
Administrator
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ከፈተ
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለደንበኞቹ የሚሰጠውን ዘርፈ ብዙ የባንክ አገልግሎት ዘመኑን የዋጀ እንዲሁም ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ የሚረዳውን በአይነቱ ልዩ የሆነ የዲጅታል ባንኪንግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ ገልፀዋል፡፡ ይህ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል የ24 ሰዓት የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዶ/ር ተስፋዬ እንደገለፁት ይህ የዲጂታል ባንኪንግ ማዕከል የባንክ ስራን የሚያቀላጥፉ ቴክኖሎጂዎችን ስራ ላይ በማዋል እንዲሁም ብቃት ያለው የሰው ኃብትን በመፍጠር ባንኩ ከምንጊዜውም በላይ ተወዳዳሪ እንዲሆን ከማድረጉም ባሻገር፣ የባለአክሲዮኖችን ጥቅም ከፍ በማድረግ የሀገርን ኢኮኖሚ የመደገፍ ስራውን በተሻለ መልኩ ለማስቀጠል የራሱን ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል ፡፡
የባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ ማዕከል ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል የባንክ ሂሳብ መክፈት፣ ገንዘብ ገቢና ወጪ ማድረግ፣ ቀሪ ሂሳብና የሂሳብ መግለጫ ማሳየት፣ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን መመንዘር፣ የተለያዩ ክፍያዎችን መፈፀም፣ ያለ ኤቲኤም ካርድ አገልግሎት ማግኘት፣ ቼክ መመንዘርና ገቢ ማድረግን ጨምሮ ደንበኞች የኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት መጠቀም በሚፈልጉበት ወቅት በማዕከሉ በመገኘት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጁ ታብሌቶች መጠቀም ይችላሉ፡፡
በዚህ ብቻ ሳይወሰን ማዕከሉ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ክፍል ያለው ሲሆን ተቀዳሚ (corporate) ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው የቪዲዮ ባንኪንግ አገልግሎት ማገኝት የሚያስችላቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተለይም በአዲስ አስተሳሰብ፣ አቀራረብና ብራንድ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ እጅግ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ሥራ አስፈፃሚው በዘንድሮው አመትም ከታክስ በፊት 757.6 ሚሊዮን ብር በማትረፍ በከፍተኛ የእድገት ግስጋሴ ላይ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
ባንኩ ይህን ውጤት ማሳካት የቻለው ባሳለፈው አመት በቅርንጫፍ ማስፋፋት፣ በቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃብት ልማትና በወጪ አስተዳደር ሥርዓት ላይ በሰራው ዘርፈ ብዙ ውጤታማ ሥራዎች መሆኑ ተገልጧል፡፡ ባንኩ በመላው ሃገሪቱ ተደራሽነቱን ለማስፋት በሰራው ስራ የቅርንጫፍ ብዛቱን 238 ያደረሰ ሲሆን በአሁን ሰአትም ከ 1.7 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉት አሳውቋል፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ፤ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የባንክ ካፒታል ዕድገት ዝቅተኛ ጣሪያ በቀረው ጊዜ ውስጥ እንደሚያሳካ የገለፁት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ፤ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተረባርበው በጋራና በላቀ ቁርጠኝነት ለጋራ ሥኬት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ባንኩ የገበያውን ተለዋዋጭነት በመረዳትና በዛው መሰረት የሚንቀሳቀስ የስራ አመራር በመገንባት እንዲሁም ሀብት ለማሰባሰብ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ የተቀማጭ ሂሳቡን ከ 20.6 ቢሊዮን ብር በላይ ያደረሰ ሲሆን፤ የባንኩ ጠቅላላ ሃብት ደግሞ ከ 26.6 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱ ታውቋል ፡፡
