Administrator
የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
(ከእስራኤል ምክትል አምባሳደር ጋር የተደረገ ልዩ ቃለ መጠይቅ)
ኢራን ባለፈው ቅዳሜ ሚያዝያ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት ከ300 በላይ የድሮኖችና የሚሳኤሎች ጥቃት በእስራኤል ላይ ያደረሰች ሲሆን፤ እስራኤል አሜሪካና እንግሊዝን ጨምሮ ከአጋሮቿ ጋር በመተባበር ከተወነጨፉት ድሮኖችና ሚሳኤሎች ውስጥ 99 በመቶውን ከአየር ክልሏ ውጭ ማምከን መቻሏን አስታውቃለች፡፡ ኢራን የፈጸመችው ጥቃት የዛሬ 20 ቀን ገደማ በሶሪያ በሚገኝ ቆንስላዋ ውስጥ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት ለገደለቻቸው ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦቿ አጸፋዊ ምላሽ መሆኑን ገልጻለች፡፡ የእስራኤል ጦር አዛዥ ጥቃቱን ተከትሎ ከሰሞኑ በሰጡት መግለጫ፤ በእስራኤል ግዛት ለተወነጨፉ ድሮኖችና ሚሳኤሎች ምላሽ መስጠታችን አይቀርም ብለዋል፡፡
የጆ ባይደን አስተዳደር፤ በኢራን ላይ በሚወሰድ የአጸፋ እርምጃ አሜሪካ ተሳታፊ እንደማትሆን ግልጽ አድርጓል፡፡ ኢራን በበኩሏ፤ እስራኤል የአጸፋ እርምጃ ከወሰደች ፈጣንና ከአሁኑ የከፋ ምላሽ እንደምትሰጥ ዝታለች፡፡ አሜሪካ የእስራኤልን የአጸፋ እርምጃ የምትደግፍ ከሆነም፣ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት እንደምትሰነዝር ኢራን አስጠንቅቃለች፡፡ የእስራኤል አጋሮች የኢራንን ጥቃት አጥብቀው ቢያወግዙም፣ የጠ/ሚኒስትር ኔታንያሁ አስተዳደር አጸፋዊ ምላሽ ላይ እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል፡፡
በሌላ በኩል፤ እዚህ አዲስ አበባ የሚገኘው በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ በጥቃቱ ማግስት እሁድ ሚያዝያ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ኢራን ለመጀመሪያ ጊዜ በእስራኤል ላይ ያስወነጨፈቻቸውን ድሮኖችና ሚሳይሎች አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ያወጣ ሲሆን፤የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ፣ ከእስራኤል ምክትል አምባሳደር ሚስተር ቶመር ባር-ላቪ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተከታዩን ቃለ መጠይቅ አድርጓል፡፡
***
እስቲ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ ኢራን በእስራኤል ላይ ስለፈጸመችው የድሮንና የሚሳኤል ጥቃት ይንገሩን ?
ቅዳሜ ሌሊት፣ ኤፕሪል 13፣ የኢራን አገዛዝ፣ በእስራኤል ላይ ታይቶ የማይታወቅና ግዙፍ ጥቃት አድርሷል፤ከ300 በላይ የባላስቲክ ሚሳኤሎች፣ ክሩዝ ሚሳኤሎችና ድሮኖዎችን በእስራኤል ኢላማዎች ላይ በማስወንጨፍ፣ ከፍተኛ እልቂትና ውድመት ለማድረስ ሞክሯል። ደግነቱ፣ በእስራኤል የላቀ ወታደራዊ አቅምና በአጋሮቻችን ትብብርና ድጋፍ ከተወነጨፉት ውስጥ 99 በመቶ የሚሆኑት ወደ እስራኤል የአየር ክልል ከመግባታቸው በፊት መትተን መጣል ችለናል።
በኢራን አብዮታዊ ጋርድ (IRGC) የተፈፀመው ይህ ጥቃት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተርን የሚጥስ ሲሆን፤ሌላ ቀይ መስመር ያለፈና እስራኤል ለዓመታት ስትናገረው የኖረችውን የሚያረጋግጥ ነው፤ የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ በመካከለኛው ምስራቅ ለሚታየው አለመረጋጋትና ሽብርተኝነት ዋነኛ ምንጭ መሆኑን፣ እንዲሁም ለአካባቢያዊና ለዓለም ሰላም ስጋት መደቀኑን፡፡ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ባለቤት እንድትሆን ፈጽሞ ሊፈቀድላት የማይገባው ለምን እንደሆነም የሚያጎላ ድርጊት ነው፤ ጥቃቱ፡፡
የእስራኤል የጦር አዛዥ፣ ለዚህ ጥቃት የአጸፋ ምላሽ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡ እስራኤል እንዴት ነው ምላሽ ልትሰጥ ያቀደችው?
ለዚህ ግዙፍ ጥቃት የሚሰጠው ምላሽ መከናወን ያለበት በብዙ ግንባሮች ነው፡- በመጀመሪያ ደረጃ ይህን ጥቃት ያደረሰው የኢራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC) በአስቸኳይ በመንግስታትና በአለም አቀፍ አካላት በአሸባሪነት መፈረጅ አለበት። የኢራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC)፤ በጋዛ ሃማስና ኢስላሚክ ጂሃድን፣ በሊባኖስ ሂዝቦላን፣ በየመን ሁቲዎችንና በኢራቅ የሺአ ሚሊሻዎችን ጨምሮ፣ በአካባቢው የኢራን አገዛዝ ተጨማሪ የሽብር ተላላኪዎችን በገንዘብ፣ በማሰልጠንና በማስታጠቅ ይደግፋል፡፡ የኢራንን እኩይ ተጽእኖ ለማስፋፋትና የመካከለኛው ምስራቅን ለዘብተኛ ኃይሎች ለማተራመስ በአካባቢው ምስቅልቅል ይፈጥራል፡፡
በሁለተኛ ደረጃ ይህ ጥቃት፣ የኢራን የተራቀቁ ሚሳኤሎችንና ተዛማጅ ቴክኖሎጂዎችን ጨምሮ ስልታዊ አቅሞችን ማሳደድ፣ የአገዛዙን ወረራ ለማራመድና እስራኤልንና የአለምን ስርዓት ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑን አሳይቷል፡፡ የኢራን አገዛዝ ላይ በሚሳኤል መስክ ብቻ ሳይወሰኑ እንደዚህ አይነት ስትራቴጂካዊ አቅሞችን የማሳደድ እንቅስቃሴው ላይ ጥብቅና አስጨናቂ ማዕቀብ ሊጣልበት ይገባል።
በመጨረሻም፣ እንደማንኛውም እንዲህ አይነት መጠነ ሰፊ ጥቃት የተፈፀመባት ሀገርና የእስላማዊ ሪፐብሊክ ባለስልጣናት ሀገራችንን ለማጥፋት በየእለቱ የሚሰነዝሩትን የዘር ማጥፋት ዛቻ ተከትሎ፣ እስራኤል ከዚህ ጥቃት ራሷን የመከላከል መብቷ የተጠበቀ ነው። ከዚህ ቀደም እንዳደረግነው ወደፊትም ራሳችንን ከኢራን ጥቃቶች መከላከል እንቀጥላለን።
ኢራን ላይ የአጸፋ እርምጃ መውሰድን በተመለከተ የእስራኤል ጦር ካቢኔ ለሁለት መከፈሉ ተነግሯል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ሊሰጡን ይችላሉ ?
ቀደም ሲል እንደገለጽኩት፣ እስራኤል ከዚህ የኢራን መንግስት ህገወጥ ጥቃት ራሷን የመከላከል መብቷ የተጠበቀ ሲሆን፤ እኛም ከዚህ ቀደም እንዳደረግነው እናደርጋለን።
አሜሪካ፤ እስራኤል በኢራን ላይ በምትወስደው የአጸፋ እርምጃ፣ እጄን አላስገባም ማለቷን በተመለከተ እርስዎ ምን ይላሉ?
