Administrator

Administrator

Monday, 05 October 2026 14:54

ቃለ መሃላ ፈጸሙ!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ለሁለተኛ ግዜ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰየመ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መደበኛ ስብሰባ ላይ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት 7ኛው የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል። በጉባኤውም ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል አፈ ጉባኤ ሆኖ ተመርጠዋል። በተጨማሪም አቶ ደስታ ሌዳሞ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ በመሆን ተመርጠዋል።

ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው የየመን መንግሥት ጦር፣ ከሁቲ ታጣቂዎች ጋር ተዋግቶ ወሳኞቹን የባብ-አልመንድብ የባህር መስመር እና ዱባብን መቆጣጠሩን አስታወቀ። ዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦች የሚያልፉበት ይህ ቦታ ከዚህ ቀደም በሁቲዎች እጅ ነበረ።
በሌላ በኩል የመንግሥት ጦር ከሳዑዲ አረቢያ ጋር በመተባበር፣ ከ2014 ጀምሮ በሁቲዎች ቁጥጥር ሥር በምትገኘው ዋና ከተማ ሰንዓ ላይ ጥቃት መክፈቱን አሳውቋል። ይህ እርምጃ በየመን ጦርነት ውስጥ ትልቅ ለውጥ እያመጣ መሆኑ ተገልጿል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
በአንድ ውብ የገጠር መንደር ውስጥ፣ መምህር አበበ የተባሉ አርአያነት ያላቸው መምህር ይኖሩ ነበር። በወቅቱ ትምህርት ቤቱ መብራትና በቂ መማሪያ መጻሕፍት ባይኖሩትም፣ መምህር አበበ ለተማሪዎቻቸው የነበራቸው ፍቅር ግን የትየለሌ ነበር።
በክፍሉ ውስጥ አጸደ የተባለች ድሃ እና ታታሪ ተማሪ ነበረች። አጸደ ከትምህርት ቤት መልስ ከብት በማገድ ቤተሰቧን ታግዛለች፤ ማታ ማታ ደግሞ በጧፍ ብርሃን ለማጥናት ትጥር ነበር። ነገር ግን ደብተር እና እስክሪብቶ ለመግዛት አቅም አልነበራትም።
አንድ ቀን መምህር አበበ፣ አጸደ በዛፍ ቅጠል ላይ በእንጨት እየቧጠጠች ፊደል ስትለማመድ አዩዋት። ልባዊ የትምህርት ፍላጎቷን ተረድተውም ከደረት ቦርሳቸው አሮጌ ግን ንጹህ የሆነ ደብተር እና የሰም እርሳስ ሰጧት።
"ዕውቀት ብርሃን ነው። ዛሬ በሰም ሰሌዳ ላይ የምትጽፊው ጽሑፍ፣ ነገ የሕይወትሽን ጎዳና ያበራል። መምህርነት ማለት ራስን እንደ ጧፍ አቅልጦ ሌሎችን ማብራት ነው።" አሏት።
ዓመታት አለፉ። መምህር አበበ አረጁ፤ አጸደ ግን በትምህርቷ ገፍታ ዩኒቨርሲቲን አጠናቀች። ከዚያም ተመልሳ በዚያው ትምህርት ቤት መምህርት እና ዋና አስተዳዳሪ ሆና ተሾመች።
በአንድ የዓለም አቀፍ መምህራን ቀን ክብረ በዓል ላይ አጸደ እንባ እየተናነቃት እንዲህ ስትል ተናገረች፦"ዛሬ እዚህ ለቆምኩበት ክብር መሠረት የሆኑኝ፣ ፊደል ብቻ ሳይሆን ልባምነትን ያስተማሩን ውዱ መምህራችን አበበ ናቸው። መምህርነት ማለት ራስን አቅልጦ የሌሎችን ጨለማ ገፎ ብርሃን መስጠት ነው።"
በዚያች ዕለት፣ መምህር አበበ የሰጡት ዕውቀት ፍሬ አፍርቶ መመልከታቸው ታላቅ ደስታን አጎናጸፋቸው።
****
ዛሬ የዓለም መምህራን ቀን ነው
የተመሠረተበት ዓመት፦ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (UNESCO) ከዓለም አቀፉ የሠራተኛ ድርጅት (ILO) ጋር በመሆን እ.አ.አ ከ1994 ጀምሮ በየዓመቱ ጥቅምት 5 (October 5) እንዲከበር ወስኗል።
ቀኑን የመረጡበት ምክንያት፦ ጥቅምት 5 ቀን 1966 ዓ.ም. በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ የመምህራንን መብት፣ ኃላፊነት፣ የስራ ሁኔታ እና ሥልጠና አስመልክቶ ታሪካዊው የጋራ ውሳኔ የጸደቀበት ዕለት በመሆኑ ነው።
ዓላማው፦ የመምህራንን ድምጽ ከፍ ለማድረግ፣ ማህበራዊ አበርክቷቸውን ለመገንዘብ እና ሙያውን ይበልጥ ለማጠናከር ታስቦ የሚከበር ዓለም አቀፍ በዓል ነው።
(ምንጭ፦ ከዩኔስኮ እና ከዓለም አቀፍ የትምህርት
ድርጅቶች የተገኙ ታሪካዊ መረጃዎች)
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Monday, 05 October 2026 14:22

