Administrator
Saturday, 02 August 2025 09:40
"ፑቲን ማዕቀቦችን እንዴት ማምለጥ እንዳለባቸው ያውቃሉ" - ትራምፕ
የዩክሬን ስምምነት ከተቀመጠው የአሥር ቀን ቀነ ገደብ በፊት ካልተደረሰ፤ ዋሽንግተን በሩሲያ ላይ ማዕቀብ እንደምትጥል ትራምፕ ለአሜሪካ ሚዲያ በሰጡት ቃለ ምልልስ ደግመው ተናግረዋል፡፡
ባለፉት ጥቂት ወራት ስለፑቲን ያላቸው ሐሳብ ተቀየሮ እንደሆነ የተጠየቁት ትራምፕ፣ "የሩሲያው ፕሬዚዳንት ጽኑ ሰው መሆናቸው የታወቀ ነው" ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ ለዩክሬን የሰላም ስምምነት አዲስ ቀነ ገደብ ማክሰኞ ይፋ አድርገዋል፡፡ ቀነ ገደቡ እንዳበቃ ሩሲያን በሁለተኛ ደረጃ ታሪፎች አስፈራርተዋል፡፡
ሆኖም ክሬምሊን "የሩሲያ ኢኮኖሚ ማዕቀብ የሚቋቋምበት አንዳች የመከላከል አቅም አዳብሯል" ብሏል፡፡
(sputnik)
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ከአለም ዙሪያ
Tagged under
Saturday, 02 August 2025 09:12
ታግቶ የነበረው ህፃን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ ተገኘ
• አጋቾቹ 2 ሚሊዮን ብር ጠይቀው ነበር
ከ5 ቀናት በፊት በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን፣ እንዳባጉና ከተማ፣ ቀበሌ 01 ነዋሪ የሆነው ህፃን ናኦድ ተኽላይ ብርሃነ፣ በአጋቾች ታፍኖ መወሰዱንና ለማስለቀቅያ 2 ሚሊዮን ብር መጠየቃቸውን የሚገልጽ መረጃ በማህበራዊ የትስስር ገፆች ሲዘዋወር ነበር።
ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች ወደ ህፃኑ ቤተሰብ ደውለውም የማስለቀቅያ ብሩን መጠየቃቸውን የተሰራጨው መረጃ ይጠቁማል፡፡
ዛሬ ሀምሌ 25 ቀን 2017 ዓ.ም የተሰማው ግን እጅግ አስደንጋጭና ኢ-ሰብአዊ የጭካኔ ተግባር ነው።
ህፃን ናኦድ ተኽላይ በጭካኔ ተገድሎ አስክሬኑ በፍሳሽ መተላለፍያ ቦይ ተጥሎ ተገኝቷል።
የሟች ህፃን ናኦድ ተኽላይ አስክሬን ለምርመራ ወደ ሆስፒታል መላኩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከእንዳስላሰ-ሽረ የመረጃ ምንጮቹ ለማረጋገጥ እንደቻለ አመልክቷል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Saturday, 02 August 2025 09:11
አየር መንገዱ አራተኛውን ኤርባስ A350-1000 ዛሬ ተረከበ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞቹን ረጅም ርቀት ለማጓጓዝ የሚያስችለውን አራተኛውን ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ዛሬ ተረክቧል፡፡
አየር መንገዱ የተረከበው አዲሱ ኤርባስ አውሮፕላን፤ የኢትዮጵያን ገፅታ በአዲስ ዕይታ ከፍ የሚያደርግ መሆኑን አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ አሁን ላይ እጅግ ዘመናዊ 4 ኤርባስ A350-1000 እና 20 ኤርባስ A350-900XWB አውሮፕላኖች ባለቤት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
Published in
ዜና
Tagged under
Friday, 01 August 2025 00:00
ንባብ ህይወትም አገርም ይገነባል!!
