Administrator

Administrator

         43 የመንግስት ተቃዋሚ ግብጻውያን በእድሜ ልክ እስራት ተቀጡ

       የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ፣ በአገሪቱ የድንበር ከተሞች የሚገኙ ተቋማትንና ፕሮጀክቶችን ከጥቃት ለመከላከል ታስቦ የተገነባውንና በመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ በግዙፍነቱ ቀዳሚው እንደሆነ የተነገረለትን አዲስ የጦር ሰፈር መርቀው መክፈታቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
የተለያዩ የአረብ አገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ተመርቆ የተከፈተው ይህ የጦር ሰፈር፣ ከአሌክሳንድሪያ በስተምዕራብ በማርሳ ማትሮ ግዛት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ በአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ኖጊብ ስም መሰየሙም ተነግሯል፡፡
የግብጽ መንግስት ታጣቂዎች ወደ ግዛቱ ሰርገው እንዳይገቡ ለመከላከል ሲል አገሪቱን ከሊቢያ ጋር በሚያዋስነው የድንበር አካባቢ ባራኒ የተባለ የጦር ሰፈር ማቋቋሙን በቅርቡ ማስታወቁንም ዘገባው አስታውሷል፡፡
በተያያዘ ዜና ደግሞ፣ በአገሪቱ የሚገኝ አንድ ፍርድ ቤት መንግስትን ተቃውመዋል ባላቸው 43 ዜጎች ላይ ባለፈው ማክሰኞ የዕድሜ ልክ እስራት ቅጣት ማስተላለፉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ በ2011 መጨረሻ መንግስትን ተቃውመው በመዲናይቱ ካይሮ አደባባይ በመውጣት ብጥብጥ ፈጥረዋል፣ አመጽ ቀስቅሰዋል፣ በጸጥታ ሃይሎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል በሚል የተከሰሱት ግለሰቦቹ፣ በወቅቱ በተፈጸመው ግጭት 17 ሰዎች ለህልፈተ ህይወት እንዲዳረጉና 2 ሺህ ያህል ሌሎች ግብጻውያን እንዲቆስሉ ሰበብ ሆነዋል መባሉን ዘገባው ገልጧል፡፡
ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹን በዕድሜ ልክ እስራት ከመቅጣቱ ባለፈም፣ በወቅቱ በህዝብ ተቋማት ላይ ለፈጸሙት የዝርፊያ ወንጀል በድምሩ ከ948 ሺህ ዶላር በላይ እንዲከፍሉ የገንዘብ ቅጣት እንደጣለባቸውም ዘገባው አመልክቷል፡፡ ሌሎች ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የተከሰሱ 9 ግብጻውያን በአስር አመት እስራት፣ አንድ ግለሰብ ደግሞ በአምስት አመት እስራት መቀጣቱንም ዘገባው አክሎ ገልጧል።

  ኳታር ባለፈው ወር በኤርትራና ጅቡቲ ድንበር ላይ አስፍራቸው የነበሩ ሰላም አስከባሪ ወታደሮቿን ማስወጣቷን ያስታወሰው አሶሼትድ ፕሬስ፣ ቻይና ይህንን ክፍተት ለመሙላት በአካባቢው የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ልታሰፍር እንደምትችል የአገሪቱ ከፍተኛ ዲፕሎማት ማስታወቃቸውን ዘግቧል፡፡
በአፍሪካ ህብረት የቻይና ከፍተኛ ዲፕሎማት ኩዋንግ ዌሊንን ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው፣ ቻይና ጥያቄው ከቀረበላት በሁለቱ አገራት መካከል ለአመታት የዘለቀውን የድንበር ይገባኛል ውዝግብ ለመፍታት የአደራዳሪነት ሚናን ለመጫወትም ዝግጁ ናት፡፡
ቻይና ከግዛቷ ውጭ ያቋቋመቺው የመጀመሪያው የጦር ሰፈር ወደሆነውና ጅቡቲ ውስጥ ወደሚገኘው የጦር ሰፈር በዚህ ወር መጀመሪያ በርከት ያሉ ወታደሮቿን መላኳን ያስታወሰው ዘገባው፣ ይህም አገሪቱ የኢኮኖሚ ፍላጎት በምታሳይባቸው አካባቢዎች በምታደርገው የጦር ሃይል መስፋፋት ውስጥ እንደ አንድ ቁልፍ እርምጃ ተደርጎ እንደሚወሰድም ዘገባው አስታውሷል፡፡