መቀሌ ከተገባ አይቀር ---

(የግል ምልከታ)
መቀሌ ከተገባ ዘንድ መንግስት ፈጥኖ ሰላምና መረጋጋት ከማስፈንም ባሻገር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልል መካከል ያለውን የኬላና የድንበር ጉዳይ በማላላት የንግድ ፍሰቱ እንዲቀልጥ ማድረግ አለበት። ህዝቡም ወደ ፈለገው የኢትዮጵያ ክፍል በነፃነት እንዲገባና እንዲወጣ በማድረግ፣ ህወሃት የፈጠረባቸውን የተሳሳቱ ትርክቶች እና መጥፎ ምስሎች ማጥፋት ይገባል። እንደ ባለፉት አመታት "ሸቀጥና እህል ወደ ትግራይ ከአማራ ክልል አይገባም" በማለት መራራቁን የሚያባብሱ ፖለቲካ ያልገባቸው አጉል ተቆርቋሪዎችና ጥቅመኞች ድርጊት መቆም አለበት።
በተለይ የአማራ ክልል ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች ለሁለቱ ክልሎች መልካም ግንኙነት ከዚህ የተሻለ አጋጣሚ እንደሌለ ተረድተው መስራት ይኖርባቸዋል። ህወሃት አማራን ሰይጣን አድርጎ የሳለበትን የተሳሳተ ትርክት በመስበር፣ ህዝባችን በሁሉ ነገር ወገንተኝነቱንና ፍቅሩን በመግለጽ ወደ ቀደመው ወንድማማችነት መመለስ አለበት። የህወሃት "አማራ ጠል" ትርክት አንዱና ዋና መቋጫው ጠንካራ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ነው። በዚህ መንገድ ምስኪኑ የትግራይ ህዝብ ሊታገዝና የኢትዮጵያ ህዝብ ለእሱ ስጋት አለመሆኑ በተግባር ሊረጋገጥ ይገባል።
Seid Yesuf Ali Tessema-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
ከኢትዮጵያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ውስጥ ያሉት ግብጽ እና ኤርትራን ጨምሮ አራት የጎረቤት ሀገራት መሪዎች በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ለመነጋገር በግብጿ አል-አሚን ከተማ ተገናኝተው እየመከሩ ነው ተባለ።
የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ፣ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ እና የሱዳኑ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል-ቡርሀን የተሳተፉበት ይኸው ስብሰባ፣ የመከላከያ ሰራዊት እና አጋር ኃይሎች መቐለ ከተማን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ጦርነቱ የመስፋፋት አደጋ ይኖረው ይሆን በሚለው ዙሪያ ትኩረት አድርጓል።
በሌላ በኩል በመቐለ ከተማ ከአንድ ሳምንት በላይ ተዘግቶ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት ዛሬ ወደ ሥራ የተመለሰ ሲሆን፣ የፌዴራል የጸጥታ ኃይሎች ቁልፍ ተቋማትን መቆጣጠራቸው ተገልጿል። የሕወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ቡድኑ ወደ ሽምቅ ውጊያ እንደሚገባ መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
ኢትዮጵያን ወክለው በአቡዳቢ በተካሄደው 15ኛው የተባበሩት መንግሥታት የወንጀል መከላከልና የወንጀል ፍትሕ ጉባኤ ላይ የተሳተፉት የዓለም አቀፍ ጠበቃና የሕግ አማካሪ ክብርት ወ/ሮ መሠረት ስዩም፣ የሜዳልያ ሽልማትና የምስክር ወረቀት እውቅና ተበረከተላቸው። ከመስከረም 15 እስከ 20 ቀን 2019 ዓ.ም. በተካሄደው በዚህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ወ/ሮ መሠረት ሙያዊ እውቀታቸውንና ልምዳቸውን በማካፈል የወንጀል ፍትሕ ስምምነቱ እንዲጸድቅ እና ወሳኝ ጉዳዮች በውይይቱ እንዲካተቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።
