን እና የኮርያ ዘማቹን ደራሲ ገዛኸኝ ደስታ ታሪክ፣ የመጀመሪያ ባለቤቱን እና ‹‹ትዳር ያስጠላሽ በልጅነት›› ዜማን ቁርኝት የሚዳስሱት ትረካዎች ለዚህ በአብነት ይጠቀሳሉ፡፡

‹‹ . . . የጥንቱ ትዝ አለኝ››

የኢትዮጵያ የሙዚቃ ፈርጥ የሆነውን የጥላሁንን ታሪክ ማስታወስ የግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያን የሙዚቃ ታሪክ ማስታወስ ነው፡፡ ዘከሪያ ግን ከዚህም አልፎ ከዘመናዊ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ጅማሮ ተነስቶ በሀገሪቱ ውስጥ የተስተዋሉትን ወሳኝ ሙዚቃዊ ለውጦች እና ክስተቶች ለመዳሰስ ሞክሯል፡፡ ከእነዚህ ክስተቶች ውስጥ አንዱ የሆነውን ጥላሁንንም ለሙዚቃው ያበረከተውን አስተዋጽኦና ሙያዊ ውርስ፣ ድክ ድክ ይል ለነበረው ዘመናዊ ሙዚቃ ያመጣውን በረከት፣ በሙዚቃው ሥራ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን ተጠቃሚነት እና መብት ለማስከበር ያደረገውን ጥረት፣ በሙዚቃው ታሪካዊ ዐውድ ውስጥ አሳይቷል፡፡ ዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ፣ የሐገር ፍቅር ማኅበር፣ የክብር ዘበኛ እና የጥላሁን ገሠሠ ወርቃማ ዘመናት በስፋት ተዳስሰዋል፡፡ ጥላሁን ከተለያዩ የሀገራችን ኦርኬስትራዎች እና ባንዶች ጋር የነበሩትን ቆይታዎች እና በምሽት ክበባት ሲዘፍን የነበረባቸውን ጊዜያት በተቻለ መጠን ለመዳሰስ ሞክሯል፡፡

እነዚህ የመጽሐፉ ክፍሎች፣ ከዝክረ ጥላሁን ባለፈ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ታሪክ በአጭሩ ለማወቅ ለሚሻ አንባቢ ጥሩ መረጃዎችን ይዘዋል፡፡ ሙዚቃችን እንደ ክብር ዘበኛ እና ፖሊስ ኦርኬስትራ ተቋማዊ አደረጃጀት በነበረው ወቅት የነበረውን ጥራት፣ በሂደት የታዩት በጎ እና ዕኩይ ለውጦች በሙዚቃችን ጥራት ላይ ያሳረፉትን አሻራ በጥላሁን የሙዚቃ ካሴቶች አማካይነት ለመጠቆም መሞከሩ የሚመሰገን ነው፡፡

‹‹አካም ነጉማ ፈዩማ

ሂሪያ ሂንቀቡ ኮቡማ››

 እኒህን የኦሮምኛ ስንኞች ‹‹ብቻዬን ነኝ እኔ›› በሚለው በጥላሁን በራሱ ዜማ እንተርጉማቸው፡፡ ‹ብቻዬን ነኝ አጋርም የለኝ› የሚለው ጥላሁን፤ አብዛኛውን ሕይወቱን እንዲህ ባለ አጋር መሻት ውስጥ አሳልፏል፤ ይለናል ጸሐፊው፡፡ የዚህን ግላዊ፣ ስነ ልቦናዊና ስነ አዕምሯዊ ምክንያት ለማብራራት የሚሞክረው ጸሐፊው፤የጋብቻ ሕይወትን  በሚተርከው ክፍል የጥላሁንን ባለቤቶች እና ልጆች፣ የትዳር ሕይወቱን ምስቅልቅሎች፣ እንዲሁም ‹‹ታሞ ከመማቀቅ፣ አስቀድሞ መጠንቀቅ›› ይሉት አባባል ከማይገዛው ባህርይው በመነጨ ቸልተኝነት ሳቢያ  የደረሰበትን ጉዳት ይተርካል፡፡ በመጨረሻዎቹ የሕይወት ዘመናቱ ያጋጠሙትን ችግሮች ስናነብ የቀደመ ሰብዕናውና ግዝፈቱ፣ ክብሩና ሞገሱ እየታሰበን ማዘናችን አይቀርም፡፡ በአንድ ወቅት [እ.ኤ.አ በ2008] ጥላሁን ገሠሠ አሜሪካ ውስጥ በተሽከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጦ፣ በገረጣ ፊቱ እና በደከመ ድምጹ የግዱን በሚያዜምበት ሰአት፣ የሙያ አጋሩ ማህሙድ አህመድ ሊያግዘው ወደ መድረክ ሲመጣ የነበረውን ደማቅና ጥልቅ ሕዝባዊ ስሜት የሚያስታውሱ ትረካዎችን በያዘው በዚህ ክፍል የጥላሁን ሕይወት ድምድማት ይበጅለታል፡፡