አሜሪካና ሌሎች አጋሮች ከእኛ ጋር መቆማቸውን እስራኤል ታደንቃለች፤ ይህ ደግሞ የቅዳሜውን ጥቃት ለመከላከል በተደረገው ትብብር በግልፅ ታይቷል። በአሜሪካ የሚመራው ድጋፍና ትብብር በዋጋ የማይተመንና ወደር የለሽ ነው።
የትኛውም ሀገር በህልውናዋ ላይ የመጣ አደጋን ሊቀበል አይችልም ፤ እስራኤልም ከዚህ የተለየች አይደለችም። እስራኤል ከኢራን የሚደቀንባትን ስጋት አትታገስም፤ ጉዳት ለማድረስ ለሚደረገው ማንኛውም ሙከራ ሁሉ ጠንከር ያለ ምላሽ ትሰጣለች። እስራኤል፤ ኢራንም ሆነች ተላላኪ ድርጅቶቿ በዜጎቿ ላይ ስጋት አለመፍጠራቸውን ታረጋግጣለች።
የኢራን የድሮንና የሚሳኤል ጥቃት፣ በተለይም፣ ከቀጠናዊው ውጥረት አንጻር ያለውን አሁናዊና የረዥም ጊዜ የደህንነት አንደምታ እስራኤል እንዴት ትገመግመዋለች?
ኢራን ሽብርተኝነትንና አለመረጋጋትን በማስፋፋት፣ ቀጣናዊ ወኪሎቿን በገንዘብ በመደገፍና በማስታጠቅ ለዓመታት ዘልቃለች፡፡ ሃማስ በገንዘብ የሚደገፈው፣ የሚሰለጥነውና የሚታጠቀው በአብዛኛው በኢራን አገዛዝ ሲሆን፤ ለዚህ የዘር ማጥፋት አሸባሪ ቡድን የኢራን ድጋፍ ባይኖር ኖሮ፣ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 7 ቀን 2023 በእስራኤል ላይ የተፈፀመው ጥቃት አይከሰትም ነበር፡፡ ላለፉት ስድስት ወራት ኢራን በተላላኪዎቿ - ሃማስና ኢስላሚክ ጂሃድ በጋዛ፣ ሂዝቦላ በሊባኖስ፣ ሁቲዎች በየመንና የሺዓ ሚሊሻዎች በኢራቅ፣ አማካኝነት በእስራኤል ላይ ጦርነት ስትከፍት ቆይታለች። በእስራኤል ሰሜናዊ ድንበር የሚሰነዘረው የሂዝቦላ ጥቃት ቀስ በቀስ እያደገና ሙሉ ለሙሉ የባለብዙ ግንባር ጦርነት ስጋት እየሆነ መምጣቱን እንዲሁም በቀይ ባህር ላይ በአለም አቀፍ መርከቦች ላይ በሁቲዎች የሚፈጸመው ጥቃት ዓለማቀፍ ንግድን እየጎዳውና የመላው ዓለም ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖ ማድረሱን እናያለን።
የሰሞኑ ጥቃት የእስላማዊ ሪፐብሊክ፣ እስራኤልን ከኢራን ግዛት በቀጥታ ሲያጠቃ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመሆኑ አንጻር፣ ግጭትን የማባባስ ተግባር ተደርጎ የሚታይ ነው፡፡ ይህ መባባስ ክልሉን ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ወደ አለመረጋጋት እንዲመጣ በማድረግ፣ የከፋ ግጭት እንዳይፈጠር ያሰጋል። ክልላዊና ዓለም አቀፋዊ ትብብር በእንደዚህ ዓይነት ምክንያታዊ ያልሆኑ ተዋናዮች ላይ ያለውንም ጠቀሜታ ያሳያል።
ከዚህ ጥቃት አንጻር፣ እስራኤል፣ የኢራን ወታደራዊ አቅም የጋረጠውን መጠነ ሰፊ ስጋት እንዴት ትመለከተዋለች?
እስራኤል ይህ ጥቃት እስላማዊ ሪፐብሊክ በኢራን አብዮታዊ ዘብ በኩል፣ አካባቢውን ለማተራመስና ሽብርተኝነትን ለማስፋፋት እንዲሁም ተጽእኖውን ለማስፋትና በመካከለኛው ምስራቅ ላይ ትርምስ ለመፍጠር የሚያደርገውን ጥረት በተመለከተ ለብዙ አመታት ያስጠነቅቅነውን እንደ ማረጋገጫ አድርጋ ነው የምትመለከተው፡፡ በክልሉ ውስጥ ያሉ ብዙ ለዘብተኛና ኃላፊነት የሚሰማቸው ተዋናዮች፣ ይህን እውነታ ከረጅም ጊዜ በፊት ተገንዝበዋል።
የኢራን ተጽዕኖ ፈላጊነት ከመካከለኛው ምስራቅ ባሻገር የተስፋፋ ሲሆን፣ በዓለም ላይ ያሉ ኃላፊነት የሚሰማቸው ተዋናዮች፣ የኢራን መንግስት ተፅእኖ ለመፍጠርና የአለምን ስርዓት ለማተራመስ የሚያደርገውን ጥረት ትኩረት ሰጥተው መቃወም አለባቸው። በቅርቡ የተፈፀመው ጥቃት፣ የኢራን አገዛዝ ስለ እስራኤል መጥፋትና ስለ ሽብርተኝነትን ማስፋፋት ጥሪ ሲያደርግ፣ ከምሩ ለመሆኑ ለሚጠራጠሩ ሁሉ እንደ ማንቂያ ደወል ማገልገል አለበት። የዚህ አገዛዝ ድርጊት እጅግ ጽንፈኛ የሆኑ መሪዎቹን ቃል የሚያረጋግጥ ነው፡፡
እስራኤል የኢራንን ጥቃት ለመግታት ምን ዓይነት ዲፕሎማሲያዊ መንገዶችን ትከተላለች?
የቅዳሜ ሌሊቱን ጥቃትን ተከትሎ፣ በተባበሩት መንግሥታት የእስራኤል አምባሳደር፣ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲያደርግና በጉዳዩ ላይ እንዲወያይ ጠይቀዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ተጨማሪ አካላት እንዲሁም ሀገራት የኢራንን ጥቃት በማያሻማ መልኩ እንዲያወግዙና እስላማዊ ሪፐብሊክና ደጋፊዎቿ ጥቃታቸውን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ጥሪያችንን ማቀረባችንን እንቀጥላለን፡፡
እስራኤል፣ በዓለም ዙሪያ በርካታ ሀገራት፣ ኢራን በፈጸመችው ጥቃት ላይ ጠንከር ያለ ውግዘት ማሰማታቸውን በበጎነቱ ተቀብላለች፣ ሌሎች ሀገራትም ይህን አስከፊ የአለም አቀፍ ህግ ጥሰት የሚያወግዙትን እንዲቀላቀሉ እናበረታታለን።
እደግመዋለሁ፣ በዲፕሎማሲው መስክ፣ ሁለት ፈጣን ተግባራዊ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው፣ እነዚህም፡-
1- የኢራን አብዮታዊ ዘብን (IRGC) በአሸባሪነት መፈረጅ።
2- ኢራን ለማሳካት እየሰራች ያለችውን ባላስቲክ ሚሳኤሎች፣ ድሮኖች፣ በመካሄድ ላይ ያለውን የኒውክሌር መርሃ ግብርና የህዋ አቅሞችን ጨምሮ የኢራን ስትራቴጂካዊ አቅሞች ላይ ያነጣጠረ ጉዳት የሚያስከትል ማዕቀብ መጣል። አለም ኢራንን እንደዚህ አይነት ስትራቴጂካዊ አቅሞች እንዳታገኝና እንዳታዳብር ማገድና መከልከል አለበት፡፡
ጥቃቱ፤ እ.ኤ.አ. በጥቅምት 2023 በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ 2231 ጊዜው ያለፈበትን የማዕቀብ ስርዓት፣ በአማራጭና ሁሉን አቀፍ በሆነ የማዕቀብ ሥርዓቶች በመተካት ማዕቀቡን የማስፋፋትና የመጣል አስፈላጊነትን አጽንኦት ሰጥቶታል፡፡ ጥቃቱ በተጨማሪም የኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር፣ ከመርፈዱ በፊት በአስቸኳይ የማቆምና የመቀልበስ አስፈላጊነቱን አጉልቶታል፡፡
እስራኤል ተጨማሪ የግጭት መባባስን ለማስቀረትና በቀጣናው መረጋጋትን ለማስፈን ምን እርምጃዎችን ልትወስድ አስባለች?
