Administrator

Administrator

Wednesday, 14 August 2019 10:36

የዘላለም ጥግ


(ስለ ይቅር ባይነት)
• ይቅር ባይነት ያለፈውን አይለውጠውም፤ የወደፊቱን ግን ያሰፋዋል፡፡
ፓውል ሌዊስ ቦሴ
• ያለ ይቅር ባይነት ፍቅር የለም፤ ያለ ፍቅርም ይቅር ባይነት የለም፡፡
ብሪያንት ኤች.ማክጊል
• እርስ በርስ ይቅር እንባባል - ያን ጊዜ ብቻ ነው በሰላም የምንኖረው፡፡
ሊዮ ኒኮላቪች ቶልስቶይ
• ይቅርታ ማድረግ እስረኛን ነፃ ማውጣትና እስረኛው አንተ እንደነበርክ መገንዘብ ነው፡፡
ሌዊስ ቢ. ስሜዴስ
• ደካሞች ፈጽሞ ይቅርታ ማድረግ አይችሉም፡፡ ይቅር ባይነት የጠንካሮች ባህርይ ነው፡፡
ማህትማ ጋንዲ
• ፍቅርን ከልባችን የምንፈልግ ከሆነ፤ ይቅር ባይነትን መማር አለብን፡፡
ማዘር ቴሬሳ
• ማንም ሰው እስክትጠላው ድረስ ወደ ታች እንዲያወርድህ አትፍቀድለት፡፡
ማርቲን ሉተር ኪንግ
• ኢየሱስ የሞተው እኛ የሰው ልጆች ምህረትና ይቅርታ እንድናገኝ ነው፡፡
ሊ ሰመር
• ለሃምሳ ጠላቶች ማርከሻው፣ አንድ ወዳጅ ነው፡፡
አሪስቶትል
• ይቅር ባይነት የአንዳንድ ጊዜ ተግባር አይደለም፤ ዘላቂ ባህርይ ነው፡፡
ማርቲን ሉተር ኪንግ
• ፈጣሪ ሃጢአተኞችን ይቅር ባይላቸው፣ ገነት ኦና ይሆን ነበር፡፡
ያልታወቀ ሰው
• ፈጣሪ ይቅር ይለናል… እኔ ታዲያ ማን ነኝና ነው ይቅር የማልለው?
ክላሪሳ ፒንኮላ ኢስቴስ
• ይቅር ባይነት፤ የነፃነት ሌላ ስሙ ነው፡፡
ባይሮን ኬቲ
• ይቅር ባይነት የጀግኖች ባህርይ ነው፡፡
ኢንዲራ ጋንዲ
• ያለ ይቅር ባይነት የተኖረ ሕይወት እስር ቤት ነው፡፡
Quote ambition
• ማህበረሰብ ብዙ ጊዜ ወንጀለኛን ይቅር ይላል፤ ህልመኛን ግን ጨርሶ ይቅር አይልም፡፡
ኦስካር ዋይልድ
• ሰው የበለጠ ሲያውቅ፣ የበለጠ ይቅርታ ያደርጋል፡፡
ኮንፉሺየስ
• ይቅር ባይነት የታላቅነት ዘውድ ነው፡፡
ኢማም አሊ
• ያለ ይቅር ባይነት መጪ ዘመን የሚባል ነገር
የለም፡፡
ዴዝሞንድ ቱቱ
• ፍቅር፤ ዘላለማዊ ይቅር ባይነት ነው፡፡
ራድሃናዝ ስዋሚ
• ይቅር ባይነት ያለፈውን መርሳት ነው፡፡
ጌራልድ ጃምፓልስኪ