ቻይና ምንም እንኳን በሰላም ማስከበር መስክ የአጭር ጊዜ ልምድ ቢኖራትም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሰላም አስከባሪ  ወታደሮችን ከሚያሰማሩ አምስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላት መካከል አንዷ መሆኗን ያስታወሰው ዘገባው፣ እስካለፈው ሰኔ ወር ድረስ በተመድ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ያሰማራቻቸው ወታደሮች ቁጥር ከ2 ሺህ 500 በላይ መድረሱንም አመልክቷል፡፡

 አሜሪካ በኢራንና በሩስያ ላይ አዳዲስ ማዕቀቦችን ለመጣል እየተዘጋጀች ባለችበት ወቅት፣ የሁለቱ አገራት መሪዎችና ከፍተኛ ባለስልጣናት ማዕቀብ የምትጥይብን ከሆነ ምላሻችን የከፋ ነው ሲሉ አሜሪካን አስጠንቅቀዋል፡፡
አሶሼትድ ፕሬስ ከቴህራን እንደዘገበው፣ የአሜሪካ ኮንግረስ በኢራን የባለስቲክ ሚሳኤል ፕሮግራም ላይ በተሳተፉ ግለሰቦች ላይ ለመጣል የታሰበውን ህግ የሚያጸድቀው ከሆነ፣ አገራቸው የከፋ ምላሽ እንደምትሰጥ የኢራኑ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሩሃኒ ባለፈው ረቡዕ አስጠንቅቀዋል፡፡
ኢራን በባለስቲክ ሚሳኤል ፕሮግራሟ ላይ በሚሳተፉ ግለሰቦችና ከእነሱ ጋር የንግድ ግንኙነት ባለው ማንኛውም አካል ላይ የከፋ ቅጣትና ማዕቀብ ለመጣል በእንቅስቃሴ ላይ የምትገኘው አሜሪካ ያሰበቺውን የምታደርግ ከሆነ፣ አገራቸው ጥቅሟን ለማስከበር ስትል አፋጣኝ ምላሽ እንደምትሰጥ አስታውቀዋል፡፡ አሜሪካ በኢራን ላይ ለመጣል ባሰበቺው አዲሱ ማዕቀብ፣ በአገሪቱ የጦር ሃይል ላይ የሽብርተኝነት ማዕቀቦችን እስከመጣል እና የጦር መሳሪያ እገዳ እስከማድረግ የሚደርስ እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል መነገሩንም ዘገባው አመልክቷል፡፡
ሩስያ በበኩሏ፣ አሜሪካ ልትጥልባት ያሰበቺው አዲስ ማዕቀብ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የሻከረ ግንኙነት ወደ ከፋ ደረጃ ሊያሸጋግረው እንደሚችል ባለፈው ረቡዕ ማስጠንቀቋን ሮይተርስ ዘግቧል። የሩስያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጊ ራብኮቭ፣ አሜሪካ በሩስያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን ለመጣል እያደረገቺው የምትገኘው እንቅስቃሴ፣ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል የሚቻልበትን ዕድል የሚያጨልምና ግንኙነቱን ወደባሰ መሻከር የሚያመራ እንደሆነ ባለፈው ረቡዕ ከኢንተርፋክስ የዜና ወኪል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ መናገራቸውን ዘገባው አስታውቋል፡፡
የአሜሪካ የማዕቀብ ዕቅድ ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ የሩስያ መንግስት ጉዳዩን በጥልቀት በመመርመር፣ በፕሬዚዳንት ፑቲን በሚሰጥ ውሳኔ ምላሽ የሚሰጥ መሆኑንም የፕሬዚዳንቱ ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸው ተነግሯል፡፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ፣ በሁለቱ አገራት መካከል የነበረውን የሻከረ ግንኙነት ያሻሽሉታል የሚል ተስፋ የነበረ ቢሆንም፣ ሩስያ ባለፈው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጣልቃ ገብታለች በሚል የተፈጠረው አተካሮ ተስፋውን እንዳጨለመው ዘገባው አመልክቷል፡፡