እስከ ኦክቶበር 7, 2023 ድረስ መካከለኛው ምስራቅ ወደ ሁለንተናዊ ለውጥ እየገሰገሰ ነበር። ከ2020 ጀምሮ በአብርሃም ስምምነት፣ እስራኤል ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ባህሬንና ሞሮኮ ጋር የመደበኛ ግንኙነትና የሰላም ስምምነቶችን ተፈራርመናል፣ከሱዳን ጋር ያለውን ግንኙነት መደበኛ ለማድረግ እየሰራንም ነበር። ሂደቱ ቀጠለና፣ ይህ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ባሉት ወራት ውስጥ ከሳውዲ አረቢያ ጋርም እንኳን ወደ መደበኛ ግንኙነት ለመግባት እየተጓዝን ነበር። ይህ የመካከለኛው ምስራቅ የበለጠ ትስስርና ትብብር ያለው ራዕይ፣ቀጣዩ መንገድ ነበር፡፡
እንደ አለመታደል ሆኖ፣ የኢራን አገዛዝና በአካባቢው ያሉ ፅንፈኛ ተላላኪዎቹ፣ እንደዚህ አይነት አዎንታዊ ዲፕሎማሲያዊ እድገቶች ስጋት ውስጥ ጣላቸው፡፡ ይህ ለቀጣናው ህዝብ የተሻለ የወደፊት ተስፋ ቢፈነጥቅም፣ በመካከለኛው ምስራቅ የኢራን ቀጣይ ተጽእኖና ሽብርተኝነት መስፋፋት ላይ እንቅፋት ፈጥሯል። በትንሹም ቢሆን፣ በጥቅምት 7 የተፈጸመው አሰቃቂ የሃማስ የሽብር ጥቃት ጽንፈኞች - በኢራን የሚመራው የኔትዎርክ አካል -- ባለፉት ጥቂት ዓመታት በእስራኤልና በአረቡ ዓለም መካከል የተደረጉትን አዎንታዊ ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ስኬቶች ለማስቆምና ወደ ኋላ ለመመለስ ያደረጉትን ሙከራ ይወክላል።
በዚህ የለዘብተኞች እና ጽንፈኞች ጦርነት፣ የቀጣናው ለዘብተኞች ያሸንፋሉ ብለን እናምናለን፤ እናም የእኛ ይበልጥ የተሳሰረና የተባበረ የመካከለኛው ምስራቅ የመፍጠር የጋራ ራዕያችን፣ ይህ ጦርነት አብቅቶ፣ እስራኤል የድንበሯና ዜጎቿ ደህንነት ጉዳይ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ከተመለሰ በኋላ ዳግም መስመር ይይዛል፡፡
እስራኤል የዓለማቀፍ አጋሮች፣ በተለይም የቀጣናው አጋሮች፣ የኢራንን የጥቃት እርምጃ በማውገዝና በመቃወም የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ እንዴት ታየዋለች?
አሁንም ይህ የለዘብተኞችና የአክራሪዎች ጦርነት ነው -- ወደፊት የተሻለና ሰላማዊ ይሆናል ብለው በሚያምኑ እና ግጭት፣ ሽብርተኝነትና ትርምስ ቀለባቸው በሆኑት መካከል የሚደረግ ጦርነት ማለት ነው፡፡ በዚህ ጦርነት ደግሞ በአለም አቀፍም ሆነ በክልል ደረጃ አጋሮች አሉን፤ ባለፈው ቅዳሜ ለደረሰው ጥቃት ምላሽ በሰጡበት ወቅት ይህንን ለማየት የቻልን ይመስለኛል። እነዚህ አጋርነቶችና ትብብሮች ጠቃሚ ናቸው፡፡ በአሜሪካ የሚመራው የእስራኤል አጋሮችና ተባባሪዎች እኩይ ባላጋራ ሲገጥማቸው በጋራ መስራት ይችላሉ።
ከዚህ ክስተት ጋር በተገናኘ ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ ምን መልዕክት ማስተላለፍ ይፈልጋሉ?
እስራኤል፤ አሜሪካና ሁሉም አጋሮቿ ከጎኗ መቆማቸውን ታደንቃለች፤ የኢራንን ጥቃት ለመከላከል ያደረጉትን እገዛም እናደንቃለን። የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በዚህ ጥቃት ላይ የሚያደርሰውን ውግዘት በበጎነቱ ስንቀበል፣ ሌሎችም ኃላፊነት የሚሰማቸው ተዋናዮች፣ የኢራንን ጥቃት በማውገዝ ከእስራኤል ጎን እንዲቆሙና የእስራኤልን እራሷን የመከላከል መብት እንዲደግፉ እናበረታታለን።
በተጨማሪም እስራኤል፣ የኢራንን ህዝብ እንደ ጠላት እንደማታየው ማጤን አስፈላጊ ነው፤ ይልቁንም ትኩረቷ የገዛ ህዝቡን በሚጨቁነውና ግቡ እስራኤልን ማጥፋት በሆነው አክራሪ የኢራን አገዛዝ ላይ ነው፡፡ በእርግጥ ከቅዳሜው ጥቃት ወዲህ ባሉት ቀናት #IraniansStandWithIsrael የሚለው ሃሽታግ በማህበራዊ ትስስር X (የቀድሞው ትዊተር) ላይ እየታየ ነበር። የኢራን ህዝብ በዚህ አገዛዝ እየተሰቃየ መሆኑን እንረዳለን፤ እናም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ላሉቱ ድጋፋችንን እንገልፃለን።
Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
In the wake of the recent Iran attack on Israel, Addis Admass had the opportunity to sit down with Mr. Tomer Bar-Lavi, the Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia, to gain valuable insights into Israel's response to this significant event. Join us as we delve into the implications, strategies, and diplomatic considerations in the aftermath of this attack.
***
Can you provide us with an overview of the recent drone and missile attack by Iran on Israel?
On Saturday night, April 13, the Iranian regime carried out an unprecedented and massive attack against Israel, firing over 300 ballistic missiles, cruise missiles and attack UAVs from its territory at Israeli targets, trying to cause significant death and destruction. Thankfully, due to Israel's advanced military capabilities and in cooperation with our allies and partners, we were able to shoot down 99% of the projectiles before they landed in Israeli territory.
This attack, carried out by the Iranian Revolutionary Guard Corps (IRGC), violates the UN Charter and crosses another red line and proves what Israel has been saying for years: that the Islamic Republic of Iran is the primary source of instability and terrorism across the Middle East, and poses a threat to regional and world peace. It also underscores why Iran must never be allowed to acquire nuclear weapons.
How does Israel plan to respond to this aggression?
The response to this massive aggression should be carried out on multiple fronts:
First of all, the IRGC, the body that carried out this attack, should be immediately designated as a terrorist organization by governments and international bodies around the world. The IRGC funds, trains and arms additional terror proxies of the Iranian regime in the region, including Hamas and Islamic Jihad in Gaza, Hezbollah in Lebanon, the Houthis in Yemen, and Shia militias in Iraq. It sows chaos in the region in an effort to spread Iran's nefarious influence and destabilize the moderate forces of the Middle East.
Secondly, this attack showed that Iran's pursuit of strategic capabilities, including advanced missiles and related technologies, is meant to advance the regime's aggression and threaten Israel and the world order. Strict and painful sanctions must be imposed on the Iranian regime's pursuit of such strategic capabilities including but not limited to the field of missiles.
Finally, as any country that has been attacked on such a massive scale, and following the daily genocidal threats of Islamic Republic officials to destroy our country, Israel reserves the right to defend itself from such aggression. As we have done in the past, we will continue to defend ourselves against Iranian attacks in the future.
How does Israel assess the immediate and long-term security implications of Iran's recent drone and missile attack, particularly in the context of ongoing regional tensions?
