Administrator
Wednesday, 13 August 2025 17:07
2.8 ሚ. ዓመት ያስቆጠረ አዲስ ቅሪተ አካል በአፋር ተገኘ
በአፋር ክልል ለዲ ገራሩ፣ ሁለት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን አመት እድሜ ያስቆጠረ ቅሪተ አካል መገኘቱን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አስታውቋል። ይህም ኢትዮጵያ የሰዉ ልጅ ምንጭ ስለመሆኗ ለዓለም የሚያሳይ ተጨማሪ ማረጋገጫ መሆኑን ባለስልጣኑ ጠቁሟል፡፡
ጥናቱ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ከአሪዞና ስቴት ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር የተሰራ ሲሆን፤ ኔቸር በተሰኘዉ ዓለም አቀፍ የሳይንስ መጽሄት ላይ ይፋ ተደርጓል።
በጥናቱ፤ የተገኘዉ መሉ የጥርስ አካልና ግኝቱ አዉስትራሎፒከስ መሆኑ ተጠቅሷል። ይሁን እንጂ ሙሉ አካል ባለመገኘቱ ጾታዉ አለመታወቁና ስም ለመስጠት አለመቻሉ ተገልጿል።
ከዚህ በፊት ይህን ያህል ዓመት ያስቆጠረ አዉስትራሎፒቲከስ ተገኝቶ የማይታወቅ ሲሆን፤ የዛሬዉ ግኝትም ሁለቱ ዝርያዎች አብረዉ ይኖሩ እንደነበረ ያሳያል ተብሏል።
Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 13 August 2025 17:04
የ1 አመት ከ8 ወር ህፃን አግተው 2 ሚ. ብር የጠየቁ አራት ግለሰቦች ተያዙ
የአንድ አመት ከስምንት ወር እድሜ ያለውን ህፃን በማገት ሁለት ሚሊዮን ብር የጠየቁና በወንጀሉ ተባብረዋል የተባሉ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
ወንጀሉ የተፈፀመው ሀምሌ 30 ቀን 20017 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 1፡40 ሰዓት ገደማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አፍሪካ ህብረት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን ፖሊስ አስታዉቋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ፋኑኤል ብርሃነ የተባለን የ1 አመት ከ8 ወር ዕድሜ ያለውን ህፃን ከመኖሪያ ቤቱ በስውር በመውሰድ ወደ ወላጅ አባቱ ስልክ ደውለው ህፃኑን እንዳገቱት በመግለፅና ሁለት ሚሊዮን ብር በአካውንት ገቢ እንዲያደርጉ በመጠየቅ፣ በቤተሰብ ላይ ጭንቀትና ድንጋጤን ፈጥረዋል፡፡
አቶ ብርሃነ ገ/ፃዲቅ የተባሉት የህፃኑ ወላጅ አባትም ስለ ሁኔታው በአቅራቢያቸው ለሚገኝ ፖሊስ በወቅቱ አሳውቀዋል።
የህፃኑ መጥፋት ሪፖርት የደረሰው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የቄራ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የምርመራና የክትትል ክፍሉ ተቀናጅተው በተደረገ ከፍተኛ ጥረት ካህሳይ ተክላይ የተባለውንና ከህፃኑ ወላጅ አባት ጋር ዝምድና ያለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ፖሊስ አስታዉቋል፡፡
የወንጀሉ አቀነባባሪ ነው ተብሎ ተጠርጥሮ በተያዘው በካህሳይ ተክላይ ላይ በተከናወነ ምርመራ የማስፋት ስራ በህፃኑ እገታ ከሚገኝ ገንዘብ የጥቅም ተካፋይ ለመሆን በመስማማት ወንጀሉን የተባበሩ ፊሊሞን ገ/ማርያም፣ ተክሊት ህሉፍ እና ምህረት ዕድሉ የተባሉ ተጨማሪ ሶስት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
