Administrator
Sunday, 17 August 2025 14:08
አንጋፋው የኪነጥበብ ባለሙያ ደበበ እሸቱ በ83 ዓመት ዕድሜው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ የመድረክ ፈርጥ የነበሩ አርቲስቱ ተዋናይ፣ አዘጋጅና የመድረክ መሪ በመሆን ለረዥም ዓመታት በሙያው አገልግሏል። ደበበ እሸቱ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ድራማና ፊልሞች ተዋናይ እንዲሁም ጋዜጠኛም ነበር። የዝግጅት ክፍላችን በአርቲስቱ ህልፈት ጥልቅ ሃዘኑን እየገለጸ፣ ለቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂ
በኪነ-ጥበቡ ዓለም ታላቅ ዐሻራቸውን ያሳረፉት አርቲስት ደበበ እሸቱ ማረፋቸውን ከቤተሰባቸው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አርቲስት ደበበ እሸቱ ለሀገራቸው ያላቸውን የማይናወጥ ፍቅር እስከ እስትንፋሳቸው መጨረሻ ያሳዩ ፅኑ ሀገር ወዳድ ነበሩ።
የታሪክ ድርሳናቸው እንደሚያስረዳው አርቲስት ደበበ እሸቱ በ1934 ዓ.ም ነው የተወለዱት። የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ተከታትለዋል።
በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ተማሪ እያሉ ቲያትር የመስራት ዕድሉ ገጥሟቸው ነበር።
ከዛ በመቀጠል የአብራሪነት ስልጠና ለመውሰድ እጩ መኮንን ሆነው የኢትዮጲያ አየር ሀይልን ተቀላቀሉ። በአየር ኃይል የመዝናኛ ክፍሉ ላይ በመሳተፍ ቲያትር ሰርተዋል።
አርቲስት ደበበ እሸቱ፤ በሀገር ፍቅርና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ (የአሁኑ ብሔራዊ ቴአትር) መድረክ ላይ ለረዥም ዓመታት በተዋናይነትና በአዘጋጅነት አገልግለዋል።
በተለያዩ ፊልሞች ላይ በመሪ ተዋናይነትም ተሳትፈዋል። በሆሊውድ በተሠራው 'ሻፍት ኢን አፍሪካ' በተሰኘው ፊልም ላይ በመሳተፍም ስማቸውን በደማቁ ፅፈዋል።
በእንግሊዘኛ ከሠሩባቸው ፊልሞች መካከል 'ዘ ሴይለር ፍሮም ጂብራልታር'፣ 'ጉማ'፣ 'ዘ አፍሪካን ስፓይ'፣ 'ዜልዳ'፣ 'ዘ ግሬቭ ዲገር' እና 'ዘ ግሬት ሪቤሊየን ' ይጠቀሳሉ።
'ዘ ጌም ኦፍ ቼዝ' ላይ በትወና ፣ 'ኦቴሎ' ላይ በመተወን እና በማዘጋጀትም የጥበብ አሻራቸውን አኑረዋል።
ደበበ እሸቱ ከአርቲስቱ በተጨማሪ በራድዮና በቴሌቪዥን ሥራዎችም ላይ ተሳትፈዋል። 'ያላቻ ጋብቻ'፣ 'ሮሚዎና ዡልየት' እና 'ዳንዴው ጨቡዴ' ከተወኑባቸው ሥራዎች ጥቂቶቹ ናቸው።
አርቲስት ደበበ እሸቱ በአውሮፓውያኑ 1985 ዚምባቡዌ በተካሄደው ቴአትር ለልማትና ዕድገት ወርክሾፕ ላይ በብቃት በመሳተፍ የአፍሪካ የመድረክ ባለሙያዎች ማሕበርን አስተባብረው በማቋቋም የማሕበሩም መስራች ፕሬዚዳንት ሆነው ለ12 ዓመታት አገልግለዋል፡፡
ለአፍሪካ ቲያትር ባደረጉት አስተዋጽኦ የዚምባብዌን ማላካይት አዋርድ ወስደዋል። ጣይቱ ኢንተርቴንመንት በዋሽንግተን ዲሲ በቲያትር ዘርፍ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ አድርጓቸዋል፡፡
በአትላንታ ጂኦርጂያ የከተማው ምክር ቤት ለዓለም ቲያትር ባደረጉት አስተዋጽኦ ኖቬምበር 24ን የደበበ እሸቱ ቀን በሚል ሰይሞላቸዋል፡፡
የኢትዮጲያ ባህል ሚኒስትርም ለኢትዮጲያ ፊልም እድገት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሸልሟቸዋል፡፡
በጉማ አዋርድም የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