Iran has been funding and arming regional proxies for years, spreading terrorism and instability. Hamas was funded, trained and armed in large part by the Iranian regime, and the attacks of October 7 2023 would not have happened without Iranian support for this genocidal terrorist organization. For the last six months, Iran has been waging a war against Israel through its proxies - Hamas and Islamic Jihad in Gaza, Hezbollah in Lebanon, the Houthis in Yemen, and Shia militias in Iraq. We see that the Hezbollah attacks from Israel's northern border have been gradually increasing and threatening a full-out multi-front war, and the Houthi attacks on international shipping in the Red Sea have damaged global trade and affected economies around the world.
The most recent attack is an escalation in that it represents the first time that the Islamic Republic has directly targeted Israel from Iranian territory. This escalation destabilizes the region in an unprecedented way, threatening a larger conflict. It also signals the importance of regional and international alliances against such irrational actors.
In light of this attack, how does Israel perceive the broader threat posed by Iran's military capabilities and regional ambitions?
Israel sees this attack as confirming what we have warned about for many years regarding the Islamic Republic's efforts, through its Iranian Revolutionary Guard Corps, to destabilize the region and spread terrorism in an attempt to expand its influence and sow chaos across the Middle East. Many moderate and responsible actors in the region have long ago realized this fact.
Iran's ambitions spread further than just the Middle East, and responsible actors around the world need to pay attention and oppose the Iranian regime's attempts to gain influence and destabilize the world order. The recent attack needs to serve as a wake-up call to all those who questioned the Iranian regime's seriousness when calling for the destruction of Israel and the spread of terrorism. This regime's actions confirm the words of its most extreme leaders.
. What diplomatic channels is Israel pursuing to address Iran's aggression?
Immediately following Saturday night's attack, Israel's Ambassador the UN requested an urgent UN Security Council meeting to discuss the issue. We continue to call on the UN and additional bodies and countries to unequivocally condemn Iran's aggressive actions and call on the Islamic Republic and its proxies to immediately cease their attacks.
Israel welcomes the strong condemnations of Iran's attack made by many countries around the world, and we encourage additional countries to join those condemning this egregious violation of international law.
I will repeat, in the diplomatic sphere, there are two immediate practical steps that must be taken, and those are:
1- The designation of the IRGC as a terrorist organization.
2- The imposition of painful sanctions targeting Iran's strategic capabilities including ballistic missiles, attack UAVs, the ongoing nuclear program, and space capabilities that Iran is working to attain. The world must learn to block Iran and deny it from obtaining and continuing to develop such strategic capabilities, which will end up in the hands of Iran's emissaries in the region and around the world.
The attack has accentuated the necessity of imposing and expanding alternative and comprehensive sanctions regimes as a replacement for the sanctions regime that expired in October 2023 under UN Security Council Resolution 2231, as well as the urgent need to stop and reverse Iran's nuclear program while it is still possible.
What message would you like to convey to the international community regarding this incident?
Israel appreciates that the United States and all its allies stand with Israel, and we appreciate their assistance in containing the recent Iranian attack. This stance clearly demonstrates that we are in a struggle between the free world and an axis of evil whose roots are based in Tehran's regime.
As we welcome the international community's condemnations of this attack, we encourage additional responsible actors to join in the condemnation of Iranian aggression and to stand alongside Israel by supporting Israel's right to defend itself.
It's also important to note that Israel does not see the people of Iran as its enemies, but rather the radical regime of Iran, which oppresses its population and whose stated goal is Israel's eradication. In fact, in the days following Saturday's attack, the hashtag #IraniansStandWithIsrael was trending on the social network X (formerly Twitter). We understand that the Iranian people are suffering under this regime, and we express our support for them in their difficult situation.
. Looking ahead, what steps does Israel intend to take to prevent further escalation and promote stability in the region?
Until October 7 2023, the Middle East was moving towards a complete transformation. Starting in 2020 with the Abraham Accords, Israel signed normalization and peace agreements with the United Arab Emirates, Bahrain, and Morocco, and we were working on normalizing relations with Sudan. The process continued, and in the months before this war began, we were even moving towards normalization with Saudi Arabia. This vision of a more interconnected and cooperative Middle East was, and remains, the way forward.
Unfortunately, the Iranian regime and its extremist proxies throughout the region felt threatened by such positive diplomatic developments, which gave hope for a better future for the people of the region but created obstacles for the continued spread of Iranian influence and terrorism across the Middle East. In no small part, the horrific Hamas terrorist attack of October 7 represented an attempt by the extremists -- part of the network directed by Iran -- to stop and roll back the positive diplomatic, economic and social achievements that had been made between Israel and the Arab World over the last few years.
We hope and believe that in this battle of moderates vs. extremists, the moderates of the region will prevail, and that our shared vision of a more interconnected and cooperative Middle East will get back on track once this war comes to an end and Israel restores security to its borders and its citizens.
How does Israel view the role of international partners, particularly allies in the region, in countering Iran's destabilizing actions?
Again, this is a battle of moderates versus extremists -- those who believe in a better and more peaceful future, versus those who feed off of conflict, terrorism and chaos. In this battle, we have partners both globally and regionally, and I think we were able to witness this during the response to last Saturday's attack. These partnerships are important, and come from shared core interests which overshadow any kind of political rhetoric in one direction or another.
Led by the United States, Israel's allies and partners are able to work together when facing a common, vicious adversary.
Is there anything you can explain to us about the information that the Israeli military cabinet is divided into two regarding taking retaliatory measures against Iran?
As I mentioned earlier, Israel reserves the right to defend itself against this illegal aggression by the Iranian regime, and we will do so, as we have done in the past.
What do you say about America saying that it will not participate in Israel's retaliatory measures against Iran?
Israel appreciates that the US and additional allies stand with us, and this was most clearly seen in the cooperation in containing Saturday's attack. The support and cooperation led by the US are invaluable and unparalleled.
No country could accept threats to its very existence, and Israel is no different. Israel will not tolerate the threats Iran poses to it and will respond strongly to any attempt to cause it harm. Israel will ensure that neither Iran nor its proxy organizations will pose a threat to its citizens.
Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
Iran’s president has warned that the “tiniest invasion” by Israel would bring a “massive and harsh” response, as the region braces for potential Israeli retaliation after Iran’s attack over the weekend.
President Ebrahim Raisi spoke Wednesday at an annual army parade that was moved to a barracks north of the capital, Tehran, from its usual venue on a highway in the city’s southern outskirts. Iranian authorities gave no explanation for its relocation, and state television didn’t broadcast it live, as it has in previous years.
Iran launched hundreds of missiles and drones at Israel over the weekend in response to an apparent Israeli strike on Iran’s embassy compound in Syria on April 1 that killed 12 people, including two Iranian generals.
Israel, with help from the United States, the United Kingdom, neighboring Jordan and other nations, successfully intercepted nearly all the missiles and drones.
(By THE ASSOCIATED PRESS)
Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
By Amy B Wang
National politics reporter
Former attorney general William P. Barr effectively endorsed former president Donald Trump on Wednesday, despite having previously criticized Trump’s conduct while in office and once comparing him to a “defiant, 9-year-old kid.”
Asked Wednesday whether he would vote for Trump, the presumptive GOP presidential nominee, in November, Barr told Fox News that he would vote for the Republican ticket.
“I’ve said all along, given two bad choices, I think it’s my duty to pick the person I think would do the least harm to the country, and in my mind, that’s — I will vote the Republican ticket,” said Barr, who remains a Republican. “I’ll support the Republican ticket.”
Barr served as U.S. attorney general under Trump from 2019 to 2020, resigning from Trump’s Cabinet on Dec. 14, 2020, after publicly disputing the former president’s claims that there was widespread fraud in the 2020 election. Trump would later claim he had demanded Barr’s resignation.
Barr also later cooperated with the House select committee investigating the Jan. 6, 2021, insurrection, and defended special counsel Jack Smith’s prosecution of Trump as a “legitimate case.”
In his 2022 memoir, “One Damn Thing After Another: Memoirs of an Attorney General,” Barr wrote about how his relationship with Trump had soured, citing how Trump and his legal team — including Barr’s nemesis, Trump lawyer and former New York mayor Rudy Giuliani — pushed absurd claims of mass voter fraud.
“His legal team had a difficult case to make, and they made it as badly and unprofessionally as I could have imagined,” Barr wrote. “It was all a grotesque embarrassment.”