እነዚህ ተጠርጣሪዎች የተያዙት ወንጀሉ በተፈፀመ በማግስቱ ሳሪስ አካባቢ በሚገኘው ማራኪ በተባለ ሆቴል ውስጥ አልጋ በመከራየት ህፃኑን ይዘው በተሸሸጉበት ወቅት ፖሊስ ባደረገው ክትትል መሆኑ ታውቋል፡፡
በአጠቃላይ በወንጀሉ የተጠረጠሩት አራት ግለሰቦች በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ፖሊስ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡



Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 13 August 2025 17:03
የጉበት ንቅለ ተከላ ህክምና በቅርቡ ሊጀመር ነው
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የጉበት ንቅለ ተከላ ህክምና በቅርቡ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ንዋይ ፀጋዬ፤ የሆስፒታሉ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያዎች ልዑክ በጉበት ንቅለ ተከላ ህክምና ከፍተኛ ልምድ ባለው የካሊፎርኒያው ፓሲፊክ የህክምና ማዕከል ለሳምንታት የቆየ የምልከታስልጠና ሲያደርግ መቆየቱን ለአራዳ ኤፍ ኤም ገልፀዋል።
በትውልደ አትዮጵያዊቷ አሜሪካዊት የጉበት ንቅለ ተከላ የህክምና ባለሙያ ዶ/ር ቅድስት ኪዳነ ይልማ አመቻችነት የተካሄደው መርሐ ግብር፥ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የጉበት ንቅለ ተከላ አገልግሎት ለማከናወን በምታደርገው ጥረት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው ብለውታል።
የባለሙያዎች ቡድን አባላቱ በርካታ የጉበት ንቅለ ተከላ ሂደቶችን የተመለከቱ ሲሆን፤ ከዋነኛ የንቅለ ተከላ ቀዶ ጥገና ሐኪሞች የተግባር ስልጠና እና የዕለት ተዕለት ምክር ማግኘታቸውንም ነው የተናገሩት።
ቡድኑ በቆይታው ንቅለ ተከላ የሚያስፈልጋቸውን ታካሚዎች የጤና ደረጃ፣ የለጋሾች ልየታና በህክምናው ዙሪያ ያሉትን ስርዓቶች በተመለከተ አስፈላጊ እውቀት ማግኘቱን ጠቁመዋል።
ሆስፒታሉ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በበቂ ዝግጅት ወደ ሥራ ሲገባ፣ ለጉበት ንቅለ ተከላ ህክምና ውጭ ሀገር መሄድን ያስቀራል መባሉን ጣቢያው ዘግቧል፡፡

Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 13 August 2025 17:01
"የአባይ ተፋሰስ ሀገሮች “ታሪካዊ መብቶች” ላይ ከማተኮር
ይልቅ ዓለም አቀፍ ፍላጎትን ማጤን አለብን" -ሙሴቪኒ-
የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ከግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር በካይሮ ተገናኝተው በአባይ ወንዝ ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ በኤክስ ገጻቸው ላይ ከአልሲሲ የተለየ እንደውም ፍጹም ተቃራኒ ሃሳብ አጋርተዋል፡፡
ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች በውይይታቸው ወቅት በአባይ ወንዝ የወደፊት ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ሙሴቪኒ ጠቅሰዋል፡፡
የአባይን ጉዳይ ሰፋ ባለ እይታ መመልከት አለብን ያሉት የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት፤ አንዳንድ ጊዜ ችግሮች የሚያጋጥሙት ለጉዳዩ ባለን አቀራረብ ነው ብለዋል፡፡
የአባይ ተፋሰስ ሀገሮች “ታሪካዊ መብቶች” ላይ ከማተኮር ይልቅ ዓለም አቀፍ ፍላጎትን ማጤን አለብን ሲሉም ጽፈዋል፡፡