ትላንት ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ የተከፈተው ዓመታዊው "ንባብ ለህይወት" የመጽሐፍት ዐውደ ርዕይ፤ እስከ ተነገ ወዲያ እሑድ ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
በዚህ ዓመታዊ የመጽሐፍ ፌስቲቫል ላይ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬስ፣ ዋልያ መጽሐፍ፣ ጃፋር መፅሐፍት፣ እንሆ መጽሐፍና በርካታ ደራሲያን እንዲሁም አሳታሚዎችና አከፋፋዮች እየተሳተፉበት ነው፡፡
በዐውደ ርዕዩ ላይ የልጆች መጽሐፍት፣የታሪክ፣ የፖለቲካ፣ የቢዝነስ (ኢኮኖሚ)፣ ልብወለድ፣ ግጥም፣ የጠፉና አዳዲስ መጻሕፍትን ጨምሮ በተመጣጣኝ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርበዋል፡፡
የመጽሐፍ ፌስቲቫሉ ፋይዳ በጨረፍታ
• የንባብ ልማድን ያነቃቃል
• ደራሲያንን ከአሳታሚዎች ያቀራርባል
• መጻሕፍትን ከአንባቢያን ያገናኛል
• የመጻሕፍትን ህትመት ያበረታታል
ከዚህ አንጻር ሁላችንም አውደ ርዕዩን በመጎብኘት አጋር ልንሆን ይገባል፡፡
ንባብ ህይወትም አገርም ይገነባል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…




Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና
Tagged under
Saturday, 02 August 2025 08:37
ካፍ አዲስ ያሰራውን ዋንጫ አስተዋወቀ
• የቻን አፍሪካ ዋንጫ ነገ በይፋ ይጀመራል
•
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ካፍ አዲሱን የቻን አፍሪካ ዋንጫ ይፋ አድርጓል፡፡
ለ8ኛ ጊዜ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በጣምራ የሚዘጋጀው የቻን አፍሪካ ዋንጫ ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ካፍ አዲስ ያሰራውን ዋንጫ አስተዋውቋል፡፡
ነገ የሚጀመረው የቻን መድረክ በኬንያ፣ ታንዛኒያና ኡጋንዳ በጣምራ የሚዘጋጅ ሲሆን፤ አዲሱን ዋንጫም ኡጋንዳዊው የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ግብ ጠባቂ ዴኒስ ኦንያንጎ፣ ኬንያዊው የቀድሞው የቶተንሀም ሆትስፐር አማካይ ቪክቶር ዋኒያማ፣ እና ታንዛንያዊው መሪሾ ነጋሳ እንዳስተዋወቁት ኢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡
በሀገር ውስጥ ሊግ ብቻ የሚገኙ ተጫዋቾች የሚሳተፉበት የቻን አፍሪካ ዋንጫ ነገ በይፋ የሚጀመር ሲሆን፤ለ29 ቀን በሚቆየው ውድድር 19 ብሔራዊ ቡድኖች እንደሚሳተፉበት ዘገባው አመልክቷል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ስፖርት አድማስ
Tagged under
Saturday, 02 August 2025 08:36
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ያቀደውን ገቢ ማሳካት አልቻለም ተባለ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ባለፈው በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ ለማግኘት ያቀደውን ገቢ ሙሉ በሙሉ ማሳካት አልቻለም። ኮርፖሬሽኑ 146 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ ማግኘት የቻለው 124 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው። ይህም ከታቀደው በ22 ሚሊዮን ዶላር ያነሰ መሆኑ ከዘገባው ለመረዳት ተችሏል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሃ ይታገሱ እንደተናገሩት ፣ የውጭ ንግድ ገቢው የእቅዱን 85 በመቶ ያህል ማሳካት መቻሉን አስታውቀዋል። በተቃራኒው፣ በበጀት ዓመቱ የተገኘው አጠቃላይ የ4 ቢሊዮን ብር ገቢ የእቅዱን 99 በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልጸዋል።