‹‹በአካል ሳይፈተን በአካል ሳይነካ

የማን ምንነቱ ግብሩ ሳይለካ

እርግጥ በተፈጥሮ በወል ስም ይጠራል

በቁም ነገር መድረክ ሰው ከሰው ይለያል››

 የዚህ ዘፈን ግጥም ደራሲ ሻምበል ክፍሌ አቦቸር እንዳሉት፤ በእርግጥም ‹‹ሰው ከሰው ይለያል››፡፡ ጥላሁን ገሠሠም ከብዙዎቹ ዘመነኞቹና መሰሎቹ በብዙው ይለያል፡፡ ግማሽ ምዕተ ዓመት የፈሰሰ የድምጽ ማዕበል፣ በተግባር የተፈተነ ሀገር ወዳድነት እና ጥልቅ የሙያ ክብር በእርግጥም ጥላሁንን የተለየ ሰውና የተለየ ሙያተኛ ያደርጉታል፡፡

ቀደም ብዬ እንደጠቀስሁት፣ ይህን ዳጎስ ያለ መጽሐፍ ያበረክትልን ዘንድ ደራሲ ዘከሪያ መሐመድን የቀሰቀሱት፣ ከ1934 አንስቶ የቤተሰባቸውን እና የጥላሁንንም የልጅነት ታሪክ በጽሑፍ ከትበው ያኖሩት አቶ ፈይሣ ኃይሌ ናቸው፡፡ እኒህ ሰው የሙዚቃውን ንጉሥ ታሪክ በእናቱ ወገን፣ ከሰባተኛ ቅድመ‑አያቱ ጀምሮ በዝርዝር ጽፈው ከማኖራቸውም ባሻገር፣ ጥላሁንን /ገና የአንድ ዓመት ሕጻን ሳለ/ እና የቅርብ ቤተሰቦቹንም ፎቶግራፍ በማንሳት ለትውልድ አኑረዋል፡፡ ነገር ግን አቶ ፈይሣ በጽሑፍ ያኖሩት የጥላሁን የልጅነት ሕይወትን የሚመለከት ጥሬ ሐቅ ብቻውን ስለ ሙዚቃው ንጉሥ ሰብዕና ብዙ ላይነግረን ይችል ነበር፡፡ የአቶ ፈይሣ ኃይሌን የቤተሰብ ታሪክ ማስታወሻዎች በጥንቃቄ በማንበብና በመመርመር፣ የጥላሁንን የጉልምስና፣ በተለይም የትዳር ሕይወቱን፣ ምስቅልቅሎሽ ምሥጢር ከቤተሰብ ታሪክ ማሥታወሻዎቹ ውስጥ የመዘዘ እና በጥልቀት የተነተነልን ደራሲው ነው፡፡ ጥላሁን ገሠሠ፡ የሕይወቱ ታሪክና ምሥጢር የተሰኘውን መጽሐፍ የወለደው ደራሲው በዚህ ረገድ ያደረገው የግል ጥረት ነው፡፡ በዚህ ጥረቱም የዚህን ልዩ ሰው አስደማሚ ታሪክ ልዩና ውብ በሆነ አቀራረብ ስለከተበልን ለዘከሪያ መሐመድ በእውነት ምስጋና ይገባዋል፡፡ 