በዚህ ብቻ ሳይወሰን ባንካችን የያዘውን የዕድገትና የሥኬት ጉዞ በማስቀጠል ባለፈው አመት በግል ባንኮች ዘርፍ ባስመዘገበው የላቀ አፈፃፀም የአቢሲንያ አዋርድ የ2016 ዓ.ም የወርቅ ደረጃ የኢንደስትሪ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ባንኩ ‹‹ለጋራ ስኬታችን›› የሚለውን መሪ ቃል በተግባር መሬት ላይ በማውረድና ማህበራ ኃላፊነቱን በመወጣት በአካባቢ ጥበቃ ፤ በማህበራዊ ደህንነት፤ በሰብዓዊ እርዳታና በልማት ስራዎች አሻራውን ያሳረፈ ስኬታማ ባንክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሜክሲኮ አካባቢ ለዋና መ/ቤት ግንባታ በተረከበው 5,550 ካ.ሜ ቦታ ላይ የወደፊት የዋና መ/ቤት ህንፃ ለመገንባት በሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ እየሰራ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡
የህንድ የልዑካን ቡድን ኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታልን ጎበኘ
የአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
“ሺ ጊዜ እንዳፈቅር” የግጥም መድበል አርብ ይመረቃል
በገጣሚት መሠረት አዛገ “ሺ ጊዜ እንዳፈቅር” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የግጥም መድበል፣ ከነገ ወዲያ አርብ 4 ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት፣ አንጋፋ የኪነጥበብ ሰዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የሥነጽሑፍ ቤተሰቦች በተገኙበት እንደሚመረቅ ተገለጸ፡፡
በምረቃው ሥነስርዓት ላይ ጸሐፌ ተውኔትና ገጣሚ አያልነህ ሙላቱ፣ ጸሐፌ ተውኔትና ገጣሚ ሥዩም ተፈራ፣ ደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላ፣ ደራሲና መምህር ኃ/መለኮት መዋዕል፣ መምህር የሻው ተሰማ (የኮተቤው) እና ወጣት ገጣሚያን ሥራቸውን ያቀርባሉ፡፡
ገጣሚ መሠረት አዛገ፣ የ”መሠረት የበጎ አድራጎት ድርጅት” መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ስትሆን፣ ላለፉት 14 ዓመታት በህጻናትና በእናቶች ድጋፍና እገዛ ላይ በሠራቻቸው ሥራዎች በርካታ ሽልማቶችን ከሀገር ውስጥና ከተለያዩ የውጪ ሀገራት እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተቋማት ማግኘት የቻለች እንስት ናት፡፡
የ25 ዓመት የሃሳብና የዕውቀት ጉዞ!!
የመጀመሪያው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ታትሞ ለንባብ የበቃው ታህሳስ 29 ቀን 1992 ዓ.ም ነበር - የዛሬ 25 ዓመት በዕለተ ቅዳሜ፡፡ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ያለ አንድ ቅዳሜ በስተቀር ጋዜጣው ያልታተመበት ጊዜ የለም፡፡ ያም ቢሆን የተከሰተው በ97 ምርጫ ማግስት በተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስ ሳቢያ ነበር፡፡
የዛሬ 20 ዓመት፣ የአዲስ አድማስ ጠንሳሽ፣ መሥራችና ባለቤት አሰፋ ጎሳዬ (አሴ) በድንገተኛ ህመም ህይወቱ ባለፈበት ወቅት እንኳን ጋዜጣው ሳይታተም አልቀረም፡፡ ረቡዕ ከቀብር በኋላ ቢሮ ገብተን የቅዳሜውን ጋዜጣ ስናዘጋጅ ነበር፡፡ ከሃዘናችን ጋር እየታገልንም ቢሆን የቅዳሜውን ሳምንታዊ ጋዜጣ በጉጉት ለሚጠብቁን ውድ አንባቢያን አድርሰናል፡፡ በዚህም ኩራትና ክብር ይሰማናል፡፡ የጋዜጣው መሥራች አሰፋ ጎሳዬም ቢሆን፣ ከምንም በፊት ቅድሚያና ትኩረት የሚሰጠው ለአንባቢያን ነበርና፡፡
እነሆ አዲስ አድማስ ከዚያም በኋላ ሁለት አሰርት ዓመታትን አስቆጥራ፣ በብዙ ውጣ ውረዶችና ተግዳሮቶች አልፍ፣ እነሆ ለ25ኛ ዓመቷ በቅታለች፡፡ ኮረኮንች በበዛበት የአገራችን የግል ፕሬስ፣ ሩብ ክፍለዘመን ቀላል ዕድሜ አይደለም፡፡ ረዥም ዕድሜ ነው፡፡ ትልቅ ስኬትም ነው ማለት ያስደፍራል፡፡
ለዚህ የደረስነው ግን በውድ አንባቢያን ገንቢ አስተያየትና ድጋፍ ነው፡፡ ስለዚህም በዚህ አጋጣሚ ልባዊ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን፡፡ ለአዲስ አድማስ ህልውናና በስኬት መቀጠል ከእኛ ከአዘጋጆቹ እኩል የሚጨነቁና የሚጠበቡት የረዥም ጊዜ ጽሁፍ አቅራቢዎችም ሌሎቹ ትልቅ ምስጋና የምንቸራቸው ባለውለታዎች ናቸው፡፡
ማስታወቂያቸውን በጋዜጣችን ላይ የሚያወጡ የንግድ ድርጅቶችና የመንግሥት ተቋማትም ሁነኛ አጋሮቻችን ናቸውና ከልብ ልናመሰግናቸው እንወዳለን፡፡
መጪው ጊዜም ነጻ ሃሳብ በነጻነት የሚንሸራሸርበት፣ ዕውቀትና ሥልጡንነት የሚያብብበት፣ የንባብ ባህል የሚዳብርበት እንዲሆን እንመኛለን፤ ለዚያም በትጋት መሥራታችንን እንቀጥላለን፡፡
እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!