 ‹‹ታላቁ ተቃርኖ›› የተሰኘ ፖለቲካዊ መፅሀፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡ ደራሲው ከቅርብ አመታት ወዲህ ታሪካዊ ልቦለድ ተብሎ በሚጠራው የስነ-ፅሁፍ ዘርፍ ተቀባይነት ያገኙትን ‹‹አውሮራ››፣ ‹‹የቀሳር እንባ›› እና ‹‹የሱፍ አበባ›› የተሰኙ በኢትዮ ኤርትራ፣ ጉዳይ፣ በኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማሪያምና በኢህአፓ ዋና ዋና መስራቾች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ታሪኮች ያስነበቡ ሲሆን የአሁኑ ስራቸው ከታሪክ ልቦለድ ዘውግ ወጣ ብሎ አገሪቱ የገባችበትን ወቅታዊ የፖለቲካ ምስቅልቅል፣ ከስር መሰረቱ የሚተነትን ነው ተብሏል፡፡ በ400 ገፆች የተቀነበበው መፅሀፉ፤ በ119 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

   የእውቋ ገጣሚ ረድኤት ተረፈ ወጋየሁ ‹‹አንድ ሐሙስ›› የተሰኘ የግጥም ስብስብ መፅሀፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ በአገር ፍቅር ዙሪያ የሚያጠነጥኑ 52 ግጥሞችን የያዘው መድበሉ በ108 ገፆች ተመጥኖ በ47 ብርና በ20 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡
ገጣሚዋ ከዚህ ቀደም ከሌሎች ገጣሚዎች ጋር ‹‹መስቀል አደባባይ›› የተሰኘ የግጥም መፅሀፍ በጋራ ያሳተመች ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሸገር ኤፍኤም የሚተላለፈው ‹‹አደረች አራዳ›› የሬዲዮ ሾው አዘጋጅ ናት፡፡ ገጣሚዋ በቅርቡ በብሔራዊ ቴአትር እየታየ በሚገኘው “ሲራኖ” የተሰኘ ትያትር ላይ እየተወነችም ትገኛለች፡፡

  ፀሀፊና ተርጓሚ መክብብ አበበ የታዋቂውን ሩሲያዊ ደራሲ ፊዮዶር ዶስቶቪስኪ 10 አጫጭር ታሪኮችን ተርጉሞ ‹‹የሚያቄለው ሰው ህልም›› በሚል ርዕስ ለንባብ አበቃ፡፡
መድበሉ ‹‹ትንሹ ልጅ››፣ የገና ዛፍና ሰርጉ››፣ ‹‹ቦቦክ››፣ ‹‹ዘጠኙ ደብዳቤዎች››፣ ‹‹ታማኙ ሌባ››፣ ‹‹ፈሪዋ ልብ››፣ ጨዋ መንፈስ፣ ‹‹ገበሬ ማሬይ›› እና ‹‹ፓልዘንኮከ›› የሚሉ ታሪኮችን አካትቷል፡፡
ተርጓሚው ከዚህ ቀደም ‹‹ሰውና ሀሳቡ›› እና ‹‹ህይወት በጠንቋዩ ቤት ውስጥ” የተሰኙ መፅሐፍትን ለንባብ ማብቃቱ የሚታወስ ሲሆን በቀጣይም የፊዮዶር ዶስቶቭስኪን ‹‹የሌላ ሰው ሚስት›› ወይም ‹‹አልጋ ስር የተደበቀው ባልና አዞው›› ሥራዎች ለመተርጎም በዝግጅት ላይ መሆኑም ተገልጿል፡፡ ‹‹የሚያቄለው ሰው ህልም›› በ204 ገፆች ተመጥኖ፣ በ71 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

 በደራሲ ስዩም ገብረ ሕይወት ተጽፎ በ1994 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ለንባብ የበቃውና በድጋሚ የታተመው “ሚክሎል - የመቻል ሚዛን” የረጅም ልቦለድ መጽሃፍ፣ ዛሬ ተሲያት ላይ በጁፒተር ሆቴል ተመርቆ በገበያ ላይ እንደሚውል  ደራሲው በተለይ ለአዲስ አድማስ ገልጧል፡፡
ወጣትና አንጋፋ ገጣሚያን ስራዎቻቸውን በሚያቀርቡበትና የተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች በተካተቱበት ፕሮግራም የሚመረቀው “ሚክሎል - የመቻል ሚዛን”፣ በደርግ መንግስት የመጨረሻ አመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተከስቶ በነበረው የፖለቲካ እንቅስቃሴና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የብላቴ የጦር ማሰልጠኛ ዘመቻ ዋዜማ ላይ መቼቱን በማድረግ፣ የተለያዩ አገራዊ ጉዳዮችን በፍልስፍና እየነቀሰ የሚተነትን መጽሃፍ ነው፡፡