 

 

 

Published in ጥበብ
Saturday, 30 May 2015 12:40

የግጥም ጥግ

እልፍ ከሲታዎች ቀጥነው የሞገጉ

“ሥጋችን የት ሄደ” ብለው ሲፈልጉ

በየሸንተረሩ በየጥጋጥጉ

አስሰው አስሰው በምድር በሰማይ

አገኙት ቦርጭ ሆኖ አንድ ሰው ገላ ላይ፡፡

(“ኗሪ አልባ ጎጆዎች”፤ በዕውቀቱ ስዩም)

Published in የግጥም ጥግ
Saturday, 30 May 2015 12:39

የፍቅር ጥግ

 

 

 

* ፍቅር በፈገግታ ይጀምራል፤በመሳሳም ያድጋል፤በእንባ ይቋጫል፡፡

            ያልታወቀ ሰው

* ፍቅር እንደ ነፋስ ነው፤አታየውም ግን ይሰማሃል፡፡

            ኒኮላስ ስፓርክስ

* ምክንያት የሌለው ፍቅር ዕድሜው ረዥም ነው፡፡

            ያልታወቀ ሰው

* ፍቅር አብሮን የተፈጠረ ሲሆን ፍርሃት እዚህ የምንማረው ነው፡፡

            ማሪያኔ ዊላምሰን

* የሚወደን ሰው ከሌለ፣ ራሳችንን መውደድ ትተናል ማለት ነው፡፡

      ማዳም ዲ ስቴል

* ራሳችሁን ማፍቀር እንዳትረሱ፡፡

      ሶረን ኪርክጋርድ-

* ሰውን መውደድ የእግዜርን ፊት ማየት ነው፡፡

      ሌስ ሚዘረብልስ

* ፍቅር ከባድ ሥራ ነው፡፡ ከባድ ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ይጎዳል፡፡

      ያልታወቀ ሰው

* ፍቅር ሲይዘን በጣም የምናምነውን ነገር እንጠራጠራለን፡፡

      ላ ሮቼፎካልድ

* ስለፍቅር የምናውቀውን ብዙውን ነገር የምንማረው ከቤት ነው፡፡

      ያልታወቀ ሰው

* ፍቅር ከምንም በላይ የራስ ስጦታ ነው፡፡

      ጄን አኖይልህ

* በፍቅር መውደቅ ቀላል ነው፤ከባዱ የሚያነሳህ ሰው ማግኘቱ ነው፡፡

      በርትራንድ ራሴል

* ልብህን ለከፈትክላቸው ሰዎች አንደበትህን አትዝጋባቸው፡፡

      ቻርልስ ዲከንስ

* ፍቅር፤የሌላው ሰው ደስታ ለራስህ ወሳኝ የሚሆንበት ሁኔታ ነው፡፡

      ሮበርት ሄይንሊን

ሰው ሊደብቃቸው የማይችላቸው ሁለት ነገሮች፡ ስካር እና ፍቅር፡፡

አንቲፋንስ

* ሰዎችን የምትተች ከሆነ ለመውደድ ጊዜ አይኖርህም፡፡

ማዘር ቴሬዛ

 

 

 

 

Published in ጥበብ

 

 

 

ኢትዮጵያዊ ፊልሞችን የሚሰራው “ካም ግሎባል ፒክቸርስ” የተመሰረተበትን 20ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ባለፈው ረቡዕ ለስድስት እውቅ ተዋንያን የክብር ሽልማት ሰጠ፡፡ ተሸላሚዎቹ አርቲስት ኪሮስ ኃ/ሥላሴ፣ ሰለሞን ቦጋለ፣ ግሩም ኤርሚያስ፣ ማህደር አሰፋ፣ አማኑኤል ሀብታሙ እና የትናየት ታምራት ሲሆኑ ሁሉም ተዋናዮች ባለፉት ዓመታት ”ካም ግሎባል ፒክቸርስ” በሰራቸው ፊልሞች ላይ መተወናቸው ታውቋል፡፡ ድርጅቱ ከሰራቸው ፊልሞች መካከል “ስውሩ እስረኛ”፣ “በራሪ ልቦች”፣ “አማላዩ”፣ “ሼፉ” (ቁጥር 1 እና 2)፣ “ወደ ገደለው” እና “አማረኝ” ይገኙበታል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