በአውሮፓውያኑ 2015 በቫንኮቨር ዓለማቀፍ ፊልም ፌስቲቫልም በምርጥ መሪ ተዋናይ ዘርፍ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ በ2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለሃገራቸው ባበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሸልሟቸዋል።
አርቲስት ደበበ እሸቱ በ1995 ዓ.ም በሃገራዊ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ በመሳተፍ የምክር ቤት አባል እና የፓርቲያቸው የሕዝብ ግንኙነት በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሰው ናቸው። በዚህም ከሌሎች አመራሮች ጋር በተለያዩ ጊዜያት ለእስር ተዳርገው ነበር።
ኢቢሲ ለቤተሰባቸው፣ ለወዳጅ ዘመድ እና ለመላው አድናቂዎቻቸው መጽናናትን ይመኛል።
የኢፌዲሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ሚና ከተጫወቱ አንዱና ግንባር ቀደሙ አንጋፋው የመድረክ ፈርጥ፣ ደራሲ፣ ተርጓሚ፣ ተዋናይ፣ ከያኒ፣ ጋዜጠኛ፣ የመብት ተሟጋች እና ሀገር ወዳዱ የክብር ዶክተር አርቲስት ደበበ ህልፈተ ሕይወት የተሰማውን ሐዘን ገልጿል።
በ83 ዓመታቸው ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን በመስማታችን ታላቅ ሀዘን ተሰምቶናል ሲልም ሚኒስቴሩ መግለጫ አውጥቷል።





Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 13 August 2025 17:12
“ታሪኩን የማያከብር ትውልድ መቼም ታሪክ አይሠራም"
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በማራኪ ግቢ የሚገኘውን የፊልም ትምህርት ክፍል አዳራሽ "ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ሲኒማ አዳራሽ" ብሎ ሰይሟል። የአማራ ሚዲያ ኮሙኒኬሽን ይህን ምክንያት በማድረግ የፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማን ሥራዎችና ማንነት የሚያስቃኝ ዘገባ አስነብቧል፡፡ ከመጠነኛ አርትኦት ጋር እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
***
በ1959 ዓ.ም ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በፈጠራ ጥበብ ማዕከል ውስጥ አጭር ቆይታ ካደረጉ በኋላ በልጅነታቸው የፊልም ተዋናይነትና ደራሲነትን ለመማር ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ሰሜን አሜሪካ አቅንተው የአንደኛና የሁለተኛ ዲግሪያቸውን አጠናቅቀዋል።
በዚያ በተማሪነት ዘመናቸው ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ሁለት ፊልሞችን ማለትም ሐወር ግላስ ("Hour Glass" በ1963 ዓ.ም) እና ቻይልድ ኦፍ ሪዚስታንስ ("Child of Resistance" በ1964 ዓ.ም) የተሰኙ ፊልሞችን መድረስ ችለዋል።
በመጨረሻም መመረቂያ ፊልማቸውን ስለ አንዲት ሴት ልጅ እናትና ነፍሰ ጡር ጥቁር አሜሪካዊት ስለሚደርስባት በደል ብሎም ስለምትኖርበት የድህነት አረንቋ እና ቡሽ ማን ("Bush mama") የተሰኙ ፊልሞችን ሠርተዋል።
በእነዚህ ጊዜያት ነው ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ የፊልም ዳይሬክተር ብቻም ሳይኾኑ ታሪክ ተራኪ፣ በፊልም ሥራቸው ለሰው ልጅ ክብርና መብት ለሚደረግ ትግል በተለይም ለአፍሪካ ብሎም በዓለም ላይ ተበትኖ ለሚኖረው ጥቁር ሕዝብ ፋና ወጊ እንደሚኾኑ የታመነበት።