መጽሃፉ ጠንካራና ፈታኝ ሀገራዊ ጉዳዮችን በሠመረ ኪናዊ ውበት የሚዳስስ፣ የተሻለ ሀገራዊና ግለሰባዊ የእድገት ጥያቄዎችን እያነሳ ልማዳዊውን የማንነት ገበና የሚጋፈጥ፣ ሀገራዊ ብልፅግናን ከተፈጥሮአዊ አቅም ጋር አስተሳስሮ የሚመረምር፣ ለአንባቢ እጅግ የነጠሩ ቁም ነገሮችን የሚያስጨብጥና የሚያነቃ እንደሆነ ያነጋገርናቸው የሥነጽሁፍ ባለሙያዎች መስክረዋል፡፡
በ395 ገጾች የተቀነበበው መጽሃፉ፣ በቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ አሳታሚነት በድጋሚ ታትሞ ለንባብ የበቃ ሲሆን፣ በተለያዩ የመጽሃፍት መደብሮችና በአዟሪዎች በ150 ብር የመሸጫ ዋጋ ለገበያ ቀርቦ እየተሸጠ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ወቅት ኑሮውን በእንግሊዝ አገር ያደረገው ደራሲ ስዩም ገብረ ሕይወት፣ የ“ሚክሎል - የመቻል ሚዛን” ቀጣይ ክፍል የሆነውና ከ15 አመታት በፊት የጻፈውን “የማቃት አንጀት” የረጅም ልቦለድ መጽሃፍ በቅርቡ ለንባብ ለማብቃት እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝም ለአዲስ አድማስ ገልጧል፡፡
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢንፎርሜሽንና ኮምፒውተር ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው ደራሲ ስዩም ገብረ ሕይወት፣ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያውን ቤተ መጽሃፍትና ኮምፒውተር ማዕከል በማቋቋምና በማስተማር ያገለገለ ሲሆን፣ በብሪቲሽ ካውንስል በፕሮጀክት ማናጀርነትና በቤተ መጽሃፍትና ኢንፎርሜሽን አገልግሎት ዋና ሥራ አስኪያጅነት ለሰባት አመታት ያህል ሰርቷል፡፡

 አንድ የሩሲያ ተረት እንዲህ ይላል፡-
ባልና ሚስት ዓሳ ሊያጠምዱ ወደ አንድ ሀይቅ ይወርዳሉ፡፡ ገና መንገድ ሳሉ፤
ሚስት፤
“የሚያዙት ዓሳዎች ግማሾቹ ለልጆቻችን ምግብ ይሆናሉ፡፡ ግማሾቹን ደግሞ ወደ ገበያ ወስደን እንሸጣቸውና፤ ሌሎቹ ኑሯችንን ማሟያ ገንዘብ ያመጣሉ፡፡” ትላለች
ባል፤
“እስቲ መጀመሪያ ዓሳዎቹ ይገኙ፡፡ ከዚያ ደግሞ መረባችን የሚይዘውን ብዛት እንይ፡፡ የዛሬ ዓሳዎች እኮ እንደ ድሮዎቹ ዓሳዎች በማንኛውም መረብ ውስጥ ተንደርድረው ጥልቅ አይሉም”
ሚስት፤
“ዓሳ ዓሳ ነው፤ ብርብራ ካየ ዘሎ ጥልቅ ማለቱ አይቀሬ ነው”
ባል፤
“አይምሰልሽ፤ እኛ ያለን የዱሮ መረብ ነው፡፡ ዓሳዎቹ የአሁን ጊዜ ናቸው፡፡ የዱሮ መረብ በቶሎ ይበጣጠሳል፡፡ ወይ መረቡ በአዲስ ክር መሰራት አለበት፤ አሊያም ሙሉ በሙሉ ተለውጦ አዲስ መሆን አለበት፡፡ እንጂ የዛሬን ዓሶች ችሎ አፍኖ አያስቀምጥም”
ሚስት፤
“ግዴለህም ባሌ፤ አታስብ፡፡ ሀይቁም ያው የዱሮው የምናውቀው ሀይቅ ነው፡፡ ዓሳዎቹም የዱሮዎቹ ዓሳዎች ናቸው፡፡ ድንገት ተነስተው ብልጥ ዓሳዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ እኛ ተጃጅለን፤ ቅልጥፍና አንሶን የማምለጥ እድል ካልሰጠናቸው ባንድ አፍታ እጃችን እናስገባቸዋለን”
ባል፤
“እስቲ ይቅናን! ወዳጄ”
ተያይዘው እሀይቁ ዳርቻ ደረሱ፡፡ መረቡን ዘረጉት፡፡ የተያዙት ግን በጣም ደቃቃ ደቃቃ ዓሳዎች ብቻ ናቸው፡፡
ሚስት፤ በጣም ገረማትና፤
“ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል፤ መረቡ ትናንሽ ዓሳዎችን ብቻ እየመረጠ ነው እንዴ የሚይዘው?” ስትል ባሏን ጠየቀችው፡፡
ባሏም፤
“ይሄውልሽ ጊዜው እንደዚህ ሆኗል፡፡ ትናንሾችን ዓሳዎች እኛ እንይዛቸዋለን፤ትላልቆቹ እርስ በርስ ይበላላሉ!!”