"ግባችን ሊሆን የሚገባው ብልፅግና ለሁሉም ፣ የኤሌክትሪክ ሀይል ተደራሽነት ለሁሉም፣ መስኖ መጠቀም ለሁሉም፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ለሁሉም የሚል ነው" ብለዋል፡፡
እነዚህን አላማዎች በማዕቀፍ ውስጥ በማስገባት ሳይንሳዊና ፍትሃዊ ዘዴዎችን ተጠቅመን ተግባራዊ ልናደርገው እንችላለን ሲሉም ሙሴቪኒ አክለዋል፡፡
በተቃራኒው የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ፣ ከሙሴቪኒ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ በአባይ ወንዝ ላይ የሚደረጉ ማናቸውንም የአንድ-ወገን እርምጃዎች ውድቅ በማድረግ፣ ግብፅ የውኃ ሀብት መብቷን ችላ ትላለች ብሎ የሚያምን ማንኛውም ሰው «ተሳስቷል» ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን ዘግበናል፡፡
Published in
ዜና
Tagged under
Tuesday, 12 August 2025 00:00
"ክቡር ልጆች" የሕንጸት ቡክ አዋርድን አሸነፈ
"--አንዲት እናት ልጆቿን ብቻዋን ታሳድጋለች፡፡ የአስተዳደግ ዘይቤዋ ከሌሎች ወላጆች ለየት ይላል፡፡ ልጆቿ ከሰፈር ልጆች ጋር ተቀላቅለው ሲጫወቱ አይቼ አላውቅምና ሁሌም ጥያቄ ይፈጥርብኝ ነበር፡፡ ልጆችሽ ከእድሜ እኩዮቻቸው ጋር ሲጫወቱ አይቼ አላውቅም አልኳት፡፡
“በልጅነቴ ብቸኛ ወንድሜን ያጣኹት ሰፈር ውስጥ በተወረወረ ድንጋይ ነው” ወዲያውም ስቅስቅ ብላ አለቀሰች፡፡
“በጣም አዝናለሁ፤ መጠየቅ አልነበረብኝም” አልኳት
“እነዚህን ብርቅዬ ልጆች እንደ ወንድሜ ማጣት አልፈልግም፡፡ ውጭ እንደ ሌሎች ልጆች ቢጫወቱ ይሞቱብኛል ብዬ እፈራለሁ፡፡” አለችኝ
ህክምና ያላገኘ የልጅነት ጠባሳ ጊዜ ጠብቆ በትዳር ህይወትም ይገለጣል::"
***
ከላይ የተነበበው ጽሁፍ በደራሲ ብርሃኑ በላቸው "ክቡር ልጆች" በሚል ርዕስ ከተጻፈውና የዘንድሮን የ2017 የሕንጸት ቡክ አዋርድ ካሸነፈው መጽሐፍ የተቀነጨበ ነው፡፡
ደራሲ ብርሃኑ በላቸው፤ የበኩር ሥራው እውቅና ማግኘቱን በብዙ ትህትና መቀበሉንና ለቀጣይ ስራው ትልቅ ሃላፊነት መቀበሉን ተናግሯል።
"Hintset Christian Society- ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር"፤ ዘንድሮ መጽሐፍትን አወዳድሮ እውቅና ሲሰጥ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና
Tagged under
Wednesday, 13 August 2025 06:58
እንዳያመልጣችሁ - ከ50ሺ እስከ 300 ሺ ብር ያሸልማል!
ማንበብ ያሸልማል፤እውቀት ያሻግራል!!!
አዲስና ልዩ ዕድል ለአንባቢዎችና ለሥራ ፈጣሪዎች!
በዶክተር ያሬድ ኢሳያስ የተጻፈውን " *ኒዩሮ ሳይንስ ለሥራ ፈጠራ* " እና " *የኒዩሮ አመራር ሳይንስ* " የተሰኙ ሁለት መጻሕፍትን ገዝታችሁ አልያም ተውሳችሁ አንብቡ!
ለሥራ ዕቅድና ፈጠራችሁ
"ኒዩሮ ሳይንስ ለሥራ ፈጠራ" ከተሰኘው መጽሐፍ ያገኛችሁትን ሀሳቦችና ጥቅሞች ከየትኛው የመጽሐፉ አንቀጽና ገጽ እንዳጣቀሳችሁ በመግለጽ ከሁለት ገጽ ባልበለጠ ዘርዝራችሁ አስቀምጡ።
የፈጠራችሁትን የሥራ ዕቅድ እንዴት እንደምትመሩት "የኒዩሮ አመራር ሳይንስ" ከተሰኘው መጽሐፍ ባገኛችሁት ሀሳብና መረጃዎች መሠረት በግማሽ ገጽ አስፍሩ።
በአጠቃላይ የቢዝነስ ዕቅዳችሁንና ከመጽሐፍቶቹ ያገኛችሁትን ተግባራዊ ዕውቀቶች በአምስት ገጽ ጽፋችሁ አዘጋጁ።
በዛጎል የመጻሕፍት ባንክ (ZAGOL BOOK BANK) የቴሌግራም ገፅ አድራሻ @ZAGOLBOOK የሥራ ዕቅዳችሁን
ላኩ!