Trump in turn has castigated Barr, calling his former attorney general a “coward” and vowing that, if reelected, he would not make Barr attorney general again.
"አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል
ዛሬ ሰኞ ሚያዝያ 7 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ በዓለም ሲኒማ ጥሪ የተደረገላቸው የጥበብ ቤተሰቦች እና እንግዶች በተገኙበት በቀይ ምንጣፍ ሥነ-ሥርዓት ይመረቃል::
ፊልሙ በደራሲና ዳይሬክተር ፍፁም ክብረት ተዘጋጅቶ በሪች ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበ ሲሆን አርቲስት ሰለሞን ሙሄ ፣አርቲስት ማራማዊት አባተ አርቲስት ሙሉአለም ጌታቸው፣ አርቲስት እየሩሳሌም ገበየሁ ፣ አርቲስት ሔቨን ሀብቱ፣ አርቲስት ያሬድ ኤጎ እና ሌሎችም በተዋናይነት የተሳተፉበት ፊልም ነው።
"አቦ ሰም" ተውኔት በነፃ ለታደሚያን ይቀርባል!
መግቢያው በነፃ!
"አቦ ሰም" ተውኔት በነፃ ለታደሚያን ይቀርባል!
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአምስተኛ ዓመት የቴአትር ጥበባት ተማሪዎች "አቦ ሰም" በሚል ርዕስ ተውኔት አዘጋጅተዋል። የተውኔቱ ደራሲና አዘጋጅ መቅደላዊት አሰፋ ስትሆን ይህም ተውኔት ሰኞ ሚያዚያ 7 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:30 ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ይቀርባል።
በጭለማ እየሄዱ ጅብ ነገረኛ ነው ይላሉ
ከዕለታት አንድ ቀን ድመት አንድ ጫካ ውስጥ ቀበሮ ታያለች፡፡ ከዚያም ለራሷ እንዲህ ትላለች፡-
“ቀበሮ በጣም ቀልጣፋ ነው፡፡ ብዙ ልምድ ያለው ነው፡፡ በሰፊውም የተከበረ ነው፡፡ ስለዚህ መልካም ሰላምታ ላቀርብለትና ልቀርበው ይገባል”፡፡ ቀጥላም፤ “እንደምን አደርክ አያ ቀበሮ! እንዴትስ ከርመሀል? ለመሆኑ ሁሉ ነገር በጣም በተወደደበት በዚህ በአሁኑ ጊዜ ኑሮን እንዴት ተቋቋምከው?”
ይሄኔ ቀበሮ በጣም እየተኩራራ ተጎማለለ፡፡ ድመቷንም ሽቅብ ቁልቁል እያየ ገረመማት፡፡ ከኩራትና ከእብሪቱ የተነሳም ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ መስጠት ብዙ ጊዜ ፈጀበት፡፡ በመጨረሻም እዲህ አላት፡-
“አንቺ ምስኪን ጢም-ላሽ ፍጥረት! አንቺ የቤት አሽከር! ደካማ፣ የአይጥ-አባራሪ! ማነሽና ነው እኔን የተከበርኩትን ቀበሮ ኑሮ ከበደህ ወይ የምትይኝ? ማነሽናስ ነው የኑሮ ውድነቱን ተቋቋምከው ወይ? ብለሹ የምትጠይቂኝ? ለመሆኑ እስከዛሬ ድረስ አንቺ ምን ተምረሻል? በምንስ ጥበብ ሰልጥነሻል? ምን ችሎታ አለሽ?”
ድመቲትም፤ ትህትና በተላበሰ ቃና፤
“አንድ ጥበብ ብቻ ነው ያለኝ” አለችው፡፡
አያ ቀበሮም፤
“ምን ጥበብ ትችያሽ? ተናገሪ እስቲ?” አለና ጠየቃት፡፡
ድመቲትም፤
“ውሾች ድንገት መጥተው ሲያባርሩኝ ፈጥኜ ዛፍ ላይ እወጣለሁ፡፡ ይሄ ነው ጥበቤ”
ቀበሮም በጣም በኩራት ተነፋፍቶ፤
“ይሄ ብቻ ነው እንዴ ችሎታሽ? ጥበብሽ ይሄ ብቻ ሆኖ እንዲህ በአደባባይ ስትፎክሪ መስማትሽ በጣም የሚያስገርም ነገር ነው፡፡ ጉረኛ ነሽ! እኔን ስላላየሽ ነው፡፡ እኔ ከመቶ በላይ ጥበብና ችሎት አለኝ፡፡ ከዛ በተጨማሪም አንድ ከረጢት ሙሉ ዘዴና ትሪክ አለኝ፡፡ እኔ አንቺን ከልቤ እወድሻለሁ፡፡ ነይ፡፡ ነይ አብረን እንሂድና ከውሾች የምታመልጪበትን ዘዴ አስተምርሻለሁ” አላት፡፡
በድንገት ከየት መጣ ሳይባል አንድ አዳን ይመጣል፡፡
አራት ትላልቅ አዳኝ - ውሾች ይዟል፡፡
ይሄኔ እመት ድመት በከፍተኛ ፍጥነት ተቀላጥፋ ዛፍ ላይ ትወጣለች፡፡ በቅርንፎቹም ተንጠላጥላ ሙሉ በሙሉ በቅጠሎቹ ተሸፋፍና ተደብቃ ትቀመጣለች፡፡ እቅጠላ -ቅጠሎቹ መካከል ሆና፤
“አያ ቀበሮ፤ ቦርሳህን ከፈተው፡፡ ቶሎ ብለህ ቦርሳህን ክፈትና ከዘዴዎህ አንዱን አውጥተህ ተጠቀም” እያለች ትጮህ ጀመር፡፡
ግን ምን ያደርጋ፤ አያ ቀበሮ!” አለች በጮክታ፡፡ “አሁን የገባህበትን አጣብቂኝ ተመልከት፡፡
አጠራቅሜያለሁ ካልካቸው ከመቶ በላይ ዘዴዎች አንዱን እንኳ ስራ ላይ ሳታውል ፈፅሞ ከማትወጣበት ችግር ውስጥ ገባህ፡፡ እኔ ከልቤ አምኜ የያዝኳትና በረዥም ጊዜ ልምድ የተካንኳትን ሀቀኛና ፈጣን ዘዴ ተጠቀምኩ፡፡ ዛፍ የመውጣት ዘዴ ብታውቅ እንደዚህ ሆነህ አትቀርም ነበር” ብላው የበለጠ ጥቅጥቅ ወዳለ ቅጠል - ቅጠል ውስጥ ገብታ ስታበቃ በመጨረሻ አዳኙና ውሾቹ ሲሄዱ ወረደች፡፡
***
በአንድና በሁለት ነገር ብልጥ ሆኖ ሌሎችን መብለጥ ይቻላል፡፡ በሁሉም ነገር ብልጥ መሆን ግን ዘበት ነው፡፡ ሁሉ መፎከር፣ ሁሉ እኔ እበልጣለሁ እያለ መደንፋት፤ ሁሌ የትም አይደርስም እያለ መናቅ፤ ሁሌ በጊዜያዊ ድል መኩራራት የሚሰምርና ፍሬ ያለው ውጤት ሆኖ አለመገኘቱ ብቻ ሳይሆን ለችግር የሚያጋልጥ አባዜ ነው፡፡ ሥጋት፣ ጥርጣሬና አለመረጋጋትን ያነግሳል፡፡ ጥንት እንሰማ ከነበረው “አብዮታችን ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ተሸጋግሯል” ከሚባልበት አይነት ሁኔታ ወጥተን በውይይት ወደምናምንበት ደረጃ መሸጋገር መቻል አለብን፡፡ አለበለዚያ ሁሌ የግጭት ሁሌ የእልቂት ሀገር መሆን አንድንችም፡፡ አንድ የሀገራችን ምሁር “ታሪክ ራሱን ይደግማል” የሚባለውን አነጋገር በእኛ አገር አንፃር ሳየው ያስገርመኛል፡፡ በእኛ አገር አንዳንዴ ታሪክ፤ ታሪክ ሆኖ ሳያልቅ ይደገማል፡፡ ሲብስበትም ከናካቴው ታሪክ ሳይሆን በፊት ራሱን ይደግማል” ብለው ነበር፡፡ የበለጠ እሚያስገርመው ደግሞ የሚገርመው ክፉ ክፉው፣ ተንኮል ተንኮሉ፣ ምሬት ምሬቱ መሆኑ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ሀገር ስታለቅስ ትኖራች፡፡ የሐዘን እንባ አይለያትም፡፡
መሰረታዊው የኢኮኖሚ ውስብስብ ችግርና ጥያቄ ሳያበቃ በፖለቲካው መስክ መልስ ያላገኙ ጥያቄዎች እየበዙ፣ እየተሸረቡ፣ እየደነደኑ፣ ሲመጡና ትላንት ያከማቸነው ጥበብና ዘዴ ሁሉ አልሰራ ሲል፣ ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ “መድሃኒቱን ሰውነትህ ለምዶታልና አይሰራልህም፡፡ ሌላ ለውጥ”፤ እንዲል መጽፅሀፈ-ሀኪም፡፡ የዲሞክራሲ ጥያቄ፣ የፍትህ ጥያቄ፣ የፕሬስ ነፃነት ጥያቄ፣ የብዙሃን ፓርቲ ጥያቄ፣ የሰብአዊ መብት ጥያቄ… መልስ ካላገኙ ሰልፉ ሁሉ ቀኝኋላ ዙር ነው!