           ወቅቱ 1982 ዓ.ም ነው፡፡ ባህልና ስፖርት ጉዳይ ሚኒስቴር አንድ የሥነ-ፅሑፍና የቴአትር ስልጠና ለወጣቶች አዘጋጅቶ ነበር፡፡ እዚያ ስልጠና ላይ ገጣሚ ደበበ ሠይፉ ስለግጥም እንዲያብራራ ተጋብዞ መጥቷል፡፡ እንደሚመስለኝ ደበበ ያንን ሁሉ የሥነ-ፅሁፍ ሰልጣኝ አልጠበቀም፡፡ ገና እንደገባ ፊቱን አኮፋትሮ ተመለከተን፡፡

“ይሄ ሁሉ ምንድነው?”

“የሥነ-ፅሁፍ ሰልጣኝ” የሚል መልስ አገኘ፡፡

“ይሄ ሁሉ?” ባለማመን፡፡

“አዎ”

ወደተዘጋጀለት መድረክ ወጥቶ ድጋሚ ተመለከተን፡፡ ሁለት መቶ እንሆናለን፡፡ እንዲህ አለን፡-

“እኔ ከእናንተ የምጠብቀውን ልንገራችሁ? አንድ ደራሲ፣ አምስት ሀያሲ እና አሥር ጥሩ አንባቢ”

በወቅቱ እኔ የተቀመጥኩት መካከል ላይ ነበር፡፡ ወደፊትና ወደኋላ አየሁ፡፡ ብዙ እሳት የለበሱ ወጣት ፀሐፊያን እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ እኔን የደበበ ትንቢት ተቋዳሽ የሚያደርገኝ አንድም መነሻ አልነበረኝምና፣ ያኔውኑ አዳራሹን ጥዬ መውጣት ተመኘሁ፡፡ ግን ድፍረት አጣሁ፡፡ የሚገርመው ከሃያ አምስት አመታት በኋላ የእነዚያን ሰልጣኞች ሁኔታ ሳጤን፣ ሁሉም ውሻ እንደገባበት የዝንጀሮ መንጋ በየአቅጣጫው ተበትኖ ቀርቷል፡፡ አንዳንዱን ጋዜጠኝነት፣ ሌሎቹን ኑሮ፣ የተቀሩትን ደግሞ የፍላጎት ለውጥ ከሥነ-ፅሁፍ አሰናከላቸው፡፡ ከሞላ ጎደል የደበበ ሠይፉ ትንቢት ሞላ፡፡፡ የሀያሲዎቹንና የጥሩ አንባቢዎቹን ባላውቅም የደራሲዎቹ መረጃ ግን አለኝ፡፡ ያኔ ከነበሩት ሰልጣኞች ደራሲነትን የገፋበት ድርቡ አደራ ብቻ ነው፡፡ (እኔን እናንተ ቁጠሩኝ)

ሌላኛው ሥነ-ፅሁፋዊ “ትንቢት” በዚያው ዘመን፣ በዚያው ሰው (በደበበ ሰይፉ) የተሰጠ ነው፡፡ “ብሌን” የደራሲያን ማህበር መፅሔት ላይ ሀያሲ አብደላ ዕዝራ አምስት የሥነ-ፅሁፍ ምሁራንን በአማርኛ ልቦለድ ዕድገት ላይ አወያይቶ ነበር፡፡ መነሻው ልቦለድ “ጦቢያ” ሲሆን መድረሻው ደግሞ “አደፍርስ” ነው፡፡ ደበበ ሠይፉ ትንቢት የተናገረው የዳኛቸው ወርቁ ሥራ በሆነው “አደፍርስ” ላይ ነበር፡፡ እንዲህ፡-