በፊልም በተመረቁ ዋዜማም ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ በ1967 ዓ.ም በመመለስ "የ3 ሺህ ዓመት ምርት" የተሰኘውን ጥቁርና ነጭ 16 ሚሊ ሜትር ፊልምን ቀርጸዋል። ዛሬ በዋሽግተን ዲሲ የሚገኘው ሀዋርድ ዩኒቨርሲቲ፣ የሎሳንጀለስ ዩኒቨርሲቲ፣ ኒዎርክ የሚገኘው ዘ ሴንተር ፎር ሂውማን ራይት ኤንድ ዘአርት አት ባርድ ኮሌጅ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የፊልም ተቋማት "የ3 ሺህ ዓመት ምርት" ፊልምን የአፍሪካ ታሪክ፣ ማኅበራዊ ፍትሕ፣ አፍሪካ ድህረ ቅኝ ግዛት እንዲሁም ገለልተኛ ፊልም ሰሪ በሚል ለማስተማሪያ ይጠቀሙበታል።
ከ1975 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በሀዋርድ ዩኒቨርሲቲ በፊልም ፕሮፌሰርነት ለረጅም ዓመታት በማስተማር ብዙ ጥቁር የፊልም ደራሲያንን ኮትኩተው አሳድገዋል። በገለልተኛ ፊልም ሥራዎች አንቱ በመባል በጥቁሮች የሲኒማ ታሪክ ከፍተኛ ማማ ላይ መድረስም ችለዋል። ሎሳንጀለስ ካሊፎርኒያ የሚገኘው "ዘ አካዳሚ ሙዝየም ኦፍ ሞሺን ፒክቸርስ" የቫንቴጅ ሽልማት የመጀመሪያው ተሸላሚ ኢትዮጵያዊም ናቸው፤ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ።
ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ በሠሯቸው ሥራዎችና በሕይወታቻው ሁሉ ኢትዮጵያ ከልባቸውና ከአፋቸው አትጠፋም።
“ታሪኩን የማያከብር ትውልድ መቼም ታሪክ አይሠራም፤ እንደ ዓመድ ክምር በኖና ተበትኖ ይጠፋል እንጅ” በሚል ንግግራቸውም ይታወቃሉ።
የፊልም ሥራዎቻቸው በኢትዮጵያዊ ማንነታቸው ላይ የተመሠረተ ቢኾንም፣ ከምንምና ማንም በላይ በሰፊው የፓን አፍሪካን ራዕይ የሚያቀነቅኑ ጠቢብ ናቸው። የፊልም ሚዲያን ለነጻነት መታገያና ፍትሕ ለተጓደለባቸው መሳሪያነት የሚጠቀሙ ታዋቂ አፍሪካዊ ምሁርና የሲኒማ ተራኪም በመኾን ታላቅ ክብር ለመጎናጸፍ በቅተዋል፡፡
ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ በአበረከቷቸው አስደናቂ የሲኒማ ሥራዎቻቸውም ኾነ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ኢትዮጵያዊነትን በማስተዋወቅ አቻ የማይገኝላቸው ሲኾኑ፤ አፍሪካዊነትንም ከፍ አድርገው የሚያቀነቅኑ ምርጥ አፍሪካዊ ምሁርም ጭምር ናቸው፡፡
ሥራዎቻቸውም በአብዛኛው የተጨቆኑና የተገለሉ ሕዝቦችን ሕይወት ያማከሉ፤ ተቃውሞን፣ ነፃነትንና ፍትሕን የሚያበረታቱ ናቸው። ሥርዓታዊ ዘረኝነትን በማጋለጥና በእኩልነት ላይ ያለማመንታት ጥብቅና በመቆም ታዋቂ ዓለም አቀፍ ድምጽ መሆንም ችለዋል።
የፕሮፌሰር ኃይሌ ሥራዎች በተደጋጋሚ በምዕራባዊያን የፊልም ኢንዱስትሪ አጋፋሪዎች የተገለሉበት ምክንያትም በድፍረት ዕውነትን፣ ፍትሕና የሰብዓዊ እኩልነትን በመሥበክ የዓለም አቀፍ ድምጽ በመኾናቸው ነው።
ከታዋቂ የፊልም ሥራዎቻቸው መካከልም በጥቂቱ ለመጥቀስ ፦
አድዋ — የአፍሪካ ድል ( Adwa: An African Victory)
ሳንኮፋ — ስለ ዝርያዊ ባርነት፣ የአፍሪካ ማንነት እና የባሕላዊ ነፃነት
ጤዛ — ስለ ስደት እና የፖለቲካ ትግል
እነዚህ ፊልሞች ከመዝናኛ ባለፈ የአፍሪካ ጽናትና ባሕልን አጉልተው የሚያሳዩም ናቸው።
እነዚህንና ሌሎች በርካታ አበርከቷቸውን ለመዘከር ብሎም ትውልድ እንዲማርባቸው ለማድረግ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በማራኪ ግቢ የሚገኘውን የፊልም ትምህርት ክፍል አዳራሽ "ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ሲኒማ አዳራሽ" ብሎ በመሰየም ከፍተኛውን የክብር ምልክትና ዕውቅና ሰጥቷቸዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…