በተጨማሪም፣ በተተኪ ምርት እንቅስቃሴ ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶች መመረታቸውን ጠቁመዋል ያለው ካፒታል ጋዜጣ፤ ይህም ከእቅዱ በላይ መሆኑን አመልክቷል፡፡ ከ48,900 በላይ ለሚሆኑ ዜጎችም የስራ እድል መፍጠር መቻሉ ተገልጿል።
Published in
ዜና
Tagged under
Saturday, 02 August 2025 08:33
ብሔራዊ ባንክ ባንኮች ራሳቸውን ለውድድር እንዲያዘጋጁ አሳሰበ
"ብዙ የውጭ ባንኮች ፈቃድ እየጠየቁ ነው"
የውጭ ባንኮች የኢትዮጵያን የባንክ ዘርፍ መቀላቀላቸው የማይቀር በመሆኑ ለሚጠበቀው ጠንካራ ውድድር፣ የአገር ውስጥ ባንኮች ራሳቸውን ማዘጋጀት እንደሚኖርባቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አሳሰቡ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምሕረቱ አቢሲኒያ ባንክ ከወረቀት ነፃ አገልግሎትን በይፋ ባስጀመረበት ፕሮግራም ላይ፣ የባንክ ዘርፍ እስካሁን ከነበረው በተለየ ውድድርና ፉክክር ይካሄድበታል ብለዋል፡፡
የባንክ ኢንዱስትሪው በሁሉም የአገልግሎት መሥፈርቶች ዘመናዊና ተወዳዳሪ እንዲሆን ግድ የሚልበት፣ ይህንንም የበለጠ አሁናዊ የሚያደርገው ሁለት ምክንያቶች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡
አንደኛው ኅብረተሰቡ ከባንኮች የተሻለ ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚፈልግ በመሆኑ፣ በተለይ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች ክፍት እንዲሆን ከመፈቀዱ ጋር በተያያዘ ጠንከር ያለ ውድድር ስለሚኖር እንደሆነ ማስረዳታቸውን ሪፖርተር በዘገባው ጠቁሟል፡፡
‹‹ብዙ የውጭ ባንኮች ፈቃድ እየጠየቁና ማመልከቻ እያስገቡ ነው፡፡ የውጭ ባንኮች መግባታቸው እርግጥ በመሆኑ፣ ወደድንም ጠላንም በሒደት በጣም ተወዳዳሪና የፉክክር ዘርፍ መሆኑ አይቀርም፤›› ያሉት ገዥው፤ የአገር ውስጥ ባንኮችም ይህንን ታሳቢ ያደረገ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል ተብሏል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Saturday, 02 August 2025 08:31
"በንባብ ለሕይወት” ፕሮግራም ላይ እነዚህ ደራሲያን መጽሐፎቻቸው ላይ ፊርማቸውን እያኖሩ ከአንባቢያን ጋር የማስታወሻ ፎቶግራፍ እየተነሱ ይገኛሉ!
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና
Tagged under
Saturday, 02 August 2025 08:20
“ኢትዮጵያ ውጊያውን ሳይሆን ጦርነቱን አሸንፋ ሪቫን ልትቆርጥ ተዘጋጅታለች”
• መሰናክሎቻችንን ሁሉ የእንቧይ ካብ አድርገን ለመጨረሻዋ ቀን ደርሰናል
“ታላቁን የህዳሴ ግድብ እንዳንገነባ መሰናክሎቻችንን የነበሩትን ሁሉ የእንቧይ ካብ አድርገን ሪቫን ለመቁረጥ ተዘጋጅተናል” ሲሉ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ተናገሩ።
ፕሬዚዳንቱ ለህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ምክር ቤት አመራርና ባለሙያዎች ስለ ግድብ ሀይል ስልጠና ሲሰጡ እንደተናገሩት፤ “የህዳሴ ግድብን ገንብተን የታሪክ እጥፋትን ለመቀየር መንገድ መጀመራችን፤ ቆርጠን ወደ ስራ መግባታችን፤ ወደፊት ለመገስገስ ማለማችን፤ ውሀን ማርከን ለብሄራዊ ኩራት የማዕዘን ድንጋይ እንዲሆን መስራታችን ያልተመቻቸው ሀይሎች የሰጡንን ፈተና በድል ተወጥተን፤ መሰናክሎቻችንን ሁሉ የእንቧይ ካብ አድርገን ለመጨረሻዋ የብርሀን ቀን ደርሰናል” ብለዋል።