• ምክረው ምክረው እንቢ ካለ በሴት አስመክረው::
• አንድ ማፍቀር ግድ ነው፤ ሁለት ማፍቀር ንግድ ነው፤ ሦስት ማፍቀር ኮንትሮባንድ ነው፡፡
• ምን ጊዜው ቢረዝምም ቋንጣና ባለሥልጣን መውረዱ አይቀርም፡፡
• ሹፌሩን በፍቅር ማሳቅ እንጂ በነገር ማሳቀቅ ክልክል ነው፡፡
• ድብርትንና ጥይትን ተኝቶ ማሳለፍ ነው፡፡
• በፍርፍር ያዘነ በጥብስ ይደሰታል፡፡ በፍቅር ያዘነ…?
• የዓለም ሙቀት መጨመር መንስኤ ጭቅጭቅ ነው፡፡
• ባለጌና ዋንጫ ወደ አፉ ሰፊ ነው፡፡
• ባጃጅን አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት ታፔላ አወጡላት::
• ይሄ አናት ለቴስታ እንጂ ለትምህርት አይሆንም፡፡
• ሲጠሉህ ሳይሆን ሲወዱህም ለምን በል፡፡
• ማንም ሰው የጣለውን ሲያነሱበት አይወድም፡፡
• የኪስ ሌቦች ቆዩ! ሂሳቡን ሳንቀበል ሥራ እንዳትጀምሩ፡፡
• ሂሳብ ሳይከፍሉ ሀሳብ አይጀምሩ፡፡
• ኑሮና ታክሲ ካልታገሱት አይሞላም፡፡
• እስክናውቅ እንጂ እስክናብድ አንማርም፡፡
• ሱሪህን ሳይሆን ራስህን ዝቅ አድርገህ ኑር፡፡
• ያለውን የሰጠ ባዶውን ይቀራል፡፡
• ምክርና ቦክስ ለሰጪው ቀላል ነው፡፡
• ቅን ሁን እንጂ ቅንቅን አትሁን፡፡
• ለማይጨቃጨቅ የፀባይ ዋንጫ እንሸልማለን፡፡
• ለከፈሉት መጠነኛ ታሪፍ ዘና ይበሉ እንጂ አይኮፈሱ፡፡
• 3 ቀን ለመኖር 4 ቀን አትጨነቅ፡፡
• ሻወርና ትችት ከራስ ሲጀምር ጥሩ ነው፡፡
ምንጭ፡- (ሃበሻ ኢንተርቴይንመንትና አሪፍ ነገር ቲዩብ)

Wednesday, 14 August 2019 10:34

አስገራሚ የመሪዎች አባባል


• ሰዎች የመሪንና የአለቃን ልዩነት ይጠይቃሉ፡፡ መሪ ይመራል፤ አለቃ ደግሞ ይነዳል፡፡
ቴዎዶር ሩስቬልት
• በትልቅ ቡድን ውስጥ ያሉ ደደቦ፣ ያላቸውን ሀይል አሳንሳችሁ አትመልከቱ፡፡
ጆርጅ ካርሊን
• የስኬት ጎዳና ሁልጊዜም በግንባታ ላይ ነው፡፡
ያልታወቀ ሰው
• ስሜቶችህን መቆጣጠር ካልቻልክ፣ ገንዘብህን መቆጣጠር አትችልም፡፡
ዋረን በፌ
• በፍቅር ለወደቁ ሰዎች የመሬት ስበት ተጠያቂ ሊደረግ አይችልም፡፡
አልበርት አንስታይን
• ከሰላማዊ ባርነት ይልቅ አደገኛ ነፃነትን እመርጣለሁ፡፡
ቶማስ ጄፈርሰን
• ሰዎች ከእኔ ጋር ሲስማሙ የተሳሳትኩ መስሎ ይሰማኛል፡፡
ኦስካር ዋይልድ
• ስብሰባ የሚያስደስታቸው ሰዎች የምንም ነገር ሃላፊነት ሊሰጣቸው አይገባም፡፡
ቶማስ ሶዌል
• እርካታ ሲርቅህና ወደ ወጣትነት ዘመንህ መመለስ ስትሻ፣ ስለ አልጀብራ አስብ፡፡
ዊል ሮጀርስ
• መሪነት፤ ፍርሃትህን ከሌሎች የመደበቅ ችሎታ ነው፡፡
ላኦዚ
• የስኬት ቀመርን ልሰጥህ አልችልም፡፡ የውድቀት ቀመርን ግን ልሰጥህ እችላለሁ - እሱም ሁሉንም ሰው ለማስደሰት መሞከር ነው፡፡
ኸርበርት ባያርድ ስዎፕ
• ብርሃኑ እንዲታያቸው ማድረግ ካልቻልክ፣ ሙቀቱ እንዲሰማቸው አድርግ፡፡
ሮናልድ ሬጋን
• በእኛ አገር መጀመርያ እስር ቤት እንገባለን፤ ከዚያ በኋላ ነው ፕሬዚዳንት የምንሆነው፡፡
ኔልሰን ማንዴላ
• ሞት ለሁሉም ችግሮች መፍትሄ ነው፡፡ ሰው የለም - ችግር የለም፡፡
ጆሴፍ ስታሊን