“… እንደተባለውም ልቦለዱ (አደፍርስ) ከታመመ ሃያ ዓመት ሆኖታል፡፡ ዛሬ ቢታተም ብለን ብንጠይቅ በዕውነት ተቀባይነቱ ይጨምራል ባይ ነኝ፡፡ የዛሬ ሰላሣ አርባ አመት ደግሞ በጣም በጣም ይጨምራል” (“ብሌን” 1982፤ ገፅ 37)

ደበበ ይሄን ካለ ሃያ አምስት ዓመት ሞልቶታል፡፡ “ትንቢቱ” ሊፈፀም አምስት ቀሪ አመታት አሉ፡፡ ይሁንና “አደፍርስ” በዚህ ዘመን ከሙታን የመነሳት ያህል የአንባቢያንና የሀያሲያን ጥያቄ እየሆነ መምጣቱን ስንመለከት ደበበ ያዘለት ለማለት እንገደዳለን? “አደፍርስ” ከአርባ አምስት ዓመታት በኋላ በዚህ ዘመን ዳግም ለመታተም መብቃቱስ “ትንቢቱ” ቀድሞ ለመፈፀሙ እንደጠቋሚ ይታያል? ለመሆኑ እኛ የትውልዱ ተሳታፊዎች እንኳን ቀና ግምት የሌለን እዚህ ዘመን ላይ እንዴት ደበበ አሸጋግሮ ተስፋ ሊጥልበት ቻለ? ደበበ እዚህ ትውልድ ላይ ትንቢት የወለደ ተስፋ እንዲጥል ያደረገው ምክንያት አለው?

ደበበ እና ዘመኑ ተምኔታዊያን አልነበሩምና ጥሬ እምነት የወለደው “ትንቢት” አያሳድጉም፡፡ ደበበ እዚህ ትውልድ ላይ ተስፋ ለመጣሉ ያቀረበው ምክንያት የዲያሌክቲካዊ ሥነ-አመክንዮን (Dialectical logic) ጠገግ የያዘ ነበር፡፡ ደበበ እንዲህ ይላል፡-

“… (አደፍርስ) ተቀባይነት ቢያጣ በጊዜው በተደራሲ የኪነ ውበት ንቃተ ህሊና ማነስ ነው እኔ የሚመስለኝ፡፡ ተደራሲያን እንደሌላው አይነት ንቃተ ህሊና ሁሉ ኪነ ውበታዊ ንቃተ ህሊናቸው እያደገ ይሄድና ይህንንም መፅሀፍ የሚያጣጥሙበት ጊዜ ይመጣል፡፡ …. ምክንያቱም የህዝብ ንቃተ ህሊና ወደፊት ነውና የሚሄደው፡፡ በዚህም በኪነ ጥበብም ረገድ ንቃቱ ያድጋል፡፡ ለዚህ ነው ይህ ልቦለድ ትናንት ተነባቢት ባይኖረው እንዲገርመን ያማያስፈልገው”

ደበበ “አደፍርስ”ን ያለዘመኑ ተፈጥሮ ትውልድ በዲያሌክቲካዊ ሥነ አመክንዮ እስኪበስል በባይተዋርነት የሚጠብቅ ዘመናዊ ልቦለድ ነው እያለን ነው፡፡ እዚህ ላይ ሁለት ድምዳሜዎችን ለይተን መፈተሽ ግዳችን ይሆናል፡፡ እነሱም የአደፍርስ ዘመናዊነት እና አሁን ያረፈበት ትውልድ ናቸው፡፡ አደፍርስ ዘመናዊ ልቦለድ ነው? በምን? ይሄስ ትውልድ “አደፍርስ” ሲጠብቀው የነበረው ልከኛ አንባቢ ነው? እንዴት? …

… የ “አደፍርስ”ን ዘመናዊነት በተመለከተ ዋቢ የምናደርገው ቴዎድሮስ ገብሬን ነው፡፡ “አደፍርስ ዘመናዊው ልቦለድ” የሚል ጥናት አላቸው፡፡ እዚህ ጥናታቸው ላይ ዘመናዊ ልቦለድነትን ከቨርጂኒያ ውልፍ እና ከዣኔት ዊንተርሰን መደምደሚያ አንፃር በመነሳት “አደፍርስ”ን ይዳኛሉ፡፡ ከጅማሬው የ“አደፍርስ”ን ዘመናዊነት በማወጅ ማሳያዎቹን ያስተነትናሉ፡፡