የሃያሎች አማላጅነትም ቢሆን የሀገርን ችግር በዘላቂነት ፈትቶ አያውቅም፡፡
የሃያላኖች እርዳታም ሆነ ምልጃ፤ የህመም ማስታገሻ እንጂ መፈወሻ አይደለም፡፡ እነሱም የራሳቸውን ጥቅም መሰረት ያደረገ አቅጣጫ እዳላቸው አለመዘንጋት ነው፡፡
ሥራና ሰራተኛን ለማገናኘት ዋንኛ መመዘኛው ሙያዊ ብቃት ነው፡፡ ፖለቲካዊና ወገናዊ ድልደላ ካለ ከሙስና የተለየ ትርጓሜ የለውም፡፡ ለምሁር፣ ለባለሙያ፣ ለሰለጠነ የሰው ኃይል ያለን እምነት ከፖለቲካ ታሳቢነት ነፃ ካልሆነ፣ ኖሮ ኖሮ የአገርን ጥቅም የሚሸረሽር፣ ነገ ፍሬ የማያፈራ የብልጣ ብልጥ ተግባር ከመሆን አያልፍም፡፡ ስለሆነም የኋሊት እንጂ ወደፊት አያራምድም፡፡
በዲፕሎማሲው ረገድም ሊደርስ የሚለውን ቀውስ አለመዘንጋት ተገቢ ነው፡፡ ብቃት ያላቸው አምባሳደሮችን አለመመደብ የሚያስከትለውን ቀውስ ማስዋብ ያሻል፡፡ በዚህ በሰለጠነው ዓለም አምባሳደርነት አገርን የመወከል ታላቅ ኃላፊነት እንጂ መጦሪያም ግዞትም፤ ፖለቲካም ማስታመሚያም፣ ቁሳቁስ በሻንጣ መሸከፊም አሊያም ደግሞ ቤተሰብ ማጓጓዣም አይደለም፡፡ የሀገርን ክብር በባህል፣ በኢኮኖሚና በዲፕሎማሲ ማጎልበቻ ነው፡፡ ውሎ አድሮ ከሚከሰት ዲፕሎማሲያዊ ሽንፈትም መዳኛ ነው፡፡
“አውቀን በድፍረት ሳናውቅ በስህተት በሰራነው ሁሉ ይቅር ይበለን” የሚለው የማሳረጊያ ንሥሐ የሚያስፈልግበት ዘመን ነው፡፡ ደፍሮ ተናግሮ መፅደቅ የሚሸዳ ጠፋ እጂ!!
በሀገራችን ውስጥ በየፈርጁ የሚታየው በቂም መፈላለግ ሆነ ብሎ አለመግባባት፣ ሰበብ እየፈጠሩ ነገር መፈላለግ፣ የ”ሳታመሀኝ ብላኝ” እሮሮ፣ “የብቆጣም እመታሻለሁ፣ ብትቆጪም እመታሻለሁ” ድንፋታና ማን አለብኝ፤ “በጨለማ እየሄዱ ጅብ ነገረኛ ነው ይላሉ” አለ አያ ጅቦ፤ የሚለውን ተረት የሚያስጠቅስ ክስተት ሆኗል፡፡ በዚህ ክስተት አገር አታድግም፡፡
የአጼ ቴዎድሮስ የልጅ ልጅ ልጅ አዳዲስ ምስጢሮች
• ኢትዮጵያዊ መሆኑን ያወቀው ከ30 ዓመቱ በኋላ ነው
• የልዑል አለማየሁ አስከሬን በእንግሊዝ የለም ብሏል
• ልዑሉ በ18 ዓመቱ በለጋ ዕድሜው አልተቀጨም ባይ ነው
ባለፈው ረቡዕ ወዳጄ ዘነበ ወላ ስልክ ደውሎ፣ የአጼ ቴዎድሮስ የልጅ፣ ልጅ ልጅ እዚህ እንደሚገኝና መጽሐፉን ማሳተምእንደሚፈልግና የሚዲያ ሰው ማነጋገር እንደሚሻ ነግሮኝ ስሙንና ስልኩን በቴሌግራም ላከልኝ፡፡ ”ስሜ ሲሰን አለማየሁ ቴዎድሮስይባላል፡፡ በአሜሪካን አገር ያደግሁኝ
ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ ደራሲና የፊልም ፕሮዱዩሰር ስሆን፤ መጻሕፍቶቼ በኢትዮጵያ ገበያ ላይእንዲወጡልኝ እፈልጋለሁ” ይላል በቴሌግራም የደረሰኝ መልዕክት፡፡ ይህን ስም የሰማሁት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ አላውቀውም፡፡ ጉግል አደረግሁ፡፡ ጉግል ግን በደንብ ያውቀዋል፡፡ማንነቱን፣ ሥራዎቹን ወዘተ ዘረገፈልኝ፡፡ ጥቂት መረጃዎች ከሰበሰብኩ በኋላ ሰውየው ዘንድ ደወልኩለት፡፡ ለቃለ መጠይቅ ፈቃደኛ መሆኑንጠየቅሁት፡፡ አላቅማማም፡፡ ሲሰን አለማየሁ ቴዎድሮስ፤ የልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስና የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስን ጨምሮ ከ7 ያላነሱመጻኅፍትን ለንባብ ያበቃ ታታሪ ብዕረኛ በመሆኑ ደራሲ ነው ብንል አልተሳሳትንም፡፡ ደራሲ ብቻ ግን አይደለም፡፡ ደራሲና ሁለገብ ብንለው ሳይቀል አይቀርም፡፡ ምክንያቱምየፊልም ፕሮዱዩሰር ነው፣ የታሪክ ልሂቅም ነው፡፡ በተጨማሪም ቪዲዮግራፈርና ግራፊክ ዲዛይነርም ነው፡፡ ይህ ሁሉ ታዲያ ቆፍጣናየአሜሪካ ወታደር መሆኑን ሳንረሳ ነው - አሁን ጡረታ ቢወጣም፡፡ የኢራቅ ግዳጁን ፈጽሞ ሲመለስ አባቱ አንድሪውቻርልስ ሊንዚ የነገሩትምስጢር የህይወቱን ዕጣ ፈንታ እንደቀየረው ይናገራል፡፡
አባቴ ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ የነገረኝ ይህ የቤተሰብ ምስጢር፤ አስቤውም አልሜውም የማላውቀው ነውይላል፡፡ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ታዲያ የተነገረውን ምስጢር ገላልጦ እውነቱን ለማወቅ ያልፈነቀለው ድንጋይ፣ ያልረገጠው የዓለም ዳርቻ የለም፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ፡፡ እውነቱን
አወቀ ማለት ደግሞ ራሱን ማንነቱን አወቀ ማለት ነው፡፡ በዚህ ከአዲስ አድማስ ጋር ባደረገው ልዩ ቃለ ምልልስ፣ ሲሰን አለማየሁ፣ስለ ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ ደረስኩበት ያለውን አዲስ እውነት ወይም ምስጢር ያጋራናል፡፡ የቤተሰቡን የዘር ሃረግ ለማግኘት የተጓዘበትን ርቀትናየደረሰበትንምያወጋናል፡፡
አሁን በቀጥታ ወደ ቃለ ምልልሱ፡-
እስቲ ከትውልድህና አስተዳደግህ እንጀምር---የት ተወለድክ? የትስ አደግህ?