“ኢትዮጵያ ውጊያውን ሳይሆን ጦርነቱን አሸንፋ ሪቫን ልትቆርጥ ተዘጋጅታለች” የሚሉት አቶ ዛዲግ “ከግድቡ ጋር ተያይዘው ያጋጠሙንን ቀውሶች ታግለን፤ መንበርከክን ከአያቶቻችን አልወረስንም ብለን፤ ስነ-ልቦናዊ መዳንን ሽተን በድህነት የሚወሳውን ብሄራዊ ሀፍረታችንን አሽቀንጥረን ጥለን፤ አዲስ ታሪክ ልናዋልድ የወራት እድሜ ቀርተውናል” ሲሉም አክለዋል።
ኢትዮጵያ በድህነቷ ምክንያት ተጣብቷት የኖረውን ስነ-ልቦናዊ ቁስል ልታክም ከጫፍ እንደደረሰች የሚገልጹት አቶ ዛዲግ፤ “ዓባይ ከህዳሴ ግድብ በፊት የቁጭት ዋርካ ሆኖ፤ ዜማ እና ግጥም ተደርሶለት አለመቻላችንን ሲተርክ ነበር። ከ85 በመቶ በላይ የውሀው ምንጭ ሆነን ሳለ፤ ከስምምነቶች ሁሉ እንድንርቅና ህጋዊ መሰረት እንዳይኖረን፤ በቤታችን ባይተዋር እንድንሆን ተደርገን ዓመታትን ተሻግረናል። ጎረቤቶቻችን ተባብረው ሲጥሉን የሚገባንን ሲነጥቁን ኖረዋል። ተጠራርተው ህልማችንን ሲያጨናግፉ ጉልበት አልባ ሆነን ስንከተላቸው ኖረናል፡፡” ዛሬ ግን ይላሉ አቶ ዛዲግ፤ “ዛሬ ግን ያ አለመቻላችን አብቅቶ፤ የታሪክ ጠረጴዛ በአፍጢሙ ተደፍቶ፤ የስምምነቱ አካል ብቻ ሳይሆን የስምምነቱ ጸሀፊዎች እኛ ሆነናል። የመደራደር አቅማችን ወሰኑን ተሻግሮ፤ የጥያቄው መልክና ቅርጽ ተቀይሮ፤ ከሳሽ ሳንሆን ተከሳሽ ሆነናል” ብለዋል።
የገንዘብ እጥረት፤ የፖለቲካ አለመረጋጋትና ዓለም አቀፍ ተቃውሞ ቆመን እንድንቀር የሚያደርጉ ስብራቶቻችን ቢሆኑም ተሻግረናቸዋል የሚሉት አቶ ዛዲግ፤ “ኢትዮጵያ ለጠላቶቿ ማስፈራሪያና ዛቻ ጆሮ ሳትሰጥ፤ የህዝቧን ሀብት፤ ዕውቀትና ጉልበት ተመክታ በትውልድ ቅብብሎሽ ያሰበችውን አሳክታለች። ታላቁ የህዳሴ ግድብ የመንግስትን ቅቡልነት ያረጋገጠ ማህተም፤ የተቋማት የመፈጸም አቅም ፊርማ፤ የህዝብ ተሳትፎ ማረጋገጫ ሰነድ ሆኖ ሊመረቅ ነጋሪት ተመቷል” ሲሉ ገልጸዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Friday, 01 August 2025 16:29
ከ84 ሺ በላይ መምህራንና የት/ቤት አመራሮች በ30 ዩኒቨርስቲዎች ስልጠና ሊጀምሩ ነው
• ዓምና ከ52 ሺ የሚበልጡ መምህራን ሰልጠነዋል
ከመጪው ሰኞ ሐምሌ 28 ቀን 2017 ጀምሮ ከ84 ሺሕ በላይ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች በ30 ዩኒቨርስቲዎች ስልጠና እንደሚወስዱ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስትሩ ለሁለተኛ ደረጃ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የክረምት ስልጠና ስኬታማነት፣ የዩኒቨርስቲ አመራሮች ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ አመራሮቹ ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
ይህንንም ስልጠና የሚሰጡ 30 ዩኒቨርስቲዎች፣ ሰልጣኝ መምህራንንና የትምህርት ቤት አመራሮችን በአግባቡ በመቀበልና በማሰልጠን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
አክለውም፤ ስልጠናው ለትምህርት ጥራት ወሳኝ በመሆኑ፤ ዩኒቨርስቲዎች መምህራኑና አመራሮቹ የተዘጋጀላቸውን የስልጠና ሞጁል መጨረሳቸውን፣ ስልጠናውንም በአግባቡ መከታተላቸውንና መመዘናቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡት መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች በሚያስተምሩት የትምህርት ዓይነት ላይ መሰረት ያደረገ ስልጠና ወስደው ከተመዘኑ በኋላ፤ የምስክር ወረቀት እንደሚሰጣቸው መገለጹን አሐዱ ከሚኒስቴሩ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ባለፈው ዓመት ከ52 ሺ የሚበልጡ የ2ኛ ደረጃ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የክረምት ስልጠና መውሰዳቸው ይታወሳል፡፡

Published in
ዜና
Tagged under