Published in
ህብረተሰብ
Tagged under
Wednesday, 13 August 2025 17:11
“ግብጻዊያን ትብብር የዜሮ ድምር ውጤት ነው የሚል አመለካከት አላቸው”
ግብጻዊያን ትብብር የዜሮ ድምር ውጤት ነው የሚል አመለካከት የሚያራምዱ መሆኑን በውሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ቡድን ሰብሳቢ አቶ ፈቅአህመድ ነጋሽ ገለጹ፡፡
አቶ ፈቅአህመድ ከጋዜጣ ፕላስ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ ትብብርን በተመለከተ ግብጻዊያን የዜሮ ድምር ውጤት ነው የሚል አለመካከት አላቸው፡፡
የላይኛው ተፋሰስ ሀገር አንድ ጠብታ ውሀ ከተያዘ ከእኛ ድርሻ ላይ ይቀንሳል የሚል የተሳሳተ አመለካከትና ፍራቻ አለባቸው ብለዋል፡፡
ነገር ግን ከግድቡ ኃይልን በማመንጨት ውሀውን መልሶ የሚለቀቅ እንዲሁም በሂደቱ በትነት የሚጠፋ ውሀን በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሁሉም ከተባበሩ በተፋሰሱ ውስጥ ተጨማሪ ውሀ ማግኘት እንደሚቻልም ገልጸዋል፡፡
Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 13 August 2025 17:07
2.8 ሚ. ዓመት ያስቆጠረ አዲስ ቅሪተ አካል በአፋር ተገኘ
በአፋር ክልል ለዲ ገራሩ፣ ሁለት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን አመት እድሜ ያስቆጠረ ቅሪተ አካል መገኘቱን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አስታውቋል። ይህም ኢትዮጵያ የሰዉ ልጅ ምንጭ ስለመሆኗ ለዓለም የሚያሳይ ተጨማሪ ማረጋገጫ መሆኑን ባለስልጣኑ ጠቁሟል፡፡
ጥናቱ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ከአሪዞና ስቴት ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር የተሰራ ሲሆን፤ ኔቸር በተሰኘዉ ዓለም አቀፍ የሳይንስ መጽሄት ላይ ይፋ ተደርጓል።
በጥናቱ፤ የተገኘዉ መሉ የጥርስ አካልና ግኝቱ አዉስትራሎፒከስ መሆኑ ተጠቅሷል። ይሁን እንጂ ሙሉ አካል ባለመገኘቱ ጾታዉ አለመታወቁና ስም ለመስጠት አለመቻሉ ተገልጿል።
ከዚህ በፊት ይህን ያህል ዓመት ያስቆጠረ አዉስትራሎፒቲከስ ተገኝቶ የማይታወቅ ሲሆን፤ የዛሬዉ ግኝትም ሁለቱ ዝርያዎች አብረዉ ይኖሩ እንደነበረ ያሳያል ተብሏል።
Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 13 August 2025 17:04
የ1 አመት ከ8 ወር ህፃን አግተው 2 ሚ. ብር የጠየቁ አራት ግለሰቦች ተያዙ
የአንድ አመት ከስምንት ወር እድሜ ያለውን ህፃን በማገት ሁለት ሚሊዮን ብር የጠየቁና በወንጀሉ ተባብረዋል የተባሉ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
ወንጀሉ የተፈፀመው ሀምሌ 30 ቀን 20017 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 1፡40 ሰዓት ገደማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አፍሪካ ህብረት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን ፖሊስ አስታዉቋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ፋኑኤል ብርሃነ የተባለን የ1 አመት ከ8 ወር ዕድሜ ያለውን ህፃን ከመኖሪያ ቤቱ በስውር በመውሰድ ወደ ወላጅ አባቱ ስልክ ደውለው ህፃኑን እንዳገቱት በመግለፅና ሁለት ሚሊዮን ብር በአካውንት ገቢ እንዲያደርጉ በመጠየቅ፣ በቤተሰብ ላይ ጭንቀትና ድንጋጤን ፈጥረዋል፡፡