Wednesday, 14 August 2019 10:33

የግጥም ጥግ

ማዘዝ ቁልቁለቱ
‹‹… ብረር ስልህ ብረር
ስበር ስልህ ስበር
ተኩስ ስልህ ተኩስ
ግደል ስልህ ግደል
ለሙሴ የተሰጠሁ
አሮን የተረከኝ
የኦሪት ሕግ ነኝ
ሀዲስ የማያውቀኝ?
(ለአንዳንድ አለቆች)
ከፈለቀ አበበ ‹‹ብርሃን እና ጥላ››
* * * * * *
ሀገርህ ናት በቃ!
ይቺው እናት ኢትዮጵያ… ሀገርህ ናት በቃ!
በዚህች ንፍቀ ክበብ፤ አይምሽ እንጂ መሽቶ፣
ማታው ከጠረቃ
የነቃም አይተኛ የተኛም አይነቃ፡፡
ይህቺው ናት ዓለምህ ብቻዋን የተኛች ከዓለም
ተደብቃ!!
አኪሯ ቀዝቅዞ ‹‹ያንቀላፋች ውቢት›› ያንተው
የክት ዕቃ!
ምን ትሆን እንግዲህ ሀገርህ ናት እሷ!
ልቧን አታውልቃት አትጨቅጭቃት በቃ፤
አብረህ አንቀላፋ፤ ወይ አብረሃት ንቃ!!
(ለማትጠገብ አገርና ለልብ አውልቆች)
ከነቢይ መኮንን ‹‹ጥቁር ነጭ ግራጫ››

Wednesday, 14 August 2019 10:32

የነገር ጥግ

 ታሪክ ሰሪና ታሪክ ዘጋቢ አንድ ጊዜ በአገራችን አንድ ከፍተኛ ኮሚቴ ይቋቋማል፡፡ ይህ ኮሚቴ የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ባህል፣ ሥነ ቃል ወዘተ… በማጥናት ስለ ሕዝቡ ሥነ ልቦናዊ ሁኔታ በቂ ግንዛቤ ለመጨበጥ እንዲቻል እንዲያደርግ ኃላፊነት የተሰጠው ነው፡፡ ከኮሚቴው አባላት መካከል አንደኛው ዶክተር የዩኒቨርሲቲ መምህር ሲሆን በጊዜው ከነበረው መንግስት የፖሊት ቢሮ አባላት ከአንደኛው ጋር የድሮ የት/ቤት ጓደኞች ናቸው፡፡ ይህንኑ የፖሊት ቢሮ አባል ለኮሚቴው ሥራ ኢንተርቪው ሊያደርገው ሄዶ ያገኘዋል፡፡ የፖሊት ቢሮው ባለሥልጣን፤ ከዶክተሩ ጋር ከረዥም ጊዜ በኋላ በመገናኘታቸው ተገርሞ፤ ‹‹ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? አንተ ወደኛ ግቢ (ቤተ-መንግስት ማለቴ ነው) እንድትመጣ የሚያደርግ ምን ሁኔታ ተፈጠረ?›› ሲል ይጠይቀዋል፡። ዶክተሩም ሲመልስ፤ ‹‹እኔም ገርሞኛል፤ አንተን ታሪክ ሰሪ፣ እኔን ታሪክ ዘጋቢ ያደረገን ጊዜ ነው!›› አለው፡፡ ታሪክ ዘጋቢ አያሳጣን!!
(አዲስ አድማስ፤ ሰኔ 1 ቀን 1994 ዓ.ም)


Wednesday, 14 August 2019 10:31

የፖለቲካ ጥግ


 • ፖለቲካ ዝግጅት ምናልባት ምንም እንደማያስፈልገው ተደርጎ የሚታሰብ ብቸኛ ሙያ ነው፡፡
ሮበርት ሉዊስ ስቴቨንሰን
• ሃይማኖት ከፖለቲካ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም የሚሉ ስለ ሃይማኖት የማያውቁ ናቸው፡፡
ማሃትማ ጋንዲ
• ፖለቲካ እንደ ኤክስሬይ ማሽን ይመስለኛል፡፡ ሁሉም ነገር በመጨረሻ ላይ ይታወቃል፡፡
ኒኮሌ ዋላስ
• ፖለቲካ ትክክለኛ ሳይንስ አይደለም፡፡
ኦቶ ቮን ቢስማርክ
• እውነት በአብላጫ ድምፅ አይረጋገጥም፡፡
ዱግ ግውይን
• ፖለቲከኛ ራሱ የሚናገረውን ስለማያምን፣ ሌሎች ሲያምኑት ይገረማል፡፡
ቻርልስ ደጎል
• መንግስት ሲወፍር፣ ነፃነት ይቀጭጫል፡፡
ሮናልድ ሬጋን
• አሳቢ ፈጽሞ የፓርቲ ሰው አይሆንም፡፡
ፍሬድሪክ ኒቼ
• ፖለቲከኞች የትም ቦታ አንድ ናቸው፡፡ ወንዞች በሌሉበትም ጭምር ድልድይ ለመስራት ቃል ይገባሉ፡፡
ኒኪታ ክሩሼቭ
• የትኛውንም መንግስት አትመን… በተለይ የራስህን መንግስት፡፡
አር. ፔሸንት
• ሀሳብ ያለቀበት ማንኛውም መሪ፤ ከሃላፊነት መልቀቅ አለበት፡፡
ንክዋቹክው ኦግቡአጉ
• ግንብ የሚገነባ ሰው፣ ድልድይ ለመገንባት የሚፈራ ነው፡፡
ጄሮሜ ሞንትጎሜሪ
• እኔ ፈጽሞ ፖለቲከኛ ልሆን አልችልም፤ ብዙ ጊዜ ሃቀኛ የመሆን ችግር አለብኝ፡፡
ካርል አር. ዋይት
• ትክክለኛ መሪ አገልጋይ ነው፡፡
ላይላህ ጊፍቲ አኪታ

Wednesday, 14 August 2019 10:17

የማን ቤት ልበለው?