“አደፍርስ ዘመናዊ ልብወለድ ነው ስንል፤ ያነሳቸውን ጉዳዮች፤ የተመሰረተባቸውን ጽንሰ ሐሳቦች፤ የተረከባቸውን ቴክኒኮች እና የተከየነበትን ዘይቤ አዲስነት ተመልክተን ነው፡፡ የአማርኛን የረጅም ልቦለድ አተራረክ ልማድ በእጅጉ የፈተነው አደፍርስ፤ ከነባሮቹ የሥነ ልሳናትና የሥነ ፅሑፍ ደንቦች ያፈነግጣል፡፡ በትልም አነዳደፉ ከተለመደው የአከያየን ሥርዓት አይገጥምም፡፡ በሰርክ አይን ሲታዩ የተበጣጠሱ የሚመስሉ ሁነቶችና ገጠመኞች እየተፈራረቁና እየተጎራበቱ ይቀርብበታል፡፡ ይህ ልብወለድ ይሁነኝ ተብሎ በሚፈፀም አሻሚነት (deliberate Ambiguity) እና የአጨራረስ እንጥልጥልነት የተሞላ ነው፡፡”

ቴዎድሮስ ገብሬ የ“አደፍርስ”ን ዘመናዊነት ለማስረገጥ ብዙ ማሳያዎችን ጠቅሰዋል፡፡ “አደፍርስ” በተወለደበት ዘመን መግባባት የተሳነውና ሌሎች ትውልዶችን ጥበቃ የተቀመጠው በወቅቱ አማርኛ ልቦለድ የማያውቀውን ዘመናዊነት ይዞ በመምጣቱ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡

አሁን ወደ ሁለተኛው ጥያቄያችን እናምራ፡፡ ይሄ ትውልድ የ“አደርፍርስ” አቻ አንባቢ ነው? ኪነ - ውበታዊ ንቃተ ህሊናው የ “አደፍርስ” ተገዳዳሪ ያደርገዋል? “አደፍርስ”ን የሚሸከም “ጉልበት” አበጅቷል? ወይስ ሆሆታ ብቻ ነው? “አደፍርስ” ዳግም ለመታተሙ ጥያቄው የትውልዱ ነው? ወይስ የሚዲያዎች ጉልበታም ግፊት ጎርፍ ሆኖ ወሰደው? …. ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ብዙ ጥያቄዎች መልስ የሚያገኙበት ጥናት መከናወን አለበት፡፡ እስከዚያው ደግሞ እጅ አጣምሮ መቀመጥ ተገቢነት የለውምና አንዳንድ ፍተሻዎችን እናከናውን፡፡

“አደፍርስ” የዚህ ዘመን ልከኛ ልቦለድ መሆኑን አስረግጦ ለማሳየት የትውልዱን መንፈስ መቃኘት በቂ ይመስላል፡፡ ትውልዱ ጊዜና ቴክኖሎጂ በሰጠው ጠባይ በሉት ንቃተ ኅሊና ተመስርቶ የራሱን ተደናቂዎች ሰይሟል፡፡ ሌላውን ትተን በሥነ-ፅሁፍ ረገድ ከሄድን አዳም ረታ የዚህ ዘመን ተመራጭ ደራሲ ሆኗል ማለት ይቻላል፡፡ አዳም በዚህ ዘመን አንባቢ የተመረጠበትና ዳኛቸው በዚያ ዘመን አንባቢ ተገፍታሪ የሆነበት ምክንያቶች ከሞላ ጎደል አንድ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ዳኛቸው አዲስ አይነት የአፃፃፍ ስልት ይዞ መጥቶ ነባሩን፣ ተረታማውን ተጋፋ፡፡ አዳምም ያደረገው ይሄንኑ ነው፡፡ እንደውም ዳኛቸው ለአዳም የበረሃ ላይ ሰባኪ (መጥምቁ ዮሐንስ) ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ቴዎድሮስ ገብሬ ከዘመናዊ ልቦለድ አንፃር አደፍርስን የመጠነበት ገለፃ ለአዳም ሥራዎች በልክ የተሰፉ ናቸው፡፡ ዳኛቸው እና አዳም ሒስ ለመዋዋስ የሚያስችል አንድ አይነት የደራሲነት ቁመና አላቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል በጀማሪነት ዳኛቸውን፣ በቀጣይነት አዳምን እያነሳን የጋራ የሆኑ አንዳንድ የአፃፃፍ ቴክኒኮችን እንመዝን፡፡