አቶ ብርሃነ ገ/ፃዲቅ የተባሉት የህፃኑ ወላጅ አባትም ስለ ሁኔታው በአቅራቢያቸው ለሚገኝ ፖሊስ በወቅቱ አሳውቀዋል።
የህፃኑ መጥፋት ሪፖርት የደረሰው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የቄራ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የምርመራና የክትትል ክፍሉ ተቀናጅተው በተደረገ ከፍተኛ ጥረት ካህሳይ ተክላይ የተባለውንና ከህፃኑ ወላጅ አባት ጋር ዝምድና ያለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ፖሊስ አስታዉቋል፡፡
የወንጀሉ አቀነባባሪ ነው ተብሎ ተጠርጥሮ በተያዘው በካህሳይ ተክላይ ላይ በተከናወነ ምርመራ የማስፋት ስራ በህፃኑ እገታ ከሚገኝ ገንዘብ የጥቅም ተካፋይ ለመሆን በመስማማት ወንጀሉን የተባበሩ ፊሊሞን ገ/ማርያም፣ ተክሊት ህሉፍ እና ምህረት ዕድሉ የተባሉ ተጨማሪ ሶስት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
እነዚህ ተጠርጣሪዎች የተያዙት ወንጀሉ በተፈፀመ በማግስቱ ሳሪስ አካባቢ በሚገኘው ማራኪ በተባለ ሆቴል ውስጥ አልጋ በመከራየት ህፃኑን ይዘው በተሸሸጉበት ወቅት ፖሊስ ባደረገው ክትትል መሆኑ ታውቋል፡፡
በአጠቃላይ በወንጀሉ የተጠረጠሩት አራት ግለሰቦች በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ፖሊስ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡



Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 13 August 2025 17:03
የጉበት ንቅለ ተከላ ህክምና በቅርቡ ሊጀመር ነው
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የጉበት ንቅለ ተከላ ህክምና በቅርቡ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ንዋይ ፀጋዬ፤ የሆስፒታሉ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያዎች ልዑክ በጉበት ንቅለ ተከላ ህክምና ከፍተኛ ልምድ ባለው የካሊፎርኒያው ፓሲፊክ የህክምና ማዕከል ለሳምንታት የቆየ የምልከታስልጠና ሲያደርግ መቆየቱን ለአራዳ ኤፍ ኤም ገልፀዋል።
በትውልደ አትዮጵያዊቷ አሜሪካዊት የጉበት ንቅለ ተከላ የህክምና ባለሙያ ዶ/ር ቅድስት ኪዳነ ይልማ አመቻችነት የተካሄደው መርሐ ግብር፥ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የጉበት ንቅለ ተከላ አገልግሎት ለማከናወን በምታደርገው ጥረት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው ብለውታል።
የባለሙያዎች ቡድን አባላቱ በርካታ የጉበት ንቅለ ተከላ ሂደቶችን የተመለከቱ ሲሆን፤ ከዋነኛ የንቅለ ተከላ ቀዶ ጥገና ሐኪሞች የተግባር ስልጠና እና የዕለት ተዕለት ምክር ማግኘታቸውንም ነው የተናገሩት።
ቡድኑ በቆይታው ንቅለ ተከላ የሚያስፈልጋቸውን ታካሚዎች የጤና ደረጃ፣ የለጋሾች ልየታና በህክምናው ዙሪያ ያሉትን ስርዓቶች በተመለከተ አስፈላጊ እውቀት ማግኘቱን ጠቁመዋል።
ሆስፒታሉ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በበቂ ዝግጅት ወደ ሥራ ሲገባ፣ ለጉበት ንቅለ ተከላ ህክምና ውጭ ሀገር መሄድን ያስቀራል መባሉን ጣቢያው ዘግቧል፡፡

Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 13 August 2025 17:01
"የአባይ ተፋሰስ ሀገሮች “ታሪካዊ መብቶች” ላይ ከማተኮር
ይልቅ ዓለም አቀፍ ፍላጎትን ማጤን አለብን" -ሙሴቪኒ-
የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ከግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር በካይሮ ተገናኝተው በአባይ ወንዝ ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ በኤክስ ገጻቸው ላይ ከአልሲሲ የተለየ እንደውም ፍጹም ተቃራኒ ሃሳብ አጋርተዋል፡፡
ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች በውይይታቸው ወቅት በአባይ ወንዝ የወደፊት ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ሙሴቪኒ ጠቅሰዋል፡፡
የአባይን ጉዳይ ሰፋ ባለ እይታ መመልከት አለብን ያሉት የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት፤ አንዳንድ ጊዜ ችግሮች የሚያጋጥሙት ለጉዳዩ ባለን አቀራረብ ነው ብለዋል፡፡
የአባይ ተፋሰስ ሀገሮች “ታሪካዊ መብቶች” ላይ ከማተኮር ይልቅ ዓለም አቀፍ ፍላጎትን ማጤን አለብን ሲሉም ጽፈዋል፡፡
"ግባችን ሊሆን የሚገባው ብልፅግና ለሁሉም ፣ የኤሌክትሪክ ሀይል ተደራሽነት ለሁሉም፣ መስኖ መጠቀም ለሁሉም፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ለሁሉም የሚል ነው" ብለዋል፡፡
እነዚህን አላማዎች በማዕቀፍ ውስጥ በማስገባት ሳይንሳዊና ፍትሃዊ ዘዴዎችን ተጠቅመን ተግባራዊ ልናደርገው እንችላለን ሲሉም ሙሴቪኒ አክለዋል፡፡
በተቃራኒው የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ፣ ከሙሴቪኒ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ በአባይ ወንዝ ላይ የሚደረጉ ማናቸውንም የአንድ-ወገን እርምጃዎች ውድቅ በማድረግ፣ ግብፅ የውኃ ሀብት መብቷን ችላ ትላለች ብሎ የሚያምን ማንኛውም ሰው «ተሳስቷል» ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን ዘግበናል፡፡
Published in
ዜና
Tagged under
Tuesday, 12 August 2025 00:00
"ክቡር ልጆች" የሕንጸት ቡክ አዋርድን አሸነፈ
"--አንዲት እናት ልጆቿን ብቻዋን ታሳድጋለች፡፡ የአስተዳደግ ዘይቤዋ ከሌሎች ወላጆች ለየት ይላል፡፡ ልጆቿ ከሰፈር ልጆች ጋር ተቀላቅለው ሲጫወቱ አይቼ አላውቅምና ሁሌም ጥያቄ ይፈጥርብኝ ነበር፡፡ ልጆችሽ ከእድሜ እኩዮቻቸው ጋር ሲጫወቱ አይቼ አላውቅም አልኳት፡፡
“በልጅነቴ ብቸኛ ወንድሜን ያጣኹት ሰፈር ውስጥ በተወረወረ ድንጋይ ነው” ወዲያውም ስቅስቅ ብላ አለቀሰች፡፡
“በጣም አዝናለሁ፤ መጠየቅ አልነበረብኝም” አልኳት
“እነዚህን ብርቅዬ ልጆች እንደ ወንድሜ ማጣት አልፈልግም፡፡ ውጭ እንደ ሌሎች ልጆች ቢጫወቱ ይሞቱብኛል ብዬ እፈራለሁ፡፡” አለችኝ
ህክምና ያላገኘ የልጅነት ጠባሳ ጊዜ ጠብቆ በትዳር ህይወትም ይገለጣል::"
***
ከላይ የተነበበው ጽሁፍ በደራሲ ብርሃኑ በላቸው "ክቡር ልጆች" በሚል ርዕስ ከተጻፈውና የዘንድሮን የ2017 የሕንጸት ቡክ አዋርድ ካሸነፈው መጽሐፍ የተቀነጨበ ነው፡፡
ደራሲ ብርሃኑ በላቸው፤ የበኩር ሥራው እውቅና ማግኘቱን በብዙ ትህትና መቀበሉንና ለቀጣይ ስራው ትልቅ ሃላፊነት መቀበሉን ተናግሯል።
"Hintset Christian Society- ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር"፤ ዘንድሮ መጽሐፍትን አወዳድሮ እውቅና ሲሰጥ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና
Tagged under
Wednesday, 13 August 2025 06:58
እንዳያመልጣችሁ - ከ50ሺ እስከ 300 ሺ ብር ያሸልማል!