            ለረጅም ጊዜ የተሰጠኝን ኃላፊነት ለመወጣት ስል ከመሯሯጥ በስተቀር ወደ ግል ጉዳይ አላልኩም፡፡ የነበረብኝ ኃላፊነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ክብደት ነበረው፡፡ ከ1963 ዓ.ም እስከ 1966 ዓ.ም በደቡብ ግንባር በጦር አለቅነት (ሻለቃ አዛዥነት)፣ ድንበራችን በሱማሌ እንዳይደፈር በኃላፊነት አሠራ ነበር፡፡ በ1966 ዓ.ም መጨረሻ፣ በአብዮቱ ፍንዳታ ጊዜ፣ የአራተኛ ክፍለ ጦር ዘመቻ መኮንን እንደነበርኩ፣ የአስተባባሪ ደርግን ሥራ አስፈፃሚነት ደርቤ መስራት ጀመርኩ፡፡
በ1969 ዓ.ም መጀመሪያ ጀምሮ አንድ ክፍለ ጦር በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዳሰለጥን ታዝዤ፣ በአምስት ክፍለ ሀገሮች በመከፋፈል ማለትም በሸዋ፣ በሲዳሞ፣ በከፋ፣ በሐረርጌና በጎንደር ማሰልጠን ጀመርኩ:: ክፍለ ጦሩ እንደተዘጋጀ በአዛዥነት ይዤ አስመራ ዘመትኩ፡፡ እዚያ እያለሁ የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ሆንኩ፡፡ ይህ ኃላፊነት በወቅቱ ምን ዓይነት እንደነበረ ያየ ያውቀዋል፡፡ውጤቱ ግን ክፉ አልነበረም፡፡
በ1972 ዓ.ም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሆንኩኝ፤ጥሩ ሹመትና ጥሩ ስራ ነበር ፡፡
በ1973 ዓ.ም በጥር ወር፣ ባላሰብኩት ሰው ገጭቼ ጡረታ ተባልኩ፡፡
አሁን ጎጆዬን ማየት ግድ ሆነ፡፡ ፈራርሳለች፣ ተጣማለች፣ ማቃኛዋ ቀላል አልሆነም፡፡ ለጊዜው 1,200፡00 ብር ብቻ እጄ ላይ ነበረች፡፡ በሷ ምን መስራት ይቻላል ቀደም ሲል የመጣ ሁለት መኪና ድንጋይ በራፍ ላይ ነበረኝ  ብቻውን ምን ዋጋ አለው?
‘’ጡረታ ወጥቷል ያውም  በጥፋት ነው’’ የሚባለው ወሬ ተሰማ፡፡ በዚህን ጊዜ ባለቤቴ ሆስፒታል  ልጄ እስር ቤት ነበሩ፡፡ ጡረታ የወጣው በጥፋት ነው  የሚለው  ቃል  የዕለት  ጓደኞቼን ሲያርቅ እውነተኛ ጓደኞቼን ይበልጥ ሰበሰበልኝ፡፡
ጀነራል መርዕድ በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ እያለ ከቤታችን ከማይጠፉት ዘመዶቻችን መካከል ከጋሽ ተሰማና ከአቤ (ኢንጂነር ተሰማ ያኢና ኢንጂነር አበበ ነጋሽ) ጋር ማታ ቁጭ ብለው መወያየት ይጀምራል:: በማስታወሻው ላይ ስብሰባ ብሎ በሰየመው ርዕስ ይህንን ጭውውት  ከምን ተነስቶ ምን እንደደረሰ እየተረከ እንዲሁም በችግሩ ጊዜ የደረሱለትን ሰዎች እያነሳ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
ስብሰባው፡-የሀዘንና የትካዜ አልነበረም፡፡ በሚያሳፍር ተግባር አልወጣህም፣ ነገ ትመለሳለህ ትፈልጋለህ፡፡ እስከዚያ  እኛ አለንልህ ፡፡የትናንቱ የኢትዮጵያ ድንበር አስከባሪ ፣ የትናንቱ ጀግና፣ የተሻለ እንጂ ያነሰ አትኖርም፡፡ የኛ ወዳጅነት ትርጉም የሚኖረው ዛሬ ነው፡፡ ስለዚህ አታስብ ይልቁንስ ሃሳብህን ግለፅልን ሲሉ፣ ተሰማ ያኢና አበበ ነጋሽ ጠየቁኝ፡፡
“ቤት አድሳለሁ ብዬ ያመጣሁትን ድንጋይ ሸጡልኝ” አልኳቸው፡፡
“ለምን?” አሉኝ
ገንዘብ ስለሌለኝ እድሳቱን ማቆም ስላለብኝ ነው ብዬ መለስኩ፡፡
ነገ ማታ እመጣለሁ ብለው ሄዱ፡፡
በማግስቱ ማታ መጥተው ይህንን ቤት እናድሰዋለን፤ በሠራዊት በኩል እንደጀመሩት፣ በድንጋይና በአሸዋ ማቅረብ በኩል፣ እንዲረዱህ ጠይቅ አሉኝ፡፡ ኮሎኔል መሐመድና ሻለቃ ኪዳኔ ተክሉን ጠይቄ፣ የሚቻለውን ሁሉ እናደርጋለን አሉ:: የቤቱ ስራ በአበበና በተሰማ መሐንዲስነት ኃላፊነት ተጀመረ፡፡
በአምስተኛ ቀን ባለቤቴ ከሆስፒታል ልጄ ከእስር ቤት ወጥተው በአንድ ቀን አሮጌዋ ቤቴ ሞቀች፡፡ ዘመድ ወዳጅም እንደ ዛሬው ተሰበሰበ፡፡ የቤቱም ስራ ቀጥሎ ዛሬ ካለበት ደረጃ ደረሰ፡፡
(“ለወገንና ለአገር ክብር”
ሜጀር ጀኔራል መርዕድ ንጉሤ)   - በስራ ምደባ ለውጥ ሳቢያ ባለፈው ሳምንት 2 ፖሊሶች በጥይት ሞተዋል
   - አንዱ ላይ ብቻ ነው የተኮስኩት ብሏል - በግድያ የታሰረው ፖሊስ
 - በአዲስ አበባ በአመት 220 ግድያዎች ተፈጽመዋል