የ25 ዓመት የሃሳብና የዕውቀት ጉዞ!!
የመጀመሪያው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ታትሞ ለንባብ የበቃው ታህሳስ 29 ቀን 1992 ዓ.ም ነበር - የዛሬ 25 ዓመት በዕለተ ቅዳሜ፡፡ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ያለ አንድ ቅዳሜ በስተቀር ጋዜጣው ያልታተመበት ጊዜ የለም፡፡ ያም ቢሆን የተከሰተው በ97 ምርጫ ማግስት በተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስ ሳቢያ ነበር፡፡
የዛሬ 20 ዓመት፣ የአዲስ አድማስ ጠንሳሽ፣ መሥራችና ባለቤት አሰፋ ጎሳዬ (አሴ) በድንገተኛ ህመም ህይወቱ ባለፈበት ወቅት እንኳን ጋዜጣው ሳይታተም አልቀረም፡፡ ረቡዕ ከቀብር በኋላ ቢሮ ገብተን የቅዳሜውን ጋዜጣ ስናዘጋጅ ነበር፡፡ ከሃዘናችን ጋር እየታገልንም ቢሆን የቅዳሜውን ሳምንታዊ ጋዜጣ በጉጉት ለሚጠብቁን ውድ አንባቢያን አድርሰናል፡፡ በዚህም ኩራትና ክብር ይሰማናል፡፡ የጋዜጣው መሥራች አሰፋ ጎሳዬም ቢሆን፣ ከምንም በፊት ቅድሚያና ትኩረት የሚሰጠው ለአንባቢያን ነበርና፡፡
እነሆ አዲስ አድማስ ከዚያም በኋላ ሁለት አሰርት ዓመታትን አስቆጥራ፣ በብዙ ውጣ ውረዶችና ተግዳሮቶች አልፍ፣ እነሆ ለ25ኛ ዓመቷ በቅታለች፡፡ ኮረኮንች በበዛበት የአገራችን የግል ፕሬስ፣ ሩብ ክፍለዘመን ቀላል ዕድሜ አይደለም፡፡ ረዥም ዕድሜ ነው፡፡ ትልቅ ስኬትም ነው ማለት ያስደፍራል፡፡
ለዚህ የደረስነው ግን በውድ አንባቢያን ገንቢ አስተያየትና ድጋፍ ነው፡፡ ስለዚህም በዚህ አጋጣሚ ልባዊ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን፡፡ ለአዲስ አድማስ ህልውናና በስኬት መቀጠል ከእኛ ከአዘጋጆቹ እኩል የሚጨነቁና የሚጠበቡት የረዥም ጊዜ ጽሁፍ አቅራቢዎችም ሌሎቹ ትልቅ ምስጋና የምንቸራቸው ባለውለታዎች ናቸው፡፡
ማስታወቂያቸውን በጋዜጣችን ላይ የሚያወጡ የንግድ ድርጅቶችና የመንግሥት ተቋማትም ሁነኛ አጋሮቻችን ናቸውና ከልብ ልናመሰግናቸው እንወዳለን፡፡
መጪው ጊዜም ነጻ ሃሳብ በነጻነት የሚንሸራሸርበት፣ ዕውቀትና ሥልጡንነት የሚያብብበት፣ የንባብ ባህል የሚዳብርበት እንዲሆን እንመኛለን፤ ለዚያም በትጋት መሥራታችንን እንቀጥላለን፡፡
እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!
ቅድመ ታሪክ
ቅድመ ታሪክ
ማግባት ምፈልገው
አሪፍ ገንዘብ ያለው
ምርጥ ቪላ ያለው
ሐብታም ነጋዴ ነው ማለትሽ መልካም ነው።
በተዘዋዋሪ
እንደዚህ ዓይነት ሐሳብ
ሊፈጠር “ሚችለው ከቆንጆ ሴት ላይ ነው .....
ይህ ማለት ምንድ ነው?....
እንዲህ ዓይነት ሐሳብ በብዛት ሚሰማው
በየቡና ቤት ነው።
ስለዚህ .....
በዛም አለ በዚህ
አንቺም በውበትሽ የምትፈልጊው
የቡና ቤቷም ሴት የምትፈልገው
ቪላና ገንዘብ ነው።
ታዲያ በዚህ አገር - የፍቅር ማደርያው የትኛው ልብ ነው?