*       *      *
ዘመኑ እንደዚህ ነው! ትላልቆቹ ሌቦች አይነኩም፡፡ ትናንሾቹ ብቻ ይጠመዳሉ፡፡ ባለ ከፍተኛ ንግድና ሀብት ባለቤቶች የሚነካቸው የለም፡፡ ትናንሾቹ ጉልት ቸርቻሪዎች፣ ከገቢ ገማች እስከ ወንጀል መርማሪ ይፈራረቅባቸዋል፡፡ ይህንን ዕውነታ መለወጥ የትራንስፎርሜሽን ያህል ከባድ ነው፡፡ ምነው ቢሉ፣ ከባድ ከባድ፣ ንክኪ በሥሩ አለ፡፡ አብ ሲነካ ወልድ ይነካ ነው!
ስለሆነም የላይኞቹ ክፉኛ ይጮሀሉ!! የታችኞቹ ወንጀሉ የዓለም መጨረሻ እንደሆነ አድርገው ያወራሉ፤ ይጮሃሉ! ባለ ፎቆቹ፣ ባለ ቪላዎቹ፤ ባለ ብዙ ኤከር መሬት ባለቤቶቹ፤ ንፁሀን ሆነው ቁጭ ይላሉ! በየሸንጎውም ላይ ጨዋዎቹ እነዚህ ባለፀጎች ይሆኑና የክብር እንግዶች ተብለው ክብር ትሪቡን ውስጥ ይቀመጣሉ፡፡ አዳዲስ ተቋም ሲመረቅ መድረኩን ይሞላሉ፤ ግንባር ግንባር ቦታውን ያጣብባሉ! በደህና ጊዜ የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ እያሉ፣ የአንበሳውን ድርሻ ሲቀራመቱ የነበሩ ናቸው፡፡
በሌላ ወገን፤ ዝቅተኛው መደብ፣ ሱቁ ሲመዘበር፣ ያልሆነ ዋጋ ሲተመንበት፣ ሰሚ ያጣ ጩኸት ሲጮህና የአገር ያለህ፣ የመንግሥት ያለህ ሲል፤ “ስህተት ያለ ነገር ነው፤ ለቅሬታ ሰሚ አመልክት እንጂ ምን ታካብዳለህ” ይሆናል የምላሹ ዘይቤ! ሱቃቸውን ዘግተው የጠፉ፣ ዕቃቸውን ያሸሹ፣ ንብረት አናስገምትም ያሉት ዕውን ከግንዛቤ ማነስ ነውን? ግንዛቤ እንዲጨብጡ ተደርጎስ፣ ወደ ሰላማዊ ኑሮአቸው ተመልሰዋል ማለት ዕውን ነባራዊው ሀቅ ነውን? መሬትና ሰማይን ያነካካ ገመታ፣ የምስኪኑ ችርቻሮ ነጋዴ ደስታ ሊሆን ይችላልን? ግልፁ ጨዋታ ሌባው በወርቅ አልጋ፣ በእርግብ ላባ ላይ፣ ከዝሆን ጥርስ በተሰራ ፎቅ ውስጥ መኖሩ ነው! ማን ይንካው? የማይታረቁ ግጭቶች ተፋጠው ይገኛሉ!! የማይታረቁ ግጭቶችን ለመፍታት ቢያንስ ገጣሚና ፀሐፌ - ተውኔት መንግሥቱ ለማ፤ በባ‘ለ ካባና በባለዳባ’ ተውኔታቸው ውስጥ፡-
“ቀማኛን መቀማት፣ ከሌባ መስረቅ ……….. (‘ቅ’ ይጠብቃል)
ከማቅለል ከሆነ፣ የድሆችን ጭንቅ ………….. ( ‘ቅ’ ይጠብቃል)
በእኔ ቤት፣ ፅድቅ ነው፣ አንድ ሰው ይሙት …………(‘ሙት’ ይጠብቃል)
አንድ መቶ ሺ ሰው፣ ኪኖር በምፅዋት!!” …..…………(‘ዋት’ ይጠብቃል)
ያሉትን ማስታወስ ግድ ይሆናል!!