                ሟች ብርቱካን ፍሬው ከዋና ሳጅን ብርሃነ ግደይ ጋር በጋብቻ ተሳስረው ሲኖሩ፣ አንድ ወንድ ልጅ አፍርተዋል፡፡ ለ9 ዓመታት በትዳር ቢቆዩም በመሀከላቸው በነበረ አለመግባባት ፍቺ መጠየቋን የፖሊስ መዝገብ ያስረዳል፡፡
ለፍ/ቤት የቀረበው የፍቺ ጥያቄ ለመጋቢት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ነበር የተቀጠረው፡፡ ሆኖም ከቀጠሮ በፊት የካቲት 28፣ የፌደራል ፖሊስ ካምፕ አጠገብ በሚገኝ ካፌ ውስጥ ከወንድ ጋር ተቀምጣ አየኋት የሚለው ዋና ሳጅን ብርሃነ፤ ክላሽ በመውሰድ ሟች ብርቱካንን በ15 ጥይት እንደመታትና ህይወቷ እንዳለፈ መዝገቡ ይጠቁማል፡፡
ክስ ተመስርቶ ጉዳዩም ወደ ፍ/ቤት አምርቷል፡፡ የፌደራል ፖሊስ ረዳት ሳጅን ከበደና ዋና ሳጅን ፈይሳ ከድር፤ ከሁለት ዓመት በላይ አብረው ቢሠሩም፣ መልካም ግንኙነት እንዳልነበራቸው ለፖሊስ በሰጠው ቃል ላይ ይገልፃል - ረ/ሳጅን ከበደ፡፡
በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ተመድቦ ይሰራ የነበረው ሳጅን ከበደ፣ ሀምሌ 29 ቀን 2011 ዓ.ም ለስራ ወደ ጃንሜዳ አካባቢ እንዲሄድ መልዕክት የደረሰው በዋና ሳጅን ፈይሳ ከድር ነበር፡፡ ለምን አንተ ትነግረኛለህ? ጥፋትም ካለብኝ በደብዳቤ ተገልፆልኝ ነው የምሄደው…›› በማለት ውዝግብ እንደተነሳ ተጠቅሷል፡፡ ወደ በር ሲሄድ ለስራ የተሰጠውን መሳሪያ ከአምስት ካርታ ጥይት ጋር ይዞ እንደነበርና ዋና ሳጅን ፈይሳን በመመልከቱ ሁለት ጊዜ ተኩሶ መግደሉን ለፖሊስ ተናግሯል::
በረዳት ሳጅን ታሪኩ ላይም ግድያ ፈጽመሃል ተብሎ ፖሊስ ቢጠረጥርም፣ እኔ የተከሰስኩት በዋና ሳጅን ፈይሳ ላይ ብቻ ነው፤ ምናልባት እሱን አልፎ በወጣ ጥይት ም/ሳጅን ታሪኩ ተመቶ ሊሆን ይችላል በማለት ነው ቃሉን የሰጠው፡፡
በአዲስ አበባ አስራ አንድ ሰዎች ህይወታቸው ያለፈው የፖሊስ አባላት ነው፡፡ አስሩ በስራ ላይ ባለመግባባት ሰበብ የተፈፀሙ ግድያዎች እንደሆኑ የምርመራ መዝገቦች ያሳያሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከሐምሌ 1 ቀን 2010 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ሁለት መቶ ሃያ ሁለት ግድያዎች መፈፀማቸውን የፖሊስ መረጃዎች ይገልፃሉ፡፡   


           እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2016 ይፋ የሆነው መረጃ እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ ኤችአይቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ በሚደረገው ጥረት ፀረ ኤችአይቪ የሚወስዱ ቫይረሱ በደማቸው ያለ እርጉዝ እናቶች 69% ነበሩ፡፡ ይህንን መረጃ ያወጣው የአለም ባንክ ሲሆን ዳሰሳው የተካሄደውም የልማት አመላካች ሁኔታዎችን ከመገምገም አንጻር ነበር፡፡
ከ2010-2018 ድረስ ባለው መረጃ በአለም ላይ ወደ 1.4 ሚሊዮን የሚሆኑ ህጻናት በ PMTCT ፕሮግራም መሰረት በኤችአይቪ ቫይረስ እንዳይያዙ ሆነዋል፡፡
ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ የሚተላለፈው በእርግዝና ወቅት በወሊድ ጊዜ እና ጡት በማጥባት ወቅት ነው፡፡ እድሜአቸው ከ0-14 አመት የሚሆናቸው ሕጻናት በአብዛኛው የቫይረሱ ተጎጂ የሚሆኑት ከእናቶቻቸው በሚሰራጨው ቫይረስ ምክንያት ነው፡፡
አንዲት ሴት የኤችአይቪ ቫይረስ በደምዋ ውስጥ እያለ እርጉዝ ከሆነች እና ምንም አይነት የህክምና እርዳታ ካላገኘች ቫይረሱ ወደልጅዋ የመተላለፉ እድል ከ15%-45% ይሆናል፡፡ ነገር ግን በጊዜው ሕክምና አድርጋ ፀረ ኤችአይቪ (ART) መውሰድ ከጀመረች አደጋውን ወደ 5% ዝቅ ያደርገዋል፡፡
ኤችአይቪ ኤይድስን በሚመለከት አለም አቀፉ የመረጃና ትምህርት ድረገጽ www.avert.org እንደሚያስነብበው በአለም አቀፍ ደረጃ ሊተኮርባቸው የሚገቡ ዋና ዋና  ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፡፡
ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ የሚያደርገው (PMTCT) ፕሮግራም እድሜያቸው ለስነተዋልዶ የደረሱ እና ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ወይንም ለቫይረሱ ይጋለጣሉ ተብለው የሚታሰቡ ሴቶችን ጤንነት በመጠበቅ እና የሚወልዱዋቸውንም ጨቅላዎች በቫይረሱ እንዳይያዙ በማድረጉ ረገድ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል፡፡
የPMTCT አገልግሎት የኤችአይቪ ቫይረስ ከመጀመሩ በፊት እና በእርግዝናው ወቅት እንዲ ሁም በመውለድ ወይንም ጡት በማጥባት ጊዜ ቫይረሱ የሚተላለፍ መሆኑን ለተገልጋዮቹ እውን በማድረግ መሰራት አለበት፡፡
የPMTCT አገልግሎት ልጆች ቫይረሱ በደማቸው ካለባቸው ሴቶች ገና እንደተወለዱ ማለትም ከአራት እስከ ስድስት ሳምንት ምርመራው ሊደረግላቸው የሚገባ እና ከዚያም በ18/ኛው ወር ወይንም የጡት ማጥባት ወቅት እንዳበቃ ያሉበት ሁኔታ በደንብ መታየትና  ለቫይረሱ ለተጋለጡት ልጆች በተቻለ ፍጥነት ART ሊጀመርላቸው ይገባል፡፡  
በእርግጥ ሴቶችንና ጨቅላዎችን ከወሊድ በሁዋላ በ PMTCT ፕሮግራም በሚያስፈልገው መንገድ መርዳት ከባድ መሆኑ እሙን ነው፡፡ በአንዳንድ አገሮች ብዙ ጨቅላዎች በእርግዝናና ወሊድ ጊዜ ከሚኖረው የቫይረስ መተላለፍ ይልቅ በጡት ማጥባት ጊዜ በሚፈጠረው አጋጣሚ በቫይረሱ የመያዝ እድላቸው እየሰፋ ይገኛል:: የዚህም ምክንያቱ መደረግ የሚገባውን ጥንቃቄ እና የሚሰጠውን አገልግሎት አንዳንድ ሴቶች ስለማይተገብሩት ነው፡፡
ከ2010-2018 ድረስ ባለው መረጃ በአለም ላይ ወደ 1.4 ሚሊዮን የሚሆኑ ህጻናት በ PMTCT ፕሮግራም መሰረት በኤችአይቪ ቫይረስ እንዳይያዙ ሆነዋል፡፡
ኤችአይቪ ቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ለማድረግ የተዘረጋው PMTCT የተሰኘው ፕሮግራም ለእናቶች እና ለጨቅላዎቻቸው ሰፋ ያለ አገልግሎትን ይሰጣል፡፡ ለምሳሌም በስነተዋልዶ እድሜ ላይ ያሉ (15-49) ሴቶችን በቫይረሱ እንዳይያዙ ከመከላል ጀምሮ ቫይረሱ በደማቸው ያለ ሴቶች ያልተፈለገ እርግዝናን እንዲከላከሉ እንዲሁም ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ቢኖርም እንኩዋን (ART) ፀረ ኤችአይቪን እየወሰዱ በሕይወት ዘመናቸው ጤናማ ኑሮ እንዲኖሩ ለማስቻል ይረዳል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በእርግዝና ላይ ላሉትም በእርግዝና ወቅት ወይንም በወሊድ እንዲሁም ጡት በማጥባት ቫይረሱ ወደ ልጆቻቸው እንዳይተላለፍ ማድረግ የሚችል ከፍተኛ ፕሮግራም መሆኑን www.avert.org ያስነብባል፡፡