(ከኤፍሬም ሥዩም፤ “ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር” ከተሰኘው መድበል)
****
ጭር ያለውን ሰፊ ሜዳ የመረጥኩት፣
ለመሮጥ ሳይሆን ለዕረፍት፣
በኑሮ ላይ የሸፈትኩት፣
ራሴ መንፈስ ውስጥ ለመተኛት፡፡
ከእንግዲህ---፤ ባዶ አዳራሽ ውስጥ ቦታ ስትመርጪ.
በድካም ሰዓት ጥግ ስታጪ፣
አስታውሺኝ፣
ጥጉ እኔ ነኝ፡፡
ያልተቀመጥሽበትም ወንበር፣
በሃዘን ሰዓት ትንሽ ፈገግታ ስትሰሚ፣
በጨለማ ውስጥ የሚያጠራጥር ቅርጽ
ስታይ፣
አስታውሽኝ፣
ትንሷ ፈገግታ እኔ ነኝ፡፡
የተጠራጠርሽውም ነገር፣
ከዕለታት አንድ ቀን ምን አልባትም ሌላ ቀን፣
እታይሽ ይሆናል በጨለማው፣
እሞቅሻለሁም በሚበርደው፡፡
(ከሰዓሊ መስፍን ሀብተ ማርያም)
የፊልም ማሳያ ዝግጅት ሃገር ፍቅር ቲያትር
የመዲናዋ የገበያ ማዕከላት ፋይዳ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመዲናዋ የሚስተዋለውን የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስና ገበያውን ለማረጋጋት በማለም፣ በተለያዩ አካባቢዎች የገበያ ማዕከላትን አስገንብቶ ወደ ሥራ ማስገባቱ ይታወቃል፡፡ በከተማዋ አምስቱም መግቢያ በሮች ላይ የተገነቡት እነዚህ ዘመናዊ የገበያ ማዕከላት፤ ለማሕበረሰቡ የግብርና ምርቶችንና አትክልትና ፍራፍሬዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡
በእነዚህ ማዕከላት ነጋዴዎች ምርቶችን ከህገ ወጥ ደላሎች ውጭ፣ ከገበሬዎች በቀጥታ የሚረከቡ ሲሆን፤ ጥራት ያላቸው የግብርና ምርቶችን ከመደበኛ ገበያዎች ከ15 – 20 በመቶ ባነሰ ዋጋ በማቅረብ ማሕበረሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ በሁሉም የመንግሥት የገበያ ማዕከላት የሚሸጡ ምርቶችን የዋጋ ተመን የሚያወጣው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ሲሆን፤ የአንድ ሳምንት የዋጋ ተመን ለማውጣት ቢሮው በየሳምንቱ ጥናት በማድረግ፣ ነጋዴዎች የሚሸጡበትን ዋጋ ይተምናል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ በመዲናዋ ከገነባቸውና ለአገልግሎት ክፍት ካደረጋቸው የገበያ ማዕከላት መካከል የለሚ ኩራ ሁለገብ የግብርና ምርቶች መገበያያ ማዕከል ተጠቃሽ ነዉ፡፡ በዚህ ሁለገብ የገበያ ማዕከል ተገኝተን የግብርና ምርቶችን ሲገበያዩ ያገኘናቸው ሸማቾች፣ ማዕከሉ ለነዋሪዎች እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ አስመልክተው አስተያየታቸውን አጋርተውናል፡፡
ወ/ሮ ፋጡማ መሀመድን በማዕከሉ ግብይት ሲፈጽሙ ነው ያገኘናቸው፡፡ በማእከሉ የተለያዩ የግብርና ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በመቅረባቸው ኑሮ በማረጋጋት ረገድ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይም የተለያዩ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች እንዲሁም ዱቄት ለተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ መቅረቡን ጠቁመዋል፡፡ ማእከሉ የግብርና ምርቶችን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ በማድረግ የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑንና የዋጋው ሁኔታ ከውጭ ከሚሸጠው ጋር ሲነጻጻር ማእከሉ የተሻለ አማራጭ መሆኑን ጭምር ገልጸዋል፡፡