የላካችሁት ሰነድ መሥፈርቱን የሚያሟላ ከሆነ ትጠራላችሁ፣ በዳኞች ፊት ቀርባችሁ ትወዳደራላችሁ!
ካሸነፋችሁ የገንዘብ ሽልማት ታገኛላችሁ!!!
1ኛ ለወጣ:- 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ብር!
2ኛ ለወጣ:-150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር!
3ኛ ለወጣ:-50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር!
መልካም ዕድል!!!!!
ለበለጠ መረጃ፡+251976066720 ይደውሉ
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና
Tagged under
Wednesday, 13 August 2025 06:38
"ለሀገር የታወጀ አብዮት ነው" የተባለለት አዲስ መፅሐፍ!!
የሕክምና ባለሙያ በሆነዉ ዶ/ ር ደሳለው ካሳሁን የተፃፈዉና በሥነጽሁፍ ምሁራን ብዙ የተባለለት “ፓሌሮዳ “ አዲስ መፅሐፍ በቅርብ ቀን!!
“ፓሌሮዳ “ ሜታፊዚክስን፣ መጽሐፈ ሄኖክን፣ ምናባዊ የህክምና ግኝቶችን፣ እንዲሁም ጂኦፖለቲካንና ፍቅርን አንድ ላይ አሰናስሎ ወደፊት የሚከንፍ፤ በይዘቱ ወይም በሀሳቦቹ በሐገራችን ስነጽሑፍ ያልተለመደ ድርሰት ነው።
(ደራሲ ህይወት ተፈራ)
"ፓሌሮዳ" ለኔ ልቦለድ ብቻ ሳይሆን ንቅናቄ ነው። ለትውልድ የተላለፈ ማንቂያ ደወል ነው። ለሀገር የታወጀ አብዮት ነው።
(ደራሲና ገጣሚ አያልነህ ሙላት)
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና
Tagged under
Wednesday, 13 August 2025 06:36
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ታዋቂ አርማ ዲዛይን ያደረጉት ማናቸው?
"የአዲሱ ሎጎ ትርፍና ኪሣራው በሚገባ ታስቦበታል ወይ?"
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ታዋቂ አርማ ዲዛይን ያደረጉት የቀድሞ የባንኩ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ናሥር ሐሰን ናቸው፡፡
ይህን መረጃ የእርሳቸው ዘመድ ያደረሰኝ ሲሆን፤ እኔም አቶ ናስር ሐሰንን በስልክ አግኝቼ አውርቻቼዋለሁ። በአሁኑ ጊዜ ነዋሪነታቸው በአሜሪካ ነው ። ከሳምንት በኋላም እንደምንገናኝ ተቀጣጥረናል። እስከዛው ድረስ የባንኩ አርማ ሲሰራ የነበረውን ሂደት በተመለከተ ያላቸውን ትዝታ እንዲህ አካፍለውኛል፡፡
**
የቀድሞውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አርማ (ሎጎ) ሙያዬና ሥራዬ ባይሆንም፣ ማንም ሳይጠይቀኝና ሳያዘኝ በራሴ ተነሣሽነት አንዲት ሣንቲም ሳይከፈለኝ ዲዛይን አድርጌና ክሊሼውን እንግሊዝ ሀገር በነፃ አሰርቼ፣ ለወቅቱ የባንኩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ለአቶ አለሙ አበራ አቅርቤ ሥራ ላይ እንዲውል ተደርጎ ላለፋት 50 ዓመታት አገልግሏል።
በመሆኑም አርማው በቼኮች፣ በቁጠባ ሒሣብ ደብተሮችና በባንኩ የፅህፈት መሣሪያዎች ላይ እንዲታተም አስደረግኩ። በወቅቱ የባንኩ የሒሣብና የኢንቬስትሜንት (መዋዕለ ንዋይ) መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ነበርኩ ።