“እገሌ የእኛ ወገን ነው አይነካም”፤ “እገሌ የሌላ ወገን ነው፤ በለው!”፤ “እገሌ የማንም አይደለም ጊዜውን ይጠብቅ” …. “እነ እገሌን ተውዋቸው የኛ ናቸው” … “እነገሌን ግፏቸው ጠላት ናቸው” … ዓይነት አካሄድ፤ ቢያንስ ‹ከልጅ ልጅ ቢለዩ ዓመትም አይቆዩ› አለማወቅ ይሆናልና ልብና ልቦና ይስጠን!!
የሀገራችን አንድ ፈታኝ የሆነ ችግር፣ “ህዝቡ አያውቅም” የሚለው መላምታዊ ድንቁርና ነው፡፡ የነቃው፣ ህዝቡን በትግሉ ሲያግዝ የኖረው፣ በቀውጢው ሰዓት ታጋዮችን ከክልል ክልል ሲያሳልፍ የከረመው፤ ትልቅ አድናቆት ሲቸረው የኖረ ህዝብ፤ ድንገት ድንቁር ሊል ፈፅሞ አይችልም፡፡ እንደ ሁልጊዜው የግምት ስህተት አለ!! “ይሄን ስናሰላ፣ እንዲህ እንዲህ ያለ ችግር ነበረብን” የምንለውን እንኳ ዛሬ ስለተውነው፤ ከስህተት መታረም የሚለው ቁም - ነገር ጨርሶ ጠፍቷል፡፡ ከዚህ ይሰውረን!!
ትናንሾቹን ዓሳዎች አሳዶ የሚበላቸው አይጠፋም - አቅም የላቸውምና! ትላልቆቹ ግን እርስ በርስ እስኪበላሉ መጠበቅ ነው! ከዚህም ያውጣን!!

Saturday, 29 July 2017 11:30

የአዲስ አድማስ ማሳሰቢያ

    ያለወትሮአችን ማሳሰቢያ ለመፃፍ የተገደድነው አንዲት ስማችን የተጠቀሰባት ሃሰተኛ (‹ፎርጂድ› የበለጠ ይገልፀዋል) ደብዳቤ ሰሞኑን ዝግጅት ክፍላችን በመድረሷ ነው፡፡ ደብዳቤዋ የታለመችው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ ነው፡፡ ‹‹ስፖንሰር አድርጉን›› ትላለች፡፡ መታለም ብቻ ሳይሆን ለፋብሪካውም ደርሳለች፡፡ ‹‹አፍሪካ ፖስት ሚዲያ ሴንተር›› በሚል ማህተም የተከተበችው ይህች ‹‹ጉደኛ›› ደብዳቤ፤ በአጭሩ ‹‹አዲስ አድማስ ጋዜጣ የተመሰረተበትን 15ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ ሐምሌ 7 ቀን 2009 ዓ.ም ከአፍሪካ ፖስት ሚዲያ ሴንተር ጋር በመተባበር፣ በአዲስ አበባ ቲያትርና ባህል አዳራሽ በታላቅ ድምቀት ይከበራል›› በሚል መግቢያ ትጀምራለች፡፡ (ልብ በሉ! ‹‹አዲስ አድማስ›› 15ኛ ዓመቱን የዛሬ ሁለት ዓመት በብሔራዊ ቴአትር ‹‹በታላቅ ድምቀት›› አክብሯል፡፡
የሆነው ሆኖ፣ የ15ኛ ዓመት በዓላችንን እንዳከበርን ያላወቁት ወይም ያልሰሙት እነዚህ ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቀ ‹‹ ቁጭ በሉዎች››፤ (‹‹ሿሿ›› ነው የሚሏቸው?!) ዝግጅቱን በርካታ ድርጅቶች ስፖንሰር እንዳደረጉ ይጠቅሱና፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራም በዓይነትም በገንዘብም ስፖንሰር እንዲያደርጋቸው ይጠይቃሉ፡፡ (የአዲስ አድማስን 15ኛ ዓመት በዓል ማለት ነው፡፡) በርግጥ የቢራውም ሆነ የገንዘቡ መጠን አልተጠቀሰም በዚህ ቢያበቃ ጥሩ ነበር፡፡ ቢራ ፋብሪካው ስፖንሰር ሲያደርግ የሚያገኘውን ጥቅማ ጥቅም ይገልፃሉ- ‹‹ድርጅታችሁን በሚታተመው ተከታታይ ሳምታዊ የጋዜጣ ዕትም ላይ በብዙ ብር ከፍለው ስፖንሰር ካደረጉን ድርጅቶች እኩል የምናስተዋውቅ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን” በማለት፡፡