አቶ ብርሃኑ ወልዴ በማእከሉ ሲገበያዩ ያገኘናቸው ሌላኛው ተጠቃሚ ናቸው። ጥቅል ጎመን፣ ካሮት፣ ቲማቲም፣ አቮካዶ፣ ሽንኩርት፣ ድንችና ሌሎች አትክልቶች በማዕከሉ መቅረቡን ጠቁመው፤ ዋጋውም ተመጣጣኝ መሆኑን ተናግረዋል። ሆኖም ወደ ማእከሉ የሚገቡ ምርቶች በብዛት እንዲቀርቡና የምርት ጥራትም ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል፡፡ በአካባቢያቸው ማእከሉ ተገንብቶ አገልግሎት መስጠቱ፣ የግብርና ምርት በአነስተኛ ዋጋ በማቅረብ የነዋሪዎችን ኑሮ በማረጋጋት፣ በግብይት ይጠፋ የነበረውን ጊዜ በመቆጠብ፤ ካላስፈላጊ ወጪ ማዕከሉ እንደታደጋቸው ተናግረዋል፡፡
በማእከሉ ምርት እያቀረቡ ከሚገኙት የግብርና ምርት አቅራቢዎች መካከል አቶ አለማየሁ አሮጎ ይገኝበታል፡፡ በቀጥታ ምርት በማቅረብ ሽያጭ ሲያከናውን ያገኘነው ሲሆን፤ በዋናነት ሽንኩርት፣ ድንች፣ ቲማቲም እንዲሁም እንደ ማንጎ፣ ፓፓዬና ሃብሃብ የመሳሰሉ ፍራፍሬዎችን በማምጣት ከመደበኛው ገበያ ከ15 እስከ 20 በመቶ የዋጋ ቅናሽ በማድረግ፣ ለሸማቹ ማሕበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረቡ ገበያ እያረጋጉ መሆኑን ገልጿል። የምርት አቅርቦት በተወሰነ መጠን ከእርሻው እንደሚያገኝ የገለጸው አቶ አለማየሁ፤ የተቀሩትን ከሌሎች አምራቾች በመውሰድ ለሸማቾቹ እንደሚያቀርብ ይናገራል፡፡
የገበያ ማዕከሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አበራ፣ በዚህ ማዕከል በዋናነት አትክልትና ፍራፍሬ፣ የሰብል ምርትና ጥራጥሬ፣ የኢንዱስትሪ ምርቶች እንዲሁም የእንስሳት ተዋጽኦና ውጤቶች በቅናሽና በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ሌላው የቃኘነው የአቃቂ ቃሊቲ የገበያ ማዕከልን ነው፡፡ የማዕከሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሳሙዔል ጫኔ፤ የገበያ ማዕከሉ እንቅስቃሴ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መምጣቱን ይገልፃሉ፤ በማእከሉ የግብርና ምርቶች ከ15 እስከ 20 በመቶ የዋጋ ቅናሽ ተደርጎባቸው ስለሚሸጡ፣ ሸማቾች ከመደበኛ ገበያዎች ይልቅ ማዕከሉን እንደሚመርጡና ራቅ ካሉ አካባቢዎች ጭምር እየመጡ እንደሚሸምቱ ገልጸዋል።
የአካባቢው ነዋሪ በማዕከሉ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆኑን የሚናገሩት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ ለሸማቾች ትልቅ ጥቅም በመፍጠሩ የሚፈልጉትን ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ መርጠው በአቅራቢያቸው መሸመት ችለዋል ብለዋል፡፡
ሜሮን ሰራዊት በአቃቂ ቃሊቲ የገበያ ማዕከል የእህል ምርቶችን የሚያቀርብ ድርጅት በሥራ አስኪያጅነት ትመራለች፡፡ ገበያው ጥሩ ነው የምትለው ሜሮን፤ ሆኖም ሰው በሚፈለገው ደረጃ አያውቀውም፣ የማስተዋወቅ ሥራ ቢሰራልን የበለጠ ገበያ ይመጣል ብዬ አስባለሁ ትላለች፡፡ የቦታው አለመታወቅ ነው እንጂ ቢታወቅ፣ ሸማቹ ህብረተሰብ በደንብ ተጠቃሚ ይሆናል ብላ እንደምታምን ትናገራለች፡፡
የሚያቀርቡት ምርቶች ዋጋ ከመደበኛው ገበያ ዋጋ ከፍተኛ ልዩነት እንዳለውም ትገልጻለች፡፡ “እኛ አምራች ገበሬ ነን፤ በቀጥታ ነው ምርት የምናስገባው” የምትለው ሜሮን፤ “ውጪ ላይ ማኛ ጤፍ የሚሸጠው 140 እና 145 ብር ነው፤ እኛ ጋ ግን 118 እና 120 ብር ነው የሚሸጠው” በማለት ለአብነት ጠቅሳለች፡፡