የተወለድኩት ሻን አንድሪው ሊንዚ ነው፤ ያደግሁት በከተማ ማህበረሰብ ውስጥ እንደ አፍሪካ-አሜሪካዊ፣ በሻምፓኝ፣ ኢሊኖይ ነው።የምኖርበት ሰፈር በዓመፅ፣ በአደንዛዥ ዕፅና በጠመንጃ የተሞላ ነበር። ፖሊስ የችግር ቦታ ሲል የፈረጀው ነው- አካባቢውን፡፡ ባለፉትዓመታት፣ ቤተሰቤንና የልጅነት ዘመን አብሮ አደጎቼን አጥቻለሁ፡፡ ኢትዮጵያዊ መሆኔን እስከ 30 ዓመት ዕድሜዬ ድረስ አላውቅም ነበር።በ1999 ዓ.ም የአሜሪካንን ጦርሰራዊትተቀላቀልኩ፡ በ2007 ዓ.ም የኢራቅ ግዳጄን ተወጥቼ ወደ አገር ቤት ተመለስኩ። በወቅቱ የአባቴ አንድሪው ቻርልስ ሊንዚ የጤና ሁኔታእያሽቆለቆለ ነበር፡፡ ያኔ ነው የቤተሰባችንን ምስጢሮች ለመጀመሪያ ጊዜ ገልጦ የነገረኝ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሣ ከሚባል የንጉሥቤተሰብ እንደመጣን ገለጸልኝ፡፡ መጀመሪያ ላይ
ነገሩን አምኖ ለመቀበል አዳጋች ሆኖብኝ ነበር፤ ምክንያቱም ከዚያ በፊት ስለዚህ ጉዳይ ጨርሶአንስቶ አያውቅም፡፡ ከአንድ ወር በኋላ አባቴከዚህ አለም በሞት ተለየ።
አንተስ ይህን አዲስ መረጃ ከአባትህ ካገኘህበኋላ ምን አደረግህ?
አባቴ የመጨረሻዎቹ ቀናት ላይ ማንበብ የማልችለውን የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ መያዜን አውቆ ነበር፡፡ እናም ወደ ኢትዮጵያሄጄ ቤተሰባችንን ፈልጌ እንዳገኝ ትዕዛዝ ሰጠኝ፡፡ በ2012 ዓ.ም ከአሜሪካ ጦር ሠራዊት ጡረታ ወጣሁና ወደ ኢትዮጵያ ተጓዝኩ፡፡ ወደ ባህርዳርና ጎንደርም ተሻግሬ፣ አባቴ የጠቀሰውን ሃውልት ለማየት ቻልኩ፡፡ ያኔ ነው ካሣ የሚለው ስም ለካሳ ሀይሉ ጊዮርጊስ፤ ለባለ ዘውዱ ንጉስዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ መሆኑንየተረዳሁት፡፡
በ2017 ዓ.ም አንዲት ሴት በአማራ ቲቪቃለ መጠይቅ ተደረገላት። አበበች ካሳ መሸሻ ቴዎድሮስ ትባላለች። እቺን ሴት ከሁለት ወራትበኋላ አገኘኋት፡፡ እዚህ ኢትዮጵያ ያለ የቅርብ ወዳጄ አዲስ አበባ ሠርጉ ላይ እንድገኝ ጋብዞኝነበር፡፡ በዚያ አጋጣሚ እኔና እሷ የዲኤንኤምርመራ አደረግን፤ ውጤቱም ዘመዳሞችመሆናችንን አረጋገጠ፡፡ አባቴ የተወለደው አሜሪካ ነው፣ አባቱ ቻርለስ ሊንዚ ግን አሜሪካ አይደለምየተወለዱት፡፡ ቻርለስ ሊንዚ ተብለው የሚጠሩት አባታቸው ደግሞ ከንጉሥ ቴዎድሮስልጆች አንዱ ነበሩ።
ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስን የተመለከተመጽሐፍ በአማርኛና በእንግሊዝኛ አሳትመሃል፡፡ አማዞን ላይ ለሽያጭ ቀርቦ ተመልክቼዋለሁ---
ትክክል ነው፡፡ በ2018 ዓ.ም በአንዱ ቀን፣ ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስን ለማክበር ወደእንግሊዝ ተጉዤ ነበር፡፡ ያኔ ነው ሚስጥሮቹንያገኘሁት፡፡ ለልዑል ዓለማየሁ በቦታው ላይ ምልክት ብቻ እንጂ የሬሳ ሳጥን መቃብር የለም።ሆኖም ሰ ዎች የ እኔንና የ ልዑል አ ለማየሁንበእጅጉ መመሳሰል ታል፡፡ እኔም ቅድመ- አያቴ የእውነትም ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ እንደነበሩ ተረዳሁ፡፡ ልዑል አለማየሁ፤ እስከ 113ዓመት ዕድሜያቸው ድረስ በህይወት ኖረው፣
በ1974 ዓ.ም ሻምፓኝ፣ ኢሊኖይ ነው የሞቱት፡፡
አንተ ልዑል አለማየሁ ቅድመ አያቴ ነበሩ ስትል ማረጋገጫህ ምንድን ነው?
መጀመሪያ ላይ ልኡል አለማየሁ ቅድመ አያቴ መ ሆኑን አ ላውቅም ነ በር። ነ ገር ግ ን ከልኡል አለማየሁ ጋር እንደምንመሳሰልበየፎቶው ላይ አስተውያለሁ። ከአበበች ካሣ መሸሻ ቴዎድሮስ ጋር የተደረገ የDNA ምርመራማስረጃ አለኝ፤ ከ50% በላይ የዲኤንኤ መዛመድ እንዳለን ያሳያል። በቅርቡ የካፒቴን ትሪሻም ቻርልስ ስፒዲ ቤተሰብ ከኒውዚላንድ የልዑል አለማየሁን ናሙና ከመቃብር ቦታ ሳይሆንከቤተሰቡ አምጥቶልኝ ነበር። የፀጉር ናሙናዎች ዲኤንኤ ነው፡፡ እኔም ከቅድመ አያቴ ቻርልስ ፎቶና ልዑል አለማየሁ ጋር የፎቶ ልየታ ሰርቼ፣85% የተዛማችነት ውጤት ታይቷል፡፡ቅድመ አ ያቴ በ 1879 ዓ.ም ወደ ፍ ልስጤም መሄዱን ተረድቻለሁ፡፡ ስምየን አንበሳ ዘዮን የሚለውን ስሙን ለውጦታል። አንበሳ ዘዮንበእንግሊዝኛ የጽዮን አንበሳ ማለት ሲሆን፤ ሊንዚ ደግሞ የጽዮን አንበሳ ነው። እስከ 1919 ዓ.ምድረስ ቤተ ሺአን እና እየሩሳሌም ውስጥ ነበርየቆየው፡፡ ቻርልስ ከካፒቴን ትሪሻም ቻርልስስፒዲ ይባላል። ኢትዮጵያ እያለ ከወንድሙ መሸሻ ቴዎድሮስ ጋር ተገናኘ። ሚስት እንዲሁምሴት ልጅና ወንድ ልጅ ነበረው። ሚስቱ
በ1925 ዓ.ም ልጃቸው ቻርልስ የ2 ወር ልጅእያለ፣ኢትዮጵያ ውስጥ ህይወቷ አለፈ፡፡ እሱከልጁ ጋር ወደ አሜሪካ ሲመጣ ሴት ልጁ ግን ቀረች።
ከሰባት በላይ መጻሕፍትን አሳትመሃል፡፡ ወደ ጸሃፊነትና ፊልም ሙያ እንዴት ገባህ? ወታደር ቤትን ከመቀላቀሌ በፊት የሙዚቃ ኮንትራት (ውል) ለማግኘት የሚሻ የሂፕ ሆፕ ሪከርዲንግ አርቲስት ነበርኩ። መጀመሪያ ዘፈኖችን መጻፍ ጀመርኩ፤ በኋላ ወደ መጻሕፍትገባሁ፡፡ የበኩር መጽሐፌ በ2006 የታተመሲሆን፤ ከዚያ በኋላ ሰባት ተጨማሪ መጻሕፍትን መፃፍ ቀጠልኩ። ስለ ቤተሰቤ የዘር ሐረግምጽፌአለሁ፡፡ እናም ጉዞዬን በፊልም መ ቅረጽ
ጀመርኩ፡፡ ስለ ቤተሰቤ ታሪክ ለማወቅ ያደረግኋቸውን ጉዞዎች ለማድመቅ ዘጋቢ ፊልም ሰርቻለሁ። የጉዞዬ አካል፣ ኢትዮጵያበመላው አለም በአሜሪካ፣ በእስራኤል፣ በአውሮፓና በጥንቷ ባቢሎን ታላቅ ታሪክ እንዳላት መማር ነው።
የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ በሥራዎችህ ስታጋራ ያጋጠሙህ ተግዳሮቶች ወይም የተሳሳቱአመለካከቶች የሉም? እንዴት አስተናገድካቸው?