ዳኛቸው “አደፍርስ” ውስጥ ትርክትና ጊዜን ለማጣጣም ተጨናቂ ሆኖ የቀረበበት ቦታ አለ፡፡ በልቦለድ አተራረክ ረገድ ድርጊት የተፈጸመበት ጊዜ ተፋትቶ ኢ-ተአማኒ በሆነ መንገድ መቅረቡ የተለመደ ጉዳይ ነው፡፡ ይሄን ችግር ቅድሚያ የተረዳው ዳኛቸው፤ የሦስት ማዕዘን ድርጊቶችን የጊዜ አንድነት ለማጣጣም አንድ የአተራረክ ዘዴ ተግባር ላይ አውሏል፡፡ “አደፍርስ” ውስጥ አባ ዮሐንስ ትምህርት ቤት ለማሰራት የመዋጮ ጥሪ ያደርጋሉ፤ በዚያው ላይ፣ ተደራቢ ሆኖ ፍሬዋ በላይ ፍቅረኛዋ የላከላትን ደብዳቤ ታነባለች፡፡ ከሌላ ማዕዘን ደግሞ አንድ አህያ ነጂ ይዘፍናል፡፡ እነዚህ ድርጊቶች አንድ ጊዜ ላይ የተከሰቱ ንብርብሮች ናቸው፡፡ በተለምዶ ፍርቅርቅ ትረካ አንዱን ጨርሶ ወደ ሌላው መዛወር፣ የጊዜን ግንዛቤ ማፍለስ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ዳኛቸው ድርጊቶቹን ድቅቅ አድርጎ በመክተፍ በጊዜ ጣባ ውስጥ አዋህዶ አቀረባቸው፡፡

ቀጣዩ የጊዜና የአተራረክ ተጨናቂ አዳም ደግሞ “ግራጫ ቃጭሎች” ውስጥ ባለአራት ጎን ድርጊያዎች አላግባብ የጊዜ ትዳራቸውን እንዳይፈቱ አንድ ዘዴ ተጠቅሟል፡፡ ገፅ 46 ላይ የወሰን እናት፣ ጠጅ ሻጯ፣ ተራኪው እና የእንጀራ እናቱ በጊዜ ሽራፊ ላይ ሆነው ሳይገፋፉ ያደረጉትንና ያሉትን ከነቅፅበታዊ ስሜቱ ለማስተላለፍ ሰንጠረዥ ተጠቅሟል፡፡ በደቂቃ ረድፍ ውስጥ የተከናወኑ ንብርብር ድርጊቶችና የተደበላለቁ ንግግሮች መቱን እንዲቀመጡ አድርጓል፡፡ ሰፊው የሰከንድ አፍ ስንት ድርጊትና ድምፅ ሊያነባብር፣ ሊያዳብል ይችላል?