በመለጠቅ የቃኘነው የኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የገበያ ማዕከልን ሲሆን፤ ማዕከሉ የተለያዩ የገበያ እንቅስቃሴዎች እንደሚታይበት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወ/ት ትዕግስት አይችሉህም ጠቁመዋል፡፡ በገበያ ማዕከሉ የተሻለ የገበያ እንቅስቃሴ የሚታይባቸው የእህል ምርት ሽያጭ መሆናቸውን የገለጹት ምክትል ሥራ አስኪያጇ፤ ምርት በቀጥታ ከገበሬዎች እንደሚያስመጡም ይናገራሉ፡፡
በአትክልትና ፍራፍሬ አቅራቢዎች በኩል የሽንኩርት ምርት በቀጥታ ተረክበው የሚያቀርቡ ነጋዴዎች ወደ ማዕከሉ መግባታቸውንና ቲማቲምና ሙዝ በተወሰነ መልኩ እየገቡ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
ከአርባ ምንጭ ሙዝና ፍራፍሬ እያስመጣ ለኮልፌ የገበያ ማዕከል የሚያቀርበው አቶ ግርማ ማላ፤ የገበያው እንቅስቃሴ ጥሩ መሆኑንና ዓለም ባንክ አካባቢ ከሚገኘው መጋዘኑ ሙዝ እያመጣ በመሸጥ ገበያውን እያለማመደ መሆኑን ይገልጻል፡፡ “እስካሁን ባለውም ጥሩ ተስፋ አለው ብዬ እገምታለሁ።” ይላል፡፡
ግርማ አክሎም ሲናገር፤ ”የገበያ ማዕከሉ የሚገኝበት ቦታ ማሕበረሰቡ እየለመደው አይደለም። በመንገድ ችግር ምክንያት ሊሆን ይችላል። እኛ ግን እያስለመድነው እንገኛለን። ወደፊት ያለውን ውስን ችግር በመፍታት የተሻለ ሁኔታ እንደሚፈጠር ተስፋ አለን” ብሏል፡፡
ዮሐንስ ቱፋ ደግሞ በኮልፌ የገበያ ማዕል የበቆሎ ዱቄት፣ ቂንጬ ፣ጤፍና ሩዝ አቅራቢ ነው፡፡ የፋብሪካው ወኪል በመሆንም ምርት እያከፋፈለ እንደሚገኝ ነው የገለጸው። በኮልፌ የገበያ ማዕከል ሥራ የጀመርነው በቅርቡ ነው የሚለው ዮሐንስ፤ ከዚህ ቀደም እህል በረንዳ ይሰሩ እንደነበርና አሁን በማዕከሉ ምርቶቻቸውን እያከፋፈሉ በመሆኑ የገበያ እንቅስቃሴው የተሻለ ነው ብሎ ያምናል፡፡ “ጤፍን ጨምሮ ሁሉም አይነት የእህል ምርት ስለሚገኝ፣ ከዚህ ቀደም ወደ መሳለሚያ በመሄድ ለሚገዛ ሸማች፣ አሁን በአቅራቢያው ለመግዛት የሚያስችል ሁኔታ ተመቻችቶለታል፤ ስለዚህም እዚህ መጥቶ እንዲሸምት እያስተዋወቅን ነው” ይላል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ፣ “በመዲናዋ የገበያ ማዕከላት የተከፈቱበት መሰረታዊ ዓላማ፣ የነዋሪውን የኑሮ ውድነት ጫና ለማቃለል እንዲሁም ሸማቹንና አምራቹን በማገናኘት ከደላላ ሰንሰለት ውጪ አርሶአደሩ ምርቱን ወደ ሱቅ በማምጣት፣ ሸማቹ በቀጥታ ሄዶ እንዲገዛ ነው።” ይላሉ፡፡
አንዳንድ የገበያ ማዕከላት ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ባይገቡም፣ ስራ የጀመሩት ማዕከላት ግን ገበያውን ማረጋጋት ችለዋል የሚሉት ሃላፊዋ፤ አብዛኛዎቹ ሱቆች የተሰጡት ለአምራቾች መሆኑንና የተወሰነው ለቸርቻሪዎች መሰጠቱን ይናገራሉ፡፡
አሁን ላይ እየሰሩ ያሉት ኮልፌ፣ አቃቂ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ እና ለሚ ኩራ የገበያ ማዕከላት እንደሆኑ የጠቆሙት ወ/ሮ ሃቢባ፤ ሁሉም የማስፋፊያ ስራ እየተሰራላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ የንግድ ሥርዓት በአብዛኛው የተጠላለፈው በደላላ ነው የሚሉት የቢሮ ሃላፊዋ፤ ከሌሎች ገበያዎች ጋር ስናነጻጽረው፣ የገበያ ማዕከላቱ ውስጥ ያለው የደላላ ሰንሰለት በጣም የቀነሰ ነው፤ ይላሉ፡፡ “ሥራ የሚያቀላጥፉ ህጋዊ ደላላዎች በተወሰነ ቁጥር አሉ፡፡ የገበያ ስርዓቱን የሚያስተጓጉል የደላሎች አካሄድ ግን በገበያ ማዕከላቱ ውስጥ የለም።” ሲሉም ያስረዳሉ፡፡