በነገራችሁ ላይ በዚህ የጋዜጣችንን ስም ለማጭበርበርያነት ጠቅሰው በፃፉት ደብዳቤ ላይ እውነተኛ ወይም ትክክለኛ የሚመስል ነገር አለ ከተባለ፣ ፅሁፉ የሰፈረበት ነጭ ወረቀት ብቻ ነው፡፡ በደብዳቤው ላይ የሰፈሩት ሁለት ስልክ ቁጥሮች ጨርሶ አይሰሩም። ‹‹አፍሪካ ፖስት ሚዲያ ሴንተር›› የሚባል ድርጅት በተጨባጭ መኖሩን ለማረጋገጥም አልቻልንም (ሊኖር እንደማይችል ገምቱ!)፡፡
በመጨረሻም፤ ለውድ የአዲስ አድማስ ቤተሰቦች፣ አንባቢያን፣ ድርጅቶች፣ የመንግስት ተቋማትና ሌሎችም ልንገልፅ የምንወደው፣ የአዲስ አድማስ ህጋዊ ማህተም፣ ሎጎ፣ በቂ አድራሻዎች … ወዘተ በቅጡ ሳትመለከቱ (ሳታጣሩ) ለደብዳቤዎች ጥያቄ ምላሽ እንዳትሰጡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኞችም ሆኑ ተወካዮች የድርጅቱ መታወቂያ እንዳላቸው እግረመንገዳችንን ልንገልፅ እንወዳለን፡፡ ራሳችንን እንጠብቅ!!

    በአውሮፓና በአሜሪካ ከ120 በላይ ስኬታማ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን በማቅረብ የሚታወቀው የሬጌው አቀንቃኝ ኦጄኬን ኦሊቨር ወይም በመድረክ ስሙ “ፕሮቶጄ” ዛሬ ምሽት በላፍቶ ሞል ያቀነቅናል። “The Indignation” ተብሎ በሚጠራውና በሰባት ታዋቂ የሙዚቃ ተጫዋች የተደራጀው ሙሉ ባንዱ ታጅቦ የሚያቀነቅነው  የ33 ዓመ ከታወጀ 10 ወር ገደማ ያስቆጠረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከ5 ቀን በኋላ ይነሳ ይቀጥል የሚታወቅ ሲሆን  ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ፤የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተነሳ፣ ሐምሌ 30 እና ነሐሴ 7 ቀን 2009 ዓ.ም፣ በአዲስ አበባ ህዝባዊ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት ማቀዱን አስታውቋል፡፡
ፓርቲው ሰሞኑን ባወጣው ወቅታዊ የአቋም መግለጫው፤አስር ወራትን ያስቆጠረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የማብቂያው ጊዜ ከ5 ቀን በኋላ፣ መሆኑን በመጠቆም፣ አዋጁ ለተጨማሪ ጊዜያት እንዳይራዘም መንግስትን ጠይቋል፡፡ አዋጁ ተጥሎ በቆየባቸው ጊዜያት፤ “የዜጎችን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የጣሰ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ያጠበበ፣ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እንዲያሽቆለቁል ያደረገና የህዝብን ማህበራዊ መስተጋብሮች የገታ ነበር” ያለው ሰማያዊ፤ “መንግስት ሀገሪቱን አረጋግቻለሁ ስላለ አዋጁን ማራዘም አያስፈልግም፤ ሊነሳ ይገባዋል” ብሏል፡፡ በቅርቡ በሚኒስትሮች ም/ቤት ተወስኖ፣ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የቀረበው የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ያለው ልዩ ጥቅም ረቂቅ አዋጅ፣ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ህዝብ ሳይመክርበት መውጣቱን ፓርቲው ተችቷል፡፡ የግብር አጣጣል ስርዓቱም የዜጎችን ገቢ ያገናዘበ እንዲሆን የጠየቀው ፓርቲው፤ በአጠቃላይ ህዝቡ በአግባቡ ሳይመክርባቸው እየወጡ ያሉ አዋጆች፣ በዜጎች ላይ መደናገጥ እየፈጠሩ በመሆኑ ሊታረሙ  ይገባል ሲል አሳስቧል።