avert እንደሚያስነብው ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ የተዘረጋው ፕሮግራም ደህንነታቸው የተጠበቀ ሕጻናትን መውለድ የሚቻልባቸውን መንገዶች የሚያስተምር እና ለጨቅላዎች ትክክለኛው የአመጋገብ ስልት ምን እንደሆነ እንዲሁም ለቫይረሱ የተጋለጡ ጨቅላዎች በጡት ማጥባት ወቅት ሊደረግላቸው የሚገባው ክትትል ምን እንደሆነ ለወላጆች እንዲሁም ለቤተሰብ ያስተምራል፡፡ በተለይም ህጻናቱን ከቫይረሱ ለመከላከል ART ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እና አገልግሎቱን በትክክል መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል::
avert የሚከተሉትን መረጃዎች ለንባብ አቅርቦአል፡፡  
ከ2010-2018 በአለም ላይ ወደ 1.4 ሚሊዮን የሚሆኑ ህጻናት በ PMTCT ፕሮግራም በሚደረግላቸው ክትትል ምክንያት በቫይረሱ እንዳይያዙ ማድረግ ተችሎአል፡፡
በ2017 ዓ/ም በአለም ላይ 80% የሚሆኑ እርጉዝ ሴቶች በደማቸው የኤችአይቪ ቫይረስ የነበራቸው ሲሆን የጸረ ኤችአይቪ መድሀኒት ወስደዋል፡፡
በአለም ላይ ወደ 740.000 በተዋልዶ እድሜ ላይ ያሉ ሴቶች በ2016 ዓ/ም ኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ተገኝቶአል፡፡ ከእነዚህ መካከልም ወደ 73% የሚሆኑት ሴቶች በ23 ሀገራት የሚገኙ ሲሆን በአብዛኛውም ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት ነው፡፡ እነዚህ ሀገራትም በከፍተኛ ደረጃ ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ የሚሰራው ፕሮግራም እንደሚያስፈልጋቸው እና ቅድሚያ እንዲሰጣቸው UNAIDS ይጠቁማል፡፡
በአለማችን በ2017 ዓ/ም ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኙ ሕጻናት ማለትም ከ1.8 ሚሊዮን ውስጥ ከግማሽ በላይ ማለትም (52%) የሚሆኑት ፀረ ኤችኤቪ መድሀኒት ይወስዱ የነበሩ ሲሆን ከእነዚህ መካከልም ወደ 110.000 የሚሆኑት ህጻናት ተገቢው የህክምና ክትትል ስላል ተደረገላቸው ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ በገጠማቸው ሕመም ምክንያት ለሕልፈት ተዳርገዋል፡፡
avert አክሎም በአለም ላይ በ2017 ዓ/ም በግምት ከ180.000 በአዲስ በቫይረሱ ከተያዙት ህጻናት መካከል ግማሾቹ ቫይረሱ የተላለፈባቸው ከእናቶቻቸው በጡት ማጥባት ወቅት መሆኑ ታውቆአል፡፡ ስለዚህም መረጃው እንደሚጠቁመው በተለያዩ ሀገራት እንደሚታየው ከሆነ ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸውን ሴቶች በተገቢው መንገድ በተለይም ጡት በማጥባት ወቅት ART እንዲወስዱ ማድረግ እና በተገቢው መንገድ ክትትሉን እንዲያደርጉ ማስቻል አስቸጋሪ መሆኑን ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ቫይረሱን መከላከል ወይንም መቀነስ እና በቫይረሱ የመያዝ እድልን መከላከል በተለይም በእርግዝናና ጡት ማጥባት ወቅት ተግባራዊ ማድረግ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ በዚህም ምክንያት በአንዳንድ አገሮች ጨቅላዎች በአሁኑ ወቅት በቫይረሱ የሚያዙበት ምክንያት በእርግዝና ወይንም በወሊድ ወቅት ሳይሆን ከተወለዱ በሁዋላ በጡት ማጥባት ጊዜ በመሆኑ እናቶች ወይንም መላው ቤተሰብ ልብ ሊለው የሚገባ ነገር ነው፡፡