ይሄ የጊዜና የድርጊያ ፍቺ ችግር ዳኛቸው እና አዳም በአንድ አይነት አእምሯዊ ሁኔታ ውስጥ ሆነው የሚፅፉ ደራሲዎች እንደሆኑ የሚጠቁም ነው፡፡ ሌላም አለ፡፡ ቅርፅን የሀሳብ ደጋፊ አድርጎ ማቅረብ፡፡ ዳኛቸው “አደፍርስ” ውስጥ ከገፅ 312 እስከ 319 ድረስ ቅርፅን የሀሳብና የአእምሮ ሁኔታ መግለጫ አድርጎ አቅርቧል፡፡ ፂወኔ አደፍርስ ላይ የጣለችው ተስፋ ሲንኮታኮትባት ስሜቷ ይምታታል፣ አእምሮዋ ይናውዛል፡፡ ዳኛቸው ይሄን የተምታታ ስሜትና የናወዘ አእምሮ፣ ከቃላት ይልቅ በሦስት ጎን ቅርፅ ይገልጸዋል፡፡ ሦስት ጎኑ የአንቀፅ መክፈቻና መዝጊያ ሆኖ በተደጋጋሚ ይቀርባል፡፡ ቅርፅን በማየት ብቻ የፂወኔ ሀሳብ ከብዙ ወደ ትንሽ፣ ከትንሽ ወደ ብዙ እንደሚንጠራወዝ እንረዳለን፡፡

አዳም ረታ ይሄንኑ ችግር መፍቻ ዘዴ፣ “ግራጫ ቃጭሎች” ላይ እና ሌሎቹም ሥራዎቹ ውስጥ ተጠቅሞበታል፡፡ ተራኪው መዝገቡ፤ በቃላት የማይገለፅ የከተማ ጉዞ ሲያደርግ አዳም ይሄን መናወዝ በቅርፅ ያቀርብልናል፡፡ አሁንም አዳም ረታና ዳኛቸው ወርቁ በአንድ አይነት አእምሯዊ ሁኔታ ውስጥ የሚፅፉ መሆኑን የሚጠቁም ስልት ነው፡፡

ሌላ የመጨረሻ ማሳያ እናንሳ፡፡ ዳኛቸው ወርቁ “ከአደፍርስ” ሌላ በእንግሊዝኛ የፃፋት ልቦለድ አለችው፡፡ “The Thirteenth Sun” የተሰኘች፡፡ እዚች ልቦለድ ውስጥ አንድ አዲስ የአተራረክ ስልት ተጠቅሟል፡፡ ገፀባህሪዎቹ ፊታውራሪ ወልዱ (አደፍርስ ውስጥ አሉ) ጎይቶም እና ወይኒቱ ናቸው፡፡ ወደ ዝቋላ አቦ የሚሄዱ መንፈሳዊ ተጓዦች ናቸው፡፡ የዚህ ልቦለድ ትረካ በፍርቅርቅ ነው፡፡ ዋናዎቹ ተራኪዎች ጎይቶምና ወይኒቱ ሲሆኑ አልፎ አልፎ አንዳንድ ስም የለሾች በወል ስም ተወክለው ለምሳሌ Peasant ተብለው ትረካ ይረከባሉ፡፡

አዳም ረታ ይሄንን የፍርቅርቅ ትረካ ስልት ከመጀመሪያ ሥራው ከ“ማህሌት” አንስቶ እሰከ መጨረሻው “መረቅ” ድረስ በተደጋጋሚ ተጠቅሞበታል፡፡ “ማህሌት” ውስጥ “ኤልዛቤል” የተሰኘው አጭር ልቦለድ በጳውሎስ፣ በመስፍንና በሠላማዊት ቅብብሎሽ ትረካ ይከናወናል፡፡ ዳኛቸው እና አዳም የሒስ አልባስ ለመዋዋስ የሚያስችል አንድ አይነት የደራሲነት ቁመና ቢኖራቸውም በየትውልዳቸው ተመሳሳይ አቀባበል አላገኙም፡፡ ዳኛቸው ተወግዟል፡፡ ባለቅኔው ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል፤ “አትሁን እፊት/ ያደርግሃል ወንፊት” ያሉት ይሄን ይሆን? ዳኛቸው በዚያ ዘመን የአዳም የበረሃ ላይ ሰባኪ እንደሆነው ሁሉ አዳምም በዚህ ዘመን የዳኛቸው መንገድ ጠራጊ ነብይ ነው፡፡ አዳምን የተቀበለና ከፍ ከፍ ያደረገ ትውልድ፣ ለዳኛቸው ልቡን መክፈትና ማስተናገድ ይሳነዋል?

 

 

 

Published in ጥበብ
Page 1 of 19