አምራቾች በገበያ ማዕከላቱ ውስጥ ስራ ለመጀመር ከፈለጉ፣ ሦስት መስፈርቶችን ማሟላት ይገባቸዋል፤ ይላሉ የቢሮ ሃላፊዋ፡፡ አንደኛ፤ ከ15 እስከ 20 በመቶ በሚያቀርቧቸው ምርቶች ላይ ቅናሽ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ምክንያቱም የሚከፍሉት ኪራይ አነስተኛ ነው። ወጪያቸውም የአስተዳደር ክፍያ ብቻ ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ፣ የምርት አቅርቦት መኖር አለበት። የአምራቹ የራሱ የእርሻ ማሳ መኖር አለበት፤ ወይም ኢንቨስተር ሆኖ በእርሻ ስራ ላይ መሰማራቱን እናረጋግጣለን። ትልቁ መስፈርት ደግሞ ዓመቱን በሙሉ ምርት ማቅረብ መቻሉ ነው። አምራቹ ይህንን ሲያሟላ ነው ወደ ውል መፈራረምና ኪራይ የሚገባው። ይህንን መስፈርት ያሟሉ አርሶአደሮች ወደ ማዕከሉ ከገቡ በኋላ ለቸርቻሪዎቹ ምርት ያከፋፍላሉ ብለዋል፤ ወ/ሮ ሃቢባ፡፡
የመሰረተ ልማት መሟላትን አስመልክቶ ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያም፤ “የመሰረተ ልማት ማሟላት ስራዎች ከሞላ ጎደል እየተጠናቀቁ ቢሆንም፣ የመንገድ ስራ ይቀረናል፡፡ የመንገዶች ባለስልጣን እንደነገሩን ከሆነ፣ በዚህ ወር ውስጥ ሰርተው ይጨርሳሉ። አንዳንድ ነጋዴዎች ከማዕከሉ የሚወጡት በመንገድ ምክንያት ነው።” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
“የኮልፌ የገበያ ማዕከል ብቻ ሳይሆን፣ የለሚ ኩራ ማዕከል ጭምር መብራት የገባለት በቅርብ ጊዜ ነው። በተመሳሳይ መልኩ፣ የኮልፌ ማዕከል የመንገድና የመብራት ችግር አለበት። አቃቂም ላይ የመንገድ ችግር አለ። እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር በመመካከር ወደ ስራ ተገብቷል።” ሲሉም አስረድተዋል፡፡
የምርት አቅርቦትን በተመለከተም የንግድ ቢሮ ሃላፊዋ እንዲህ ይላሉ፤ “ከሁሉም የገበያ ማዕከል በየቀኑ ዕለታዊ መረጃ እንወስዳለን። በየገበያ ማዕከላቱ ያሉ ምርቶችንና የሸማቹን ፍላጎት እንጠይቃለን። አንደኛው ገበያ ላይ የተትረፈረፈ ምርት ካለ፣ ነጋዴዎቹን የምርት እጥረት ወዳለበት እንዲወስዱ እናደርጋለን፡፡ እስካሁን ግን ያን ያህል የምርት እጥረት ችግር አልገጠመንም። አዲስ አበባ ላይ ተፈልጎ የታጣ ምርት የለም።”
በገበያ ማዕከላቱና በመደበኛው ገበያ ላይ ያለው የዋጋ ልዩነት የሚገናኝ አይደለም የሚሉት የቢሮ ሃላፊዋ፤ በጤፍ ዋጋ ላይ በትንሹ የ2500 ብር የዋጋ ልዩነት መኖሩን ይጠቅሳሉ፡፡ “ሆኖም ሌሎች ገበያዎች ላይ ያለው የሸማች እንቅስቃሴ በገበያ ማዕከላቱ ላይ አይታይም፡፡ በእኛ በኩል ማሕበረሰቡ አላወቀም ብለን ነው የምናስበው።” ይላሉ፡፡
ማዕከላቱን የማስተዋወቁ ስራ ላይ የሚቀሩ ነገሮች እንዳሉ በግምገማችን ለይተናቸዋል፤ ባይ ናቸው፡፡ ለዚህም በቀጣዮቹ ስድስት ወራት የገበያ ማዕከላቱ ከሌሎች የገበያ ስፍራዎች ያላቸውን የዋጋ ልዩነት ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ የማስተዋወቅ ሥራዎች ለመሥራት ዕቅድ መያዙን ጠቁመዋል፡፡
በቀጣይ እየሰሩ ያሉትን ሥራ አስመልክተው ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ ሲናገሩ፤ ከአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመተባበር፣ በየገበያ ማዕከላቱ የሚገኙ ካሜራዎችን የማስተሳሰር ሥራ እንሰራለን፤ ይላሉ። “ካሜራዎችን ካስተሳሰርን በኋላ፣ የየገበያ ማዕከላቱን ዕለታዊ ዋጋ የምናወጣው እኛ ነን። በማዕከላቱ ውስጥ ስክሪን ስላለ፣ ዋጋው በዚያ በኩል እንዲታይ ይደረጋል። በተጨማሪም፣ በየገበያ ማዕከላቱ ያለውን ዕለታዊ ዋጋ የሚያሳውቅ መተግበሪያ እያዘጋጀን ነው። ማንኛውም ሸማች ባለበት ቦታ ሆኖ የየማዕከላቱን ዋጋ በቴክኖሎጂ አማካይነት እንዲያውቅ ነው እየሰራን ያለነው።” ሲሉ አስረድተዋል፡፡