ይህ እውቅና ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ የሕግ ባለሙያዎች ትልቅ ፋና ወጊ ስኬት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ወ/ሮ መሠረት በጉባኤው ላይ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ከሀገር ውስጥ የፍትሕ ሥርዓት ጋር በማጣጣም እና ተጨማሪ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ረገድ አጽንኦት ሰጥተው ሐሳብ ማጋራታቸው ታውቋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
በስኮትላንድ ግላስጎው ከተማ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሳይካትሪ ዘረመል ኮንግረስ ላይ ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ምሁር ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ እና እሳቸው የሚመሩት «DepGenAfrica» የምርምር ቡድን የ«Pamela Sklar» ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ተገለጸ። ፕሮፌሰር ሰለሞን አፍሪካውያንን ለድብርት በሽታ የሚያጋልጡ በዘር የሚተላለፉ ዘረ-መሎችን ለመለየት በሚደረገው ትልቅ አህጉር አቀፍ ጥናት ላይ የአፍሪካ ዋና ተመራማሪ በመሆን ሀገራቸውን በማስጠራት ላይ ይገኛሉ።
ይህ አሸናፊ ጥናት ለወደፊቱ ድብርት ሳይከሰት ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ ዘዴዎችን ለመዘርጋት እና ለአፍሪካውያን አካላዊና አእምሯዊ ቁመና የሚስማሙ የሕክምና መድኃኒቶችን ለማዘጋጀት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ነው። ፕሮፌሰር ሰለሞን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአእምሮ ሕክምና ክፍል ውስጥ የሱስ ሕክምና ሰብ-ስፔሻሊስት በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ በግል ተቋማቸውም የሕብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ የሚረዱ የሕክምና አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
Mental wellness-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
ከትግራይ ግጭት ማብቂያ በኋላ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ አሁንም ቢሆን በቁምነገር ሊታዩ የሚገባቸው በርካታ ወሳኝ ጉዳዮች አሉ። ከእነዚህም መካከል ዋነኛው የትግራይ ሰላም ኃይል (TPF) በቀጣይ የሚኖረው ሚና እና አዲስ በሚመሰረተው አስተዳደር ውስጥ የሚኖረው ድርሻ ምን ሊሆን እንደሚገባ በግልጽ መቀመጥ አለበት።
ካለፉት ጊዜያት አገራዊ ልምዶቻችን እንደምንረዳው፣ ከመንግሥት ጎን ተሰልፈው በነፍጥ ትግል ውስጥ የተሳተፉ ታጣቂ አካላትን ከጦርነት በኋላ ማስተዳደር ሁልጊዜም ከባድ ፈተና ሆኖ ቆይቷል። ይህንን ታሪካዊ ስህተት አለማደገም ለትግራይ ሰላም መሠረት ነው። ሕዝባዊ ምርጫ ተደርጎ እውነተኛ እና ሕጋዊ አስተዳደር እስኪመሰረት ድረስ፣ የዚህ ኃይል እጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን አሁንኑ በጥንቃቄ ሊሰራበት ይገባል።
ስለሆነም የሽግግር ወቅት ሰላምና ጸጥታን አስተማማኝ ለማድረግ፣ የሰላም ኃይሉ አቀማመጥ እና ከሕዝብና ከመንግሥት ጋር የሚኖረው ግንኙነት ግልጽ ሕጋዊ ማዕቀፍ ሊኖረው ይገባል። ያለበለዚያ የሚፈጠረው የሥልጣን እና የጸጥታ ክፍተት አዲስ አለመረጋጋት ሊያስከትል ስለሚችል፣ ጉዳዩ አሳሳቢ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…