ማንበብ ያሸልማል፤እውቀት ያሻግራል!!!
አዲስና ልዩ ዕድል ለአንባቢዎችና ለሥራ ፈጣሪዎች!
በዶክተር ያሬድ ኢሳያስ የተጻፈውን " *ኒዩሮ ሳይንስ ለሥራ ፈጠራ* " እና " *የኒዩሮ አመራር ሳይንስ* " የተሰኙ ሁለት መጻሕፍትን ገዝታችሁ አልያም ተውሳችሁ አንብቡ!
ለሥራ ዕቅድና ፈጠራችሁ
"ኒዩሮ ሳይንስ ለሥራ ፈጠራ" ከተሰኘው መጽሐፍ ያገኛችሁትን ሀሳቦችና ጥቅሞች ከየትኛው የመጽሐፉ አንቀጽና ገጽ እንዳጣቀሳችሁ በመግለጽ ከሁለት ገጽ ባልበለጠ ዘርዝራችሁ አስቀምጡ።
የፈጠራችሁትን የሥራ ዕቅድ እንዴት እንደምትመሩት "የኒዩሮ አመራር ሳይንስ" ከተሰኘው መጽሐፍ ባገኛችሁት ሀሳብና መረጃዎች መሠረት በግማሽ ገጽ አስፍሩ።
በአጠቃላይ የቢዝነስ ዕቅዳችሁንና ከመጽሐፍቶቹ ያገኛችሁትን ተግባራዊ ዕውቀቶች በአምስት ገጽ ጽፋችሁ አዘጋጁ።
በዛጎል የመጻሕፍት ባንክ (ZAGOL BOOK BANK) የቴሌግራም ገፅ አድራሻ @ZAGOLBOOK የሥራ ዕቅዳችሁን
ላኩ!
የላካችሁት ሰነድ መሥፈርቱን የሚያሟላ ከሆነ ትጠራላችሁ፣ በዳኞች ፊት ቀርባችሁ ትወዳደራላችሁ!
ካሸነፋችሁ የገንዘብ ሽልማት ታገኛላችሁ!!!
1ኛ ለወጣ:- 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ብር!
2ኛ ለወጣ:-150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር!
3ኛ ለወጣ:-50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር!
መልካም ዕድል!!!!!
ለበለጠ መረጃ፡+251976066720 ይደውሉ
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና
Tagged under
Wednesday, 13 August 2025 06:38
"ለሀገር የታወጀ አብዮት ነው" የተባለለት አዲስ መፅሐፍ!!
የሕክምና ባለሙያ በሆነዉ ዶ/ ር ደሳለው ካሳሁን የተፃፈዉና በሥነጽሁፍ ምሁራን ብዙ የተባለለት “ፓሌሮዳ “ አዲስ መፅሐፍ በቅርብ ቀን!!
“ፓሌሮዳ “ ሜታፊዚክስን፣ መጽሐፈ ሄኖክን፣ ምናባዊ የህክምና ግኝቶችን፣ እንዲሁም ጂኦፖለቲካንና ፍቅርን አንድ ላይ አሰናስሎ ወደፊት የሚከንፍ፤ በይዘቱ ወይም በሀሳቦቹ በሐገራችን ስነጽሑፍ ያልተለመደ ድርሰት ነው።
(ደራሲ ህይወት ተፈራ)
"ፓሌሮዳ" ለኔ ልቦለድ ብቻ ሳይሆን ንቅናቄ ነው። ለትውልድ የተላለፈ ማንቂያ ደወል ነው። ለሀገር የታወጀ አብዮት ነው።
(ደራሲና ገጣሚ አያልነህ ሙላት)
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና
Tagged under