እነዚህ ሁሉ በሂደት እየተሟሉ ሲመጡ የገበያ ማዕከላቱ በእርግጠኝነት የታለመላቸውን ግብ ሙሉ በሙሉ እንደሚያሳኩ አያጠራጥርም፡፡ አሁንም ግን የኑሮ ውድነትን ጫና እያቃለሉና ገበያውን እያረጋጉ ስለመሆናቸው ምስክሮቹ ራሳቸው ሸማቾቹ ናቸው፡፡
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል ይካሄዳል ስፖርት ለአንድነትና ለጋራ እድገት በሚል መርህ ነው
የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዮኒቨርስቲ አዘጋጅነት ዛሬ ይጀመራል። የስፖርት ፌስቲቫሉ በተለያዩ ምክንያቶች ለዘጠኝ ዓመታት ተቋርጦ የቆየ ነበር። በአዲስ መልክ እንዲጀመር የኢትዯጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የስፖርት ማህበርና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ልዮ ትኩረት በመስጠት ተንቀሳቅሰዋል።
የስፖርት ፌስቲቫሉ እስከ ጥር 27 በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዮኒቨርስቲና በአካባቢው በሚገኙ የስፖርት ሜዳዎች የሚካሄድ ሲሆን 49 የኢትዯጵያ ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሳተፉበት ይጠበቃል። በአምስት የስፖርት አይነቶች እግር ኳስ ፤ አትሌቲክስ ፤ ዎርልድ ቴኳንዶ ፤ ቼዝና የባህል ስፖርት ውድድሮች እንደሚካሄዱም ታውቋል።
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደረጀ እንግዳ እንደተናገሩት ስፖርት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲስፋፋ መስራት ያስፈልጋል። “ስፖርት ለአንድነትና ለጋራ እድገት” በሚል መርህ ፌስቲቫሉ እንደሚካሄድ ጠቅሰው ዮኒቨርስቲያቸው ለፌስቲቫሉ ተሳታፊዎች የምግብና የማደርያ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን የስፖርት ውድድሮችን በግቢው እና በአቃቂ ቃሊቲ ሌሎች ሜዳዎች ላይ እናስተናግዳለን ብለዋል።
በፌስቲቫሉ ላይ በአህጉራዊና ዓለምአቀፋዊ ውድድሮች ኢትዮጵያን መወከል የሚችሉ ፕሮፌሽናል ስፖርተኞች ማፍራት እንደሚቻል የገለፁት ደግሞ የኢትዯጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የስፖርት ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አባይ በላይሁን ናቸው። በኢትዮጵያ ስፖርት ላይ መነሳሳትን እንደሚፈጥርና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስፖርት ማዘውተሪያዎችን ልማት ለማጠናከር እንደሚያግዝም አብራርተዋል። በፌስቲቫሉ ላይ ከሚገኙት 49 ዮኒቨርስቲዎች 46 በእግር ኳስ ቡድኖቻቸው መሳተፋቸውን የጠቆሙት አቶ አባይ በእግር ኳስ ላይ የሚሰሩ ክለቦች፤ የክለብ ባለቤቶችና መልማዮች ፌስቲቫሉን በመታደል እድሎችን እንዲፈጥሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በየክልሎቹና በከተማ መስተዳድሮች ያሉ ዮኒቨርስቲዎች በክላስተር አደራጅቶ የውስጥ ውድድሮች በማካሄድ በአሸናፊዎች አሸናፊ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫልን ለማከናወን መታቀዱን የኢትዯጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የስፖርት ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አባይ በላይሁን አስታውቀዋል።