በወቅቱ ለዚህ ሥራዬ የቃል ምስጋና እንኳን አላገኘሁም ነበር። አሁን ያን ወርቃማና ሽክርክር አርማ ለመተካት ግማሽ ቢሊዮን ብር ከማስወጣቱም በላይ በየሕንፃዎቹ ላይ ያሉትን አርማዎች አፍርሶ አዲሱን መተካት፤ ያሉትን የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የቼክና የቁጠባ ደብተሮች ፣ የኮምፒዩተር ሶፍትዌሮችና ወዘተ ለመቀየር የሚወጣው ወጪ የትየሌሌ ነው።
በዚያ ላይ አዲሱን አርማ በመላ ዓለም ላሉ ባንኮች፣ የፋይናንስ ድርጅቶች፣ ለባንኩ ደንበኞች ሀ ብሎ ለማስተዋወቅ ሚሊዮኖች ያስወጣልና ትርፍና ኪሣራው በሚገባ ታስቦበታል ወይ ያሰኛል ?" በማለት ይገልጻሉ፤ አቶ ናሥር ሐሰን ፤የቀድሞው የባንኩ ም/ፕሬዚዳንት፡፡
***
አቶ ናሥር ሐሰን በትጋት በታማኝነት፣በቅንነት ከነበረባቸው ሃላፊነት በተጨማሪ ያሳዩት ትጋት የሚያስደንቅና የሚያስተምር ነው።
(አብዱረሂም አህመድ )
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

Published in
ዜና
Tagged under
Wednesday, 13 August 2025 06:34
"የትግራይ ሕዝብ ያለበት ሁኔታ በምክክር ሂደቱ አይፈታም"
የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ሳልሳዊ ወያነ ትግራይና የውድብ ናጽነት ትግራይ፣ በአገራዊ ምክክር ኮሚሽን የምክክር ሂደት መሳተፍ እንደማይፈልጉ መግለጻቸውን ሪፖርተር አስነብቧል።
ፓርቲዎቹ ለዚህ በምክንያትነት የጠቀሱት፣ ከምክክሩ በፊት የግጭት ማቆም ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ መተግበር አለበት በማለት እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል።
ፓርቲዎቹ፣ የትግራይ ሕዝብ አሁን ያለበት ሁኔታ በምክክር ሂደቱ እንደማይፈታ ተናግረዋል ተብሏል።
ስምረት ፓርቲ በበኩሉ፤ የክልሉን ጥቅም ባስጠበቀ መንገድ በሂደቱ መሳተፍ እንደሚቀጥል መግለጡን ዘገባው አመልክቷል።
-ዋዜማ-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…


Published in
ዜና
Tagged under
Tuesday, 12 August 2025 00:00
ወጣቱ ባለጸጋ ለባቡልኸይር በጎ አድራጎት 1 ሚሊየን ብር ለገሰ
«በረከትን ያገኘሁት በድሆች ፀሎት ነው» የሚለው ወጣቱ ባለፀጋ ምረትአብ፤ በተደጋጋሚ ለባቡልኸይር በጎ አድራጎት ድርጅት ድጋፍ በማድረግ ይታወቃል።
ራሱንና ጓደኞቹን በማስተባበር ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ፤ በፆምም ሆነ በበዓል ወቅት አቅመ-ደካሞችን በመንከባከብና በአውዳመት ተደስተው እንዲውሉ ማድረግ የነፍስ እርካታ እንደሚሰጠው ይናገራል፡፡
በዛሬው ዕለትም አዲስ የገዛውን ማርቼዲስ ቤንዝ መኪና በአረጋውያን ለማስመረቅ በባቡልኸይር የተገኘው ወጣቱ ባለፀጋ፣ ድንገተኛ የአንድ ሚሊዮን ብር ስጦታ ለበጎ አድራጎት ድርጅቱ ለግሷል፡፡
ልገሳውን ወዲያውኑ በማስገባት ቃሉን የሞላው ምረትአብ፤ ለምስኪኖችና ረዳት ለሌላቸው ማድረግ ለራስ እንደማድረግ ነው ሲል ተናግሯል።
ክስተቱ በተለይም የባቡልኸይር ተጠቃሚዎችን በደስታ እንባ ያራጨና እጅግ ልብ የሚነካ ነበር።
የድርጅቱ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሀናን ሙሀሙድንም፣ የወጣቱ ባለፀጋ ድንገተኛ ልግስና በደስታ አስለቅሷቸዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…





Published in
ዜና
Tagged under