ልዑል አለማየሁ በ18 ዓመቱ ሞቷል ተብሎ ዓለም ሁሉ ስለተነገረው ብዙ ተግዳሮቶች ገጥመውኛል፡፡ የንጉሣዊው ቤተሰብ የልዑልአለማየሁን አስክሬን ለመላክ ፈቃደኛ ያልሆነው፣ ንግሥት ቪክቶሪያ ልኡሉ ሳይሞት የሞተ አስመስላ በመናገሯ ነበር፡፡ ለዚህ ደግሞምክንያቱ ንጉሥ ዮሐንስ ልዑል ዓለማየሁ
ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ የሚጠይቅ ሁለት ደብዳቤዎች ለንግሥት ቪክቶሪያ በመጻፋቸው የተነሳ ነው፡፡
አሁን ወደ ኢትዮጵያ የመጣህበት የተለየ ዓላማ ወይም ተልዕኮ ይኖርህ ይሆን?
ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ ለዘጠነኛ ጊዜ ነው፡፡ ግቤ የኢትዮጵያ መታወቂያ አግኝቼ እዚህ አገር መኖርና መማር ነው፤ ምክንያቱም ወደ ኢትዮጵያ
መምጣት የቤት ዓይነት ስሜት ይፈጥርብኛል፡፡ ህዝቤን እወዳለሁ፤ ከኢትዮጵያውያን ጋር በመሆኔ የሰማዩን አባት አመሰግነዋለሁ፡፡ሌላው ግቤ ደግሞ በአማርኛም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች መናገር፣ ማንበብና መጻፍ መማር ነው። ወደ ቤት የሚመለስበትን መንገድለማግኘት የሚሞክር የጠፋ ልጅ ዓይነት ስሜት ይሰማኛል።
በመጨረሻ፣ በሥራዎችህ ምን አሻራ ትተህ ማለፍ ትፈልጋለህ?
የኢትዮጵያ ታሪክ አካል መሆን እፈልጋለሁ። ሁሉንም ሰው የሚጠቅም ታላቅ ነገር ማድረግ እንደምችል ተስፋ አደርጋለሁ። መጽሐፎቼኢትዮጵያ ውስጥ ቢታተሙ መታደል ነው፡፡ ታሪክን በፊልም ቀርጾ መስራትና ኢትዮጵያ በአለም ላይ ያሳደረችውን ተፅእኖ ማሳየትእፈልጋለሁ።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
አሚጎስና በላይአብ ሞተር ሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ መኪኖችን በብድር ለመስጠት ስምምነት ፈጸሙ
አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅብረት ሥራ ማህበር፣ ከበላይአብ ሞተር ኃ.የተ.የግ.ማ ጋር በሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ መኪኖችን ለአባላት በብድር ለመስጠት የሚያስችል የስራ ስምምነት ዛሬ ጠዋት ረፋዱ ላይ በጎልደን ቱሊፕ ሆቴል ፈጽመዋል፡፡
አሚጎስ ከበላይ አብ ሞተርስ ጋር ባደረገው በዚህ ስምምነት መሰረት፣ መስፈርቱን ለሚያሟሉ የማህበሩ አባላት በሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ መኪኖችን በብድር ያቀርባል፡፡
በአገራችን የሚገጣጠሙ ተሽከርካሪዎች ፍላጎት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መምጣቱ የሚነገር ሲሆን፤ የዜጎችን ኑሮ ባማከለ መልኩ በብድር አማራጭ እየቀረቡ የሚገኙት ሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ መኪኖች የፋብሪካ ዋስትና ያላቸው መሆናቸው ተመራጭ ያደርጋቸዋል ተብሏል፡፡
አሚጎስ ላለፉት አስራ አንድ አመታት ከ7 ሺ 500 በላይ አባላትን በማቀፍ እንዲሁም ለ4000 ያህል አባላቱ የብድር አገልግሎትን በመስጠት በርካቶች ሥራቸውን እንዲያስፋፉና የራሳቸውን ሥራ እንዲፈጥሩ ማድረጉ ተገልጿል።
ከአስር ዓመት በፊት በዘጠኝ ሺ ብር ካፒታል የተመሰረተው የገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅብረት ሥራ ማህበሩ፤አሁን ላይ ካፒታሉን ከአንድ ነጥብ አምስት ቢሊየን ብር በላይ ማድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ነሕምያ ኦቲዝም ማዕከልን ለመደገፍ የዳንስ ፊትነስ በጎልፍ ክለብ ተዘጋጀ
• በእሁዱ መርሃ ግብር እስከ 5ሺ የሚደርሱ ደጋግ ሰዎች ይሳተፋሉ
• ለማዕከሉ እስከ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለማሰባሰብ ታቅዷል
ነሕምያ ኦቲዝም ማዕከል፣ ከኢትዮ ዳንስ ፊትነስ ጂምና ሰፖ ጋር በመተባበር ከነገ ወዲያ እሁድ ሚያዝያ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ ጦርሀይሎች በሚገኘው ጎልፍ ክለብ የዳንስ ፊትነስ መዘጋጀቱ የተገለጸ ሲሆን ዓለማውም ለማዕከሉ የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰብ ነው ተብሏል፡፡
በእዚህ ዝግጅት ላይ እስከ 5 ሺ የሚደርሱ ደጋግ ኢትዮጵያውያን እንደሚሳተፉ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በዕለቱ ከ5 ሚሊየን ብር ለማሠባሠብ መታቀዱን የሚገልጸው የኢትዮ ዳንስ ፊትነስ መስራችና ባለቤት ቶማስ ኃይሉ (ቶም ኘላስ)፤ ሁላችንም በመተባበር በነሕምያ የሚገኙ ህጻናትን እንድናግዝ ጥሪውን አስተላልፏል።
ከ10 ዓመት በፊት የተመሠረተው ነሕምያ ኦቲዝም ማዕከል፤ በኦቲዝምና ተዛማጅ ችግሮች የአዕምሮ ዕድገት እከልየገጠማቸውን ህጻናትና ወጣቶችን እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን ከተጋረጠባቸው ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ፣ ስነልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች ለመታደግ አልሞ የሚሰራ መሆኑን የማዕከሉ መስራች ወይዘሮ ራሄል አባይነህ ገልጸዋል።
በመላው ኢትዮጵያ እየተከበረ የሚገኘው የዘንድሮውን የዓለም ኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የዳንስ ፊትነስ ኘሮግራም ላይ ለመታደም የመግቢያ ዋጋው አምስት መቶ ብር ሲሆን፤ ቲኬቶቹ ቦሌ ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ ጂም እና ሰፖ ፣ ቄራ አልማዝዬ ሜዳ አካባቢ በሚገኘው ነሕምያ ኦቲዝም ማዕከል እንዲሁም በእለቱ ጎልፍ ክለብ መግቢያ በር ላይ እንደሚሸጡ ተገልጿል።