 አባት እና እናት ልጃቸውን ይድሩና ልጃቸው “ሙሽሪት ልመጂ” ተብላ ባሏ ቤት ከርማ፣ እናት አባቷን ለመጠየቅ ወደ ወላጆቿ ቤት ትመጣለች፡፡ ከዚያም ከእናቷ ጋር የሴት - የሴት ነገር ትጫወታለች፡፡
እናት - አንቺ ልጅ
ልጅ - እመት እማዬ
እናት - እንደው ዝም ዝም አልሽ’ኮ! የገንፎ እህል ማዘጋጀት አለ… ጌሾ ማዘጋጀትና ማስወቀጥ አለ፡፡ ከዚያ ድግሱን ማደራጀት አለ፡፡ ኋላ “ሠርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ” ሆነ እንዳንባል… ከወዲሁ ፈሩን ብናስይዘው ይበጀናል፡፡ እንዲያው እንዲያው፤ ለነገሩ ፀንሰሽ ይሆን?
ልጅ - እማዬ፤ እኔ ምኑን አውቄው?
እናት - ለምንድን ነው ‹‹እኔ ምን አውቄው›› የምትይው?
ልጅ - እማዬ፤ አንቺ አብረሺኝ ስለማታድሪ ነው፡፡ በየቀኑ ይጨምርበታል’ኮ!
እናት- በመጀመርያ የወር - አበባሽ ያቆመበትን ጊዜ አታውቂውም ማለት ነው?
ልጅ - ገና ወር መች ሞላኝ?
እናት - በይ አዳምጪው - ማዳመጥ ነው የዚህ አገር ችግር፡፡
***
አገራችን ኢትዮጵያ ታላቅ ችግር ላይ ናት፡፡ ምናልባት ስለ “አዝማሪና ውሃ ሙላት” ያላነበባችሁ ካላችሁ ችግሩ ያን መሳይ ነው፡፡
አዝማሪና ውሃ ሙላት
አንድ ቀን አንድ ሰው
ሲሄድ በመንገድ
የወንዝ ውሃ ሞልቶ ደፍርሶ ሲወርድ
እዚያው እወንዙ ዳር እያለ ጎርደድ
አንድ አዝማሪ አገኘ ሲዘፍን አምርሮ
በሚያሳዝን ዜማ ድምፁን አሳምሮ
ምነው አቶ አዝማሪ ምን ትሠራለህ
ብሎ ቢጠይቀው
ምነዋ ሰውዬ ምን ሁን ትላለህ
አላሻግር ብሎኝ የውሃ ሙላት
እያሞጋገስኩት በግጥም ብዛት
ሆዱን አራርቶልኝ፣ ቢያሻግረኝ ብዬ፤
አሁን ገና ሞኝ ሆንክ ምነዋ ሰውዬ
ነገሩስ ባልከፋ ውሃውን ማወደስ
ግን እንደዚህ ፈጥኖ በችኮላ ሲፈስ
ምን ይሰማኝ ብለህ ትደክማለህ ከቶ
ድምፁን እያሽካካ መገስገሱን ትቶ
እስኪ ተመልከተው ይህ አውራረድ
ያልሰማው ሲመጣ የሰማው ሲሄድ

ተግሳፅም ለፀባይ ካልሆነው አራሚ
መናገር ከንቱ ነው ካልተገኘ ሰሚ
* * *
ኢትዮጵያ ትናገራለች፤ የሚሰማ ግን የለም፡፡ ወላጅ ይናገራል፤ ልጅ ግን አያዳምጥም፡፡ ወላጅ ባለበት ሰዓት፤ ልጅ የነቃና የተጋ አዕምሮ ያስፈልገዋል፡፡ ወላጅ የልጅ ትልቁ ዐይኑ ነው፡፡ አርቆ ማስተዋያው ነው፡፡ አባት ካለህ አጊጥ፤ ጀምበር ካለች ሩጥ የሚባለው ለዚሁ ነው፡፡  

Page 12 of 449