“ሰማያዊ” የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊነሳ ይችላል በሚል መተማመን፣ ሐምሌ 30፣ ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው የመብራት ሃይል አዳራሽ፣ ህዝባዊ ስብሰባ እንዲሁም ነሐሴ 7፣ መነሻውን ሚኒልክ አደባባይ፣መዳረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ፣ ሰላማዊ ሠልፍ ለመጥራት ማቀዱን አስታውቋል፡፡ የስብሰባውም ሆነ የሰልፉ አጀንዳዎች፣ በዋናነት እየወጡ ባሉ አዋጆች ላይ እንደሚያተኩር ለአዲስ አድማስ ያስረዱት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አበበ አካሉ፤ሰልፉም ሆነ ስብሰባው የታቀደው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሊነሣ ይችላል በሚል ግምት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ቱ ፕሮቶጄ፤ ትላንት ከቀኑ 8፡00 ላይ በአምባሳደር ሆቴል ከኮንሰርቱ አዘጋጅ EML ኤቨንት ኦርጋናይዘርስ ጋር በጋራ በሰጠው መግለጫ፤ የዛሬው የላፍቶ ሞል ኮንሰርቱ በአፍሪካ የመጀመሪያው እንደሆነ ገልጿል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቱ በፊት ጣሊያን፣ ስዊድን፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይና ስፔይን ትልልቅ ኮንሰርቶችን እንዳቀረበና እዚህ ያለውን ስራ ሲጨርስም ወደ አውሮፓ ተመልሶ ስራውን እንደሚያቀርብ ተናግሯል፡፡
ዘፋኝ ባይሆን ኖሮ ሯጭ ይሆን እንደነበር በመግለጫው የጠቆመው ዘፋኙ፤ አትሌት ሃይሌ ገ/ሥላሴን ጨምሮ ብዙ የኢትዮጵያ አትሌቶችን በስም ጭምር እንደሚያውቅ የተናገረ ሲሆን “አትሌት ጥሩነሽ ዲባባን ከልቤ አደንቃለሁ” ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ሰሞኑን ለራስ ተፈሪያን የትውልደ ኢትዮጵያዊነት መብትና ዕውቅና መስጠቱን በተመለከተ የተጠየቀው ዘፋኙ፡-
“በጣም ትልቅና ታላቅ እድል ነው፡፡ እኛ ወደ ኢትዮጵያ መጥተን መኖር የምንፈልገው ለአገሪቷ ሸክም ለመሆን አይደለም፡፡ አላማ አለን፤ ራዕይ አለን፡፡ ጓዛችንን ጠቅልለን ስንመጣ ከእውቀት፣ ከሰፊ ልምድና ሙያ ጋር ነው፡፡ ኢትዮጵያ መጥተን ልንዝናና ወይም ሳንሰራ ተቀምጠን ለመኖር አይደለም፡፡ ማንም ራስ ተፈሪያን ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ሲያስብ፣ የራሱን ሀሳብ ይዞ ነው፡፡ ያንን ሀሳብ የሚፈፅመውም ኢትዮጵያን ለመጥቀም ነው” ሲል መልሷል፡፡ከዚህ በፊት ይከሰት የነበረውን ትርምስና ጭንቅንቅ ለማስቀረት ሲባል ተጨማሪ ባሮች በላፍቶ ሞል መዘጋጀታቸውን የጠቆሙት አቶ ኢዩኤል፤ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ተመልካቾች ወደ አዳራሹ መግባት ይጀምራሉ ብለዋል፡፡ ኮንሰርቱ ቀድመው ትኬት ለገዙ 300 ብር፣ በዕለቱ ለሚገዙ በመደበኛው 500 ብር፣ በቪአይፒ 700 ብር የመግቢያ ዋጋ ተተምኖለታል፡፡